Get Mystery Box with random crypto!

ስብዕናችን #Humanity

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiohumanity — ስብዕናችን #Humanity
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiohumanity — ስብዕናችን #Humanity
የሰርጥ አድራሻ: @ethiohumanity
ምድቦች: ሳይኮሎጂ
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 30.61K
የሰርጥ መግለጫ

🔆እየጠየቁ መኖር መልስን፣
መልስን ፈልጎ ማግኘት ዕውቀትን፣
እውቀት ነፃነትን፣ ነፃነት ሙሉ ስብዕናን፣
ሙሉ ስብዕና ሠላምና እርካታን፣
እርካታ ደግሞ ደስተኛ ሆኖ መኖርን ያስገኛል፡፡
አብረን እንደግ !!
@EthioHumanity @Ethiohumanity
✍የተሰማቹን አጋሩን! ቤቱ ሁሌም ክፍት ነው፣ሃሳባቹን ፃፍፍ አርጉልን @EthioHumanitybot

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 33

2021-02-28 18:41:37
Canon 5D mark 3
With 24 -105 lense
322 views15:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-27 08:23:20 #እምወድሽዋ! ቅዳሜዋ! ሸጋዬ


፩ .
ሰዓዲ ይቀጥላሉ

"ከፀደይ ደመና አንዲት የዝናብ ጠብታ ወደ ምድር ወደቀች - ሰፊውን ባህር ስታይ በሀፍረት አቀረቀረች :: እንዲህም አለች :- " ባህሩ ሁሉ በሞላበት ፤ እኔ የት ነኝ ?በእርግጥም በህለውና የለሁም ልበል እንጂ ! "

በሀዘን ስታንጎራጉር በነበረበት ወቅት ነው አንድ የባህር ኦይስተር [Oyster] ወደ ሆዱ ውጦ ያስቀራት ፤ እጣ ክፍሏም ከትንሽ የዝናብ ጠብታ ወደ ክቡር ታላቅ የከበረ - ማዕድን ወደ ዕንቁነተ ቀየራት :: "

"ይሄው ነው" ይላሉ :- "አየህ ትሁት ነበረች ፥ ተከበረች ፤ ያለ መኖርን በር አንኳኳች ፥ ራሷን አሳነሰች ህልው የክቡራን ፅዋ - ተርታ ተቸራት :: "

፪.
አሁንም ሰዓዲ ይቀጥላሉ
ቀዘል አርሰላን ብርቱ የቤተ-መንግስት አጥር ነበረው - ቁመቱ ከ አልወንድ ተራራ የሚስተካከል [alofty mountain situated in Hamden , north-west of Isfahan] :: ከግንብ አጥሩ ውስጥ እንደ ሙሽራ ፀጉር በአፀደ - ፅጌያቱ ውስጥ እየተጠማዘዙ የሚዘልቁ ጎዳናውች ሞልተውታል ፤ በውስጧ ያሉ ኖሪዎቿ ሁሉ ያላንዳች ስጋት የተጠበቁ ነበሩ ::

ቀዘል በአንድ እለት - አንድ ጠቢብ መንገደኛ ያገኝና ይጠይቀዋል - ባንዳች የኩራት መንፈስ

" ከዚህ በፊት ይህን የመሰለ ብርቱ ግርማም የግንብ አጥር በተጏዝክበት ሁሉ አይተህ ታውቅ ይሆን ?"

" በእርግጥ ግሩም ነው !" ብሎ መለሰና :- " ነገር ግን አንዳች ብርታት እንደ ጎደለው አስባለሁ ፤ ካንተ በፊት የነብረው ንጉስ እጅ ላይ እንደ ነበር ሳስታውስ ፣ አሁንም ካንት በኇላ በሚነግሰው እጅ ላይ መውደቁን ሳስብ፣ ከዛም ደግሞ የነገሰው ንጉስ ከተስፋህ አፀድ ውስጥ ያሻውን ፍሬ ሲቢላ ይታየኝና - እውንትም አንዳች ጉልበት ፥ የሚመክትበት የተነሳው ነው እላለሁ :: "

In the estimation of the wise , the world is a false gem that passes each moment from one hand to another .

፫ .
አንድዎን የወሎ ሼኽ አንድ ያዲስ አበባ ሰው ሊኻድማቸው ወስዳቸው አሉ :: አሉ ነው መቼስ

ሁሉ ሁሉ ቀረበ ፣ ተበላም ተጠጣም :: ዱዓ ተያዘ ::

"ሼኾቹ እንግዲህ ያማረ ሀብት ፣ ያማረ መሬት ፣ ያማረ ቦታ ነው 'ምሻ በሉ ዱዓ ያርጉልኝ " አለ ከፊት ሆኖ እያያቸው

"እንግዲህ " አሉ :- " እንግዲህ አላህ ታንዱ ወስዶ ቲያበቃ ላንዱ ነው 'ሚሰጥና .. " እንዳሉ ሳያስጨርሳቸው

" ኧረ እነ ሸኽ እኔ የራሴን ነው 'ምፈልገው "

ቆጣ ብለው መለሱ :-

" ኧረግ ታያ ላንተ ተብሎ አዲስ መሬት አይዘረጋ !"

ምንጭ -Sa'adi collected works (Delphi classics)

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity
@balmbaras
3.0K views05:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-27 08:22:30
2.6K views05:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-26 17:49:49
ልብህ ያሰበውን ጥሩ ነገር ከመፈጸም አትቦዝን። ሃሳቡ በውስጥህ አርጅቶ እስኪሞት አትጠብቅ። ሰዎች ምን ይሉኝ ብለህ አትፍራ። ሰዎች ብትሠራም ባትሠራም የሆነ ነገር ማለታቸው አይቀርም። ብቻ መጠንቀቅ ያለብህ አንድ ነገር አለ። ያም ነገር ድርጊትህ በጎ መሆን አለመሆኑን ማረጋገጥ ላይ ነው። ድርጊትህ ጥሩ መሆኑን ካመንክበት ለመተግበር ተጣጣር።

ድርጊትህ ሙሉ በሙሉ ባይሳካ እንኳ በመሞከርህ ብቻ የህሊና እረፍት ታገኛለህ። በተከታታይ ከሠራህ ደግሞ እየሠራህ ማሻሻልህ አይቀርም።

ጥሩ ነገር ለማድረግ ምቹ ጊዜ አትጠብቅ። ምቹው ጊዜ ሃሳቡ ወደ ጭንቅላትህ የመጣበት ጊዜ ነው።

መማር ባለብህ ጊዜ ተማር፣ መሥራት ባለብህ ጊዜ ሥራ፣ መዝፈን ባለብህ ጊዜ ዝፈን፣ መዘመር ባለብህ ጊዜ ዘምር፣ መጻፍ ባለብህ ጊዜ ጻፍ፣ ማረፍ ባለብህ ጊዜ እረፍ።
Toughe G kebede

ውብ አሁን

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
3.3K views14:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-26 08:06:16 ለጁምኣችን


የሀይማኖት መብት ሳይከበርላቸው በሀገራቸው እንደ ሁለተኛ ዜጋ እየታዩ የሀይማኖት፣የኢኮኖሚ እና የመሳሰሉት ጥያቄ እያለባቸው....ስለ ሀገራቸው ክብር የንጉሱን ጥሪ ተከትለው ለዘመቱት የሙስሊም ገበሬዎችና የጦር አበጋዞች እንዲሁም ለሁሉም የአድዋ ዘማቾች ክብር ለነሱ!

ክርስትያኑ ንጉሥ ነገሥት በማርያም እየማለ ተከተሉኝ ያለውን አዋጅ እና የዘመቻ ጥሪ ተቀብሎ የሃይማኖት ልዩነት ሳይገድበው ለእናት ሀገሩ እና ለራሱ ክብር ሲል የተዋደቀው ይህ ሙስሊም የእግረኛ እና ፈረሰኛ ጦር የሀገራችንን ዳይቨርስቲ ደመቅ አድርጎ ከሚያሳዩ ምንጊዜም ከማይረሱ ሁነቶች ውስጥ የሚመደብ እና ክብር የሚገባው ነው።

#ሙስሊሞቹ የጦር አበጋዞች እና ዓድዋ

በተለያዩ ጠሀፊወች በተደጋጋሚ እንዳስተዋልነው በታላቁ የአድዋ ጦርነት ለድሉ ከፍተኛውን ድርሻ ያበረከተው በራስ ሚካኤል ዓሊ ሥር የዘመተው የፈረሰኛ ጦር ነበር፤ በሌላ ግንባር ሲዋጉ የተማረኩት የጠላት ወታደሮች ሳይቀር የሚወረወረውን የፈረሰኛው ጦር ሚና እጅጉን የላቀ መሆኑን ሳይዘነጉ ቃላቸውን ሰጥተዋል። ይህ ጦር በዓድዋ ጦርነት ወቅት ከንጉሠ ነገሥቱ ምኒልክ በእስከ ቀኝ በኩል ተሰልፎ የጠላትን ጦር እንዳልነበር ያደረገ እና ውሽመጣቸውን የቆረጠ ነበር። በጦርነትም ጄነራል አልበርቶኒን ሊረዳ የመጣውን በጄነራል ዳቦርሜዳ የሚመራውን ሙሉ ብርጌድ ለወሬ ነጋሪ ሳያስቀር የደመሰሰው ይኼ ፈረሰኛ ሰራዊት ነው። የጄነራል ዳቦርሜዳ ሬሳ እንኴን አልተገኘም፤ ምንም ምርኮኛም አልነበረም። እንደሚታውቀው ይኼ ጦር Proper Wollo ከሚባለው የዛሬው ደቡብ ወሎ ክፍል የተውጣጣ በአብዛኛው የእስልምና ተከታይ የነበረ የገበሬ ወታደር ሲሆን በሙስሊም የጦር አበጋዞችም ይመራ ነበር።
.
ከታዋቂወቹ ከእነዚህ ሙስሊም ጦር አበጋዞች ዋናዋናወቹ የእርቄው ገዢ የሞሀመድ ቃንቄ ልጅ ደጅ አዝማች ይመር ሞሀመድ፣ የዓሊ ቤት ገዥ ራስ በሽር፣ የኮሬብ ገዥ ደጅ አዝማች ሊበን በሽር በጉልህ ስማቸው የሚነሳ ነው። አንዳንድ የውጭ ሀገር የታሪክ ጠሀፊወች ሀገራችንን ከውጭ ሆነው ክርስትያን ነገሥታቱን ብቻ በማየት በርካታ ሙስሊም ማህበረሰብ መኖሩን በመዘንጋት በጣፏቸው ማስታወሻወች ይኼን የእስልምና ተከታይ የዓድዋ ዘመቻ እግረኛ እና ፈረሰኛ ጦር በዓድዋ ላይ ያደረገውን ተጋድሎ ለክርስትያን አገር የተከፈለ መስዋትነት በማለት ድሉን ለማጥበብ ይሞክራሉ። ክርስትያኑ ንጉሥ ነገሥት በማርያም እየማለ ተከተሉኝ ያለውን አዋጅ እና የዘመቻ ጥሪ ተቀብሎ የሃይማኖት ልዩነት ሳይገድበው ለእናት ሀገሩ እና ለራሱ ክብር ሲል የተዋደቀው ይህ ሙስሊም የእግረኛ እና ፈረሰኛ ጦር የአገራችንን ዳይቨርስቲ ደመቅ አድርጎ ከሚያሳዩ ምንጊዜም ከማይረሱ ሁነቶች ውስጥ የሚመደብ እና ክብር የሚገባው ነው። ዓድዋ ከተካሄደ ከሁለት ዓመት በኋላ የትግራዩ ራስ መንገሻ ሲያምጥ ከራስ መኮነን ጦር ጋር ተቀናጅቶ በቀላሉ ራስ መንገሻን በቁጥጥር ሥር ያዋለው በእነ ራስ በሽር እና ፊታውራሪ ሥራህ ብዙ የሚመራው ይኼው ጦር ነበር።
.

ሸጋ ጁምኣ!

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity
@balmbaras
3.6K viewsedited  05:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-26 08:05:42
3.1K views05:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-25 20:59:32
በዚህ አለም ከላይ ስንደርስ ታች የነበርንበት ከንቱ ይሆናል፣ የጨበጥነውን እንረግጣለን፣ ክብር የሰጠነውን እናዋርዳለን፣ <ከዚህ በላይ የለም> ያልነውን ተራ ነገር እናደርገዋለን፤ አለሙ እንደዚሁ ነው። ንፋስ እንደመከተል ነው፣ የሚያረካ የሚያስደስት ምንም ነገር የለም።"

"ጊዜ ሲረዝም እድሜ ሲያልቅ ደሞ ሞት ነው። ሞት መራራ ከሆነ ምነው የጊዜ መባከን ቢያንስ ህመም አይሆንብንም? ሰው ቀጥሮህ ሲቀር ከእድሜህ እየቀነሰብህ ነው። የሆነ ሰው ያለ አግባብ የወሰደብህን ገንዘብ አንድ ቀን ሊመልስልህ ይችላል፤ የወሰደብህን ጊዜ ግን መቼም አይመልስልህም። አንድ ሊቅ እንዳለው ለሰው የምትሰጠው ትልቁ ስጦታህ ጊዜ ነው። እንዴት? የሰጠኸው ጊዜ ከእድሜህ ላይ የቀነስከው ነውና!"

"...መጥፎ ሰው ጥሩ ባለሙያ ሊሆን አይችልም፤ መጥፎ ባለሙያም መልካም ሰው ሊሆን አይችልም። የተዋጣላችሁ ለሀገር ለወገን መከታ የምትባሉ ምሁር ባለሙያ የምትሆኑት የተስተካከለ ስብዕና ሲኖራችሁ ነው።

ቅንነትን፣ደግነትን፣አዛኝነትን፣ታታሪነትን ለመማር ዝግጁነትንና ፈጣሪን መፍራትን ገንዘብ አድርጉ። በጋራ መስራት እንጂ በጋራ ማሰብ አይቻልም። ብቻችሁን ሁናችሁ አስቡ ስራ ላይ ግን ተባበሩ!"

በፍቅር እደሩ

@EthioHumanity
@Ethiohumanity
3.9K views17:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-23 20:08:43 ለምሽታችን!



ሰብዓዊነት የገዘፈበት የፍትህ ኮከብ!


ምነም እንኳን የአርጀንቲናዊ ተወላጅ ቢሆንም እሱ ለኔ አገር አልባ የዓለም ነው። እሱ ብዙ ነው ፊዚስት፣ፀሀፊ፣አስተማሪ፣ዲፕሎማት፣
የጦርሀይል አዛዥ እና የመብት ተሟጋች ነው ። ይህ ሰው ማነው
ስመ ገናናው ዓለማቀፋዊው የነጻነት ፋኖ ተዋጊ .....ኤርኔስቶ ቼ ጉቬራ
ያላደለው በቀበሌ ፤ በወረዳ ፤በብሄር ፤በሃይማኖት ተሰባጣጥሮ በጎጥ ተተብትቦ
ይጣመዳል ይቧቀሳል የኔ ጀግና ኤርኔስቶ ቼ ጉቬራ ለዘመዶቹ ለሰው ልጆች ዘብ ይቆማል
ይህ ሰው ቅዱስ ነው።ቅድስና ማለት ህይወትቱን ሙሉ ለሰው ልጆች ነፃነት መታገል
ብሎም አንድያ ነፍሱን መገበር አይደለምን ?ካለምንም ስስት ማንነትን ዘርን ሳይቆጥር ሰው
መሆን ክብር ነው ብሎ ለሰው ልጆች ነፃነትን ሊለግስ አቅም አልባዎችን አለሁላቹ እሚል
ለኔ ይህ አለማቀፍ የነፃነት አርበኛ ቅዱሴ ነው።


አለም ህዝቦቿ ሁሉም ሰዎች በእኩልነት እና በሰላም ይኖሩ ዘንድ ለማየት ተመኘ
ህልሙንም እውን ለማድረግ ጣረ ይህ ክንፍ አልባ በምድር የተመላለሰ መልአክ ነው።
እውነተኛ ኮሚኒስት ነው ኮሚንዝም የአለም ማህበረሰብን ወደፊት እሚያስጉዝ እና አዲስ
ማህበረሰብን ለመፍጠር ያስችላል ብሎ ለሰው ልጆች እኩልነት ለማምጣት ከጨቋኞች ጋ ታገለ ማን ?....ዶክተር ኤርኔስቶ ቼ ጉቬራ የአለም ሰዎች በሰላም የመኖር እና ያለመኖር እጣ ፈንታ በልእለ ሃያል አገሮች መውደቅ ፍትሃዊነት የገደለው ነው ያለው ኤርኔስቶ ቼ ጉቬራ ወደ ሰሜን አፍሪካ አቀና በአልጄርያ
እርእሰ ከተማ በአልጀርስ ንግግር አደረገ ቋንቋው ሁሉ ጭቆና ፤ ግፍ ፤በደል ይቁም ነው ።


ይህ ፍትሀዊ የፍትህ ተወርዋሪ ኮኮብ
በምድር እነሆ ላይፈዝ በሰው ልቦች ደሞቆ እና ህያው ሆኖ አልፏል።
# ስለአለማቀfዊነት ! ስለ ሰውነት ጥግ ሳስብ አእምሮዬን ላይ ድቅን የሚልበኝ አንድ ሰው
ነው. ....Che Guevara
ገፁ ሰውነትን የሚያገዝፍልኝ አርማ ነው!!! አለማቀፋዊነት ዜማ የሚያቀነቅን ሰንደቄ
አድራጓቱ ከመረዳት አቅም በላይ ጥልቅ የሰውነት ትርጉምን ተሸክሞል።
ህልመኛም ጭምር ነው 1956 ስምንት ሆነው ከሜክሲኮ ተነስተው የገዜው አንባገነኑን
የባቲስታ መንግሥት ለመገልበጥ ወደ ኩባ አቀኑ ለስምንት
በኩባ ጫካዎችም የጉሬላ ውጊያ ጀመሩ
አምባገነኑ የባቲስታ መንግሥት የመጣል ትግሉም ቼ ወሳኝ ሚና ተጫውቶ በድል
ተጠናቀቀ። ይህ ጀግናዬ ማለም ብቻ ሳይሆን መተግበርም ይችልበታል።
በተተኪው የካስትሮ አስተዳደርም የካስትሮ ቀኝ እጅ ሆኖ እስከ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴርነት ድረስ ላልወለደው የኩባ ህዝብ አገለገለ።ምከንያት እሱ ዘመዶቹ የሰው ልጆች ናቸውና ።
ቼኮ ከጨቋኝ ሃያላን ጋ ሲታገል ከተጨቆኝ ጋ ሲያብር ኖሯል የእውነት!!እንደምን ሰው
ከተሸናፊ ጋር በፍቅር ይወድቃል ??
ቼ!! መለክያው እኩልነት ነበር ተጨቆኝና ጨቆኝ የሌለበት ምድር ለመፍጠር ።
ዛሬ የERNESTO CHE GUEVERA መፅሀፍ ባአሜሪካ ሳይቀር በአለም መፅሀፍት ቤቶች
ይገኛል የቼ ምስል ያረፈበት ሰአቶችን ቲሸርቶች በሺዎች ይቸበቸባሉ የላቲን አሜሪካ ተማሪዎች ጠዋት ጠዋት እነደ ብሄራዊ መዝሙር ቼ እንወድሀለን ቼ አንተን እንወርስሀለን
እያሉ ያዜማሉ።


ቼ የፍትህ ተወርዋሪ ኮኮብ ነው !!

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity
@balmbaras
5.4K views17:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-23 20:06:26
4.6K views17:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-22 18:49:28
ፍቅር የልጅነት ስሜት ነው ።" ልጅነት እውነት ነው። ስሜት ደግሞ የማይዙትና የማይቆጣጠሩት። ፍቅር የማይዙትና የማይቆጣጠሩት እውነት ነው። ከተሰማ ሊክዱት የማይችል ፤ ከሌለም የማይፈጥሩትና ሊያስመስሉት የማይችል እውነት።

ፍቅር ዓመፀኛም ነው በምክንያት የማይገዛ ፤ ለዉይይት የማይመች ፤ የማያሰሩት፤ የማይጋልቡት ልጓም የሌለው ፈረሰ። ከፍት ቀዳሚ ፤ ጋላቢ ወሳጅ ፤ እምቢ ባይ ፤ ይቅርብህ አይሆንም የማያውቅ ፤ የፈለገውን እስኪያገኝ የማይተኛ ፤ የልቡ ሳይደረስ የማያርፍ።

ካፈቀረክ ፍቅር ምላሽ አይፈልግም ፤ የግድ መፈቀርን አይሻም ። ማፍቀር በራሱ ደሰ ይላል ፤ ቀኑን በመልካም ስሜት ሸፍኖ፤ ሌቱን በመልካም ህልም ያሳርፋል።

አለመኖር ከገጽ -239 የተወሰደ

@EthioHumanity
@EthioHumanity
1.0K views15:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ