Get Mystery Box with random crypto!

ስብዕናችን #Humanity

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiohumanity — ስብዕናችን #Humanity
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiohumanity — ስብዕናችን #Humanity
የሰርጥ አድራሻ: @ethiohumanity
ምድቦች: ሳይኮሎጂ
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 30.61K
የሰርጥ መግለጫ

🔆እየጠየቁ መኖር መልስን፣
መልስን ፈልጎ ማግኘት ዕውቀትን፣
እውቀት ነፃነትን፣ ነፃነት ሙሉ ስብዕናን፣
ሙሉ ስብዕና ሠላምና እርካታን፣
እርካታ ደግሞ ደስተኛ ሆኖ መኖርን ያስገኛል፡፡
አብረን እንደግ !!
@EthioHumanity @Ethiohumanity
✍የተሰማቹን አጋሩን! ቤቱ ሁሌም ክፍት ነው፣ሃሳባቹን ፃፍፍ አርጉልን @EthioHumanitybot

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 31

2021-12-03 16:59:38 ስብዕናችን #Humanity pinned « As A Man Thinketh” -By James Allen ክፍል “Thought and Character” “አስተሳሰብ እና ባህሪ” “ሰው በልቡ የሚያስበውን ሃሳብ ነው” የሚለው አባባል የሰውን ልጅ ማንነት የሚያንጸባርቅ አባባል ብቻም ሳይሆን፤ የህይወቱን መስመር እና ጉዞም የሚዳስስ  ነው። እርግጥም ሰው የሚያስበውን ሃሳብ ነው። ባህሪው እና ጸባዩ…»
13:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-03 15:46:51
"ሰው የአፉን ፍሬ ይበላል" ይባላል።

"እገሌ ጥሩ አይደለም" ማለት ስትጀምር ሰውየው/ሴትየዋ ላንተ መጥፎ መሆን ይጀምራሉ። አንተም በሰውየው/ሴትየዋ ውስጥ የምታየው ጥሩውን ትተህ፣ ክፋትና መጥፎነትን ብቻ ስለሚሆን ግምትህና የመጀመሪያ ጥንስስ ሃሳብህ የበለጠ ነፍስ ዘርቶና ተጠናክሮ በእግሩ ይቆማል። የዚህ ምክንያቱ አንተ ነህና ሃሳብህን ተቆጣጠር፣ ከክፉ ሃሳብ ራስህን አጽዳ።

በአንጻሩ ደግሞ አንተ "እገሌ ለእኔ ጥሩ አመለካከት አለው" ማለት ስትጀምር ነገሮች እንደዚያው ጥሩና በጎ መሆን ይጀምራሉ። ሰውየው ምንም ቢያደርግ "ለእኔ ግን ጥሩ ነው" ማለት ስትጀምር ሰውየውም/ሴትየዋ ስላንተ ጥሩ አመለካከት እንዳላቸው ታያለህ።

ዓለም የአስተሳሰብህ ግልባጭ ናት፣ መስታወት ናት። የጥሪ ወይም የስበት ኃይል በለው ወይም ሌላ ብቻ የገመትኸው ነገር ትክክል እየሆነ ሲመጣ ታያለህ። Such is the Power of Thinking.

ሰው በልቡ እንዳሰበ እንደዚያው ነውና እንዲል መጽሓፍ፣ የጀምስ አለን As a man thinketh ዘመን ጠገብ ተወዳጅ መጽሓፍ ነው። The Power of Positive Thinking የሚለው መጽሓፍም ጥሩ ሰብዕና ለማነጽ ጠቃሚ ነው።

ጥሩ ሰው ላለመሆንና ለመሆን ምርጫው ግን የባለቤቱ ነው።

#ምረጥ! የምርጫህን ልትኖር ግን ትገደዳለህ!

ውብ አሁን
@EthioHumanity
@EthioHumanity
6.4K views12:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-02 20:16:39
“ማንም ሰው የሞተ ውሻ እንደማይደበድብ አስታውስ” ይላል ዴል ካርኒጌ… አንድ ውሻ ኃይለኛ በሆነ ቁጥር ሌሎች እርሱን በመምታት እርካታን ያገኛሉ… ሰፈር ውስጥ የውሪዎች ድንጋይ የሚበዛው፣ የአልፎ ሂያጅ ከዘራ የሚነሳው፣ የጅብ መንጋ ሳይቀር የሚበረታው አርፎ በተኛ ውሻ ላይ አይደለም፣ ይልቁንም ቀየውንና ግቢውን አላስደፍር ባለ ጀግና ውሻ ላይ እንጂ…

ፈተናዎች የሚበዙብህና ሌሎች አንተ ላይ የሚበረቱብህ ዝም ስትል አይደለም… ‘ለምን?’ ስትል ነው፤ ዝም ስትል አይደለም… ስትጠይቅ ነው፤ ስትደክም አይደለም ስትበረታ ነው… በተገፋህ ጊዜ ሁሉ ይህን ቁምነገር አስታውስ ‘ማንም ሰው የሞተን ውሻ አይደበድብም!!!’

ውብ ምሽት
@EthioHumanity
@EthioHumanity
6.3K viewsedited  17:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-01 18:13:31
''………እዚህች ምድር ላይ ስንኖር በትንሹም ይሁን በትልቁ በየደቂቃው እንለዋወጣለን። ቢታወቀንም ባይታወቀንም ነው እንግዲህ………

ቢያንስ ገላችን የበላውን ያንሸራሽራል ሕዋሳት ይሞታሉ ይወለዳሉ። ቢያንስ አንዲት ፀጉር ትበቅላለች ወይም ትረግፋለች።ፊኛችን ሳያቋረጥ በፈሳሽ ይሞላል። ጊዜው ሲደርስም ይጎላል……

ሕይወት እንግዲህ እንዲህ ነው…………

ይሄ ዑደትና የዝግመት ለውጥ አይበቃንምና ደሞ አንዳንድ ጊዜ እጅግ የሚለውጠን ቀውስ ይመጣብናል…… ገላችን፣ አእምሮአችን ይታመማል…… እንረበሻለን፣ እንጨነቃለን።

ሕይወት እንግዲህ ይሄ ነው…………

ሰው በግሉ፣ ሕብረተሰብም ተፈጥሮው ይመስሉኛል። ይሄን ደጋግሜ መገንዘቤ፣ ደጋግሜም በነዚህ ሁኔታዎች ውስጥ ማለፌ ያስተማረኝ ነገር አለ። መረባበሽ ፋይዳ እንደሌለው………

የተረጋጋ ታዛቢ፣ የመነኩሴ አመለካከት አለኝ። ከፍ ዝቅ ያለ ነገር ሲያጋጥመኝ በረጉ ዓይኖቼ አያለሁ። በቀዘቀዘ መንፈስና አካል እቀበለዋለሁ……… እንደሚለወጥ ስለማውቅ !"

'የሚያልፍ ዝናብ አይምታህ ' ሲሉ አዛውንት 'ዝናቡን ፍራው' ማለታቸው አይደለም። ዝናቡን ማወቃቸው ነው። የተወሰነለት ዕድሜ አለው፣ ያውም አጭር ማለታቸው ነው። ሰው ቢያንስ በተስፋ የችግሮቹን ዘመን ያልፋል ማለታቸው ነው።

አይመስልህም እንዴ?''

አዳም ረታ

ውብ ምሽት
@EthioHumanity
@EthioHumanity
6.6K views15:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-29 21:24:41
ያላየኸው ሁሉ የለም ማለት አይደለም፤ ያልሰማኸው ሁሉ የለም ማለት አይደለም።

አለማየትና አለመስማት የዓቅምህን ደካማነት እንጂ የአለመኖሩ ማስረጃ አይሆንም።

ሰው ከስሜት በላይ የሆኑ መረዳቶችን ሊያዳብር ግድ ይለዋል። ይህ ግን ለተሰጣቸው እንጂ ለሁሉ አይቻልም።

ዓይናችሁ ይከፈት!

መልካም አዳር!
@Ethiohumanity
@Ethiohumanity
6.9K views18:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-27 18:33:13
የዋህነት እና ንፁህነት በእውቀት ብዛት ወይም በጥበብ ጥልቀት ተፈልጎ የማይገኝ በራሱ ንፁህ ስጦታ ነው፡፡

በገንዘብ የማይገዛ፤ በሀይልም የማይጠፋ፤በመከራም የማይደበዝዝ ለተወደደ የሚሰጥ የፈጣሪም ችሮታ ነው፡፡ ይህ ያላችሁ ውደዱት፤ተደሰቱበት- እንዳትወድቁ እና እንዳትሰናከሉም ብልሃትን በጥበብ ትገዟታላችሁ፡፡

ውብ ምሽት
@EthioHumanity
@EthioHumanity
8.6K views15:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-25 20:01:55 ምንም እንኳን ስለመልካም አስተሳሰብ እና ስለ ቀና ኑሮ ደጋግመን ብንደሰኩርም አንድ መዋጥ ያለብን እውነት ግን አለ። ይህም ህይወት ነጭ እና ጥቁር አይደለችም። የጠበቅናቸው የማይከሰቱባት ያልጠበቅናቸው የሚከሰቱባት የማትተነበይ እንጂ። ችግር የማይደርስበት ኑሮ፤ ከመከራ ከሃዘን የራቀ ህይወት ለማንም አልተሰጠም። ማንም ሰው ሁሉ ተሳክቶለት እና ሞልቶለት የሚኖር አይኖርም (ምንም እንኳን ከላይ በምናያቸው ነገሮች ሁሉ ነገር የተሳካላቸው ሰዎች ያሉ ቢመስሉንም)። አነሰም በዛ እያንዳችን የምናምርርባቸው ነገሮች በህይወታችን ውስጥ አሉ።

ኤካርት ቶሌ የተባለ ጸሃፊ፤መማረር ማለት ያለውን እውነታ መቀበል አለመቻል ነው ይላል። የምናማርረው ኑሮዋችን እኛ በፈለግነው መንገድ ስላልሄደ አልያም እንዲከሰቱ የማንፈልጋቸው ነገሮች ስለተከሰቱ  ነው። እንዲህ አይነት ችግሮች ሲፈጠሩ እራሳችንን የምናወጣባቸው መፍትሄዎች አሉ። ለዚህች አጭር ጽሁፍ “The power of Now” ከተሰኘው መጻህፉ ላይ ያገኘኋቸውን ሶስት ነጥቦች ሰፋ አድርጌ ላካፍላችሁ ወደድኩኝ።

Remove yourself from the situation–
አንዳንዴ ችግር ብለን የምንወስዳቸው ወይም የምጨነቅባቸው ነገሮች ከኛ ውጪ በሆኑ ነገሮች የሚከሰቱ ናቸው ። የሰው ልጅ ደግሞ እራሱን ከመለውጥ ባለፈ የሌላውን ሰው አስተሳሰብ እና ማንነት ለመለወጥ አይቻለውም። ስለዚህ የምንማረርባቸው  ነገሮች ከኛ የመነጩ ካልሆኑ ፤ከሁኔታው አልያም ከአካባቢው እራሳችንን በማራቅ ሰላማችንን ማግኘት እንችላለን። በዙሪያችን ያሉ ነገሮች የሚያደርሱብንን ተጽዕኖ ሙሉ በሙሉ ማስወገድ ባንችልም፤ ሁኔታዎቹ ግን ሰላም እና ደስታችንን እንዳያናውጡ ጥንቃቄ ማድረግ አለብን።

Change it– የማንፈልገውን ነገር ለመለወጥ መጣር- ብዙዎቻችን ስለችግሮቻችን ቀን እና ማታ እናወርለን ነገ ግን ለምፍትሄ የሚሆን ጊዜ የለንም። ለምሳሌ ስራ በማጣቱ የሚማረር ወጣት ቀን እና ማታ ስለስራ አጥነት ቢይወራ ምንም መፍትሄ የለውም። ከሱ የሚጠበቀው ሳይታክት ማመልከቻዎቹን ማሰራጨት ፤ ክህሎቶቹን ማዳበር እና ስራ ሊያገኝባቸው የሚችልባቸውን መንገዶች ማጤን ነው። ስለኑሮዋችን ብናማርር፤ ሌሎችን ብንወቅስ፤ እንዲህ ቢሆን ኖር እያልን በሃዘን ብንብሰከሰክ፤ ሁኔታውን ለመለወጥ ሙከራ እስካላደርግን ድረስ ምንም ጠብ የሚል ነገር የለም።

Accept it totally– በልጅነቴ የሰማሁት ጸሎት እስካሁን ድረስም አብሮኝ አለ። ለኔ ትልቅ ትርጉም ስላለው ችግሮች ሲገጥሙኝ ሁሌም አስታውሰዋለው። ጸሎቱ እንዲህ የሚል ነው “በህይወቴ ልለውጣቸው የምችላቸውን ነገሮች እንድለውጥ ብርታቱን ስጠኝ፤ ልለውጣቸው የማልችላቸውን ነገሮች እንድቀበል ጽናቱን ስጠኝ፤ እናም በሁለቱ መካከል ያለውን ልዩነት እንዳስተውል ጠቢብነቱን አድለኝ” ይላል። አዎ ልንለውጣቸው የምንችላቸው ነገሮች ላይ ጉልበት እና ጊዜያችንን በጭንቀት ከማሳለፍ ይልቅ መፍትሄው ላይ  ማተኮር ይኖርብናል። በሌላ በኩል ከኛ ቁጥጥር ውጪ የሆኑ ነገሮችን መለወጥ ካልቻልን ተቀብለናቸው መኖርን መልመድ አለብን።

ከላይ የሰፈሩት መፍትሄዎች እንዳሉ ሆነው ችግሮቻችንን ይበልጥ ግልጽ በሆነ እና ቀለል ባለ መልኩ እንድናይ የሚረዳንን አንድ ትልቅ ነጥብ ላክል እሻለው። ይኸውም ችግሮችን የምናይበትን  መንገድ በተመለከተ ነው።በብዛት የሚያሳስበን ችግሩ ሳይሆን ችግሩን የምናይበት መንገድ ነው። አይምሮዋችን እንደ እሳት ነው ለበጎ ነገር ከተጠቀምንበት ህልውናችን ፤ለመጥፎ ነገር ከተጠቀምንበት ደግሞ መጥፊያችን ይሆናል። ብዙዎቻችን ይህንን ነገር ሰለማናስትወለው የራሳችንን መንገድ እራሳችን እንዘጋለን።

እውቁ የሳይኮሎጂ ሰው ዶ/ር ኖርማን ቪንሰንት ፒል እንዲህ ይላል “የሚያሳስበን ችግሩ ሳይሆን ችግሩን የምናይበት መንገድ ነው- “how you think about the problem is more important that the problem itself” dr norman vincent peal- ምንኛውም አይነት ችግር ሲገጥመን ከችግሩ በላይ እኛን የሚጎዳን ችግሩን የምንመለከትበት መንገድ ነው። ለማሳሌ አንድን ህጻን ልጅ ከሰፈር ሱቅ አንድ የሆነ እቃ ገዝቶ እንዲመጣ ላክነው። ይህ ህጻን ለእቃው መግዣ የሰጠነውን  አስር ብር ጣለው እንበል። ታዲያ ህጻኑን የሚያስለቅሰው እና የሚያሳስበው የአስር ብሩ መጥፋት ወይም እቃው አለመግዛት ሳይሆን በአይምሮ የሚሳለው የወላጆቹ ቁጣ ነው። አይምሮ መጥፎ ነገሮችን ሲያስብ እጅግ አጋኖ ነው፤ በዚህ የህጻን ልጅ ህሊና ውስጥም የሚሳለው የወላጆቹ አስፈሪ ገጽታ፤ ግርፊያው እውን እንደሆነ ሁሉ ህጻኑን ስቅስቅ አስደርጎ ሊያስለቅሰው ይችላል።

የኛም ህይወት ከዚህ ብዙ አይርቅም። የሆነ ችግር ሲገጥመን የሚያስጨንቀን እና የሚያስስበን  ከችግሩ በላይ ችግሩን የምናይበት መንገድ ነው። ስለዚህ ዋናው መፍትሄ ከችግሩ ጋር ሊመጡም ላይመጡም የሚችሉ መላምቶችን እያሰብን እራሳችንን ገና ለገና ባልሆነው ነገር ከማስጨነቅ ይልቅ ስለ እውነተኛው ችግር በግልጽ ከራሳችን ጋር መፍትሄ መፈልግ ነው።

በመጨረሻ ማስታወስ ያለብን ነገር ብረት ከራሱ ዝገት የበለጠ የሚጎዳው ነገር የለም። እኛም እደዛው ከውስጣችን ዝገት፤ ከአስተሳሰብቻችን ዝገት የበለጠ የሚሰብረን ችግር የለም። ህይወት ቀላል ትሆናልች ብለን እራሳችንን ማዘናጋት የለብንም፤ ይበልጥ ከፍ ለማለት በጣር ቁጥር፤ የህይወት ፈተናም ይከብዳል፤ ችግሮች ይበልጥ ይከሰታሉ። ሁሌም ግን ለችግሮቻችን ትክክለኛውን እይታ ከያዝን የማይታለፍ ፈተና፤ የማይፈታ ችግር አይኖርም።

ሚስጥረ አደራው

ውብ ምሽት
@ethioHumanity
@EthioHumanity
8.6K views17:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-25 20:01:44
6.8K views17:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-20 17:31:21 ባምቡ [The Bamboo]

“አንድ የቻይና የቀርከሃ ዝርያ አለ …ባምቡ ይባላል። የቀርከሃውን ዘር ከተከልክ በኋላ ለ5 ዓመታት ያህል ምንም አይነት እድገት አታይም - ከትንሽዬ እብጠት መሰል ነገር በቀር !! በዚህ ሁሉ ጊዜ ውስጥ የቀርከሃው እድገት መሬት ውስጥ ነው፡፡ ቀርከሃው እጅግ ውስብስብ የሆነ ሥሩን ይዘረጋል፡፡
ልክ አምስተኛ አመቱ እንዳበቃ ግን በጥቂት ሳምንታት ውስጥ 25 ሜትር ይመነደጋል !!!
ሁሌም እንደሚሆነው ያየው ሁሉ አጀብ ይላል፡፡

Bamboo is flexible, bending with the wind but never breaking, capable of adapting to any circumstance. It suggests resilience, meaning that we have the ability to bounce back even from the most difficult times. . . . Your ability to thrive depends, in the end, on your attitude to your life circumstances. Take everything in stride with grace, putting forth energy when it is needed, yet always staying calm inwardly."
~ Ping Fu

በሕይወታችን፣ በሙያችን እና በሌላ ሌላውም የሚያጋጥሙን አብዛኞቹ ነገሮችም ልክ እንደዚህ የቻይና ባምቡ ናቸው፡፡

ጊዜና ጉልበትህን አፍስሰህ፣ ሰርተህ፣ ለፍተህ … ባጠቃላይ ለእድገትህ አስፈላጊ ነው ያልከውን ሁሉ ነገር አድርገህ ለሳምንታት፣ ለወራት ምናልባትም ለአመታት ምንም አይነት ውጤት ላታይ ትችላለህ፡፡

ግና ታግሰህ ከቀጠልክ … ለእድገትህ የሚያስፈልገውን ነገር ሁሉ ማድረግህን ከቀጠልክ ድንገት ያንተ 5ኛ አመት መምጣቱ አይቀርም - ያኔ ታዲያ አልመኸውም እንኳ የማታውቀው ለውጥ ድንገት ይጎበኝህና ወደ ሰማይ ትተኮሳለህ…

ልብ አድርግ … በአይን የሚታይ እድገት አላየሁበትም ብለህ ቀርከሃውን ውሃ ካላጠጣኸው፣ ካልተንከባከብከው 5ኛ ዓመት ሲሞላ ምንም አይነት ተዐምራዊ እድገት አይኖርም፡፡ አንተም እንደቀርከሃው ነህ - የሚታይ ለውጥ ባይኖርም እድገቱ በአይን የማይታይ ነውና ያንተ 5ኛ ዓመት ደርሶ ድንገት በእድገት ወደ ሰማይ እስክትተኮስ ሳትሰለች ጥረትህን ቀጥል…

አስታውስ … አንድ ሰው ወደ ታላቅ ከፍታ ይወጣ ዘንድ ጀግንነት እና ቁርጠኝነት ሊኖረው ይገባል … በዚያ ላይ ደግሞ መሬቱን ቆንጥጦ የያዘ ሥርም ያሻዋል…”

"When a storm comes, The bamboo bends. It doesn't break."
When you face difficulty in your life, you don't Always need to stand strong and against it all the time. Sometimes you just need to bend over and go with the flow.

ፓውሎ ክዌሎ - ALEPH

ውብ ቅዳሚት
@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
9.5K views14:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-20 17:31:00
7.6K views14:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ