Get Mystery Box with random crypto!

የሁላችንም ጥንካሬ ያለው በተመቻቸው ስፍራ ሳይሆን ሁኔታዎች ፈር ሲለቁ ጨለማ ሲከበንና ህይወት መው | ስብዕናችን #Humanity

የሁላችንም ጥንካሬ ያለው በተመቻቸው ስፍራ ሳይሆን ሁኔታዎች ፈር ሲለቁ ጨለማ ሲከበንና ህይወት መውጫ የሌላት መስላ ስታስጨንቀን በምንወስነው ውሳኔ ውስጥ ነው። የማንነታችን ትርጉም የሚለካው ነን ብለን የምናስበው ማንነታችን ፈተና ሲገጥመው በምንወስደው እርምጃ ነው። እራሳችንን የፍቅር ጥግ አርገን የምንይ ከሆነ የፍቅር ጥግ መሆናችንን የሚረጋገጠው ጥላቻ ግድ የሚሆንበት ቦታ ላይ የፍቅርን ፀዳል መልቀቅ ስንችል ነው። የይቅርታ ሰው መሆናችን የሚታወቀው ይቅርታ ለማረግ በሚያስቸግርበት ሁኔታ ላይ ይቅር ማለት ስንችል ነው።ምክንያቱም ነን ብለን የምናስበው ሁሉ ያልሆነው ነገር ሲመጣ ይፈተናልና። እናም በምትፈተንበት ሰዓት የምታረገው ትልቁ ነገር ትልቁ መሸጋገርያህ ይሆናል።

ታድያ ፍቅር ስትሆን ጥላቻ መሀል ትሄዳለህ። ህይወት ስትሆን ሞት መሀል ትራመዳለህ። ሰላም ስትሆን ጦርነት መሀል እራስህን ታገኛለህ። ደግ ስትሆን ክፋት ይከብሀል። እና ይሄ ሁሉ የሚሆነው ነኝ ብለህ የምታስበውን ብርሀን ነኝ ብለህ የምታስበውን ፍቅር ነኝ ብለህ የምታስበውን መልካምነት ታረጋግጥ ዘንድ ነው። " እኔ መልካም ሆኜ ሳለው ለምን መከራ በኔ ላይ ፀና" ብለህ ምታዝን ከሆነ አላማውን ስተሀል። ማንም ክፉ የለምና።ሁሉም ደግ ሁሉም ቸር ሁሉም ፍፁም ነውና። ነገር ግን አንዳንዱ ሁኔታው ሲናወጥ ማንነቱ መርሳቱ ነው። ስልጣን ፤ ገንዘብ፤ ረሀብ ፤ ጥጋብ ፤ ድህነት . . . ወዘተ ማንነትን የማስረሳት ችሎታ አላቸውና። ታድያ ሚሰርቅ ስታይ ሌባ ባለመሆንህ እራስህን እንደ ፃዲቅ አትቁጠር። ምክንያቱም የሌባው ቦታ ላይ ብትሆን እራስህ ያንን ነገር ላለማረግህ ምንም ዋስትና የለህምና። ስንቶች በተናገሩ ባወገዙት በጠሉት ነገር እራሳቸው ገብተውበት አይተናልና።

ፍጥረት ሁሉ ፍፁም መሆኑን ተረዳ። ፍፁም ያልሆነ ሁኔታ እንጂ ፍፁም ያልሆነ ሰው የለም። ሁሉም ሰው ክፍቶብህ ከታየህ ከመራገም ይልቅ ነኝ ብለህ ምታስበውን መልካምነት ሁን። ጥላቻ ሲከብህ ነኝ ብለህ ምታስበውን ፍቅር ሁን። ይሄን መሆን ካልቻልክ ግን ሁሌም ቢሆን ማንነትህን ሳታውቅ ትኖራለህ። እራስን መካድ የፈጠረን መካድ ነው። ውብ እና ድንቅ ሆነህ ከተፈጠርክ ውብ ና ድንቅ ሆነህ መኖር ብቸኛው አማራጭህ ነው። ውብ ና ድንቅ ሆኖ የተፈጠረው ደግሞ አንተ ብቻ ሳትሆን ሁሉም ነውና መንገዱን የሳተ ሰው ሲጎዳህ ከመርገም ይልቅ ወደ ውብነቱ ወደ መልካምነቱ የሚመለስበትን ብርሀን አብራበት።

ውብ አዳር

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot