Get Mystery Box with random crypto!

ስብዕናችን #Humanity

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiohumanity — ስብዕናችን #Humanity
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiohumanity — ስብዕናችን #Humanity
የሰርጥ አድራሻ: @ethiohumanity
ምድቦች: ሳይኮሎጂ
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 30.61K
የሰርጥ መግለጫ

🔆እየጠየቁ መኖር መልስን፣
መልስን ፈልጎ ማግኘት ዕውቀትን፣
እውቀት ነፃነትን፣ ነፃነት ሙሉ ስብዕናን፣
ሙሉ ስብዕና ሠላምና እርካታን፣
እርካታ ደግሞ ደስተኛ ሆኖ መኖርን ያስገኛል፡፡
አብረን እንደግ !!
@EthioHumanity @Ethiohumanity
✍የተሰማቹን አጋሩን! ቤቱ ሁሌም ክፍት ነው፣ሃሳባቹን ፃፍፍ አርጉልን @EthioHumanitybot

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 34

2021-02-21 19:06:08 . . .በዚህ ዓለም ላይ ሁሉን ነገር ለማወቅ፣ሁሉን ነገር ለማግኘት፣ሁኔታዎች በፍፁም አይፈቅዱም አንዱን የጨበጠ ሌላውን ያጣል፣ወደ አንድ ነገር የቀረበ ከሌላው ይርቃል፣ አንዱን ያወቀ ሌላውን አያውቅም ።ዝርዝሩ ብዙ ነው። ይህ ህግ በሁሉም ሰው፣በሁሉም ቦታ፣ በሁሉም ዘመን ላይ ተፈፃሚ ነው። ልዩነቱ የዓይነትና የመጠን ብቻ ነው።
. . . . እና እላችዋለው ያላቹ ላይ አተኩሩ/እናተኩር

. . . ሕይወት ትላንት ወይም ነገ አይደለችም።ሕይወት አሁን ናት። አሁንነት ሲያልፍ ትላንት ይሆናል የወደፊት አሁንነት ደግሞ ነገ ይሆናል። ሕይወት ተኖረ የሚባለው በአሁንነት ውስጥ ጤናማ በሆነ መልኩ ስንኖርበት ብቻ ነው። በአሁንነት ውስጥ ያልተኖረ ሕይወት የመከነ ሕይወት ነው።ዳሩ ግን ብዙዎቻችን በአሁንነት ውስጥ እየኖርን አለመሆኑ ነው። አእምሯችን በባለፈውና በወደፊቱ ጊዜ የተሞላ ነው። ከዚህም የተነሳ አዘውትሮ ያስባል ይጨነቃል።

እኔ ግን እደኔ ስላቹ. . በትላንትናና በነገው አፍራሽ ስሜቶች ከመሞላትና ከመረበሽ በዛሬው ማንነት ውስጥ በትክክል መኖር ምርጫቹ አድርጉ/እናድርግ።. . . !!!!!!

ውብ ምሽት

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot
2.6K viewsedited  16:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-21 19:05:58
2.4K views16:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-20 21:07:29 የማንን ግጥም ማንበብ ይፈልጋሉ?
1.3K views18:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-20 17:02:41
መጨነቅና መጨናነቅ ማንንም ሰው ከችግሩ ሲያድነው ታይቶና ተሰምቶ አይታወቅም፡፡ በመጨነቅና በመጨናነቅ ምክንያት ግን ሰዎች ቀስ በቀስ ወደሞት ሊያዘግሙ እንደሚችሉ መረጃዎችና ማስረጃዎች ሞልተዋል፡፡

እናንተ ማድረግ የምትችሉትን አድርጉ፡፡ እናንተ ማድረግ የማትችሉትን ደግሞ ሊያደርግላችሁ የሚችል ሰው ካለ አስደርጉ፡፡ ማንም ሊያደርግ የማይችለው ሁኔታ ውስጥ ካላችሁ ግን ጉዳዩን ለፈጣሪ አሳልፋችሁ ስጡና ኑሯችሁ ላይ አተኩሩ፡፡

መልካም ቀን ይሁንላችሁ!

ዶ/ር እዮብ ማሞ

@EthioHumanity
@EthioHumanity
3.9K views14:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-20 07:55:14 #እምወድሽዋ! ቅዳሜዋ! ሸጋዬዋ!


'ከሴተኛ አዳሪዋ ባሻገር'


ሴተኛ አዳሪ ነች። ለብዙ ሰው የሽፍደት ማስታገሻ ናት። እሷን ከወሲብ ጋር ብቻ አጋምደው
ነው የሚያስቧት ፤ የሚያዋሯት ፣ የሚደውሉላት የሚያገኟት።


በየቀደዳዎች ሽፍደት ፤አንሶላ ፤ቂጥ ፤ዳሌ ፤ስካር ዳንስ ዋነኛው አጀንዳቸው ያደርጉታል።


እኔ ራሴ


ውበቷ ፤ቂጧ ፤ዳሌዋ፤ ቅላቷ፤ ነፃነቷ ማርኮኝ ነበር የተዋወኳት ፤ለወሲብ ነበር የቀረብኳት


እንዳገኘኋት ነበር ማንነቷ የጣፈጠኝ ፤ብዙ ሰው ጋር ያለየሁት ወፍራም መውደድ
፤አዛኝነት፤ሃቀኝነት ያየሁባት


እሷ ራሷ
አንዲት ጠዋት ቅዳሜ እለት እንዲ አለቺኝ


ለምን ሴተኛ አዳሪነቴን ታስረሳኛለህ ፤ ለምን ካንተ ጋር ስገናኝ ሸርሙጣነቴን ታፈዘዋለህ ፤
ለምን ታገዝፈኛለህ አለቺኝ


ምን ላድርግ ብለሽ ነው


ተቃጥረን ስትመጪ የሚታየኝ ጨዋታሽ ፤ፍቅርሽ ፤የስብዕናሽ መዓዛ ነው ። እንደደረሽ
ደስስስ ይለኛል ያሻኝን ካለ ካልኩሌሽን እዘብካለሁ፤ እቀደዳለሁ። በቀደዳዬ ስትስቂልኝ ደስ
ይለኛል ፤ በቀልዴ የመጬ እከየፍ እና ከልቤ እፈግጋለሁ ።


ከዚ ደማቅ ሰው ወዳድነትሽ አልፌ

ከዚ ጣፋጭ የወዳጅነትሽ ሳቅ ነጥቤ

ከዚ ወዳጅነት ላይ የከተመች ልጅ ተሻግሬ

ከዚ የናፍቆት መጠማጠም ተሸጋግሬ

በክፉ ገጠመኝ ተጠላልፈሽ ፤በክፉ ሰዎች ተጎትጎተሽ የወደቅሽበት ግዚያዊ አንቺነትሽ
እንዴት ይታየኝ አልኳት


ቃል ሳትናገር


አቅፋኝ አንገት ውስጥ ተሸጉጣ አለቀሰች ። ሳግ ብቻ ነው የተሰማኝ


የሳጓ ትርጉም ነጋሪ ቢኖር እንዲህ የሚል ይመስለኛል
ወለድከኝ ፤ቆንጆ ሴት፤የተከበረች ፤ ለፍቅር እንደምመጥን አስዳሰስከኝ ከሚል አይዘልም


አንገቴን የሚያርሰው እምባ ውስጥ ህይወት ፍቅር ተስፋ ሲረማመድ ይሰማኛል።


ወድጃታለሁ ሴተኛ አዳሪነቷ ለኔ አይሰማኝም


ታከብረኛለች፤ሰው ትወዳለች፤ ጨዋታዬ ስጋቴ ህመሜ ሳቄ ይሰማታል። እኔ ስቀጥራት
ከፕሮፌሰሩ ፣ ከባላሃብቱ ፤ ከባለስልጣኑ በላይ ሰፍፍፍ ትልልኛለች ፤ የምላትን ትሰማኛለች
ከማንም ጋር ስሆን ከሚሰማኝ ደስታ በላይ ከእሷ ጋር ስሆን እደሰታለሁ ። እማወራው
አያልቅብኝም እ ....እ.... እ... እወዳታለሁ እንደወደድኳት ፤ ብዙ ወር መጥቶ ሄደ ፤ ፍቅራችን፣ አንዳችን ላንዳችን ያለን ነገር አልቀነሰም። የምግብ ዝግጅት ተምራ ጨረሰች ።ዘርፍ ቀየረች ።


እቺን የመሰለች ልጅ እንዴት ብዬ በትላንቷ ምክንያት ልተዋት? እንዴትም !


#ማስታወሻ ፦
ሁሉም ግርር ብሎ ከሚያየው የሚታይ ነገር ጀርባ ብዙ ያልተስተዋለ ያፈጠጠ እውነት አለ !!


* ሸጋ ቅዳሚት! *

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity
@Nagayta
4.0K views04:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-20 07:54:36
3.4K views04:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-20 07:54:35
3.3K views04:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-19 07:52:22 ለጁምኣችን!


ዓለም ሁለት ዓይነት ሌቦችን በውስጧ ይዛለች - ተራ ሌባ እና ሌባ ፖለቲከኛ።
.
.
.

ተራ ሌባ

ገንዘብህን፣ ቦርሳህን፣ ስልክህን፣ ሰዓትህን በአጠቃላይ ንብረትህን ሰርቆ ክው ያደርግሃል።
.
.
.

ሌባ ፖለቲከኛ በበኩሉ
ነገህን፣ ህልምህን፣ ስራህን፣ ደመዎዝህን፣ ትምህርትህን፣ ጤናህን፣ አቅምህን ፣ ጉልበትህን፣ ፈገግታህን ጠቅልሎ ይሰርቅሃል።
.
.
.

በሁለቱም ሌቦች መካከል ያለው አስደናቂ ልዩነት ተራ የሆነው ሌባ ስርቆት ለማከናወን አንተን ለይቶ ሲመርጥ ሌባ ፖለቲከኛውን ግን እንዲሰርቅህ የምትመርጠው አንተ መሆንህ ነው።
.
.
.

እጅግ በጣም የሚገርመው ደግሞ ተራ የሆነውን ሌባ ለመያዝ ፖሊስ በባትሪ እያደነ ሲከታተለው ሌባ ፖለተኪኛው ግን በፖሊስ አጀብ በክብር መከበቡ ነው።
.
.
ሸጋ ጁምኣ!

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity
@Nagayta
4.4K views04:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-18 21:40:15
ማድረግ በቻልነው ልክ የሰዎችን ሕይወት በመደገፍና በማሻሻል የምናገኘውን እርካታና ደስታ በሌላ በምንም መንገድ አናገኘውም፡፡

ሰሞኑን በሃሳብ፣ በምክር ወይም በቁሳቁስ የደገፋችሁት ሰው በዚያ መልኩ ለመደገፍ ስለቻላችሁ ደስተኞች ልትሆኑና ይህንን አቅም የሰጣችሁን ፈጣሪችሁን ልታመሰግኑ ይገባል፡፡

ነገ የማንን ቀዳዳ ልትደፍኑ እንደምትችሉ እያሰባችሁ ብትተኙ እንቅልፋችሁ ሙሉ ይሆናል፡፡

ጣፋጭ እንቅልፍ ይሁንላችሁ!

ዶ/ር እዮብ ማሞ

@EthioHumanity
@EthioHumanity
4.5K views18:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-18 08:52:45
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ሲናገር "ምጽዋት መስጠት ተአምር ከመሥራት ይበልጣል " ይላል ... በክርስቶስ ስም ሙት ከማስነሳት ይልቅ በክርስቶስ ስም የተራበን ማብላት ይበልጣል :: ተአምር ስትሠራ አንተ የፈጣሪ ተበዳሪ ትሆናለህ..... ግን ምጽዋት ስትሠጥ ግን አንተ ለፈጣሪ ያበደርክ ትሆናለህ.....

በእስልምና አስተምሮ ያገኘሁትን የመሳሰጠኝን ስቃኝላቹ ደሞ የተቸገሩ እና ወላጅ አልባ ልጆችን በአቅራቢያቹ ስታገኙአቸው አንድ ነገር ከራሳቹ ስጧቸው በደግነት አንደበትም አናግሯቸው ይለናል ካልቻልንስ ስንለው ሰላምታም ሰደቃ ( ምጽዋት) ነው ይለናል

እናም ዘመዶቼ በመስጠት ውስጥ ያለ መሰጠት ያግኛቹ .......


╭•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀:
@EthioHumanity
@EthioHumanity
╰ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ

ፍቅር አሁን !!
4.9K views05:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ