Get Mystery Box with random crypto!

ስብዕናችን #Humanity

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiohumanity — ስብዕናችን #Humanity
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiohumanity — ስብዕናችን #Humanity
የሰርጥ አድራሻ: @ethiohumanity
ምድቦች: ሳይኮሎጂ
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 30.61K
የሰርጥ መግለጫ

🔆እየጠየቁ መኖር መልስን፣
መልስን ፈልጎ ማግኘት ዕውቀትን፣
እውቀት ነፃነትን፣ ነፃነት ሙሉ ስብዕናን፣
ሙሉ ስብዕና ሠላምና እርካታን፣
እርካታ ደግሞ ደስተኛ ሆኖ መኖርን ያስገኛል፡፡
አብረን እንደግ !!
@EthioHumanity @Ethiohumanity
✍የተሰማቹን አጋሩን! ቤቱ ሁሌም ክፍት ነው፣ሃሳባቹን ፃፍፍ አርጉልን @EthioHumanitybot

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 30

2021-12-16 18:08:50 ትናንት ስታዜመው የነበረ፣ ለዛሬ ያላደረ አስተሳሰብ አለህ?…

አይግረምህ!!.. ይልቅ ዛሬ የምታወግዘው ሃሳብ የነገ ተረኛ ቅኝትህ ሆኖ ሊከሰት እንደሚችል አስብ… በመኖር ውስጥ ወጥ የሚባል ቅኝት፣ የማይለወጥ የሚባል የማሰብ ፍኖት የለም… ‘ልክ’ ይመስለኝ ነበር ያልከውን መረጃ ‘ልክ እንዳልሆንክ’ ባሳየህ የዛሬ ክስተት ለመለወጥ ስትንደረደርም ሆነ ሽንጥህን ገትረህ የተሟገትክለት ሃሳብ ነገ ደርሶ ብን ሲልብህ ስታይ ውል አልባነት አይሰማህ

በሕላዌ ሕዋ ውስጥ ወዲህ ቢሉት ወዲያ የማይለወጥ አንድ ነገር እውነት ብቻ ነው… እውነት እውነትነቷ ነው ውበቷ - እውነት እውነት ትባል ዘንድ የድጋፍ ሰልፍ አትፈልግም… በራሷ የምትቆም ጽኑ ናት… የተከታዮቿ ማነስና መብዛት የእውነትነቷን ሞገስ አይነቀንቀውም… “The truth is like a lion; you don’t have to defend it. Let it loose; it will defend itself.” እንዲሉ... እስስት ሆኖ የሚዘልቀው ምን ይሆን ታዲያ?… መረዳትህ ነው… ግንዛቤህ… የእይታ አንፃርህ /Level of understanding/…

የብዙ ውይይቶች ውጤት ጽንፍ ለጽንፍ በሚተያዩ ሃሳቦች መደምደም የየትኛውንም ወገን ትክክለኛነት አይናገርም… የማንኛውንም ስህትነትም አይገልጽም… የየወገኑን አንፃር እንጂ… ስለዚህ እንደኔ ካላሰብክ ብሎ ሙግት መግጠምም ሆነ የሌላውን ሌላነት የመግለጽ ነፃነት መጋፋት በደል ነው… የእውነት ተክለ ቁመና በአንፃራዊነት ባይዳኝም ታዳሚዎቿ ግን በየልካችን የምንሰፋው ‘እውነት’ ያለን መሆኑ እርግጥ ነው…

ፈጣሪ ሕይወትን ሳንሰለች እንዋብባት ዘንድ የተለያየ መነጽር እያቀበለን የእውነት ፀሐይ ከደመና ጥጥ ውስጥ ተፈልቅቃ ስትወጣ ያለውን ሂደት ጊዜ በሚሉት ሃዲድ ላይ ሆነን እንመለከታለን… ግና የገባን እንጂ ደርሶ የጨበጥነው እውነት የለንም!!!

እና ምን ለማለት ነው… ‘ፍጹም እውነትን ይዘናል’ ከሚሉኝ ይልቅ ‘እውነትን እየፈለግን ነው’ በሚሉኝ ሰዎች ዙሪያ መገኘት ያስደስተኛል…

ደምስ ሰይፉ

ውብ አሁን
@EthioHumanity
@EthioHumanity
1.6K viewsedited  15:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-16 18:08:44
1.5K views15:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-12 21:16:55
የአስተሳሰብ ለውጥ ልክ እንደ አውሮፕላን ሁለት ክንፍ አለው!

የአስተሳሰብ ለውጥ ልክ እንደ አውሮፕላን ሁለት ክንፍ አለው ፡፡ አንዱ ክንፍ እውቀት ነው፡፡ ሌላኛው ተግባር ነው፡፡ሰዎች ለመለወጥ የሚቸገሩበት አንደኛው ምክንያት ከእውቀት እጦት የተነሳ ነው፡፡ ምክንያቱም በማታውቀው ነገር ዙሪያ እንዴት ትለወጣለህ? ይሄ ቦታ አልተመቸንም ብንል የት ነው የምንሄደው? እንዴት ነው የምንሄደው? ሄደን ምን ያጋጥመናል? ካላልን አስቸጋሪ ነው፡፡

ሁሉ እውቀት ኖሮን ደግሞ ባለንበት ቁጭ ብንል ተለወጥን ማለት አይደለም። አሁን እንደውም ትልቁ ሽወዳ ያለው አንዳንዴ ብዙ ስለለውጥ ስናውቅ የተለወጥን ይመስለናል፡፡ ከእሱ ደግሞ አለማወቅ ሁሉ ይሻላል፡፡

እውቀት ብርሀን ነው፡፡ ካወክ በራልህ ማለት ነው ፡፡ ቤት ውስጥ መብራት ባይኖር ምንም ማድረግ አትችል ይሆናል፡፡ ግን ቤት ውስጥ መብራት ቢኖር ስቶቩን ለኩሶ፣ እቃውን አውጥቶ፣ ድስቱን ጥዶ ምግብ አብስሎ አያበላህም፡፡ ነገር ግን አንተ እንድትሰራ በር ይከፍትልሀል፡፡

ስለዚህ እውቀትን እና ተግባርን ማቀናጀት ነው ለውጥ የሚፈጥረው! ምንድን ነው መለወጥ የምንፈልገው? እሱን መለየት ያስፈልጋል፡፡ ምንድን ነው ማድረግ ያለብን? እሱንም መለየት እና ማድረግ ነው፡፡ ጓሮህን ከሆነ መለወጥ የምትፈልገው እንዴት መለወጥ እንደምትችል ማወቅ አለብህ፡፡ ከዛ እጅህን ሰብስበህ መነሳት አለብህ፡፡ ጓሮህ ተቀየረ ማለት ነው፡፡

ዶ/ር ምህረት ደበበ

መልካም አዳር
@EthioHumanity
@EthioHumanity
2.6K views18:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-11 09:17:03 ብቁ ናችሁ!

ከሕይወት ትልልቅ የፍርሃት ምንጮች አንዱ “ብቁ ያለመሆን” ፍርሃት ነው፡፡ በሰዎች ለመወደድ፣ ለመፈቀር፣ ተቀባይነት ለማግኘት፣ ለማወቅ፣ ለመሰልጠን፣ እድገት ለማግኘት . . .ብቁ እንዳልሆንን የማሰብ ፍርሃት!

እውነት እውነቱን እንነጋገር፡፡ አንድ ሰው እናንተን ለመቀበልና ለመውደድ የማይችል ወይም የማይፈልግ ከሆነ፣ ይህ ማለት እናንተ የዚያ ሰው አይደላችሁም ማለት ነው - አለቀ! ይህ ማለት ግን የዓለም መጨረሻ ነው ማለት አይደለም፡፡ ይህ ሰው እናንተን የመቀበልና የመውደድ ብቃቱ ወይም ፍላጎቱ የለውም ማለት ነው እንጂ እናንተ ተቀባይነት የማግኘትና የመወደድ ብቃቱና ማንነቱ የላችሁም ማለት አይደለም፡፡

እናንተን የመውደድም ሆነ የመቀበል ብቃቱና ፍላጎቱ ያለው ብዙ ሰው በዙሪያችሁ እንዳለ አስታውሱ፡፡ እነሱን ለማየትና ለመገናኘት ግን “ካልተቀበለኝና ከልወደደኝ” ብላችሁ ችክ ካላችሁት ሰው ላይ አይናችሁን ማንሳት፣ ስሜታችሁንም ማላቀቅ የግድ ነው፡፡ ይህንን ማድረግ ለጊዜው ከባድ ነው፣ ነገር ግን በሚልየን የሚቆጠሩ ሰዎች ችለውታልና እናንተም ትችላላችሁ!

አንድ ነገር አልሆን ሲላችሁ ሁል ጊዜ እናንተ ለዚያ ነገር ብቁ ስላልሆናችሁ እንደሆነ የማሰብን የእሳቤ ንድፍ መቀየር አለባችሁ፡፡ በዚያ ምትክ ያ ሰውም ሆነ ሁኔታ ለእናንተ የማይመጥን ስለሆነ እንደቀረላችሁ ማሰብም አስፈላጊ የሚሆንበት ጊዜም እንዳለ አትዘንጉ፡፡

በአጭሩ፣ ለመወደድ ብቁ ናችሁ! ለማደግ ብቁ ናችሁ! ለማወቅ ብቁ ናችሁ! በዚህ ዓለም ፈጣሪ ለሰው ልጆች ደስታና ስኬት ለፈጠረው መልካም ነገር ሁሉ ብቁ ናችሁ! ሕይወት ትክክለኛውን ሰውና ስፍራ ገልጣ እስከምታቀርብላችሁ ድረስ ግን ራሳችሁን በመቀበል የድርሻችሁን መወጣት የግድ ነው፡፡

ዶ/ር እዮብ ማሞ

ውብ ቅዳሜ

@EthioHumanity
@EthioHumanity
3.6K views06:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-11 09:16:50
3.1K views06:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-09 21:16:23 ከምንም በላይ አንዳችንን ከሌላኛችን የሚለየን ነገር ቢኖር ለራሳችን ያለን አመለካከት ወይም ምስል በእንግሊዘኛው ደግሞ "Self Image" ነው። ሁላችንም በዚህ አለም ላይ ስንኖር የኑሮዋችን መጠንና ልኩ የሚወሰነው ለራሳችን ባለን አመለካከት ወይም በአይምሮዋችን ውስጥ ስለራሳችን በምንቀርጸው ምስል ነው። ባህሪያቶቻችን፤ ውሳኔዎቻችን፤ አጋጣሚዎቻችንና በህይወታችን የምንስባቸው ሰዎች በሙሉ ለራሳችን ባለን አመለካከት ተጽዕኖ ስር ይወድቃሉ።

ለራስ የሚሰጥ አመለካከት (self Image) በህይወታችን እጅግ ወሳኝ ነገር ነው። አንድ ሰው ስኬታማና ደስተኛ ሊሆን የሚችለው ለራሱ የተስተካከለና አወንታዊ አመለካከት ሲኖረው ብቻ ነው። ችግሩ ይህንን እውነታ ማንም ሰው ከልጅነታችን ጀምሮ ስለማያስተምረን አብዛኛዎቻችን ለራሳችን የተሳሳተ አመለካከት በመያዝ እናድጋለን። አቅምና ችሎታችንን የሚገድቡ እምነቶች "Self Limiting beliefs" ሳናውቀው በአይምሮዋችን ውስጥ ስር ይሰዳሉ። እኒህ አመለካከቶቻችን ናቸው የምንፈልገውን ኑሮ እንዳንኖር እንቅፋት የሚሆኑብን።

ህይወታችንን ሊቀይሩ የሚችሉ እውነታዎች በሙሉ ቀላልና ያልተወሳሰቡ ሀሳቦች ናቸው። ምናልባት ለዛም ይሆናል በቁም ነገር ወስደን የማንተገብራቸው። እኛ ሰዎች በተፈጥሮዋችን የተወሳሰበና ከባድ ነገር ይበልጥ ተዓማኒነት ያለው ይመስለናል። ለችግሮቻችን መፍትሄ ስንፈልግ እንኳን ቀለል ያለ ሃሳብ አንቀበልም። እቃ ስንገዛ የተወደደው እቃ ሁሌም ከረከሰው የተሻለ ይመስለናል፤ በወረፋ ካልተሰለፍን በቀር የምናገኘው አገልግሎት ጥራት ያለው አይመስለንም።

ተሻምተን ካላገኘናቸው በቀር ነጻ ለምናገኛቸው ነገሮች ዋጋ አንሰጥም። እራሳችንን ለመለወጥ ስናስብም እንደዛው፤ በቀላሉ አስተሳሰባችንን በመቀየር ህይወታችንን መቀየር እንደምንችል አምነን መቀበሉ ይከብደናል። ሰው አስተሳሰቡን በመቀየር ኑሮውን መቀየር እንደሚችል ለብዙ መቶ አመታት ሲንገር የነበረ ቢሆንም፤ እኛ ግን ይህን ለመረዳት አልፎም በቀላሉ ስራ ላይ ለማዋል አልቻልንም።

እያንዳንድችን ስለራሳችን በአይምሮዋችን የምንቀርጸው ምስል አለ። ይህ ምስል መልካም ምስል ካልሆነ በኑሮዋችን ላይ የሚጸባረቁት እውነታዎችም ከዚህ ምስል የተለዩ አይሆኑም። በተቃራኒው ስለራሳችን ያለን አመለካከት ወይም በውስጣችን የምንስለው ምስል መልካም፤ጠንካራና አወንታዊ ከሆነ፤ በኑሮዋችን ላይ የሚንጸባረቁት እውነታዎች በሙሉ የአወንታዊው አመለካከታችን ነጸብራቆች ይሆናሉ።

ይህ ለራሳችን የምንሰጠው አመለካከትና ግምት ነው፤ በራሳችን ላይ የሚኖረንን እምነት የሚወስነው። በራስ መተማመናችን የሚበቅለው ለራሳችንን ባለን አመለካከት አፈር ላይ ነው።በትምህርትም ሆነ በስራ፤
በፍቅርም ሆነ በግል ህይወታችን ውስጥ የምናገኛቸው ውጤቶች ለራሳችን ካለን አመለካከት የሚመነጩ ናቸው።

ውብ አሁን
@Ethiohumanity
@Ethiohumanity
4.3K viewsedited  18:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-09 21:16:07
3.6K views18:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-07 07:24:49 የተሻለውን ማየት

በህይወት ውስጥ የልብን መሻት ለማግኘት መፍጨርጨር ያለ ነው። ያሰቡትን አግኝቶም ሆነ ሳያገኙ መቆም ግን ድክመት ነው፤ ተገቢ አይደለም። ከግቡ ባሻገር የተሻለውን የበለጠውን ማየትና እሱ ላይ ለመድረስ መገስገስ ያስፈልጋል። "እኔ የምበላውን ካገኘሁ ይበቃኛል፣ ምን ያለፋኛል?" ማለት የሰነፍ፣ የንፉግ እና የራስ ወዳድ ሃሳብ ነው። ካንተ አልፎ ለሌላው የሚተርፍ እንዳትሠራ ምን ያግድሃል? ስንፍና፣ ንፉግነት ወይም ራስ ወዳድነት ካልሆነ በቀር።

የዓለም ሊቃውንት እንዲያ ቢሆኑ ኖሮ፣ ኑሮ ምን ያህል አስቸጋሪ ይሆን ነበር? ኤዲሰን እንዲያ 10ሺህ ጊዜ ባይሞክር ህይወታችን ምን ያህል ጨለማ በዋጠው ነበር። የእጅ ስልክህ የስንት "ምን ቸገረኝ" ብለው ያልቆሙ እና የተሻለውን ማየት የቻሉ ሰዎች ውጤት ነው።

ወዳጄ ሆይ! ታካች አትሁን። በልፋት ውስጥ ደስታ አለ። እናቶች ሁሉ ልጅ የመውለድ ምጥ ምን ያህል ከባድ መሆኑን እያወቁ ልጅ ይወልዳሉ። በልጁ መወለድ የሚገኘው ደስታ የተሻለ መሆኑን ያምናሉ፣ ያውቃሉም። "ምጥ በልጅ ይረሳል" አይደል የሚባለው?

ስላለህ ነገር ተመስገን ማለት ጥሩና ተገቢ ነው። በምስጋና ውስጥ ድል አለ። ከምስጋናው ባሻገር ግን የተሻለውን ማየትና በእጅ ለማስገባት ሳይስገበገቡ መስራት ያስፈልጋል። ሳይንገበገቡ የሚሠሩ በሚያጋጥማቸው እንቅፋት አያዝኑም፣ አይቆሙም። እንቅፋቱ በጉዞው ውስጥ ሊያጋጥም የሚችል መሆኑን ይቀበላሉ፤ ተገቢውን ጥንቃቄ ያደርጋሉ። ሲያጋጥምም ለመፍትሔው ይሠራሉ።

ዛሬ የትናንት ሥራችን ውጤት ነው። ከትናንት የተሻለ ነገን ለመፍጠር ዛሬ ላይ ማሰብ፣ መሥራት፣ አዲስ ነገር መሞከር ያስፈልጋል። "የተሻለውን ዓይተው የተጓዙ ጥቂቶች ቢሆኑም የሚሻለው አካሄድ እሱ ነው።

ለሀገራችን፣ለራሳችን፣ ለሰው ልጅ የተሻለ ዓለም ለመፍጠር እንጣር!
ዛሬ አዲስ ቀን ነው። በድንግዝግዝ ውስጥ የተሻለውን ዓይተን ወደዚያ እንጓዛለን!

መልካም ቀን

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity
5.3K viewsedited  04:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-07 07:24:22
4.4K views04:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-05 18:32:48
  የደስታ ሁሉ ምንጭ አእምሮ ነው ፣ የመከራ የሥቃይ ምንጭም ራሱ አእምሮ ነው ፡የአዕምሮአችንን ተፈጥሮ በጥልቅ ተረድተን ከተጠቀምበት እውነተኛ ደስታ እና የነፃነት ውጤት ማግኘት እንችላለን ፡፡

ወዳጄ ሆይ አንድን ነገር ለመረዳት ስትፈልግ ያንን ነገር መውደድ ይኖርብሀል ፣ስትወደው ሕይወት ቀላል ይሆናል። ከዚያ ስሜት በሚነካ ሁኔታ ነገሮችን ማስተዋል እና መረዳት ትጀምራለህ።ሁሉንም ለመረዳት ግን መጀመርያ በልብህ ውስጥ ፍቅር ሊኖርህ ይገባል ፡፡

ማንነትህን ጠንቅቀህ ስትረዳ ዋጋህን ታውቀዋለህ ።የምትኖርበትን እና የምትኖርለትን ትለያለህ ።ወደ አዚች ምድር የመጣኧው ለምክንያት ነው ። አንተ የዚህች አለም ገፅ ውብ እና ሙሉ ይሆን ዘንድ እንደ አንዱ ጡብ ነህ ።ዋጋህን ባለመኖርህ አትተምን በመኖርህ እንጂ።የአንተ መኖር ለሌሎቹ ጡቦች ድጋፍ እንዲሁም ለግንባታው ውበት አስፈላጊ ነው።

ይህን ባስተዋልክ ጊዜ ራስህን ነፃ ታወጣለህ ፣ፍቅር ሲኖርህ ደግሞ የማንም ትዕዛዝ ሳያስፈልግህ የሰዎችን ሥቃይ የሚያስታግስ መንገድ ትፈጥራለህ።

ውብ አሁን
@EthioHumanity
@EthioHumanity
5.7K views15:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ