Get Mystery Box with random crypto!

ሕይወት እንደ ማዕበል ሲሆን! አንዳንድ ጊዜ ሕይወት እንደ ማዕበል ነው፡፡ በሰላም ይሄዱ የነበሩ | ስብዕናችን #Humanity

ሕይወት እንደ ማዕበል ሲሆን!

አንዳንድ ጊዜ ሕይወት እንደ ማዕበል ነው፡፡ በሰላም ይሄዱ የነበሩ ነገሮች ልክ የተመካከሩ ይመስል በአንድ ላይ ይናጋሉ፡፡ የሁኔታዎች አልሳካ ማለት፣ ድንገተኛ ወጪዎች፣ የገንዘብ እጥረት፣ የጉዳዮች መጥመም፣ የሰዎች ክህደት፣ ስጋትን የሚፈጥሩ ሁኔታዎች መከሰት፣ የጤንነት መቃወስን የሚጠቁሙ ምልክቶች . . . ልክ እንደ ማዕበል በአንድ ላይ ይመጣሉ፡፡

ስለዚህም መወገድ የሚችለውን ችግር በማስወገድ፣ የማይወገደውን ችግር ደግሞ ችግሩ የሚያስከትለውን መጨናነቅ ከእኛ በማስወገድ ነው የምናሸንፈው፡፡

ችግር ካልተወገደ በስተቀር የተሳካ ሕይወት እንደሌለህ ስታስብ፣ ዘወትር የማይለወጥ ነገርን ስትታገል ትኖራህ፣ ሁል ጊዜ “ለምን?” በሚል ጥያቄ ውስጥ ትኖራህ፣ ተስፋ ቢስነት ይጫጫንሃል፣ እንዲሁም ሁሉም ሰው ከችግር ነጻና ደስተኛ፣ አንተ ብቻ ችግረኛ እንደሆንክ በማሰብ ድብርት ውስጥ ትገባለህ፡፡

በተቃራኒ ግን የችግሩ ማዕበል ባይይረጋጋም አንተ ስትረጋጋ መነጫነጭን ታቆማለህ፣ የፈጠራ ብቃትህ ይወጣል፣ አዳዲስ መንገዶን ትቀዳለህ፣ ችግሩን ጠንካራ ለመሆን ትጠቀምበታለህ፣ ከችግሩ ባሻገር አልፈህ ከሄድክ በኋላ ለብዙዎች ደጋፊ ትሆናለህ፡፡

ይህ የተለመደ የሕይወት አካል የሆነ ክስተት በእኛም ላይ ሲደርስ መረጋጋት ወሳኝ ነው፡፡ ማዕበል ይመጣል፣ ልክ እንደመጣ ደግሞ ይሄዳል፡፡ ነፋስ ከየት እንደመጣ ሳናውቀው ወደ እኛ ይነፍሳል፣ ወደየት እንደሚሄድ ሳናውቀው ደግሞ ወደሌላ ቦታ ይነፍሳል፡፡

ተንጋግቶ የመጣው ተንጋግቶ ይሄዳል፣
የችግሩ ማዕበል ባይረጋጋም አንተ ግን ተረጋጋ!!

ዶ/ር እዮብ ማሞ

መልካም እንቅልፍ

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot