Get Mystery Box with random crypto!

ስብዕናችን #Humanity

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiohumanity — ስብዕናችን #Humanity
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiohumanity — ስብዕናችን #Humanity
የሰርጥ አድራሻ: @ethiohumanity
ምድቦች: ሳይኮሎጂ
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 30.61K
የሰርጥ መግለጫ

🔆እየጠየቁ መኖር መልስን፣
መልስን ፈልጎ ማግኘት ዕውቀትን፣
እውቀት ነፃነትን፣ ነፃነት ሙሉ ስብዕናን፣
ሙሉ ስብዕና ሠላምና እርካታን፣
እርካታ ደግሞ ደስተኛ ሆኖ መኖርን ያስገኛል፡፡
አብረን እንደግ !!
@EthioHumanity @Ethiohumanity
✍የተሰማቹን አጋሩን! ቤቱ ሁሌም ክፍት ነው፣ሃሳባቹን ፃፍፍ አርጉልን @EthioHumanitybot

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 29

2021-12-31 21:53:36
የገና ስጦታዎችን መግዛት ይፈልጋሉ?Hand made የሆኑ የማይደገሙ ምርጥ የገና ስጦታዎችን ለቤትዎ ፣ ለስራ ቦታ እና ለወዳጅ ለዘመድ ስጦታ የሚሰጡ ምርጥ ስራዎች ይዘን መጥተናል።

በዚህ ስልክ ቁጥር ያናግሩን

0912 65 97 93
0946 39 88 02

@is123aj
@Yesewqine0
901 views18:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-30 20:28:28
ለተረጋጋ አይምሮ አለም ትገበራለች ብሏል ጥንታዊው ፈላስፋ። ምንም እንኳን ብዙ ነገሮች በጥረትና በሩጫ የሚገኙ ቢሆንም፤ አንዳንድ ወሳኝ ነገሮች ግን በእርጋትና በመተው እንዲሁም በዝምታ የሚገኙ ናቸው።

ስለተቸኮለ አይደረስም ...
ስለተዘገየም አይቀርም ........
የቀርፋፋዋን ኤሊ ምግብ ፈጣንዋ ጭልፊት አትወስድባትም።ሁሉም በጊዜው በፈጣሪ ሀይል ውብ ይሆናል።

ውብ አዳር

@EthioHumanity
@EthioHumanity
1.5K views17:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-28 17:01:36 የሕይወት ግንድ ብዙ ቅርንጫፎች ነን!!

አንድ ውቅያኖስ ላይ ነን ‘የአንተ’ ታንኳ ሲናጥ ‘የእኔው’ ደንገል መንቀጥቀጥ ይጀምራል… ‘የእርሷ’ ጀልባ ሲቀዝፍ የባሕሩ ለመምቴ ይናጣል… የሰላምህ እርግብግቢት የሰላማችንን ንፋስ ይጠቅሳል… የሕመማችን ትንፋሽ የደስታ መንፈሷን ይበርዛል… ስለምን - ‘እኔም’፣ ‘አንተም’፣ ‘እርሷም’፣ ‘ሁላችንም' አንድ ነንና...

መምህሩ ማሃርሺ… “How are we Supposed to treat others?” ብለው ቢጠይቁት…
“There are no others” ሲል የመለሰው ለዚህ ነበር...

በተገበርከው ክፋት ብቻ ሳይሆን በተብሰልስሎትህ ሂደት ነገር ዓለማችን ይታወካል። በተነፈስከው በጎ ቃል አይደለም ባሰላሰልካት ደግነትም መውጣት መግባታችን ይዋባል… ብቻህን አይደለህምና የብቻ ሰላም የለህም… አልተነጣጠልንምና የብቻ ሕመምም አይኖርህም

የግዙፍ ውቅያኖስ አካል ነን… እኛም ሆንን በዙሪያችን ያለው የተፈጥሮ ስንክሳር የውቅያኖሱ አንድ ጠብታ ነው… አንዲት ጠብታ የምትፈጥረው ለመምቴ /Ripple/ የሌላውን ለመምቴ ትነካለች… እኒህ የሃሳብ፣ የስሜትና የድርጊት ለመምቴዎች በሌላኛው ተፈጥሮ ላይ ቀጥተኛ ተጽዕኖ አላቸው… በበጎም በክፉም… ተመልሰው ግን ወደ ምንጫቸው ይመጣሉ… በመዋኛ ገንዳ ውስጥ የፈጠርከው የውሃ ለመምቴ የገንዳውን ግድግዳ ገጭቶ ወዳንተ እንዲመለስ ማለት ነው…

ከኔ ቤት ላይ የረጨኸው እሳት ከሆነ ነበልባሉ ያንተን ቤት ይነካል… ሽቶ ስትረጨኝ የመዓዛው ቅንጣቶች ለአፍንጫህ ውብ ጠረን ይለግሳል… “You reap what you saw” … ሰው የዘራውን ያንኑ ደግሞ ያጭዳል… ይህን ምስራቃውያኑ Karma ሲሉት ሌሎች ደግሞ Boomerang ይሉታል… Boomerang አውስትራሊያኖቹ አቦርጂኒስቶች ከእንጨት የሚሰሩት ደጋን ቅርጽ ያለው የአደን መሳሪያ ሲሆን ወርዋሪው ዘንድ ተመልሶ እንዲመጣ ተደርጎ የሚነደፍ ነው… ለሃሳብ፣ ለስሜትና ድርጊትህ መጠንቀቅ የሚኖርብህ ወላፈኑ ‘ለእኔም’፣ ‘ለእርሷም’፣ ‘ለእነርሱም’ እንደሚተርፍ በማሰብ ነው… ምክንያቱም … We are all One!

በ ዕውቀቱ በአንድ ድንቅ ግጥሙ ላይ እንዲህ ብሏል
ይችላል ይሉሃል ፍልሚያ ማዘጋጀት፣
ያባት አጥንት ወስዶ ስሎ ጦር ማበጀት፣
አንተው ጦር ወርውረኽ አንተው ቀድመኽ ወደቅኽ፣
አካሌ ደረቴ መኾንህን መች አወቅኽ?፣

ሰው ብቻ ሳይሆን ከዋክብቱ፣ ሕዋው፣ ምድሪቱ፣ እንስሳው… በሚታየውና በማይታየው ዓለም ያለው ነገር ሁሉ በአንዳች ተፈጥሯዊ ክር የተሳሰረ ነው… ማሰሪያው ስላልታየ መተሳሰሩ የለም አይባልም… “Invisible threads are the strongest ties.” ― Friedrich Nietzsche

‘እዚያ ቤት ሲንኳኳ እኛ ቤት ይሰማል’ ‘ከወዲህ አንተን ሳማ እዚያ ከንፈር ትነክሳለህ’፣ ‘እከሊት ስታነሳኝ በስቅታዬ አውቀዋለሁ’፣ ‘የሰፈር ውሻ ሲያላዝን አንዱ አዛውንት ሊያልፉ ነው ማለት ነው’… ‘ውስጥህ ሲረባበሽ ራቅ ካለ ቤተሰብህ አልያም ወዳጅህ ቤት አንድ አደጋ አለ ማለት ነው’... 'ቅንድብህ ሲርገበገብ እንግዳ ሰው ልታይ ነው' … የጥንቶቹ ይሄ እውነት ስለገባቸው ይመስለኛል መሰል አባባሎች ያቆዩልን

በረከት በላይነህ "የመንፈስ ከፍታ" ላይ እንዲህ ይለናል

“የግልህ ወንዝ ስለሌለህ ብቻህን የምትሰራው ድልድይ የለም! የሰማዩ ርቀት፣ የምድሪቱ ስፋት በ’እኛ’ እንጂ በ’እኔ’ አይለካም፡፡ ውዱ ‘እኔ’ ከ’እኛ’ የተሰራው ነውና!”

እዚህ ጋ ነው ስለ ዝምድናና ባዳነት ያለን ግንዛቤ መፈተሸ ያለበት፣ ስለ ዘርና ቀለም ያለን መረዳት መጤን ያለበት፣
Peter Russell “The Global brain” ብሎ ባሰናዳው ቪዲዮው ላይ አንድ በጨረቃ ላይ የተጓዘ የጠፈር ሳይንስ ተመራማሪ የተናገረውን ውብ ቃል ትሰማላችሁ “When you are up there you are no longer an American citizen or a Russian citizen. Suddenly those boundaries disappear. You are a planetary citizen.”

ኑረዲን ዒሳ በአንድ ግጥሙ.

“ባዳውን አፍቅሮ፣
ከባዳው ልጅ ፈጥሮ፣
እኔን ባዳዬ አለኝ - ሰባት ቤት ቆጥሮ፣
ልጁን ዘመዴ አለው - በፍቅር ታውሮ፡፡
ቅጠሉ ነኝና ለረጂሙ ሃረግ፣
እኔም ዘመዱ ሆንኩ - መቼስ ምን ይደረግ?” ብሏል…

ፍቅር ሲገባን የልዩነት ቅዠት ይተናል… ማንነት ሲገባን ሕብራችን ይታያል… ጥበብ ሲያጥጠን ግን ልዩነት ያዜምልናል…

ጃፓንን ያጥለቀለቀው የሱናሚ ማዕበል የጠፋው አንድ ሚሊየን ሕፃናት ተሰብስበው “We pray for you” በማለታቸው ነው… ከየልቦቻቸው ቅንነት የተፈጠረው የፍቅር እርግብግቢት - የአንድነት ሞገድ ነው የጃፓንን ሕመም ያከመው… በዙሪያችን ያለው ተገልጦ የሚመላለስበት እንቅብ /field/ ምናችንን ተቀበለ ነው ቁምነገሩ

ፍቅር ስንሰጥ በዙሪያችን ባሉት ላይ እርግብግቢቱ ፍቅርን ይወልዳል፣ክፉ ስናስብ ደግሞ በተቃራኒው ክፋት ይጠነሰሳል፣ከፊልዱ ውጭ እስካልሆንን ድረስ ከምላሹ ተጽዕኖ ልናመልጥ አንችልም።
ደምስ ሰይፉ

We are all One!
ውብ አሁን

@EthioHumanity
@EthioHumanity
1.7K viewsedited  14:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-28 17:01:14
1.5K views14:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-27 22:06:29
የገና ስጦታዎችን መግዛት ይፈልጋሉ?Hand made የሆኑ የማይደገሙ ምርጥ የገና ስጦታዎችን ለቤትዎ ፣ ለስራ ቦታ እና ለወዳጅ ለዘመድ ስጦታ የሚሰጡ ምርጥ ስራዎች ይዘን መጥተናል።

በዚህ ስልክ ቁጥር ያናግሩን

0912 65 97 93
0946 39 88 02

@is123aj
@Yesewqine0
1.3K views19:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-26 18:51:24 መፈራረቅ

“Opposites follow each other as night follows day; try to cling to one or the other and you will be disappointed by your failure; let the way do its dance; be the dance of reconciliation of opposites.” Lao Tzu

ይህች አለም በተቃርኖ የተሞላች ነች፤ ለብርሃን ጨለማ፤ ለክረምት በጋ፤ ለብርድ ሙቀት፤ ለሃዘን ደስታ፤ ለውድቀት ስኬት የተጣመሩባት መንትያ አለም። የኛም አኗኗር በተቃርኖ ላይ አንጻራዊ በሆነ መልኩ የተመሰረተ ነው። በህይወታችን የሚገጥሙን ነገሮች ሁሉ በግልባጭ ሌላ መልክ አላቸው። ሆኖም አንዳንዴ ይህንን ሃቅ ቸል እንለዋለን። ቸል ማለት ስል፤ አዘውትረን ስለማንተገብረው የአለምን ተቃርኖ ረስተን አንድ ነገር ላይ ሙጥኝ ስንል፤ ሌላኛው ገጽታ ሲከሰት ደስተኛ መሆን ያቅተናል።ምክንያቱም ሁሉም ነገር እንደነብረው ሆኖ መቅረት ስለማይችል። ምንም አይነት የህይወት አጋጣሚዎች ተቃራኒ ገጽታ እንዳላቸው እና እንደሚፈራረቁ ማመን አለብን።

ለምሳሌ ደስተኛ በሆንን ጊዜ የደስታን ተቃራኒ ሃዘንን እንዘነጋዋለን፤ መቼም ተቃራኒ ነገሮች መፈራረቃቸው አይቀርምና ሃዘን ሲጎበኘን ለመቋቋም ይከብደናል። ከዛ ደግሞ ሃዘን ላይ ሙጥኝ እንልና ደስታን እንረሳዋለን፤ መፈራረቃቸው አይቀርምና ደስታ በጊዜው ሃዘንን ሲተካ ያልጠበቅነው ስለሆነ እምብዛም ስሜት አይሰጠንም። ስናገኝ ማጣት እንደሚመጣ መዘንጋት የለብንም፤ ያለንን ስናጣ ቅስማችን እንዳይሰበር። ስንቸገር ማግኘት እንዳለ ለልባችን እንንገረው፤ ዉሎ ለማደር ጉልበት እንዲያገኝ።

የአለምን የተቃርኖ ሚስጥር መረዳት ማለት፤ አሉታዊ አስተሳስብ መያዝ አይደለም። ይልቁንም እኛነታችን በቁሳዊ ነገሮች ወይም ከኛ ውጪ በሆኑ ነገሮች ላይ እንዳይንጠለጠል ይረዳናል። እጽዋት ለምን ክረምት ወደ በጋ ተለወጠ ብለው አይከፋቸውም፤ አሳዎች ለምን ሞገዱ  ተነሳ ብለው ከተፈጥሮ አይሟገቱም፤ ወንዞች አንዴ ሲሞሉ ሌላ ጊዜ ሲጎድሉ አያማርሩም። ምንም እንኳን ለኛ ለሰዎች ቢከብደንም፤ አኗኗራችን የሚቀይረው አስተሳሰብ ግን ይህ ነው። ሁሉም ነገር እስከመጨረሻው አይቆይም። ምን አልባት አሁን በመከራ ውስጥ ልትሆን ትችላለህ፤ በእርግጠኝነት ግን መከራህ በደስታ መቀየሩ አይቀርም፤ ዛሬ ኪስህ ባይሞላ ማጣት በማግኘት እንደሚተካ እመን።

ዛሬ ሁሉ የሞላልህ ከሆንክ ደግሞ፤ አንትህን ከንብረትህ ለየው ምክንያቱም ምንም ቋሚ ነገር የለምና፤ ይህንን ካሰብክ ማጣት ሲጎበኝህ ሰማይ አይደፋብህም። ዛሬ የተቀመጥክበት ወንበር ነገ ለሌላው ይሰጣል፤ በወጣህበት መሰላል መወረድህ ግድ ነው። ሁሉም የህይወት ልምድ ተቃራኒ ገጽታ አለው እና። የነገሮች መፈራረቅ እስከ አለም ፈጻሜ ድረስ ይኖራል።

ውብ ጊዜ
@EthioHumanity
@EthioHumanity
1.8K viewsedited  15:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-26 18:51:16
1.7K views15:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-24 10:10:07
አብረን እየኖርን ስትለየኝ ከፍቅሯ የተረፈኝ ብዙ እምነት አለ ከእናንተ መሃል በ- ተስፋ የሚቀይረኝ አለ?

@EthioHumanity
@EthioHumanity
2.3K views07:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-18 18:00:29 ሕይወት ረጅም ጉዞ ነው! ዘመን ጎዳና ነው!

ሕይወት ረጅም ጉዞ ነው፤ ሠው መንገደኛ ነው፡፡ ዘመን ጎዳና ነው፡፡ ወሳጁ አዕምሮ ነው፡፡ ተሳፋሪው ልብ ነው፡፡ ሠው በየዕለቱ፣ በየሠዓቱና በየደቂቃው ጉዞ ላይ ነው፡፡ ጉዞውን በአቋራጭ ለመሄድ የሚሞክር አለ፡፡ ቀጥተኛውን መንገድ ይዞ ሳይታክትና ሳይደክም የአስተሳሰብ ውሃ ጥሙን፣ የአመለካከት በረሃውን ችሎ፣ አደናቃፊውን ሽፍታ ሃሳብ እያለፈ ወደዕጣፋንታው የሚነጉድም ብዙ ነው፡፡ የዘመንን ጎዳና አሳምሮ የሚመላለስ አለ፡፡ በዚያው ልክ ደግሞ የሕይወት መንገዱን እያበላሸ፣ ድልድዩን ሃሳብ እያፈረሠ፣ የትውልድ ባህሩን እያደፈረሠ፤ እኔ ብቻ ልለፍ እንጂ ሌላኛው የራሱ ጉዳይ ብሎ ኋላውንና ጎኑን ሳያይ፣ ሌላውን መንገደኛ ትቶና ንቆ ፊቱን ብቻ እያየ የሚጓዝ አለ፡፡ የሕይወት ጎዳና ማለቂያውና መጨረሻው ሞት መሆኑን የተረዳ ግን የሕይወት እርምጃው የተስተካከለ ይሆናል፡፡

ጋሊኖስ የተባለ ፈላስፋ እንዲህ ይለናል፡-

‹‹በዚህ ዓለም የሚኖሩ ሠዎች ሁሉ አኗኗራቸው የመንገደኛ አኗኗር መሆኑን ሊያውቁ ይገባቸዋል፡፡ መንገደኛ ከደረሠበት ሐገር አድሮ ሲነጋ ተነሥቶ እንደሚሄድ ሁሉ እነሱም ከዚች ዓለም በሞት ተለይተው ይሄዳሉ፡፡›› በማለት የዓለም እንግድነታችንን ይናገራል፡፡

ብልህ ሠው ጉዞውን በድንብርብር አይጀምርም፡፡ አስቀድሞ በደመነፍስ ከመድፈር ይልቅ በመጠንቀቅ ጉዞውን ያጠናል፡፡ ጥንቁቅነት ፍራቻ አይደለምና ጥንቃቄው እንዲማር ያደርገዋል፡፡ ከተማረም ያያል፤ ካየም ያስተውላል፡፡ ካስተዋለም ዕውቀት ይኖረዋል፡፡ ዕውቀት ካለውም ይሠራል፡፡ ከሠራም ስጋዊ ዓለሙን አሸንፎ የወዲያኛው ዓለሙን በዕውቀትም፣ በግብርም፣ በእምነትም፣ በምክንያትም ይገነባል፡፡ ‹‹ካልተማሩ አያውቁ፣ ካላወቁ አይጸድቁ›› እንዲሉ አበው የሕይወት ጉዞው ስኬታማ ይሆናል፡፡

ሠው በውስጡም በውጪም ተጓዥ ነው፡፡ ሞኝ ሠው በራሱ ባልሆነ መንገድ የሌላን ሠው ዳና እየተከተለ ገደል ይገባል፡፡ ብልሕ ሠው ግን ራሱንና የራሱን መንገድ ለማግኘት ይጓዛል፡፡ ውስጣዊው ጉዞው የነፍስ ሲሆን፤ ውጫዊው ጉዞ የስጋ ነው፡፡ የነፍስ ጉዞው አሻጋሪ ሲሆን፤ የስጋው ጉዞው ግን የሆነ ጊዜ ላይ አላቂ ነው፡፡ ዕድሜ ገደብ አለው፡፡ የነፍስ ጉዞ የሃሳብ ሸንተረሩን አልፎ፣ ዳገትና ቁልቁለቱን ወርዶ ሠብዓዊነቱ ጋር ይደርሳል፡፡ የስጋዊ ጉዞ ግን ማጠናቀቂያው ሞት ነው፡፡

ከነገስታት አንዱ ዘመን እንዴት ያለ ነው ብሎ አንዱን ፈላስፋ ቢጠይቅ፡- ‹‹ዘመን ማለት አንተ ነህ፡፡ አንተ ሠላማዊ ስትሆን ዘመን ሠላማዊ ይሆናል፡፡ አንተ የከፋህ እንደሆነ እንዲሁ ይከፋል›› አለው ይባላል፡፡

እውነት ነው! ሠው ዘመኑን መፍጠር ባይችልም በዕድሜው ላይ አሉታዊም ሆነ አዎንታዊ ጫና መፍጠር ይችላል፡፡ ሠው የራሱ ሠዓሊ ነው፡፡ ቀለሙ አስተሳሰቡ ነው፡፡ ሠሌዳው ሕይወቱ ነው፡፡ ብሩሹ ምግባርና ግብሩ ነው፡፡ በሕይወት ብሩሹ ዘመኑን አሳምሮ ይቀባል፤ አልያም አበላሽቶ አስጠዪ ያደርጋል፡፡

ዘመን ውበቱ የሚገለጠው በዘመኑ ውስጥ አፍቃሪና ተፈቃሪ አንድ የሚሆኑበት ፍቅር ሕያው ሲሆን ነው፡፡ ታናሽ ታላቁን ሲያከብር፣ ታላቅ ታናሹን ሲመክር፣ አዛውንት፣ አሮጊቶች በልጆቻቸው ተከብረው ሲጦሩ፣ ሠው በሠውነቱ ሲኖር፣ ጥላቻ፣ ጦርነት፣ መካካድ፣ መገዳደል፣ መወጋገዝ፣ መናናቅ፣ መጠላላት ወዘተ ክፉ ነገሮች ሁሉ ሲወገዱና ሲጠፉ ዘመኑ መልካም ዘመን ነው እንላለን፡፡ የዚህ ዘመን አባል የሆነ ትውልድ ጉዞው ስኬታማ ይሆናል።

ወዳጆች የዘመን ክፋቱና ክርፋቱ የሚጀምረው እርስበርስ በመለያየት ነው፡፡ ጥላቻ ፅንሠቱ ካለማወቅ የሚመነጭ ነው፡፡ ዕውቀት በፍቅር ሲሟሽ አዕምሮ በጥላቻ አይሠክርም፡፡ በጥላቻ ናላውን ያጣ ሠው የሚያደርገውን አያውቅም፡፡ አላዋቂ ሠው ዘመኑን እርም የሚያሠኝ ተግባር በገዛ እጆቹ ይፈፅማል፡፡ በፈፀመውም ክፉ ነገር ሲሰቃይ ይኖራል፡፡ በስቃዩም ደስታን ያጣል፡፡ ደስታ በማጣቱም በሕይወት ተስፋ ይቆርጣል፡፡ ተስፋ በመቁረጡም ሕይወቱን ዓላማ የለሽ ይሆናል፡፡

ወዳጄ ሆይ ሕይወት ረጅም ጉዞ ነው፡፡ በዚህ ማለቂያ ባለው ጉዞ ቀሪ ታሪክ ሠርተህ ለማለፍ ልብህን በቅንነት፤ አዕምሮህን በመልካምነት መላልሶ መስራት ያስፈልግሃል፡፡ ቅንነት የጎደለው የሕይወት ጉዞ መጨረሻው አያምርም፡፡ ፍቅር ያነሠው ህይወት ብኩን ነው፡፡ ለትዝታህ የሚሆን እንኳን መልካም ነገር ማድረግ ሕይወትን ያድሳል፡፡ ስታረጅ መልካሙ ትዝታህ ያጫውትሃልና፡፡

‹‹ዘመን ማለት አንተ ነህ፡፡ አንተ ሠላማዊ ስትሆን ዘመን ሠላማዊ ይሆናል፡፡ አንተ የከፋህ እንደሆነ እንዲሁ ይከፋል››

እሸቱ ብሩ ይትባረክ

ቸር ጊዜ!
@EthioHumanity
@EthioHumanity
1.8K viewsedited  15:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-18 18:00:15
1.6K views15:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ