Get Mystery Box with random crypto!

ስብዕናችን #Humanity

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiohumanity — ስብዕናችን #Humanity
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiohumanity — ስብዕናችን #Humanity
የሰርጥ አድራሻ: @ethiohumanity
ምድቦች: ሳይኮሎጂ
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 30.71K
የሰርጥ መግለጫ

🔆እየጠየቁ መኖር መልስን፣
መልስን ፈልጎ ማግኘት ዕውቀትን፣
እውቀት ነፃነትን፣ ነፃነት ሙሉ ስብዕናን፣
ሙሉ ስብዕና ሠላምና እርካታን፣
እርካታ ደግሞ ደስተኛ ሆኖ መኖርን ያስገኛል፡፡
አብረን እንደግ !!
@EthioHumanity @Ethiohumanity
✍የተሰማቹን አጋሩን! ቤቱ ሁሌም ክፍት ነው፣ሃሳባቹን ፃፍፍ አርጉልን @EthioHumanitybot

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 36

2021-02-12 08:05:20
4.7K views05:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-11 18:33:44 ንባብ

ክፍል [የመጨረሻው ክፍል]

................ እናም እናንብብ! እናንብብ! አሁንም እናንብብ!

ግን እንዴትና ደግሞም ለምን?
ሀሮልድ ብሩም የተባሉ ጸሐፊ “ለምንና እንዴት ማንበብ አለብን?” (How to read and why) በተሰኘው መጽሐፋቸው፣ እንዴት ማንበብ እንዳለብን ሲያብራሩ፤ “ስታነብ ለምታነበው ጽሁፍ ልብህ ክፍት ይሁን፤ የምታነባቸውን ፊደላት በፍቅር፤ በእርጋታና በጽሞና በውስጠኛው ጆሮህ እያደመጥክ በጸጥታ አንብብ፡፡”

ስናነብ ትክክለኛው የልብ ዝንባሌ ሊኖረን ይገባል፡፡ ስናነብ ትክክለኛ የልብ ዝንባሌ ከሌለን ወደ ተሳሳተ ድምዳሜ ልንደርስ እንችላለን። ስናነብ እራሳችንን በባለታሪኮቹ ውስጥ አድርገን ስሜታቸውን ለመጋራት እንችል ዘንድ በፍቅርና በወዳጅነት መንፈስ ሆነን እናንብብ። ጸሀፊው ለምን ማንበብ እንዳለብን ሲገልጹም፤ የምናነበው ምክኒያታዊነታችንን ለማሳደግ እንዲያም ሲል አጠቃላዩን ንቃተ - ህሊናችንን ለማዳበር እናም ደግሞ ከህመማችን ለመፈወስ መሆን አለበት። ማንነታችንን ካላገኘንና እራሳችንን መሆን ካልቻልን፣ ለሌላው ምን መሆን እንችላለን? ሲሉም ይጠይቃሉ። ምክራቸውን እንስማ፤ ጥያቄያቸውንም ለመመለስ እንዘጋጅ፡፡

አመለካከት ማንኛውንም ድርጊት ለማድረግም ሆነ ላለማድረግ የመገፋፋት ሀይል አለው፡፡ ለአንድ ድርጊት የሚኖረን አዎንታዊ አመለካከት፤ ለድርጊት የሚያነሳሳን ሲሆን አሉታዊ … አመለካከት ደግሞ ያንን ድርጊት በንቃት እንዳናከናውን ተነሳሽነታችንን እንደሚቀንሰው በዘርፉ የተደረጉ ጥናቶች ያመላክታሉ። በዚህ ሀሳብ መነሻነትም … ለንባብ ያለንን ተነሳሽነት የሚወሰነው ለንባብ ባለን አዎንታዊ ወይም አሉታዊ አመለካከት ላይ የተመሰረተ ነው ማለት ይቻላል፡፡

በዘርፉ የተካሄዱ የተለያዩ ጥናቶች፤ በልጆች የማንበብ ልምድ ላይ አዎንታዊ ተፅዕኖን ከመፍጠር አንጻር ግንባር ቀደሙን ሚና የሚጫወቱት ወላጆችና መምህራን መሆናቸውን ይገልፃሉ፡፡ ወላጆች የልጆቻቸውን የንባብ ልምድ ከማዳበር አንጻር ሁለት ወሳኝ ሚናዎችን ይጫወታሉ፡፡ አንድም “ድርጊት ከብዙ ቃላት ይልቅ ይናገራል” (action speaks louder than words) እንዲሉ የዳበረ የንባብ ልምድ

ያላቸው ወላጆች መኖሪያ፤ በተለያዩ ጋዜጦች፤ መጽሄቶችና መጽሐፍት የተሞላ እንደመሆኑ፣ የንባብ ጠቀሜታን በተመለከተ ለህፃናት ግልጽ መልዕክትን (ያለምንም ንግግርና ገለጻ) ማስተላለፍ ይችላሉ፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥም ወጣቶች የንባብ ባህልን ከቤተሰቦቻቸው ይወርሳሉ ማለት ነው፡፡፡ እናም ሀገር አቀፍና አለም አቀፍ ሁኔታዎችን ለመከታተል፤ አዳዲስ ነገሮችን ለመማር ወይም ለመዝናናት ከሌሎች ዘዴዎች ይልቅ ንባብን ምርጫቸው ያደርጋሉ፡፡

በሌላም በኩል ወላጆች በካበቱት የንባብ ልምዳቸው አማካኝነት ለልጆቻቸው አዝናኝና አስተማሪ ድርሳናትን በማንበብ፣ በልጆቻቸው የንባብ አመለካከት ላይ አዎንታዊ ተጽዕኖን ማሳደር ይችላሉ፡፤
ከወላጆች ቀጥሎ የህፃናትንና የወጣቶችን የንባብ ባህል በማሳደግ ረገድ ጉልህና የማይተካ ሚና መጫወት የሚችሉት መምህራንና ትምህርት ቤቶች ናቸው፡፡ ተማሪችን እንዲያነቡ የሚያበረታቱ መምህራንና በባለሙያ የሚታገዙና በአግባቡ የተደራጁ ቤተ-መጽሐፍት ያላቸው ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚማሩ ወጣቶች፣ ከሌሎች ይልቅ በእጅጉ የተሻለ የንባብ ልምድ እንደሚኖራቸው ይታመናል፡፡

ይሁንና እስካሁን ድረስ የወጣቶቻችንን የንባብ ልምድ በተመለከተ ሰፊና የተቀናጀ አገር አቀፍ ጥናቶች መደረጉን እርግጠኛ ባልሆንም በአንዳንድ አካባቢዎች ላይ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚገልጹት ከሆነ፤ ወጣቶቻችን ለንባብ ያላቸው አጠቃላይ አመለካከት በአብዛኛው አሉታዊ እንደሆነ አመላካች ናቸው፡፡

ፕሮፌሰር አለም እሸቴ በቅርቡ በአዲስ አበባ ወጣቶች ላይ ያካሄዱት የጥናት ውጤት ይሄንኑ እውነት ፍንትው አድርጎ ያሳየናል፡፡ ፕሮፌሰሩ ወጣቶች ለምን እንደማያነቡ ላቀረቡላቸው ጥያቄ፣ ከሰጧቸው ሰበቦች መካከል እስቲ ጥቂቱን ለአብነት ያህል እንመልከተው፡-
ንባብን ከቤተሰቤ አልለመድኩትም፡፡
በአካባቢዬ ብዙ ቤተ - መጻሕፍት ቤት ስለሌለ አንብብ፤ አንብብ አይለኝም፡፡
ይሄ የአውሮፓ እግር ኳስ እያለ በየት በኩል ላንብብ?
ትላልቅ መጽሐፍትን ሳይ ተስፋ ስለሚያስቆርጡኝ አላነብም፡፡
አንብቦ ለመረዳት ችግር ስላለብኝ ሳነብ አይገባኝም፡፡
የሚሰለቹ መጽሐፍት በመብዛታቸው ምክኒያት አላነብም፡፡
በጊዜ ማጣት ምክኒያት አላነብም፡፡
ለምን እንደማላነብ ራሴም ምክኒያቱን አላውቅም፡፡
መጽሐፍ የማላነበው ለዓይኔ ስለምፈራ ነው፡፡

ወጣቶቹ ላለማንበባቸው የጠቀሷቸውን ሰበቦች ጠቅለል አድርገን ስንቃኛቸው፣ ለወጣቶቻችን የንባብ ችግር ዋነኛው ምክኒያት፣ የንባብ ፍላጎት ማጣት ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ለዚህም ከወጣቶች የንባብ ልምድ ጋር ተያያዥነት ባላቸው የጥናት ድርሳናት እንደምክኒያትነት የሚጠቀሰው የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያዎች ጫና፤ (እዚህ ላይ የእነ ቃና፤ የእነ ዲኤስ ቲቪ፣ የእነ ኤምቢሲ፤ የእነ ኤምቲቪ ወዘተ … ቻናሎች ለአብነት ይጠቀሳሉ፡፡)

በተጨማሪም በሉላዊነት ሳቢያ፣ ገደብ ያልተበጀላቸውና ከምዕራቡ ዓለም በብርሃን ፍጥነት እየተሰራጩ ያሉ የአሉታዊና መጤ ጎጂ ልማዶች መስፋፋትና ወረራ፤ እንዲያም ሲል ወላጆች፣ መምህራንና ትምህርት ቤቶች የንባብን ባህል ከማዳበር አንጻር መጫወት የሚገባቸውን ሚና በአግባቡ መጫወት አለመቻላቸው ነው፡፡
በመጨረሻም በተለይ ህፃናቱንና ወጣቶችን ወደ ንባብ ባህልና ልምድ ለማምጣት ሁላችንም የድርሻችንን ማድረግ እንደሚገባን መዘንጋት የለብንም፡፡
እናንብብ! እናንብብ!

ታደሰ ለገሰ
ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot
5.2K views15:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-10 22:40:36 ንባብ

ክፍል 1

ንባብ በግለሰብም ሆነ በማህበረሰብ ህይወት ውስጥ ትልቅ ስፍራ ሊኖረው የሚገባ መሰረታዊ ክህሎት ነው። የሰው ልጅ ሰብዕናውን የሚቀርፅበትና የማንነቱና የምንነቱ መገለጫ የሆኑትን ባህላዊ፣ ትረካዊና ሥነ ጥበባዊ ቅርሶቹና ዕሴቶቹ እንዳይጠፉ ለቀጣዩ ትውልድ ጠብቆ የሚያቆይበት፣ የሚያስተላልፍበትም ዓይነተኛ መሳሪያም ነው፡፡

ማንበብ የማይችል ግለሰብም ሆነ ማህበረሰብ፤ አካባቢውን የማወቅና የመግለጽ ብቃቱ፣ በማየትና በመስማት ላይ ብቻ የተመሰረተ በመሆኑ፣ ለማንኛውም የፈጠራም ሆነ የዕውነታ ጽሁፍ ዕውቀቶች እንግዳና ባይተዋር ይሆናል፡፡ ስለ ሕይወትና ስለ ተፈጥሮ … ስለ ከባቢያዊና ዓለም አቀፋዊ ኩነቶች ያለው ግንዛቤ ውሱንና የተዛባም ይሆናል፡፡

የዳበረ የንባብ ልምድ በቋንቋ የመጠቀም ብቃታችንን ከማሳደጉም በላይ ሂሳዊ አስተሳሰብና ሚዛናዊ ግንዛቤ እንዲኖረን ያደርጋል፡፡ የዳበረ የንባብ ልምድ የሌሎችንም ሀሳብና ስሜት በቀላሉ ለመረዳትና ከማንኛውም አቅጣጫ ለሚሰነዘሩ አዎንታዊም ሆኑ አሉታዊ አስተያየቶች ምክኒያታዊና በሳል፤ ቁጥብና ገላጭ በሆኑ ቃላት ፈጣን ምላሽን መስጠት የሚያስችል ብቃትና ክህሎት ያስታጥቀናል። ንባብ በአንድ ጉዳይ ላይ ትኩረትን ሰብስቦ የማሰብና የማሰላሰል ጠቃሚ ልምድና ብቃትን ያጎናጽፈናል። ታላላቅ ሳይንቲስቶችና ኢንጂነሮች፣ ስመ ጥር ደራሲያን፤ ጸሐፌ ተውኔቶች፤ ሰዓሊያን፤ ገጣሚያንና ባለቅኔዎች ወዘተ የሚፈጠሩት በዳበረ የንባብ ምናባዊ ዓለም ውስት ነው፡፡ ምናባዊ ወደ ሆነው የንባብ ዓለም ውስጥ ስንገባ፣ ግዑዙንና ገሀዱን ዓለም ጥለን፣ በታላቅ ጸጥታና ተመስጦ፣ በስፍራና በጊዜ በማይለካና በማይወሰን፣ ጥልቅና የትየለሌ ወደሆነው የዕውቀትና የጥበብ ዓለም ውስጥ እንገባለን፡፡

ከዚህ ምናባዊ የንባብ ዓለም ከምናገኘው ድንቅ የትኩረትና የተመስጦ ተመክሮ፤ በህይወት ጉዞአችን ውስጥ ሊያጋጥሙን የሚችሉትን ተግዳሮቶችና ፈተናዎች እንዴት መወጣት እንደምንችል እንማራለን። ውስብስብ ችግሮችን የመፍታት ብቃታችንን እናሳድጋለን፡፡ ከንባብ ጋር የሚኖረን ጥብቅ ቁርኝትና ትሥሥር ለሕይወትና ለተፈጥሮ የምንሰጠውን ዋጋና ክብር በእጅጉ ይጨምራሉ፡፡ የተለያዩ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት፤ የዳበረ የንባብ ልምድ ያላቸው ግለሰቦች፣ የንባብ ልምድ ከሌላቸው ግለሰቦች ይልቅ በሦስት እጥፍ የተፈጥሮ እንክብካቤና የበጎ አድራጎት (ሰብዓዊ) ድርጅቶች በሚያደርጓቸው እንቅስቃሴዎች ውስጥ ንቁ ተሳታፊዎች ናቸው። ይህ ዓይነቱ ንቁ ተሳትፎ አንባቢያንን በጎ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ከማድረጉም በላይ ለግለሰቦችም ሆነ ማህበረሰቦች ደህንነት በእጅጉ ተቆርቋሪና ኃላፊነት የሚሰማቸው ዜጎች እንዲሆኑ አስችሏቸዋል፡፡

ንባብ ጭንቀትንና ውጥረትን በማስወገድ ዘና እንድንል ይረዳናል፡፡ በንባብ አውድ ዙሪያ የተካሄዱ የተለያዩ ጥናቶች፤ ጭንቀትን እንደሚቀንስ ደርሰውበታል። ለስድስት ደቂቃ ጸጥ ብሎ ማንበብ የልብ ምትን ያረጋጋል፡፡ የተኮማተሩ የአካሎቻችን ጡንቻዎች ዘና እንዲሉ ያደርጋል፡፡

ንባብ እራሳችንን ለማስደሰትና ለማዝናናት ያስችለናል፡፡ በደራሲያን በጸሐፌ ተውኔቶችና በገጣሚያን የፈጠራ ሥራዎች ውስጥ የምናገኛቸው ገጸ-ባህሪያት በተሳሉበት ምናባዊ ዓለም ውስጥ የሚያደርጉት ልብ አንጠልጣይ እንቅስቃሴ፣ ለአእምሮአችን ምናባዊ ፍሰሀን ያጎናጽፈዋል፡፡

ንባብ ከማዝናናትም ባሻገር የህይወት ክህሎታችንን በማሳደግ ያስደንቀናል፡፡ ንባብ ከፊልምና ከቴሌቪዥን ከምናገኛቸው መረጃዎች ይልቅ የአስተሳሰባችንን አድማስ የማስፋትና ምናባዊ እይታችንን የማሳደግ ብቃት እንዳለው የተለያዩ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ የሚያሳዝነው ግን አስቂኝ ፊልሞችና የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች ከሌሎች ነገሮች ጋር ተዳምረው ንባብ በብዙ ሰዎች ህይወት ውስጥ ቦታ እንዲነፈገው ምክኒያት ሆነዋል፡፡ አንድ ሰው አዘውትሮ ቴሌቪዥን የሚመለከትና እምብዛም የማያነብ ከሆነ፣ የማንበብ ችሎታው ብቻ ሳይሆን በትክክል የማሰብና የማመዛዘን እንዲሁም ሀሳቡን አቀነባብሮ የመግለጽ ችሎታው ሊቀንስ እንደሚችል በጥናት ተደርሶበታል።

ማር ዎልፍ የተባሉ ጸሐፊ፤ “የአንባቢ አእምሮ ታሪክና ሳይንስ” (The Story and Science of the Reading Brain) በተሰኘ መፅሐፋቸው እንዲህ ብለዋል፡- “ስታነብ ለማሰብ ወይም አንድን ነገር ለማሰላሰል ጊዜ ይኖርሃል፡፡ የማሰቢያ አፍታን ታገኛለህ፡፡ በሌላ በኩል ፊልም ወይም ቴሌቪዥን ስትመለከት አልያም ሬዲዮ ወይም ቴፕ ስታዳምጥ ወደ ውስጥህ የማየትና የማሰብ ጊዜን አታገኝም፡፡ ይህ የንባብ ሂደት ውስጥ የምታገኘው አፍታ፣ የማሰብና የማስታወስ ችሎታህን በእጅጉ ያዳብረዋል፡፡”

ለማጠቃለል በተፈጥሮ ሳይንስ፤ በማህበረሰብ ሳይንስ፤ በፍልስፍና ታሪክ፤ በስነ - ጥበብና በሌሎችም ዘርፎች ያለን ዕውቀት ሊሰፋና ሊያድግ የሚችለው በንባብ ነው፡፡ንባብ በዕውቀትና በጥበብ የተካነ፣ ማንነቱንና ምንነቱን የተረዳ፣ ሁሉን ጠያቂና ተመራማሪ፣ በየተሰማራበት የሙያ መስክ ስኬታማ የሆነና እራሱንም ሆነ አገርና ወገኑን የሚጠቅምና የሚያሳድግ፣ ደስተኛና የተረጋጋ ሕይወት ያለው ዜጋ እንዲኖረን ያስችለናል፡፡

ከታሪክ ሂደት መረዳት እንደምንችለው፤መጪዎቹን ዘመንና ትውልድ መቆጣጠርና መምራት የሚችሉት በፈርጣማ ጡንቻዎቻቸው የሚያስቡ አምባገነኖች ሳይሆኑ በዳበረ የንባብ ልምድ የበለጸገ አዕምሮና ብሩህ አስተሳሰብ ያላቸው አንባቢማህበረሰቦች ስለመሆናቸው አንዳችም ጥርጥር ሆነ ብዥታ ሊኖረን አይገባም፡፡ እናም እናንብብ! እናንብብ! አሁንም እናንብብ!

ይቀጥላል......

ታደሰ ለገሰ

ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot
5.8K views19:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-10 17:52:08
"ውበትን የምታገኙት የማይታየውን ስታዩ ነው፤ በግልፅ ያልሆነውን ስትረዱ ነው፤ ድምፅ የሌለውን ንግግር ስትስሙ ነው፡፡

ውበት፣ በውስጣችሁ ተጀምሮ ከሥጋዊ ፍላጐቶቻችሁ ባሻገር የሚያበቃ ድንቅ የሀዘንና ደስታ ውህድ ነው፡፡ልቦና ውስጥ የሚገኝ ብርሃን ነው።"

ካህሊል ጂብራን

@EthioHumanity
@EthioHumanity
5.4K views14:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-09 21:19:18 ሰዓት እላፊ! (ምናለ ሁሉም ሴቶች እንደ አንቺ ቢሆኑ)



በሳቅሽ ነው እንጂ!
ባሳማኝ ስብከትሽ፥ ሰላም ጠፋ ብለን፣
ሼኹ ከፋ ብለን፣
ከመቅደስ ያልራቅን፥ ማነብነብ ያልተውን።
.
ባንቺ ባይሆን ከመቅደሱ መድረክ የተሾመው አሽሙረኛ ሰባኪ ከኮማሪዋ እኩል ቀልብያችንን ጥላሸት ሲቀባው ኤዲያ ብለን በወጣን ነበር። ተስፋ ቆርጠን በእንብርክክ በቆምን ግዜና ተብሲራቱን አንቺ ባነግሪን ከቶ ምን ነበርን? የመንደራችን ሰባኪ እና አጋፋሪዎቻቸው የእዝነቱን መምህር አስተምህሮ እያነበነቡ በጳውሎስ የወንጀል ውርስ አስተሳሰብ ምርኮ ተይዘው ሲያገሉ፤ ወንድማቸውን ሲገሉ ገለውም በእሬሳ ላይ ዳንኪራ ሲቆሙ በቃን ባልን ግዜና "ለጫማ ሲል ወንድሙን የሚገል ተምሳሌት አቅርበሽ በርቱ!" ባትይን መውደቂያችን የት ነበር? አንዳንድ ነፍሶች በዝምታ ይግባባሉ ብለሽን ነፍስያችንን ካንቺ እናቆራኛት ዘንድ ባታረጊን ምን ነበርን?
.
ፈገግ ብትይ እንጂ!
አማን በሌለበት አገር አማን የምል፣
ምክርሽን ሰምቼ ቀዬው ሰላም ብዬ፣
ጥላቻ ረስቼ፥
ከእንቅልፌ ምነሳ በእርሱ ተመጅኜ።
.
ስብከቱ ጥላሸት ቀብቷቸው የጠቆሩ፤ መንደሩ በጥሎ ማለፍ ተሞልቶ አቅም የለኝም ብለው የሸሹ፤ በጥቅሉ ስለሚዳው የማያውቁ መንፈሳዊነትን ትተው ከቁስ ሲዋጡ መፍትሄ ምን ይሆን ብሎ ላብሰለሰለ ያንቺ እና የወዳጆችሽ ስብከት እንጂ ከቶ ሌላ ምን ይታየዋል?
.
በሳቅሽ ነው እንጂ!
ፅልመት የሚገፈፈ ጨለማ ሚበራ፣
ነዳያን የሚጠግብ ድብልቁ ሚጠራ።
መገን!
እንደው ባንተው መጀን ዱበርቲ ያዳራ፣
በደስታ ታጠኚ ፊትሽ በሳቅ ያብራ።
መገን!
እንደው ባንተው መጀን!
እንደው ባንተው መጀን ሺህ አመት አኑራት፣
ብርታት አቆይላት!
ጉልበት መርቅላት፣
ይሁን!
ይሁን!
መቼ? አሁን!(በዱበርቲኛ ቢነበብ)
ጭንቀትዋን አጥፋላት!
እውቀትዋን አብዛላት፣
ስብከት ይመርላት፣
ሀሳቧ ይሙላላት፣
እንደው ባንተው መጀን!
እንደው ባንተው መጀን!
ሳቋን እያቆየህ በተስፋ አለምልመን።


ሰላም እደሩልኝ!

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity
@Nagayta
5.6K viewsedited  18:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-09 21:17:33
4.8K views18:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-08 22:01:42 ሰዓት እላፊ ፀዴ ቀደዳ (የእኔ ቼ! )


ስፓኒሽኛ ትችላለህ? ሲሉኝ! አዎ እላለው። ምሉዕ ስለሆንከው ስላንተ Hasta Siempre, Comandante በሚል የተዘፈነ አንድ መዝሙር በቃሌ አለና። ማፍቀርን የተማርኩት ባንተ ነው! በዙርያዬ ካሉ ወለፈንዲዎች ይልቅ ስላንተ የሰማውት ሰውነትን እንድረዳ፤ ለተበደለ እቆም ዘንድ ሰበብ ሆኖኛል። ከቤተ መቅደሱ ደጃፍ ከተሰበክነው ይልቅ አንተ የመፅሐፉን ኖረኸዋል። በጨለማ ጨረቃ፤ ለታረዘ መሸፈኛ፤ ለተጠማ እርካታ ቆራጭ ነህ! አንተን ማፍቀር የተማርኩት በከፍታህ ተጨንቀው፤ በሚያብብ ልዕልናህ ፈርተው በ ሰማያችን ላይ ብልጭ ያልከው ብርሀናችን ሊያጠፉ የተሰባሰቡ ግዜ ነው። በሞትህ የሚሊየኖችን ቀልብ ገዝተሀል!

We learned to love you
from the historical heights
where the sun of your bravery
laid siege to death

ገዳዮችህ ፈሪ ነበሩ! ያፈኑህ መስሏቸው አገነኑህ፤ ያጠፉህ ይመስል ትግልህ ያፈራ ዘንድ ሰበብ ሆኑ። ስራህ በጥልቅ ሰመመን ያለ ሁሉ ቢሰማው ከእንቅልፉ ያነሳዋል። ካለበት ቅዥት ያነቃዋል! ገዳዮችህ ከእነ ግርብራበሮቻቸው ሀሳብህን ሊደፍቁ ቢሞክሩም በሳንታ ክላራ ያለው አፀደ ሰውነትህን ይፈሩታል! ስምህ ሲነሳ ብርክ ይይዛቸዋል።

Your glorious and strong hand
over History it shoots
when all of Santa Clara
awakens to see you

በስቃይ ሳለን ነበር የመጣህ። ባባርነት ቀንበር መሀል ሆነን ከ ፊታችን አንዳች ፈገግታ እንኳ አልነበረም። የስቃያችን ጀንበር ጠልቃ ሰላም እንሆን ይሆን? ወይስ ከነስቃዩ ወደ ሚሉት ድቅድቅ ጨልማ እንገባ ይሆን ስንል ነበር። አንተ ግን ቀልብ የሚያረደው ፈገግታህን ይዘህ መጣህ! ነፃ መሆን ይቻላል "ከታገልክ/ሽ" ብለህ በአንባገነኖች ደጃፍ የነፃነትን ባንዲራ ተክለህ አሳየሀን።

You come burning the breeze
with springtime suns
to plant the flag
with the light of your smile

ለሰው ልጅ ያለህ ፍቅር በ መንግስትም በቤተክህነት ወንበር ተለጥፈው የድሀውን ጉርሻ እንደሚነጥቁት ትቀመጥ ዘንድ አላረገህምና ብርቱ እርዳታህን ለሚሹ ሁሉን ትተህ እንደሄድክ አውቃለው። ነፃ አውጪ አይደለውም ብለሀል! አዎ ማንም በራሱ እንጂ በማንም ነፃ አይወጣም። አንተ ግን ወደ ነፃነት መንገድ የምትወስደን እረኛ ነበርክ።

Your revolutionary love
leads you to new undertaking
where they are waiting for the firmness
of your liberating arm

ብትሞትም! አፀደ ነፍስህ ከስጋህ ብትለይም ራዕይህ በቀልቦቻችን አሉ። ለልጅ ልጆቻችንም ይደርሳል! ትግልህ ያፈራ ዘንድ ሁሌም ሁሌም በመንገድህ ነን። ረሀብ፣ በደል፣ መታረዝ እና ስቃይ መቼም መቼም ከጎዳናህ እናፈነግጥ ዘንድ አያደርገንም።
.
.
.
"Until forever, Commander!"
.
usaid

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity
@Nagayta
6.1K views19:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-08 21:59:14
5.1K views18:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-08 07:52:32 #ሁላችሁንም በጣም አመሰግናለሁ አብዛኛው ሰው እንዳነበበው መልእክቱን በውስጥ መስመር ከሚመጣው ሰው ማየት ችያለው የተጠቀሰውን መፅሐፍም ብዙሃኑ ጠይቆኛልና ከዚህ በታች አስቀምጣለሁ....

የንባብ ሳምንት ይሁንልን!

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity
@Nagayta
5.1K views04:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ