Get Mystery Box with random crypto!

ጨርሶ አይጨልምም። ፀሐይ ስትጠልቅ፣ ጨረቃና ከዋክብት ይወጣሉ። ዘጠኝ በሮች ሲዘጉ አንዱ ይከፈታል። | ስብዕናችን #Humanity

ጨርሶ አይጨልምም። ፀሐይ ስትጠልቅ፣ ጨረቃና ከዋክብት ይወጣሉ። ዘጠኝ በሮች ሲዘጉ አንዱ ይከፈታል። ዘጠኝ ወዳጆች ሲሄዱ አንዱ ይተርፋል። ፀሐይ ባትጠልቅ ጨረቃ አትታይም። ፈተና ካልመጣም የማናውቃቸው ሰዎች አሉ። ፈተናው የሚሰጠን የመጨረሻ ውጤት የቅርብ ያልነው ሩቅ፣ የሩቅ ያልነው የቅርብ መሆኑን ነው።

ሁሌም ቢሆን ጥቁር ብቻ መስሎ ከሚታይህ ቀን ጀርባ የታዘለ ደማቅ ብርሃን አለ ሊገፈትሩህ ከበረቱ እልፍ ክንዶች ኋላ ሊያቀኑህ የቆሙ ልስልስ መዳፎች አሉ አንሸራትተው ከሚደፉህ ሃሳቦች ባሻገር በተስፋ ሞልተው የሚያቆሙህ ቅን ሀሳቦች ተሰልፈዋል ያላየኸው ነገ ብዙ አዲስ የህይወት ገፆችን ይዞ ይጠብቅሃል ካጎነበስክበት ቀና ትላለህ ሀዘንህ በሳቅ ይተካል ጉስቁልናህን ወዝ ይሽረዋል ይህ እንዲሆን ግን ነገን ጠብቀው ፣ ተስፋ አትቁረጥ ነገ ያንተ ሲሆን ብቻ አሸናፊ ነህ::

ፀሐይ ስትጠልቅ ያልጠበቅናቸው ጨረቃና ከዋክብት ይወጣሉ። የማታ ብርሃኖች ዙሪያውን በደንብ ባያሳዩንም ለእግራችን መርገጫ ያሳዩናል። ሰማዩን በውበት ይገልጡልናል። የብርሃንን ዋጋ እንድናስብና እንድንሰስት ያደርጉናል። እንደ ፀሐይ እርግጠኛ የሆንባቸው ወዳጆች ድንገት ሊጠልቁ ይችላሉ። ያልጠበቅናቸው ደግሞ ብቅ ይላሉ። ጨርሶ አይጨልምምና።

“ፀሐይ ስለ መጥለቋ ከተማረርክ ፣ ከዋክብትም ይሰወሩብሃል” ይባላል። ቢወጡም አታያቸውም ማለት ነው። ምሬት ዓይንን ያጨልማልና። "ከምንማረርባቸው ነገሮች ይልቅ..ልናመሰግንባቸው የሚገባን ብዙ ነገሮች አሉ።ሁሉም በግዜው ውብ ሆኖ መደረጉ አይቀርምና ፣ ለሆነልህ፣ ላለሆነልህ፣ ላለህ፣ ለሌለህ ዘወትር አመስግን ሁሌም ቢሆን ፈጣሪ ሁሉን በግዜው ውብ አድርጎ መስራት፣ ማከናወን ያውቅበታልና።

ውብ አሁን

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot