Get Mystery Box with random crypto!

በዓሉ ግርማ እድር የለውም ፣ እቁብ የለውም ፣ ማኅበረ የለውም። ስለ ነገ አይጨነቅም። “ መስከረም | ስብዕናችን #Humanity

በዓሉ ግርማ እድር የለውም ፣ እቁብ የለውም ፣ ማኅበረ የለውም። ስለ ነገ አይጨነቅም። “ መስከረም በዓሉ ግርማ ” የነገረችኝም ይህንኑ ነው ፣ 'በዓሉ አሁንን ነው የሚኖረው። እሱ ብቻ ሳይሆን መሪ ወንድ ገፀባሕርያቱ የአሁን ሰው ናቸው። ኦሮማይ ውስጥ የምናነበው ፀጋዬ ኃይለማርያም የሚናገረው ነገር በዓሉን የሚገልጸው ሆኖ አግኝቼዋለሁ።
እንዳለጌታ ከበደ

ስለ ሕይወት እቅድ የለኝም ከመኖር ሌላ:: የሕይወት ግቡ እራሱ መኖር ነው::
ይህችም ውድ የሆነች ትንሽ ቁራሽ ሕይወት እንደአብርሃም ቤት የለኝ፣ እንደሙሴም መቃብሬ ሳይታወቅ መኖር፣ መጻፍ ፣ ሕይወትን በተስፋ ወደፊት እየኖርኩና ወደኋላም እያስተዋልኩ ስለ ኑሮ ቀርቶ ስለምጽፈው ልብወለድም ቢሆን እቅድ አላወጣም።
ደራሲው

« ስለሞት አስቤ አላውቅም። የሙያዬ ባህርይ ፣ ያለምንም ሥጋትና ጭንቀት በማያቋርጥ አሁን ሁኔታ ውስጥ የመኖር ልማድ አሳድሮብኛል። ስለ ወደፊቱ ለምን ይታሰባል ?” ትኩስ ዜና ፣ ትኩስ ሕይወት ! ሞት ለእኔ ምኔም አልነበረም ፣ ሆንም አያውቅም። ትኩስ ዜና ከማጣት ፣ አበቦችን ካለማየትና የቆንጆ ሴት እጅን ለመንካት ካለመቻል የበለጠ ስቃይና መለየት ምን ይኖራል ?” ሞት ትርጉም ሰጥቶኝ አያውቅም . . . እውን ነገር አሁን ብቻ ነው። አሁን አለሁ ፣ ደህና ነኝ ፣ እተነፍሳለሁ ፣ ውብ ኮከቦች እቆጥራለሁ ፣ ይበቃል።
ኦሮማይ

በዓሉ ግርማ

ውብ አዳር

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot