Get Mystery Box with random crypto!

ስብዕናችን #Humanity

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiohumanity — ስብዕናችን #Humanity
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiohumanity — ስብዕናችን #Humanity
የሰርጥ አድራሻ: @ethiohumanity
ምድቦች: ሳይኮሎጂ
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 30.71K
የሰርጥ መግለጫ

🔆እየጠየቁ መኖር መልስን፣
መልስን ፈልጎ ማግኘት ዕውቀትን፣
እውቀት ነፃነትን፣ ነፃነት ሙሉ ስብዕናን፣
ሙሉ ስብዕና ሠላምና እርካታን፣
እርካታ ደግሞ ደስተኛ ሆኖ መኖርን ያስገኛል፡፡
አብረን እንደግ !!
@EthioHumanity @Ethiohumanity
✍የተሰማቹን አጋሩን! ቤቱ ሁሌም ክፍት ነው፣ሃሳባቹን ፃፍፍ አርጉልን @EthioHumanitybot

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2023-01-04 21:44:15
በዓሉ ግርማ እድር የለውም ፣ እቁብ የለውም ፣ ማኅበረ የለውም። ስለ ነገ አይጨነቅም። “ መስከረም በዓሉ ግርማ ” የነገረችኝም ይህንኑ ነው ፣ 'በዓሉ አሁንን ነው የሚኖረው። እሱ ብቻ ሳይሆን መሪ ወንድ ገፀባሕርያቱ የአሁን ሰው ናቸው። ኦሮማይ ውስጥ የምናነበው ፀጋዬ ኃይለማርያም የሚናገረው ነገር በዓሉን የሚገልጸው ሆኖ አግኝቼዋለሁ።
እንዳለጌታ ከበደ

ስለ ሕይወት እቅድ የለኝም ከመኖር ሌላ:: የሕይወት ግቡ እራሱ መኖር ነው::
ይህችም ውድ የሆነች ትንሽ ቁራሽ ሕይወት እንደአብርሃም ቤት የለኝ፣ እንደሙሴም መቃብሬ ሳይታወቅ መኖር፣ መጻፍ ፣ ሕይወትን በተስፋ ወደፊት እየኖርኩና ወደኋላም እያስተዋልኩ ስለ ኑሮ ቀርቶ ስለምጽፈው ልብወለድም ቢሆን እቅድ አላወጣም።
ደራሲው

« ስለሞት አስቤ አላውቅም። የሙያዬ ባህርይ ፣ ያለምንም ሥጋትና ጭንቀት በማያቋርጥ አሁን ሁኔታ ውስጥ የመኖር ልማድ አሳድሮብኛል። ስለ ወደፊቱ ለምን ይታሰባል ?” ትኩስ ዜና ፣ ትኩስ ሕይወት ! ሞት ለእኔ ምኔም አልነበረም ፣ ሆንም አያውቅም። ትኩስ ዜና ከማጣት ፣ አበቦችን ካለማየትና የቆንጆ ሴት እጅን ለመንካት ካለመቻል የበለጠ ስቃይና መለየት ምን ይኖራል ?” ሞት ትርጉም ሰጥቶኝ አያውቅም . . . እውን ነገር አሁን ብቻ ነው። አሁን አለሁ ፣ ደህና ነኝ ፣ እተነፍሳለሁ ፣ ውብ ኮከቦች እቆጥራለሁ ፣ ይበቃል።
ኦሮማይ

በዓሉ ግርማ

ውብ አዳር

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot
3.1K views18:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-28 22:19:03
ሕይወት እንደ ማዕበል ሲሆን!

አንዳንድ ጊዜ ሕይወት እንደ ማዕበል ነው፡፡ በሰላም ይሄዱ የነበሩ ነገሮች ልክ የተመካከሩ ይመስል በአንድ ላይ ይናጋሉ፡፡ የሁኔታዎች አልሳካ ማለት፣ ድንገተኛ ወጪዎች፣ የገንዘብ እጥረት፣ የጉዳዮች መጥመም፣ የሰዎች ክህደት፣ ስጋትን የሚፈጥሩ ሁኔታዎች መከሰት፣ የጤንነት መቃወስን የሚጠቁሙ ምልክቶች . . . ልክ እንደ ማዕበል በአንድ ላይ ይመጣሉ፡፡

ስለዚህም መወገድ የሚችለውን ችግር በማስወገድ፣ የማይወገደውን ችግር ደግሞ ችግሩ የሚያስከትለውን መጨናነቅ ከእኛ በማስወገድ ነው የምናሸንፈው፡፡

ችግር ካልተወገደ በስተቀር የተሳካ ሕይወት እንደሌለህ ስታስብ፣ ዘወትር የማይለወጥ ነገርን ስትታገል ትኖራህ፣ ሁል ጊዜ “ለምን?” በሚል ጥያቄ ውስጥ ትኖራህ፣ ተስፋ ቢስነት ይጫጫንሃል፣ እንዲሁም ሁሉም ሰው ከችግር ነጻና ደስተኛ፣ አንተ ብቻ ችግረኛ እንደሆንክ በማሰብ ድብርት ውስጥ ትገባለህ፡፡

በተቃራኒ ግን የችግሩ ማዕበል ባይይረጋጋም አንተ ስትረጋጋ መነጫነጭን ታቆማለህ፣ የፈጠራ ብቃትህ ይወጣል፣ አዳዲስ መንገዶን ትቀዳለህ፣ ችግሩን ጠንካራ ለመሆን ትጠቀምበታለህ፣ ከችግሩ ባሻገር አልፈህ ከሄድክ በኋላ ለብዙዎች ደጋፊ ትሆናለህ፡፡

ይህ የተለመደ የሕይወት አካል የሆነ ክስተት በእኛም ላይ ሲደርስ መረጋጋት ወሳኝ ነው፡፡ ማዕበል ይመጣል፣ ልክ እንደመጣ ደግሞ ይሄዳል፡፡ ነፋስ ከየት እንደመጣ ሳናውቀው ወደ እኛ ይነፍሳል፣ ወደየት እንደሚሄድ ሳናውቀው ደግሞ ወደሌላ ቦታ ይነፍሳል፡፡

ተንጋግቶ የመጣው ተንጋግቶ ይሄዳል፣
የችግሩ ማዕበል ባይረጋጋም አንተ ግን ተረጋጋ!!

ዶ/ር እዮብ ማሞ

መልካም እንቅልፍ

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot
1.4K views19:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-27 21:22:23 የሁላችንም ጥንካሬ ያለው በተመቻቸው ስፍራ ሳይሆን ሁኔታዎች ፈር ሲለቁ ጨለማ ሲከበንና ህይወት መውጫ የሌላት መስላ ስታስጨንቀን በምንወስነው ውሳኔ ውስጥ ነው። የማንነታችን ትርጉም የሚለካው ነን ብለን የምናስበው ማንነታችን ፈተና ሲገጥመው በምንወስደው እርምጃ ነው። እራሳችንን የፍቅር ጥግ አርገን የምንይ ከሆነ የፍቅር ጥግ መሆናችንን የሚረጋገጠው ጥላቻ ግድ የሚሆንበት ቦታ ላይ የፍቅርን ፀዳል መልቀቅ ስንችል ነው። የይቅርታ ሰው መሆናችን የሚታወቀው ይቅርታ ለማረግ በሚያስቸግርበት ሁኔታ ላይ ይቅር ማለት ስንችል ነው።ምክንያቱም ነን ብለን የምናስበው ሁሉ ያልሆነው ነገር ሲመጣ ይፈተናልና። እናም በምትፈተንበት ሰዓት የምታረገው ትልቁ ነገር ትልቁ መሸጋገርያህ ይሆናል።

ታድያ ፍቅር ስትሆን ጥላቻ መሀል ትሄዳለህ። ህይወት ስትሆን ሞት መሀል ትራመዳለህ። ሰላም ስትሆን ጦርነት መሀል እራስህን ታገኛለህ። ደግ ስትሆን ክፋት ይከብሀል። እና ይሄ ሁሉ የሚሆነው ነኝ ብለህ የምታስበውን ብርሀን ነኝ ብለህ የምታስበውን ፍቅር ነኝ ብለህ የምታስበውን መልካምነት ታረጋግጥ ዘንድ ነው። " እኔ መልካም ሆኜ ሳለው ለምን መከራ በኔ ላይ ፀና" ብለህ ምታዝን ከሆነ አላማውን ስተሀል። ማንም ክፉ የለምና።ሁሉም ደግ ሁሉም ቸር ሁሉም ፍፁም ነውና። ነገር ግን አንዳንዱ ሁኔታው ሲናወጥ ማንነቱ መርሳቱ ነው። ስልጣን ፤ ገንዘብ፤ ረሀብ ፤ ጥጋብ ፤ ድህነት . . . ወዘተ ማንነትን የማስረሳት ችሎታ አላቸውና። ታድያ ሚሰርቅ ስታይ ሌባ ባለመሆንህ እራስህን እንደ ፃዲቅ አትቁጠር። ምክንያቱም የሌባው ቦታ ላይ ብትሆን እራስህ ያንን ነገር ላለማረግህ ምንም ዋስትና የለህምና። ስንቶች በተናገሩ ባወገዙት በጠሉት ነገር እራሳቸው ገብተውበት አይተናልና።

ፍጥረት ሁሉ ፍፁም መሆኑን ተረዳ። ፍፁም ያልሆነ ሁኔታ እንጂ ፍፁም ያልሆነ ሰው የለም። ሁሉም ሰው ክፍቶብህ ከታየህ ከመራገም ይልቅ ነኝ ብለህ ምታስበውን መልካምነት ሁን። ጥላቻ ሲከብህ ነኝ ብለህ ምታስበውን ፍቅር ሁን። ይሄን መሆን ካልቻልክ ግን ሁሌም ቢሆን ማንነትህን ሳታውቅ ትኖራለህ። እራስን መካድ የፈጠረን መካድ ነው። ውብ እና ድንቅ ሆነህ ከተፈጠርክ ውብ ና ድንቅ ሆነህ መኖር ብቸኛው አማራጭህ ነው። ውብ ና ድንቅ ሆኖ የተፈጠረው ደግሞ አንተ ብቻ ሳትሆን ሁሉም ነውና መንገዱን የሳተ ሰው ሲጎዳህ ከመርገም ይልቅ ወደ ውብነቱ ወደ መልካምነቱ የሚመለስበትን ብርሀን አብራበት።

ውብ አዳር

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot
2.2K viewsedited  18:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-27 21:20:30
2.2K views18:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-26 07:08:52 https://t.me/UltraBonda
1.1K views04:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-23 21:29:52
ጉንዳኖች ውሀ ሲሻገሩ አይተህ ታውቅ ከሆነ በውሃው ላይ ተያይዘው ተያይዘው ይቆማሉ። ጉንዳኖች ተያይዘው በወንዝ ላይ በሚሰሩበት መንገድ ሌሎች ብዙ ጉንዳኖች ይሻገራሉ። ተያይዘዉ ይሻገራሉ። ተደጋግፈው አስፈሪውን ወንዝ ይሻገሩታል። ባይያያዙና ባይደጋገፉ ግን አይቻላቸውም። አንዲት ጠብታ ዝናብ ለአንድ ጉንዳን ውቅያኖስ ብትሆንም ብዙ ጉንዳኖች አንድ ላይ ከተያያዙ ግን ውቅያኖስ መሻገር ይችላሉ።.

ያንተ መኖር ለሌሎችም አንድ ቀን ለሌላ ከለላ ይሆናል።ያንተ መቆም አንድ ቀን ሌሎችን ከመውደቅ ይታደጋል ። ያንተ መኖር ላንተ ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም አስፈላጊ ነው።ስትኖር ለራስህ ብቻ ሳይሆን ሌላን ታሳቢ ማድረግም የግድ ነው ። ሕይወት ልክ እንደ ሰንሰለት እርስ በእርስ ተያይዘው የሚያዘግሙባት የትብብር መድረክ ናት ።

አኗኗራችን ነፃና ውብ መሆን ይችላል ፣ከጉብዝና ይልቅ ደግነትና ሩህሩህነት ያስፈልገናል ያለነዚህ ብቃቶች ሕይወት ቀውስ ውስጥ ትሆንና ሁሉንም እናጣለን። ይህንን ሕይወት ነፃ ውብ የተሻለ የማድረግ ኃይል አላችሁ አዲስ ስለሆነ ዓለም, ቀና ለሆነ ዓለም, የመስራት ዕድል ለሰው ስለሚሰጥ ዓለም እንልፋ ! ለወጣቱ መፃኢ ተስፋ ለአዛውንቱ እፎይታና ዕረፍትን ስለሚሰጥ ዓለም እንልፋ ጥላቻና አለመቻቻልን ለመጣል ምክንያት ስለሆነች ዓለም እንልፋ , ልፋታችን ለመልካም ብቻ ይሆን ዘንድ እንልፋ።

             ውብ አሁን
@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot
1.3K views18:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-20 22:14:10 ትላንት አልፏል ስለዚህ ሞቷል።
እከሌ ህይወቱ አለፈ ስንል፡ ሞተ ከአሁን ቡሃላ እዚ ምድር ላይ አይኖርም እያልን ነው። በተመሳሳይ ሁኔታ ትላንት አልፏል (አለፈ) ስንል ሞቷል በህይወታችንም ዋጋ የለውም እያልን ነው። ነገ ደሞ ሚስጥር ነው ካልደረስንበት አናውቀውም።እንዲሁም ነገ ስጦታ ነው ካልተሰጠን አንደርስበትም።ዛሬ ግን በእጃችን ላይ ነው። ስለዚህ ስለ ትላንት በማሰብ ስለነገም በመጨነቅ ዛሬን አናበላሽዉ። ትልቅ ጥበብ ዛሬን መኖር ነው ከዛሬም ደሞ አሁን። ወዳጄ ትላንት ስላሳለፍከው ነገም ስለምትሆነው አትጨነቅ። ነገን ስትደርስበት ህይወት እራሷ ትገልፅልሀለች።

የህይወት ትልቁ ስጦታ በህይወት
መኖር ነው። ትዳር የምትመሰርተው ሀብት ንብረት የምታፈራው በህይወት ስላለክ ነው። ህይወት ደግሞ የሚኖሯት እንጂ የሚመልስዋት ጥያቄ ፣የሚፈቷት እንቆቅልሽ አይደለችም።የሆነው ሁሉ መሆን የኖረበት ነው ፣ የሚሆነውም መሆን ያለበት ነው። ለምን ሆነ ? ህይወት ምንድነች ? የመሳሰሉትን በመጠየቅ እራስህን አታድክም። የህይወት ጥያቄዎች ሁሉ መልስ ያለው እራስዋ ህይወት ውስጥ እንጂ አይምሮህ ውስጥ አይደለም።

አንተ ያስከፋህን ነገር አይደለህም ፡አንተ ያስደሰተህንም ነገር አይደለህም አንተ የሁለቱም መውረጃ ቦይ ነህ የሚያስደስትህም የሚያስከፋህም ነገር በአንተ ውስጥ ያልፉል አንተግን ሁለቱንም አይደለህም። ይህ የህይወት ህግ ነው።

ከ24 ሰአት ውስጥ 12ቱ ብርሀን 12ቱ ጨለማ ነው፣1አመትም በጋና ክረምት ነው ። አየህ በህይወት ብርሀንና ጨለማ በጋና ክረምትም ይፈራረቃሉ።ባንተም በተመሳሳይ መልኩ ማግኘትና ማጣት ፣ማዘንና መደሰት ይፈራረቃሉ ይህ ይሆን ዘንድ ግድ ነው ። በሌላው ከሆነው ይልቅ ባንተ ብቻ የሆነ ምንም የለም። ካንተ በፊትም አሁን በሚኖሩትም የሆነ ነው አንተ ላይም እየሆነ ያለዉ። የሚሟሽ የሚከለስ እንጂ አዲስ መከራ የለም። ፀደይ፣ መኸር፣በልግ እያሉ ወቅቶች እንደሚፈራረቁ ስሜቶችም አንተ ላይ ይፈራረቃሉ።ንዴት ፣ ቁጣ ፣ መረጋጋት፣ መስከን እያሉ ማለት ነው። አስታዉስ አንተ ግን ስሜቶችህን አይደለህም አንተ ከዛ በላይ ነህ።

ሰለዚህ ህይወት ምንድናት እያልክ አትጨነቅ ።እስዋ የህፃን ልጅ ሳቅና ለቅሶ፣ የወጣት ድንፋታ ፣የሽማግሌ ስክነት፣ አለቶች ከውሀ ጋር ሲጋጩ የሚያሰሙት ድምፅ፣ ንፋስ የሚያወዛውዘው ቅጠል ይህ ሁሉ ናት። አንተ ግን የህይወትን ሚስጥር በቃላት ለመግለፅ በመሞከር እና ስለትላንት በማሰብ እንዲሁም ስለነገ በመጨነቅ ዛሬን ታበላሻለህ።እውነት ዛሬ ነው! ። ስለዚህ ዛሬን ኑር !

ውብ አሁን

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity

@Ethiohumanitybot
1.3K views19:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-20 22:13:50
1.2K views19:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-19 22:03:06
ደግነትን ፣ ርህራሄን ፣ አዛኝነት ፣ ቅንነት እና በጎ አሳቢነት በተፈጥሮ ለሰው ልጅ የተቸረ ነው።

ከትሕትና የበለጠ መልካም ነገር የለም። የደካማነት መገለጫ አይደለም።
የዋህነት ደካማነት ሳይሆን የለስስት የመኖር ችሎታ ነው፣ ደግነት የመልካም ሰው የህይወት መምርያ ነው። ደጎች የፍቅር ልብ ያላቸው፣የሰው ችግር የሚገባቸው ።ከራሳቸው ሰውን የሚስቀድሙ ፣በሰው ላይ የማይፈርዱ ና ሩህረሩህ ናቸው ።ውስጣቸው ከክፋት የጠራ ብዙ ደስታ ና ፍቅር የሚገኝባቸው ጥበበኞች ናቸው።

ሰው በውስጡ በመልካም እና ሰናይ ምግባራት የተሞላ ፍጥረት ነው።
እኩይ ተግባር ግን የልምምድ ወጫዊ ተፅእኖ ተግባር ነው።በውጫዊ ተጽእኖ ሳይደናቀፉ እና ሳይቀየሩ ይህን የተፈጥሮ ጸጋ መጠቀም ደግሞ ታላቅነት ነው ሰብአዊነት ነው አርቆ አሳቢነት ነው አስተዋይነት ነው።

በአስተዋይነት ከተጓዝን ደስታ ፣ ፍቅር ፣ እርካታ እና ነጻነት ደግሞ የህይወት ሽልማት ናቸው።

           ውብ አዳር

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot
854 views19:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-15 19:23:27
"የምትጓዝበት መንገድ ወደ ጥሩ አሊያም ወደ መጥፎ የሚመራው አንተን እንጂ ተመልካችህን አይደለም፤የምትለብሠው ልብስ የሚያሞቀውም ሆነ የሚያበርደው አንተኑ እንጂ የሚያይህን አይደለም፤የምትበላው ምግብ የሚጣፍጠው ወይም የሚመረው አንተን እንጂ ሌላውን አይደለም።

ብዙ ውጫዊ ነገሮች አስደሳች ቢሆኑም ከጊዜ ጋር የተሳሰሩና ሃላፊ ናቸው። ዛሬ ያስደሰተን ጓደኛ ነገ ላይኖር ይችላል ዛሬ ያጌጥንበት ውበት ነገ ይረግፋል፤ ዛሬ የተመካንበት አስተሳሰብ ነገ በቆመበት አይጸናም። ከውጪ የምናገኘው ማንኛውም አይነት ደስታ በመጣበት እግሩ ጥሎን መሄዱ አይቀርም። ከዛም አልፎ ዋጋ ያስከፍለናል። ከጊዜ ጋር የማይለዋወጥ ደስታን ለማግኘት ብቸኛ መፍትሄው ደስታና ሰላምን በውስጣችን መፈለግ ነው። እንደ ኩሬ ውሃ ያነሰች፤ እንደ ኩራዝ መብራት የቀጨጨች፤ እንደ ሰናፍጭ ቅንጣት የደቀቀችም ብትሆንም እንኳን ውስጣዊ ደስታን በልባችን መትከል ነው። ይህ ነው ማንም ሊነካውና ሊደፍረው የማይገባው ስፍራ።

በርግጠኝነት ለሰው ብለን የምንይዘው ማንነት፤ ለኛ በልክ እንዳልተሰፋ ልብስ አያምርብንም፤ ቀላሉ መፍትሄ እራሳችንን መሆን እና፤ መክሊታችንን መኖር ነው። በዚህ ስፍራ ውስጥ ሙሉ ነን፤ እውነተኛ እኛነታችን የሚታየው በዚህ ስፍራ ነው። ወደ ውስጣችን ዘልቀን በዚህ ስፍራ ላይ ቆመን ህይወታችንን ብናየው፤ እንደምናስበው ደካማ አይደለንም፤ የሚጎድለን ብዙ አይደለም፤ ከምንም በላይ በፈጠረን ፈጣሪ አይን ውስጥ ውብና ንጹህ ነን። ታዲያ ከዚህ በላይ ምን አለ? ደስታና ሰላማችን በሰው እጅ ፤ ፍርድና ቅጣታችን በሰው ወንበር ፈጽሞ አይሁን.!!

ውብ ምሽትን ተመኘን

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot
1.3K views16:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ