Get Mystery Box with random crypto!

ስብዕናችን #Humanity

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiohumanity — ስብዕናችን #Humanity
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiohumanity — ስብዕናችን #Humanity
የሰርጥ አድራሻ: @ethiohumanity
ምድቦች: ሳይኮሎጂ
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 30.71K
የሰርጥ መግለጫ

🔆እየጠየቁ መኖር መልስን፣
መልስን ፈልጎ ማግኘት ዕውቀትን፣
እውቀት ነፃነትን፣ ነፃነት ሙሉ ስብዕናን፣
ሙሉ ስብዕና ሠላምና እርካታን፣
እርካታ ደግሞ ደስተኛ ሆኖ መኖርን ያስገኛል፡፡
አብረን እንደግ !!
@EthioHumanity @Ethiohumanity
✍የተሰማቹን አጋሩን! ቤቱ ሁሌም ክፍት ነው፣ሃሳባቹን ፃፍፍ አርጉልን @EthioHumanitybot

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2022-11-14 21:07:47 በአንዲት ትንሽየ ከተማ ውስጥ ለብዙ ዘመናት ማራኪ ስዕሎችን በመሳል ለከተማዋ ነዋሪዎች እና ከሩቅ አካባቢ ለሚመጡ እንግዶች በጥሩ ዋጋ እየሸጠ ደስታ የተሞላበት ሕይወት የሚኖር አዛውንት ነበር። ከዕለታት አንድ ቀን በከተማዋ ውስጥ ከሚገኙ ድሃዎች
መካከል አንዱ መጣና ሰዓሊውን «በሥራህ ብዙ ገቢ እያገኘህ ለምንድን ነው በከተማዋ ያሉ የኔ ቢጤ ደሃዎችን ለመርዳት ንፉግ ያደረገህ ??...

የዚያ ልኳንዳ ቤት ባለቤት እዚህ ግባ የሚባል ገንዘብ ሳይኖረው ለድሃዎች በየቀኑ ስጋ ያድላል፤ በተመሳሳይ ሁኔታ የዚያ ዳቦቤት ባለቤት ዘወትር በየቀኑ በነፍስ ወከፍ ለድሃዎች ዳቦ ይሰጣል» በማለት ጠየቀው። ሰዓሊው ምንም መልስ ሳይሰጠው በሰከነ መንፈስ ታጅቦ በስሱ ፈገግ አለ።

ድሃው በሰዓሊው ዝምታ ተበሳጭቶ ከቤቱ ውስጥ ተስፈንጥሮ ወጣ። ወደ መሃል ከተማ በመገስገስ አላፊ አግዳሚውን እያስቆመ «ሰዓሊው ብዙ ኃብት ቢያከማችም ድሃወችን
ለመርዳት ፍላጎት የሌለውና ስስታም ነው» በማለት ወሬ መንዛት ጀመረ። የአካባቢው ነዋሪዎች በሰዓሊው ላይ ጥርስ ነከሱበት። ማህበራዊ መገለል ደረሰበት። የሚያናግረው አንድ ሰው እንኳ አጣ።

ከተወሰኑ ቀናት በኋላ አዛውንቱ ሰዓሊ ክፉኛ ታመመ። ከአካቢቢው ነዋሪዎች መካከል አንድም ሰው ትኩረት የሰጠው አልነበረም። ከጎኑ ማንም ሳይኖር ብቻውን ሞተ።

ቀናት በንፋስ ፍጥነት ነጎዱ። የከተማዋ ነዋሪዎች የልኳንዳ ቤቱ ባለቤት ለድሃዎች በነጻ የሚያድለውን ስጋ እንዳቆመ አስተዋሉ። የዳቦ ቤቱ ባለቤትም ለሚስኪኖች በነጻ
የሚያከፋፍለውን ዳቦ እንዳቋረጠ ተገነዘቡ። ድሃዎቹ በልኳንዳ ቤቱ በር ፊት ለፊት ቆመው የለመዱትን ስጋ ለማግኘት ቢማጸኑም ሰሚ አጡ። በዳቦ ቤቱ መስኮት ዙሪያ ቢያንዣብቡም
ለስም እንኳ የሚያዳምጣቸው አንድ ሰው አጡ።

የከተማዋ ነዋሪዎች ተሰብስበው የልኳንዳ እና ዳቦ ቤቶቹን ባለቤቶች «ዘወትር በየቀኑ ለድሃዎች ትሰጡ የነበረውን ስጋ እና ዳቦ ለምን
አቆማችሁ» ብለው ሲጠይቋቸው «በየቀኑ ለከተማዋ ድሃዎች በነጻ የምንሰጠውን የስጋና ዳቦ ዋጋ በየወሩ የሚከፍለን አዛውንቱ ሰዓሊ ነበር። ከሱ ህልፈት በኋላ ክፍያ የሚፈጽምልን
ሰው ባለመኖሩ በነጻ ማደሉን አቋርጠነዋል» በማለት ወሽመጥ ቆራጭ ምላሽ ሰጧቸው።

የተወሰኑ ሰዎች ባንተ ላይ ክፉ ጥርጣሬ ሊያሳድሩ ይችላሉ። አንዳዶች ደግም እንደ ሐጫ በረዶ የጠራህ አድርገው ሊስሉህ ይችላሉ። ሁለቱም አይጠቅሙህም። አይጎዱህምም።
ቁም ነገሩ ያለው ፈጣሪ ስላንተ የሚያውቀው ትክክለኛ ማንነትህ ላይ ነው። ለክፉ አሳቢዎች ክፋ ምላሽ ላለመስጠት ጥረት አድርግ።

ደግነትህ ለብዙዎች የዕድሜ ማራዘሚያ ሰበብ ስለሆነ እንዳይከስም ጠብቀው። ለጋስ በመሆንህ በምላሹ ከሌሎች ምንም ነገር አትጠብቅ። የጊዜ ጉዳይ ቢሆን እንጂ መልካም ነገር ሁሌም ከፈጣሪህ በጎ ምላሽ አለው።
ህሊናህ ይረካ ዘንድ ከመቀበል ይልቅ ሰጪ ሁን። በምግባርህ ፈጣሪህን ለማስደሰት ሁሌም ጥረት አድርግ። እርሱ ከወደደህ ደስታ በእጅህ ትገባለች።በመልካም ስነ ምግባር ሽቶ የተርከፈከፈ ስብዕና ከመሬት በታች አፈር ለብሶ እንኳ መዓዛው ያውዳል።
               
ውብ  አሁን
@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot
4.1K viewsedited  18:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-14 21:07:26
3.6K views18:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-13 19:05:29 አፍርሰህ አትገነባም.

የሄደ ነገር ተመልሶ ይመጣል። ሰብረህ ያጠፍኸው የመሰለህ ነገር ይዘገይ ይሆናል እንጂ አይቀርምና አፀፍውን መልሶ ሊያስታቅፍህ ምንአልባትም እጥፍ ድርብ አድርጎ ደጃፍህ ላይ ቆሞ በርህን ያንኳኳል። ኃላፊነት በንግግር፣ ተግባርና ሁሉም መስክ ላይ እንዲንፀባረቅ የተገባው በእዚህና መሰል ምክንያቶች ነው።

እርግጥ ነው ኃላፊነትን በፀጋ መቀበል እና ሳይሸራርፉ በተጨባጭ መወጣት ፈታኝ ነው። አስተዋይ አእምሮ እና ቅን ልቦና በምርጫና መንገድህ ካልተለየህ ግን በድል ትወጣዋለህ። ድሉም ከበደል የፃዳ ይሆናል። ድሉ ከራስህ አልፎ አለምን ስለሚጠቅም መልካሙ ስርህ ሄዶ ዞሮ ሲመለስ በጎ ምላሽ ማግኘትህ አይቀሬ ነው። ወርቅ ለሰጠ ወርቅ እና ጠጠርም ለሰጠ ጠጠር ማግኘት ተፈጥሯዊ ህግና የህይወት ነባራዊ እውነታ ነውና።

መልካምነት ከማንም በላይ ላራስ ነው ጥቅምና ፍይዳው። ቅን ሀሳብ አሳቢውን ይባርካል። ሴራ፣ ተንኮል እና ክፍት ህሊናና ልብህን ከሞላው ግን ሌላው ይቅርና መልካም እንቅልፍ እንኳ ብርቅ እና ሩቅ እንደሚሆኑብህ ልነግርህ እችላለሁ።

አዳርህ በመባነን እና መበርገግ ይሞላል። ቀን ያሳደድከው በህልምህ መግቢያና መሸሸጊያ ጥግ ያሳጣሀል። ቀን ከሌት የዘራሀቸው ክፋቶች ሌሎችን ብቻ ሳይሆን የአንተን የገዛ ራስህንም ገላም ይቧጥጣሉ። ከአንተ የመነጨና ተንደርድሮ የተተኮሰ ኃይል በእኩል መጠን እና ልክ አጥፊ እንደሆነ ራስህንም ያጠፍል፤ አልሚ ከአደረከው ደግሞ ቅድሚያ አንተን እና የእኔ የምትለውን ሁሉ ባርኮ ለሌሎች ይተርፋል።

ይህ የህይወት ሀቅ ከፊዚክስ action/reaction ተፈጥሮአዊ ህግ ጋር ይመሳሰላል። አፍርሰህ አትቆምም። ጠልተህ ፍቅርን አታተርፍም። ወደህ ላትከበር፣ ትህትናን ሰጥተህ ልትናቅ፣ አሳቢና አስታዋሽ ሆነህ ሳለ ልትረሳ አትችልም። ምክንያቱ ደግሞ ምዕራባዊያን እንደሚሉት የሄደ ነገር ተመልሶ ይመጣልና ነው (what goes around comes around)። አበውም አሳ ጎርጓሪ ዘንዶ ያወጣል፣ የሰው ፈላጊ የራሱን ያጣል፤ በቆፈሩት ጉድጒድ መቀበር አይቀርም ወዘተረፈ ብለውናል።

ነጋሽ አበበ

ሰናይ ምሽት ይሁንልን

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
1.8K viewsedited  16:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-13 19:05:19
1.7K views16:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-09 21:13:05
የሚያልፍ ዝናብ አይምታህ!!

እዚህች ምድር ላይ ስንኖር በትንሹም ይሁን በትልቁ በየደቂቃው እንለዋወጣለን። ቢታወቀንም ባይታወቀንም ነው እንግዲህ ቢያንስ ገላችን የበላውን ያንሸራሽራል፣ ሕዋሳት ይሞታሉ ይወለዳሉ። ቢያንስ አንዲት ፀጉር ትበቅላለች ወይም ትረግፋለች። ፊኛችን ሳያቋረጥ በፈሳሽ ይሞላል። ጊዜው ሲደርስም ይጎላል።

ሕይወት እንግዲህ እንዲህ ነው፤ ይሄ ዑደትና የዝግመት ለውጥ አይበቃንምና ደሞ አንዳንድ ጊዜ እጅግ የሚለውጠን ቀውስ ይመጣብናል ገላችን፣አዕምሮአችን ይታመማል እንረበሻለን፣እንጨነቃለን።ሕይወት እንግዲህ ይሄ ነው ሰው በግሉ፣ ሕብረተሰብም ተፈጥሮው ይመስሉኛል።

ይሄን ደጋግሜ መገንዘቤ፣ደጋግሜም በነዚህ ሁኔታዎች ውስጥ ማለፌ ያስተማረኝ ነገር አለ።መረባበሽ ፋይዳ እንደሌለው የተረጋጋ ታዛቢ፣ የመነኩሴ አመለካከት አለኝ። ከፍ ዝቅ ያለ ነገር ሲያጋጥመኝ በረጉ ዓይኖቼ አያለሁ። በቀዘቀዘ መንፈስና አካል እቀበለዋለሁ እንደሚለወጥ ስለማውቅ!"የሚያልፍ ዝናብ አይምታህ" ሲሉ አዛውንት ዝናቡን ፍራው ማለታቸው አይደለም። ዝናቡን ማወቃቸው ነው። የተወሰነለት ዕድሜ አለው፣ ያውም አጭር ማለታቸው ነው። ሰው ቢያንስ በተስፋ የችግሮቹን ዘመን ያልፋል ማለታቸው ነው።

/ከአዳም ረታ አንደበት/

በእርግጥም የሚገጥሙንና የሚያጋጥሙንን ክስተቶችና ፈተናዎች መወሰን ባንችል እንኳን፣ ምላሻችንንና ግብረ-መልሳችንን መወሰን እንችላለንና ዘወትር የመጣው እስኪያልፍ፣ የቀለጠው እስኪ ረጋ፣ የነደደው እስኪ ከስል፣ በሰከነ አዕምሮ፣ በተረጋጋ መንፈስ፣ በአንድ ልብ መቀበሉንና ማሳለፋን እንወቅበት።

       ሰናይ ምሽት ይሁንልን

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
844 views18:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-07 19:30:49
ጊዜ ሰታችሁ ቀና ምልክታችሁን ስላከፈላችሁን ክበሩልን።ብርታት ስለሆናችሁንን ከልብ እናመሰግናለን።

ፈጣሪ ያክብርልን 

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity
1.3K views16:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-05 19:54:09 እራስን ሆኖ መጓዝ ብልህነት ነው
. . . . ብሎ የተነሳው የስብዕና ቻናላችን. . .
በአብሮነት ከእናንተው ጋር ተጉዞ አሁን ላይ ደርሷል

ከጎናችን በመሆን አጋርነታቹን እደምሰሶ ላፀናቹልን ቤተሰቦቻችን ልባዊ ምስጋናችን በያላችሁበት ይድረሳችሁ . . !!

እደትላንቱ ዛሬም ታስፈልጉናላቹ እና ቤታችንን በአዲስ መልክ እንድንገባ
ሁላችንም ስለቻናሉ የሚሰማንን እዚች ላይ ፃፍፍ አናርግ
            
@Ethiohumanitybot @Ethiohumanitybot
     
  ሁሉም የለንምና በእናንተ ሀሳብ  
           የጎደለውን እንሞላለን!!
.  . .ለአብሮነቶ ከልብ እናመሰግናለን!!!
@EthioHumanitybot @EthioHumanitybot
1.4K views16:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-04 19:58:17
ደስታ የምኞት ውጤት፣ የማሳደድ ትርፍም አይደለም። ደስታን ተመኝቶ ያገኘ፣ አሳድዶ የያዘ የለም።

ደስታ ከገንዘብ ብዛት፣ከስልጣን ሹመት፣ ስጋዊ ስሜትን ከማርካት ወይም ከሳይንስ አይመነጭም፡፡ ደስታ በቁጥር አይመጠንም፡፡ መጋዘኖች አያከማቹትም፡፡ ዩሮ ወይም ዶላር አይገዛውም፡፡ ደስታ ከውስጥ የሚሰማ ነገር ነው፡፡ የነፍስ መስከን፣ የቀልብ መረጋጋት፣ የልቦና መስፋት፣ የሕሊና መርካት ውጤት ነው፡፡የአዕምሮአችንን ተፈጥሮ በትልቅ ተረድተን ከተጠቀምበት እውነተኛ ደስታ እና ነፃነት ማግኘት እንችላለን ፡፡

አትኩሮትህን በሌለህ ነገር ላይ ሳይሆን ባለህ ነገር ላይ አድርገው። ደስተኛ ለመሆን ሁሉም ነገር ሊኖርህ አይገባም። በደንብ ካስተዋልከው አሁን ያለህ ነገር ደስተኛ ለመሆን በቂ ነው።ምክንያቱም አንተ ያለህን ሙሉ ጤና የሚመኙ ምስኪኖች ብዙ ናቸውና።

ቁሉፉ ነን እኛ…የራሳችን ደስታ
ውብ አሁን!!

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
492 views16:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-02 19:34:21
መዘግየትህን አትጥላው!

ነገሮች በፍጥነት እንዲሳኩልህ አትፈልግ! መዘግየትህን አትጥላው! በትምህርት፣ በስራ፣ በሀብት፣ በፍቅር ግንኙነት ወይ በትዳር አንተ እንዳሰብከው አለመሆኑ ለበጎ እንደሆነ አስብ።

ልብ እንበል!!

ጉንደን ካስበችው ለመድረስ ሺ ጊዜ ከምሰሶው ላይ ትወድቃለች።

ንብ ጣፋጩን ማር ለመጋገር ሚሊዮን ጊዜ አበቦች አካባቢ ትመላለሳለች:: ወዳጄ ስኬት ትኩረትንና ትእግስትን ይጠይቃል..

ወደ ኋላ የተንደረደረ ረጅም ርቀት እንደሚተኮስ አስብ፤ ወዳጄ ጥያቄህ ቶሎ ያልተመለሰው ጊዜው ስላልደረሰ ወይ ደግሞ ፈጣሪ የተሻለውን ሊሰጥህ ይሆናል። አንተ ብቻ ጥረትህን ሳታቋርጥ ታገስ፤ የህይወትህ ፀሀይ መውጣቷ አይቀርም!

ፋንዲሻ እንዴት አማርሽ ቢሏት እሳቱን ስለቻልኩት አለች ይባላል ፣ በህይወት መስመር ስኬትን ለማግኘት የግድ መከራውን ማለፍ አለብን!!

ውብ ምሽት!

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
1.6K viewsedited  16:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-01 18:06:34
2.2K views15:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ