Get Mystery Box with random crypto!

ሰዓት እላፊ! (ምናለ ሁሉም ሴቶች እንደ አንቺ ቢሆኑ) በሳቅሽ | ስብዕናችን #Humanity

ሰዓት እላፊ! (ምናለ ሁሉም ሴቶች እንደ አንቺ ቢሆኑ)



በሳቅሽ ነው እንጂ!
ባሳማኝ ስብከትሽ፥ ሰላም ጠፋ ብለን፣
ሼኹ ከፋ ብለን፣
ከመቅደስ ያልራቅን፥ ማነብነብ ያልተውን።
.
ባንቺ ባይሆን ከመቅደሱ መድረክ የተሾመው አሽሙረኛ ሰባኪ ከኮማሪዋ እኩል ቀልብያችንን ጥላሸት ሲቀባው ኤዲያ ብለን በወጣን ነበር። ተስፋ ቆርጠን በእንብርክክ በቆምን ግዜና ተብሲራቱን አንቺ ባነግሪን ከቶ ምን ነበርን? የመንደራችን ሰባኪ እና አጋፋሪዎቻቸው የእዝነቱን መምህር አስተምህሮ እያነበነቡ በጳውሎስ የወንጀል ውርስ አስተሳሰብ ምርኮ ተይዘው ሲያገሉ፤ ወንድማቸውን ሲገሉ ገለውም በእሬሳ ላይ ዳንኪራ ሲቆሙ በቃን ባልን ግዜና "ለጫማ ሲል ወንድሙን የሚገል ተምሳሌት አቅርበሽ በርቱ!" ባትይን መውደቂያችን የት ነበር? አንዳንድ ነፍሶች በዝምታ ይግባባሉ ብለሽን ነፍስያችንን ካንቺ እናቆራኛት ዘንድ ባታረጊን ምን ነበርን?
.
ፈገግ ብትይ እንጂ!
አማን በሌለበት አገር አማን የምል፣
ምክርሽን ሰምቼ ቀዬው ሰላም ብዬ፣
ጥላቻ ረስቼ፥
ከእንቅልፌ ምነሳ በእርሱ ተመጅኜ።
.
ስብከቱ ጥላሸት ቀብቷቸው የጠቆሩ፤ መንደሩ በጥሎ ማለፍ ተሞልቶ አቅም የለኝም ብለው የሸሹ፤ በጥቅሉ ስለሚዳው የማያውቁ መንፈሳዊነትን ትተው ከቁስ ሲዋጡ መፍትሄ ምን ይሆን ብሎ ላብሰለሰለ ያንቺ እና የወዳጆችሽ ስብከት እንጂ ከቶ ሌላ ምን ይታየዋል?
.
በሳቅሽ ነው እንጂ!
ፅልመት የሚገፈፈ ጨለማ ሚበራ፣
ነዳያን የሚጠግብ ድብልቁ ሚጠራ።
መገን!
እንደው ባንተው መጀን ዱበርቲ ያዳራ፣
በደስታ ታጠኚ ፊትሽ በሳቅ ያብራ።
መገን!
እንደው ባንተው መጀን!
እንደው ባንተው መጀን ሺህ አመት አኑራት፣
ብርታት አቆይላት!
ጉልበት መርቅላት፣
ይሁን!
ይሁን!
መቼ? አሁን!(በዱበርቲኛ ቢነበብ)
ጭንቀትዋን አጥፋላት!
እውቀትዋን አብዛላት፣
ስብከት ይመርላት፣
ሀሳቧ ይሙላላት፣
እንደው ባንተው መጀን!
እንደው ባንተው መጀን!
ሳቋን እያቆየህ በተስፋ አለምልመን።


ሰላም እደሩልኝ!

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity
@Nagayta