Get Mystery Box with random crypto!

ስብዕናችን #Humanity

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiohumanity — ስብዕናችን #Humanity
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiohumanity — ስብዕናችን #Humanity
የሰርጥ አድራሻ: @ethiohumanity
ምድቦች: ሳይኮሎጂ
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 30.61K
የሰርጥ መግለጫ

🔆እየጠየቁ መኖር መልስን፣
መልስን ፈልጎ ማግኘት ዕውቀትን፣
እውቀት ነፃነትን፣ ነፃነት ሙሉ ስብዕናን፣
ሙሉ ስብዕና ሠላምና እርካታን፣
እርካታ ደግሞ ደስተኛ ሆኖ መኖርን ያስገኛል፡፡
አብረን እንደግ !!
@EthioHumanity @Ethiohumanity
✍የተሰማቹን አጋሩን! ቤቱ ሁሌም ክፍት ነው፣ሃሳባቹን ፃፍፍ አርጉልን @EthioHumanitybot

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 35

2021-02-17 21:56:16
ታዳጊ ንስሮች እድሜያቸውን ሁሉ ከከተሙበት ከገደሉ አፋፍ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ጨክነው ሲዘሉ ነው በእርግጥም የሚበሩበት ክንፍ እንዳላቸው የሚገባቸው፡፡

እኔና እናንተም እንደዚሁ ነን፡፡ ከትመን ከቆየንበት “አስተማማኝ” ስፍራ ለመጀመሪያ ጊዜ ተራምደን ብንወጣ በእርግጥም ወደ ሕልማችን የሚወስደን ክንፍ እንዳለን ያን ጊዜ ይገባናል፡፡

ይህን ሃሳብ እያሰላሰላችሁ ተኙ!
ጣፋጭ እንቅልፍ ይሁንላችሁ!
ዶ/ር እዮብ ማሞ

@EthioHumanity
@EthioHumanity
5.1K views18:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-16 09:46:33
የአማዞኑ አታከስ አትላስ- በአማዞን ከሚገኙ ከግዙፋን ቢራቢሮዎች ውስጥ አንዱ ነው

“Butterfly Effect” ሲባል ሰምታችሁ ልታውቁ ትችላላችሁ

በአጭሩ ይህ ሀሳብ የሚያትተው የቢራቢሮ የክንፏ እርግብግቢት በጥቂት በጥቂቱ የአለም የአየር ሁናቴ ላይ ለውጥ ይፈጥራል ብሎም ይህ ጥቂት ለውጥ ተዳምሮ ወደ መብረቅ ማዕበል ያድጋል የሚል ነው

ከላይ የተሰቀለው ፎቶ ለምን እንደሆነ አሁን ግልፅ ይመስላል

በህይወታችን ከአንድ ጊዜ በላይ ከልባችን ስለምንፈልገው ነገር ተመኝተን እናውቅ ይሆናል

የህይወታችን የመጀመርያው ምኞት ምን ያህል ከፍተኛ ዋጋ እንዳለው ከዚህ መረዳት እንችላለን

ልክ በአንድ የአለማችን ጫፍ በአይን የማናየው እና የማይቀረው የቢራቢሮ ክንፍ መማታት በሌላኛው የአለማችን ጫፍ በአየሩ ሁናቴ ላይ ከፍተኛ ጫና መፍጠር ከቻለ የእኛም እያንዳንዷ የምናረጋት ነገር የህይወታችንን መስመር በዋናነት የምትቆጣጠር ሆና ልናገኛት እንችላለን

ጥቂቷ የአስተሳሰብ እና የስሜት እንዲሁም የተነሳሽነት መቀነስ ወይም አለመኖር በማናቸውም ልንሰራ ተነሳሽነት ላጣንለት ወይም ላልተሰጠንለት ነገር መጨረሻ ውጤት ከፍተኛ ተፅእኖን ይዞ ብቅ ይላል

በተፈጥሮአችን ሰው ሆነን ስንፈጠር ለውጥ እናመጣ ዘንድ ነውና ማናችንም ብንሆን በውስጣችን የተቀበረ ከፍተኛ መሰጠት ፣ የልብ ሙላት እና ጥንካሬ አለን

ቀን መቁጠር ትርጉም የለውም

ይልቁንስ ቀኖቻችን በአላማ የተሞሉ ፣ በስነልቦና የጠነከሩ እንዲሁም ከህልማችን አንፃር ትርጉም የተቸራቸው እንዲሆኑ የዛሬን ቀን አንድ ብለን እንጀምር

╭•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀:
@EthioHumanity
@EthioHumanity
╰ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ

ፍቅር አሁን !!
5.7K views06:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-15 21:03:43 እስከ የካቲት 26 ድረስ ይሄንን ኮፍያ ለሚያገኝልኝ ሰው ወሮታውን እከፍላለሁ ፤ አመሰግናለሁ !

@balmbaras
5.1K viewsedited  18:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-15 21:02:04
5.0K views18:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-15 19:33:34
''………እዚህች ምድር ላይ ስንኖር በትንሹም ይሁን በትልቁ በየደቂቃው እንለዋወጣለን። ቢታወቀንም ባይታወቀንም ነው እንግዲህ………

ቢያንስ ገላችን የበላውን ያንሸራሽራል ሕዋሳት ይሞታሉ ይወለዳሉ። ቢያንስ አንዲት ፀጉር ትበቅላለች ወይም ትረግፋለች።ፊኛችን ሳያቋረጥ በፈሳሽ ይሞላል። ጊዜው ሲደርስም ይጎላል……

ሕይወት እንግዲህ እንዲህ ነው…………

ይሄ ዑደትና የዝግመት ለውጥ አይበቃንምና ደሞ አንዳንድ ጊዜ እጅግ የሚለውጠን ቀውስ ይመጣብናል…… ገላችን፣ አእምሮአችን ይታመማል…… እንረበሻለን፣ እንጨነቃለን።

ሕይወት እንግዲህ ይሄ ነው…………

ሰው በግሉ፣ ሕብረተሰብም ተፈጥሮው ይመስሉኛል። ይሄን ደጋግሜ መገንዘቤ፣ ደጋግሜም በነዚህ ሁኔታዎች ውስጥ ማለፌ ያስተማረኝ ነገር አለ። መረባበሽ ፋይዳ እንደሌለው………

የተረጋጋ ታዛቢ፣ የመነኩሴ አመለካከት አለኝ። ከፍ ዝቅ ያለ ነገር ሲያጋጥመኝ በረጉ ዓይኖቼ አያለሁ። በቀዘቀዘ መንፈስና አካል እቀበለዋለሁ……… እንደሚለወጥ ስለማውቅ !"

'የሚያልፍ ዝናብ አይምታህ ' ሲሉ አዛውንት 'ዝናቡን ፍራው' ማለታቸው አይደለም። ዝናቡን ማወቃቸው ነው። የተወሰነለት ዕድሜ አለው፣ ያውም አጭር ማለታቸው ነው። ሰው ቢያንስ በተስፋ የችግሮቹን ዘመን ያልፋል ማለታቸው ነው።

አይመስልህም እንዴ?''

…አዳም ረታ ፦
ይወስዳልመንገድ ያመጣል መንገድ……

ውብ አሁን !

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
5.5K viewsedited  16:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-14 20:55:26 ጉዞ ወደ ሀሳብ!! #እንወያይ ሀሳቦቻችሁን ወርውሩልን...




የሴተኛ አዳሪነት በኢትዮጵያ በግለሰብ ደረጃ
የሚወገዝ ቢሆንም በመንግስት ህግ
ያልተከለከለ ነው:: ብዙ እህቶቻችን በዚህ
ህይወት ውስጥ እንደሚኖሩና እንደ ገቢ
ምንጭ ተጠቅመው እንደሚተዳደሩበት
ሁላችንም የምናውቀው ጉዳይ ነው::
የሴተኛ አዳሪነት ዋናው ምክነያት የኢኮኖሚ
ችግር መሆኑን አብዛኛዎቹ ሴተኛ አዳሪዎች
በራሳቸው የሚናገሩት ሲሆን በአሁኑ ጊዜ
ከ150 ሺ በላይ ሴተኛ አዳሪዎች በአዲስ
አበባ እንደሚገኙ ይገመታል::


# ሴተኛ አዳሪነት የህይወት ምርጫ ነው ወይንስ ከችግር መውጫ?


@Nagayta
2.3K viewsedited  17:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-14 18:21:35 Noble Truth [የከበሩ እውነታዎች]

by DEMIS SEIFU 

በመኖር ወዲያ ወዲህ… በመክረም ገበታ… በመውጣት መግባት መስተጋብር… በፍለጋ ላይና ታች ፍኖት… መሆናቸው እርግጥ ከሚባልላቸው ጉዳዮች ውስጥ አንዱ ነው…ድቁሳት… Dukkha ይሉታል ምስራቃውያኑ… Suffering የሚለውን ቃል ፈተና ወይም ድቁሳት እያልኩ ልረዳው ወደድኩ… ስቃይ የዘለለት ቅኝት.. ፈተና የጊዜያዊነት ስሜት አለውና…

ቡድሃ “The Four Noble Truths” በተባለው የመጀመሪያ ትምህርቱ ላይ ስለ ድቁሳት /ፈተና/ አራት ቁምነገሮችን አስተምሯል…

፩. There is suffering…

የመጀመሪያው ንዑድ እውነት “ድቁሳት አለ” ይላል… በቃ መደቆስ አለ… ይህንን እውነት መካድ አይቻልም… ከኑረት ገጾች በአንደኛው ላይ መታተሙ … ካለፍ አገደም ሁሉንም ቤት መጎብኘቱ ሳይታለም የተፈታ ነው… ስለዚህም እውቅና ከመስጠት እንጀምር ይላል ቡድሃ… አይቀሬነቱን ከመቀበል… ይህም ሁኔታውን ‘ለምን እኔ ላይ ብቻ…’ ከሚል ተጨማሪ ህመም ነፃ ያደርገዋል… መደቆስ ስላለ ተደቆስን እንጂ ‘እኛ’ ስለሆንን ሆነብን አንልም ማለት ነው… ሁሉም እንደየብጤቱ ይደቆሳል… እንደ ትከሻው… What do we have in common is suffering…

፪. There is an origin of suffering…

“እያንዳንዱ ድቁሳት የራሱ ሰበበ ኑረት አለው”… እርሱም የፍላጎት እስረኝነት ነው… ልክ ያልተበጀለት ፍላጎት የስቃይ ምንጭ ይሆናል… ስለዚህም የማይረካን ፍላጎት ወግድ ማለት ደግ ነገር ነው… እርግጥ ‘ፍላጎት’ እንዲጠፋ መፈለግም ያው ‘ፍለጋ’ ነው… ቁምነገሩ ፍላጎትን የመግራት ጥበብ ካለመፈለግ አይከሰትም… ፍላጎትህ የህመም ሰበብ መሆኑን ከመረዳት እንጂ… ደግሞም መፈለግህ ብቻ አይደለም ችግር… የሚያስፈልግህን አለማወቅም እንጂ…

ቁጭ ብለህ በእግረ ሃሳብ የምትኳትነው… በውጣ ውረድ ድግግሞሽ ባትለህ የምትውለው ለኑረትህ ግድ የሆኑትን ለማግኘት አይሆን ይሆናል… በዙሪያህ ባሉ ሁኔታዎች በቀላሉ በሚቃኝ አዕምሮህ ግፊት የአግበስባሽነት ኢጎ ተጠናውቶህ ሊሆን ይችላል… ችግሩ የፈለግኸውን አግኝተህ እንኳ ባገኘኸው አትረካም… ቀዳዳ ኪስ አይሞላማ… ሌላ ጨምር ይልሃል… ቀዳዳውን ስትደፍን ግን ሙላትህን መገንዘብ ትጀምራለህ… ፍላጎትን ፈር ማስያዝ እንግዲህ ቀዳዳን መጥቀም ነው… እኔዬ በቂ ነው ማለት…

ለኑረትህ ግድ የሚባሉ ነገሮችን ማወቅ የሰላምህ ምንጭ… የሚጎድልም የሚሞላም የሌለህ መሆንህን ማወቅ ደግሞ አብርሆት ነው… ከውጭ የምታሳድደው ሁሉ የውስጥህን አይተካም… በቅርፃዊዉ ዓለም የቁሳዊነትም ሆነ የፍለጋዎች ጡዘት ግቡ “ደስታ” ነው ቢባልም በውስጥ ውስጠኛው አንተ ውስጥ ያለውን የዘለለት ሐሴትን ግን አይተካም… ስትፈልግ የኖርከው ያለህን ግን ደግሞ ያላየኸውን ነው ማለት ነው…

በአልማዝና በከበሩ እንቁዎች የተሞላ ሳጥን ላይ ቁጭ ብሎ እርጥባን እንደመልቀም መሆኑ ነው…

፫. There is the cessation of suffering…

ድቁሳት ምን ቢከብድ… ፈተና ምን ቢረቅ… የሆነ ጊዜ ያበቃል… ይተናል… ይበናል… የ Impermanence ህግ እንዲህ ይላል… “All that is subject to arising is subject to ceasing.” ስለዚህ ድቁሳትን በመሸሽ አታመልጠውም… ለተፈጥሮአዊ ሞቱ ትተወዋለህ እንጂ…

የድቁሳትህ ምንጮች ‘መጥፎ’ የምትላቸው ነገሮች ብቻ አይደሉም… ‘ጥሩ’ ነገሮችህም ሁነኛ ማደሪያ ናቸው… ድቁሳት ከነገሩ ተፈጥሮ ይልቅ ለጉዳዩ ካለን ጥልቅ ዝማሜ ግዘፍ ይነሳል…

ሁሌም ቢሆን ከሁነቶች ጋር የመቋጠር ቅኝት አለን… ቅርፃውያን ስለሆንን ከደስታችን ቅዥትና ከሃዘናችን ጥላ ጋር ‘የዘላለሜነሽ’ ሕብረ ዜማ እናረግዳለን… Attachment (ከነገሮች ጋር መጣመር) ክፉ ነገር ነው… ከሚያልፍ ነገር መቋለፍ ደግሞ የበለጠ አደገኛ … በውድቀት ስኬት ከፍ ዝቅ መኳተንና በወዲያ ወዲህ ፔንዱለማዊ ስሌት መዋለል የመቋለፍ ውጤት ነው… ነገሮችን እንደአመጣጣቸው ተቀብሎ የሚሸኝ ግና በጊዜያዊ ደስታ ከመስከርና በሚያልፍ ሃዘን ከመሰበር ይድናል… የወንዙን አወራረድ ለማየት ሁነኛው ቦታ የወንዙ አፋፍ ነው… እዚያ ነው የ’ሁሉም ያልፋል’ ጥበብ የሚወለደው…

ለስሜት ስብራት የሚገፉኝን ሁኔታዎች በትኩረት መመልከት ስጀምር የሚገባኝ አሃዱ የትስስሬ ጥልቀት ነው… ድብርት ውስጥ ስገኝ… ብቻነት ሲሰማኝ… እጦት ሲያንገበግበኝ… ዕድሜ ከሌላቸው ነገሮች ጋር አዕምሮዬ እንደታበተ አስተውላለሁ… ለጊዜው ካበረህ ጋር ለሁልጊዜ በፍቅር መውደቅ ክፉ እርግማን ነው… ሟችን ለሞቱ ተወው…

፬. The way out of Suffering

በድቁሳት መኖር ላይ ተግባባን… ምንጭ እንዳለውም ገባን… ተፈጥሮአዊ ሞት እንደሚሞትም እንዲሁ… ከድቁሳት ነፃ መውጣትስ አይቻል ይሆን?… ይሄ የሰው ልጅ ሁሉ ጥያቄ ይመስለኛል… ቡድሐም አብርሆት ከተቀዳጀባት ዛፍ /Bodhi Tree/ የዚህን ጥያቄ መልስ ሳያገኝ አልተነሳም… አዎን ከድቁሳት ነፃ መውጣት ይቻላል… እንዴት?

ቡድሐ ‘The eightfold path’ በማለት የሰየማቸው ስምንት ‘ቀናዎች’ አሉ… ለቀናዎቹ መቅናት ከድቁሳት ነፃ ያወጣል…

RightView,
Right Intention,
Right Speech,
Right Action,
Right Livelihood,
Right Effort,
Right Mindfulness and
Right Concentration ናቸው…

ከዚህ በኋላ ደቆስቆስ የሚያደርጉህ ነገሮች ሲበረክቱ ከኒህ ስምንት ቀናዎች የትኛውን እንዳጎደልክ መርምር…

ፍቅርን ከመስጠት በላይ ዕዳ
አይኑርባችሁ!!

ምርጫችሁ ስለሆንን ስናመሰግኖት ከልብ ነው !!!
@EthioHumanity @EthioHumanity

@EthioHumanitybot
5.9K views15:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-13 07:57:10 ለ 6ተኛ ዙር ሃገሪቱን ለመምራት "Bobi Wine" ከሚባል የ 38 ዓመት ሙዚቀኛ ጋር ለምርጫ የተወዳደሩት "Museveni" ምርጫውን ዛሬ ስላሸነፉ ለ 41 ዓመት በስልጣን ላይ ይቆያሉ ማለት ነው! ከዛ በኃላ ያው እየታየ ይጨመራል!

ከትላንት በስቲያ የ "CNN" ጋዜጠኛ የሆነችው "Christian Amanpour" እንዲህ ስትል ትጠይቃቸዋለች!

".....ከዩጋንዳ አጠቃላይ የህዝብ ቁጥር ውስጥ 85% የሚሆነው ህዝብ እድሜው ከ 35 ዓመት በታች ነው! እርሶ በስልጣን ላይ አሁን 36 ዓመት ቆይተዋል! እኚህ ወጣቶች እርሶ ስልጣን ሲይዙ እንደውም አልተወለዱም ነበር! የሚያውቁት እርሶን ብቻ ነው! እነዚህ ወጣቶች ለውጥ ይፈልጋሉ! የስራ እድል ያሻሉ! ለምን አሁንም በስልጣን ላይ መቆየትን ፈለጉ?....."

የሳቸው መልስ!

"....ምን መሰለሽ "Christian"....የጤናውን ዘርፍ አዘምኜ እነዚህ 85% የሚሆኑት የሃገሪቷ ወጣቶች ተወልደው በህፃናት በሽታ(በፖሊዮ እና በመቀንጨር) ሳይሞቱ እዚህ እንዲደርሱ ያደረኩት እኮ እኔ ነኝ! ያስተማርኳቸው እኮ እኔ ነኝ! ...ዩጋንዳ በዓለማችን ሰባተኛዋ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገትን በማስመዝገብ ላይ ያለች ሃገር ናት! ከደህነት ወጥተን በቅርቡ መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሃገራት ተርታ ልንመደብ ነው! መረጃዎችሽን በደንብ አጣሪ እንጂ! ወጣቱ በስልጣን ላይ እንድቆይ ይፈልጋል!...."

ሸጋ ቅዳሜ!

ወንድዬ እንግዳ

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity
@Nagayta
5.7K views04:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-13 07:57:10 #እምወድሽዋ! ቅዳሜዋ! ሸጋዬዋ!

የቅዳሜ ቀደዳ ፰-(8)

እንዴት ነህ ጌታይ? እንዴት ነሽ እናቴ? ቅዳሜን እንደተለመደው ፈታ፣ ነቃ፣ ዘና እናድርገው! የፀዳ ነው!
.
.
የሚገርም ሃቅ!

የዚህች አፍሪካ ሃገር አጠቃላይ የህዝብ ቁጥር 45 ሚልዮን ነው። ከዛ ውስጥ 85% የሚሆነው ህዝብ እድሜው ከ 35 ዓመት በታች ነው! ይህ 85% ወይንም 39 ሚልዮን የሚሆን ወጣት በህይወቱ ከአንድ የሃገሪቱ መሪ ውጪ አይቶም ሰምቶም አያውቅም! ምክንያቱም የሃገሪቱ ፕሬዝደንት ስልጣን ላይ ለ 36 ዓመታት የሙጥኝ ብለው እስካሁን ቁጭ እንዳሉ ናቸው።

እሺ እሱን ተወው!

"Ronald Reagan" የዛሬ 39 ዓመት 40ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት በነበረበት ወቅት እሳቸው ስልጣን ላይ ነበሩ! "George H. W. Bush"(ትልቁ ቡሽ) መጥቶ ሲሄድ እሳቸው ስልጣን ላይ ናቸው። "Bill Clinton" ተመርጦ፣ አሜሪካን ሁለት ዙር አገልግሎ ስልጣን ሲለቅ እርሳቸው ግን አሁንም ስልጣን ላይ ናቸው። "George W. Bush"(ትንሹ ቡሽ) ወደ ነጩ ቤተ መንግስት ገብቶ 8 ዓመታትን አገልግሎ ጡረታ ሲወጣ እሳቸው አሁንም ስልጣን ላይ ናቸው! "Barack Obama" የመጀመርያው ጥቁር የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆኖ ተመርጦ ያንን ሁሉ ታሪክ ሰርቶ ስልጣን ሲለቅ እርሳቸው ግን አይነኬ ናቸውና አሁንም ስልጣን ላይ ናቸው። ጌታዬ እብዱ "Donald Trump" 45ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆኖ በተዓምር ስልጣን ሲይዝ እሳቸው አሁንም የዚች ምስኪን ሃገር ፕሬዝዳንት ናቸው። አሁን ደግሞ ከቀጣዩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጋሽ "Joe Biden" ጋር ሊሰሩ ነው። 6 የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች ተመርጠው፣ ህዝብ አገልግለው እና ዘመናቸውን ጨርሰው ስልጣን ሲለቁ እርሳቸው ግን አሁንም በዛሬዋ እለት ለ 6ተኛ ዙር ምርጫ አሸንፌያለሁ ብለው ተጨማሪ አምስት ዓመታትን ሊገዙ ነው። እኚህ ሰው የ "ዩጋንዳው" ፕሬዝዳንት "Yoweri Museveni" ናቸው።

አፍሪካ ላይ በወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ስልጣን የያዙ መሪዎች ተሳክቶላቸው አያውቅም! "Yoweri Museveni" እንደ አብዛኛው የአፍሪካ መሪ በወጣትነታቸው የነ "Marx እና Lennin" የፖለቲካ እና ኢኮኖሚያዊ ርዕዮተ ዓለምን አነበቡ፣ ተመሰጡ፣ ፀዳባቸው። ጎረቤት ሃገር "Tanzania" ሄደው "Economics እና political Science"ን ካጠኑ በኃላ አሁንም እንደ አብዛኛው የአፍሪካ ሃገር መሪ ጫካ ገቡ፣ ውትድርና እና ሽምቅ ውጊያን ተማሩ! ከትግል አጋሮቻቸው ጋር ስልጣን ሲይዙ የሚያሳኳቸውን 10 ነጥቦች አወጡ! ጥሩነቱ ከነዚህ አስር ነጥቦች ውስጥ "ሃገርን ስለመገንጠል" እና "አንድን ብሄር ስለማጥፋት" የሚያወራ የለም። በአብዛኛው የዴሞክራሲያዊ ስርዓትን ስለመገንባት፣ ሃገራዊ አንድነትን ስለማጠናከር እና ሙስናን ስለማስወገድ የሚያወራ ነበር።

በመጨረሻም እ.ኤ.አ 1986 ላይ የ "Uganda" ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ! ጌታዬ! "Uganda" እጅግ ጨዋ ህዝብ ያላት እና ተፈጥሮ ሳትሰስት ሁሉን ያደለቻት ሃገር ናት። ይህንን እኔም በተደጋጋሚ በአካል አይቼ ለመመስከር ችያለው። "ጋራሽ...ሸንተረሩ...ወንዙ" ምናምን የሚለው ዘፈን የሚመጥናት፣ ለም መሬትን የታደለች፣ ለግብርናው ዘርፍ ገነት የሆነች፣ ነዳጅ፣ ወርቅ እና መዳብ(copper) በሰፊው የሚገኝባት ፀዴ ሃገር ናት።

መሪ ማግኘት ላይ ግን ብዙ አይደለችም!

በርግጥ ጋሽ "Museveni" ሃገር አረጋግተዋል፣ ጦርነት ቀንሰዋል፣ የግብርናውን ዘርፍ አሳድገዋል፣ የህዝቡን ነብስ ወከፍ ገቢ ጨምረዋል፣ የትምህርት እና ጤና ዘርፉን አዘምነዋል፣ ቱሪዝሙ በዓመት ከአንድ ቢልዮን ዶላር በላይ ለሃገሪቱ እንዲያስገባ አድርገዋል። የቴሌኮም ዘርፉንም ለውጪ ገበያ ክፍት አድርገው ወደ ሰባት የሚሆኑ ዓለም አቀፍ የቴሌኮም አገልግሎት የሚሰጡ ግዙፍ ተቋማት በሃገሪቱ ይሰራሉ። የሃገሪቱ ዳያስፖራም ጨዋ ነውና ህጋዊ በሆነ መንገድ በዓመት ከ 1.5 ቢልዮን ዶላር በላይ "Remittance" ለእናት ሃገሩ ያስገባል። ህዝቡ ቢያጣ ቢያጣ ሶስቴ በልቶ ያድራል! ልብስ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ መኪና እና መሬት ርካሽ ነው! አንድ መካከለኛ ገቢ ያለው ሰው "Range Rover" ገዝቶ መንዳት እንደሚችል ያየሁት እዛ ነው!

ሰውየው!

"Yoweri Museveni" ወጣ ያሉ ሰው ናቸው። ስልጣናቸውን ይወዳሉ! ወደ ስልጣን ሲመጡ በሁለት "term" ገድበውት የነበረውን የስልጣን ዘመን ወደ አራት "term" አሳድገዋል። በመጨረሻም ስልጣን ሲጥማቸው "እንደውም የስልጣን ገደብ የሚባል ነገር አያስፈልግም!" ብለው ህገ መንግስቱን አሻሽለዋል።
ሰውየው ተቃዋሚዎቻቸውን እንደ አብዛኛውም የአፍሪካ መሪ ያስራሉ፣ ቶርች ያስደርጋሉ፣ ይገላሉ፣ ከሃገር ያሰድዳሉ! የወር ደሞዜ ወደ 1000 ዶላር ገደማ ነው ቢሉም በወር ግን ወደ 4.1 ሚልዮን ዶላር እንደሚያገኙ ይነገራል።

እንዴት?

በሃገሪቷ የሚገኙ አብዛኛዎቹ ባለ ኮከብ ቅንጡ ሆቴሎች የእሳቸው ናቸው። ሰፊ እርሻዎች እና ወደ 1000 የሚጠጉ የሆላንድ ላሞች የሚገኙበት የእንስሳት ተዋእፆ አምራች ድርጅት አላቸው! የሳቸውን ጨምሮ በሃገሪቱ ለሚገኙ ትልልቅ ሆቴሎች ወተት የሚያከፋፍሉት እሳቸው ናቸው። አጠቃላይ የሰውየው ሃብት ወደ 4 ቢልዮን ዶላር ገደማ ይገመታል! እንደ "BMW", "Limousine" እና "Mercedes benz" በመሳሰሉ ውድ ውድ መኪኖች ይንሸራሸራሉ። የግል ጀት ሳይቀር አላቸው! እሳቸው እንደሚሉት ይህንን ሁሉ ሃብት ያካበቱት 1000 ዶላር በማይሞላ ደሞዛቸው ነው እንግዲህ!

የሚገርም ነገር!

ምዕራባዊያኖቹ በ "Uganda" የግብረ ሰዶማውያን መብት አይከበርም! ልክ እንደ እኛ "Uganda" ውስጥም "ህጋዊ" መሆን አለበት!.." እያሉ ሲወተውቷቸው አንድ ነገር አደረጉ!

በሃገሪቱ አሉ የተባሉ ሳይንቲስቶችን እና የጤና ባለሙያዎችን ሰብስበው "ግብረ ሰዶማዊነትን ሰዎች ሲወለዱ ይዘውት የሚወለዱት ነገር ነው? ወይስ የሚማሩት ነገር ነው?" የሚለውን የሚያጠና መስሪያ ቤት አቋቁመው አስጠኑ! ኃላም "የሚማሩት" ነገር ነው የሚል ድምዳሜ ላይ ደረሱ መሰለኝ ግብረ ሰዶሞች ላይ የእድሜ ልክ እስራትን የሚፈርድ ህግ አፀደቁ! ምዕራባዊያኖቹንም አስነቀሏቸው!

ሰውየው ሲፈልጋቸው እራሳቸው አስመርቀው በከፈቱት "ቸርች" እሁድ እሁድ እየሄዱ ህዝቡን "የጌታ መምጫ ተቃርቧልና ንስሃ ግቡ!" እያሉ ያስተምራሉ፣ ሲፈልጋቸው ቢሯቸው ውስጥ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እያደረጉ ተቀርፀው "ህዝቤ እንዳትወፍር እነዚህን ቀለል ያሉ ስፖርቶች ስራ!" ብለው ቪድዮ ይለቃሉ፣ ሲያሻቸው ደግሞ በምርጫ ወቅት የምረጡኝ ቅስቀሳ ለማድረግ "You want another rap?" የሚል ቀውጢ የራፕ ሙዚቃ ለህዝቡ ይለቃሉ! "Kanye West" እና ሚስቱን ሳይቀር ቤተ መንግስት ድረስ አስጠርተውም ይጋብዛሉ።

"Social Media" የሃገሬን ህዝብ ስራ እያስፈታ ነው፣ ሃሰተኛ መረጃዎች እያወዛገቡት ነው፣ ህዝቤን አመፀኛ አድርጓል!" ብለው የሚሞግቱት ጋሽ "Museveni" እያንዳንዱ ማህበራዊ ሚድያ የሚጠቀም ዩጋንዳዊ ታክስ እንዲከፍል ጭምር አድርገዋል!

እጅግ የተማሩ የአፍሪካ መሪ የሚባሉት እኚህ ሰው በህግ፣ በ "Theology" እና በ ስነ-ፅሁፍ ሶስት የዶክትሬት ዲግሪዎች አሏቸው። ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎችም ሰባት የክብር ዶክትሬት ማእረጎችን አግኝተዋል!

ማጠቃለያ!
5.3K views04:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-13 07:55:17
4.4K views04:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ