Get Mystery Box with random crypto!

ስብዕናችን #Humanity

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiohumanity — ስብዕናችን #Humanity
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiohumanity — ስብዕናችን #Humanity
የሰርጥ አድራሻ: @ethiohumanity
ምድቦች: ሳይኮሎጂ
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 30.71K
የሰርጥ መግለጫ

🔆እየጠየቁ መኖር መልስን፣
መልስን ፈልጎ ማግኘት ዕውቀትን፣
እውቀት ነፃነትን፣ ነፃነት ሙሉ ስብዕናን፣
ሙሉ ስብዕና ሠላምና እርካታን፣
እርካታ ደግሞ ደስተኛ ሆኖ መኖርን ያስገኛል፡፡
አብረን እንደግ !!
@EthioHumanity @Ethiohumanity
✍የተሰማቹን አጋሩን! ቤቱ ሁሌም ክፍት ነው፣ሃሳባቹን ፃፍፍ አርጉልን @EthioHumanitybot

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2023-01-17 22:08:47 ምክር ለወዳጅ

ምክር ብትሰማ በነፃ ትማራለህ።ምክርን አልሰማ ብትል ግን በዋጋ እንደምትማር እወቀው።በዋጋ መማር ግን አድካሚ ደግሞም የሚያስመርር ነው።ብልህ ከሆንህ በሰው ከደረሰው ትማራለህ ሞኝ ከሆንህ ግን በራስህ ሲደርስ ትማራለህ።

በአመት የካብከውን በዕለት የምትንደው በቁጣህ ነውና አትቆጣ።ቁጣ አውቀህ እንዳላወቀ ለፍተህ እንዳለፋ የሚያደርግ በመልካም መሰረት ላይ የአገዳ ቤት የሚሰራ ነው።በገዛ እጅህ ዋጋህን እንዳታሳንሰው ቁጣህን ያዘው።

በወጣትነት ሁሉም ነገር ትክክል ነው ከሚል መመሪያ ውጣ።ሁሉንም ካላየሁ አላምንም አትበል።ሰምቶ ማመን ከተጎዱት መማር አስተዋይነት መሆኑን አትርሳ።የሰማንያ አመት እውቀትን ለመገብየት ግድ ሰማንያ አመት መኖር የለብህም።ሰማንያ አመት ከኖሩት በትህትና መጠየቅ ይገባሀል።

አይንህ የፊቱን ቢያይ ልብህ የኋላውን ያስብ።ነገ እንድትደርስ የትላንቱን አትርሳ።የምትሔድበት እንዳይጠፋህ የመጣህበትን አትዘንጋ።

ክፍት አይሙቅህ መልካም ነገርም ብርድ ብርድ አይበልህ።ለክፋት አቅም ካለህ ለበጎ ነገርም አቅም አለህና።ተግባርህ የምርጫህ ውጤት ነውና አስብበት።ክፋ ሰርተህ እንቅልፍ ሲወስድህ ሰይፍ ላይ መተኛትህን እወቅ።

ማግኘት ማጣት የኑሮ ተራ እንጂ አደጋ አይደለም።የተቀበልከው ያንተ ያልነበረውን ነው የተወሰደብህም ያንተ ያልሆነውን ነውና አታንጎራጉር።

ስትጠግብ የምትራብ ስትራብ የምትጠግብ አይመስልህም።ነገር ግን ሁሉም ይለወጣል።ዛሬ ያለኸው በጨለማው ከሆነ ቀጥሎ ብርሃን ነውና ደስ ይበልህ።ዛሬ ያለኸው በብርሃን ከሆነ ቀጥሎ እንዳይጨልምብህ ተጠንቅቀህ ያዘው።በመከራ ውስጥ ካለው ሰው በድሎት ውስጥ ላለው ቀጥሎ አስፈሪ መሆኑን አስብ።በእውነት ጥጋብህ እንዳለፈ ረሀብህም እንደሚያልፍ እመን።

የትላንትናውን ምሽት ስትይዝ አይነጋም ብለህ ሳይሆን ብርሃንን ተስፋ አድርገህ ነው።ከሌሊት ቀጥሎ ሌሊት አይመጣም።ከሌሊት ቀጥሎ ቀን ይሆናል።እንዲሁም ከዛሬ መከፍትህና ሀዘንህ በሀላ ታላቅ መፀጰናናት ይሆናል።

ሁሉም የራሱ ትግል አለውና እንደ እገሌ ምነው ባደረገኝ አትበል።ትዕግስት ስጠኝ ብለህ ለምን እንጂ።በዚህ አለም ላይ የሚታዘንለት እንጂ የሚቀናበት ሰው የለምና።

እገሌ ይናገርልኝ እገሌ መልስ ይስጥልኝ ከሚል ጥገኝነት ተላቀቅ።ጥቂትም ቢሆን በማታውቀው ሙያ ሰራተኞችን ተማምነህ ስራ አትጀምር።ስልጣን ሲሰጡህ መሪ እንጂ አለቃ አትሁን።ከፊት እየቀደምህ አስከትል እንጂ ከሀላ ሆነህ አትቅደም።

የመከራ ቀን ወዳጆችህን አትርሳ።የዛሬ ሰው ብቻ አትሁን።የትላንቱንም አስብ።አንገት የተፈጠረው ዞሮ ለማየት ነውና።

ታሪክን በጣም ወቃሽ አትሁን።አንተም በታሪክ ፊት ነህና ተጠንቀቅ።ያለፋት ተመልሰው መጥተው ያበላሹትን ማበጀት አይችሉም።አንተ ግን እድል አለህና እወቅበት።ታሪኬ እንዲያምር ብለህ አስመሳይ ፃድቅ አትሁን።ዛሬ በቅንነት የምትሰራው ግን ለታሪክህ ይተርፋል።ስራህን ስራ እንጂ ለስምህ አትኑር።አለም እንደ እቅድህ አይደለምና።

ሰዎች ሁሉ እንደ እኔ ካላሰቡ ብለህ አትጥላቸው።ሰው ላንተ ፈቃድ የተፈጠረ አይደለም።ደግሞም ነፃ ፈቃድ ያለው ፍጡር ነው።ነፃ ፈቃዱን እያከበርክለት ወደ እውነት ምራው።ከጠባብ ድንኳንህ ውጣ።

ዛሬ ዋሽተህ ማምለጡ ድል ይመስልሀል።የታወቀብህ ቀን ግን በውሸትህ ያመነህ ሰው በእውነትህ ግን አያምንህምና አትዋሽ።ውሸታምና አመንዝራ ተለውጠው እንኳ ቶሎ የሚያምናቸው አያገኙምና ከውሸት እራቅ።

እጅግ ግልፅነት እብድ ያደርጋል።እጅግ ዝምታም ወዳጅ ያሳጣልና ንግግርህና ዝምታህ በቦታው ሲሆን ውበት ይሆናል።

የእኔ መናገር ምን ይለውጣል?ብለህም ስህተትን አትለፍ።የእኔ አስተዋጵኦ ምን ይጠቅማል?ብለህም ስጦታህን አትጠፍ።

አሸናፊ መኮንን

ውብ አዳር

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot
999 views19:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-17 22:08:24
997 views19:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-17 11:38:03 https://t.me/UltraBonda
1.0K views08:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-15 08:59:54 https://t.me/UltraBonda
972 views05:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-14 20:57:05 ሕይወት ከሁሉም ነገር በፊት የነበረች ናት ። ቆነጃጅት ምድር ላይ ከመወለዳቸው በፊት ቁንጅና ነበረች። ስለ እውነት ከመነገሩ ቀድማ እውነት ነበረች።

ሕይዎት በዝምታችን ውስጥ ታዜማለች ፣ በእንቅልፋችን ውስጥ ታልማለች። በዝቅታ በወደቅንበት ጊዜ እንኳን ቢሆን ሕይወት ከፍ ባለ ዙፋን ላይ ትቀመጣለች። እኛ ስናለቅስ እርሷ በቀኑ ላይ ፈገግ ትልበታለች። የእሥራት ሰንሰለታችንን በምንጎትትበት ወቅት እርሷ ነፃ ናት።

ብዙ ጊዜ ሕይወትን እንማራለን። ሆኖም ግን መራራና ጨለማ እኞው እንጂ እርሷ አይደለችም። ሕይዎትን ባዶ ናት እንላለን። ሆኖም ግን ነብሳችን በምድረበዳ የተቅበዘበዘችና ስለራሷ ብቻ እያሰበች መሆኗን ልብ አንልም

ሕይዎት ትልቅ ከፍ ያለችና ሩቅም ናት። ሰፊው የእይታ አድማሳችሁ እግሯ ስር አይደርስም ፣ ሆኖም ደግሞ ቅርብ ናት ፣ እስትንፋሳችሁ ከእርሱ ልብ ባይጠጋም የጥላችሁ ጥላ ግን ፊቷ ላይ ያርፋል። የጩኸታችሁ ማስተጋባት ለእርሷ እንደ መኸርና ፀደይ ንፋስ ነው።

እንደ ነብሳችሁ ሁሉ ሕይወት ሕይወት ደግሞ ድብቅና ስውር ናት። ሕይወት ስትናገር ሁሉም ነፍሶች ቃላት ይሆናሉ ፣ ሕይዎት ስትናገር የከናፍራችሁ ፈገግታና የአይኖቻችሁ እንባ ሳይቀር ድምፆች ይሆናሉ። ሕይወት ስታዜም መስማት የማይችል ሲቀር ጆሮ ይሰጣታል ፣ ሕይወት ስትራመድ አይነስውራን እጆቿን ይዘው በአድናቆት ይከተሏታል።

( The Prophet )
ካህሊል ጂብራን

ውብ ምሽት

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot
2.2K views17:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-14 20:56:46
2.1K views17:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-09 21:22:49 የሚዋኝ ይኖራል !!

መዋኘት የሚችል ሰው በውሃ ላይ የመንሳፈፍ ጥበቡን በደንብ ያውቀዋል። ውሃ ላይ ለመንሳፈፍ ጠንካራ መሆንን አይጠይቅም። ይልቅ ውሃ ደግ ሆኖ ከመስመጥ የሚታደገን ፈታ ብለን ስንጫወትለት ብቻ ነው። ውሃ ግትር ሰው አይወድም፤ እጅ እና እግሩን ከማያፍታታ ግትር ጋር ውሃ ልጫወት አይልም። በጉልበት እንሳፈፋለው ለሚል ሰውም ውሃ እርህራሄ የለውም

አለን ዋትስ የተባለ አንድ ምሁር በአንድ ወቅት እንዲህ ሲል ሰምቸው ነበር " እምነት ልክ እንደዋና ነው። ዋናተኛ ከውሃው ላይ ለመንሳፈፍ ከፈለገ፤ እጁን ዘርጋ አድርጎ በነጻነት በውሃው ላይ ይወራጫል እንጂ፤ ላለመስመጥ ሲል ዉሃውን ልጨብጥ አይልም። ውሃውን ልጨብጥ ብሎ ግትር የሚል ሰው እጣ ፋንታው መስመጥ ብቻ ነው፤ በውሃ ላይ ለመንሳፈፍ ምንም ነገር መጨበጥ የለብንም ፤ ዋና መዋኘት እና ህይወትን መኖር በጣም ተመሳሳይነት አላቸው"

ብዙዏቻችን በህይወት ባህር ውስጥ የምንሰምጠው፤ ከኑሮ ጋር በቀላሉ መንሳፈፍን ስላለመድን ነው። እርግጥም ኑሮ እንደዋና ፈታ ብለው የሚኖሩት ባህር ነው። ግትር መሆን ውሃውን ለመጨበጥ እንደመሞከር ይሆናል። በህይወታችን ወስጥ በእኛ ቁጥጥር ስር የሆኑ ነገሮች አሉ፤ ሌሎች ከእኛ ቁጥጥር ውጪ የሆኑ ደግሞ እጅግ ብዙ ነገሮች ይኖራሉ። በኑሮ ውስጥ መስመጥ የሚከሰተው ታዲያ፤ ከእኛ ቁጥጥር ወጪ የሆኑ ነገሮች ላይ ግትርነታችንን ለማሳየት ስንሞክር ነው። መለወጥ የማንችለውን ነገር በጉልበት ለመለወጥ ስንሞክር፤ የመዋኘት ጥበቡ ጠፍቶናል ማለት ነው።

አንድ ዋናተኛ ከሆዱ እየተሳበ እጅ እና እግሩን እያወራጨ ወደፊት ካልሄደም የመስመጥ እድሉ ሰፊ ነው። ኑሮም ላይ እንደዛው ትላንት ከቆምንበት ቦታ ካልተንቀሳቀስን፤ ውሃ ላይ እንደመቆም ይከብደናል። የሚገርመው የህይወት ሚስጢር በየተፈጥሮ ገንባር ላይ ተጽፎ መገኘቱ ነው፤ እርግጥ ነው ሶስተኛ አይን ኖሮት ላስተዋለው ሰው ብቻ የሚገለጥ ሚስጢር ነው።

ሌላው ብዙዏቻችን የሚያሰምጠን ዋነኛው ምክንያት ለለውጥ ያለን አመለካከት ነው። አሁንም ከግትረነት ጋር የተያያዘ ነው። ህይወት ወደድንም ጠላንም ባልታሰቡ ስጦታዎች የተሞላች ነች። እንደ ዋናተኛው በእምነት ፈታ ብለን ካልተንሳፈፍን በፍጹም ከለውጥ ጋር ተግባብተን ለመኖር አይቻለንም።

አቤል ብርሀኑ

ውብ ምሽት

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot
1.3K views18:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-09 21:22:40
ALAN WATTS
1.3K views18:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-07 12:06:54
በመላው ዓለም ለምትኖሩ የክርስትና እመነት ተከታይ እህት ወንድሞቻችን እንኳን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን።

በአሉ የሰላም የፍቅርና የደስታ ይሁንልን

መልካም የገና  በአል


@ETHIOHUMANITY
@ETHIOHUMANITY
617 views09:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-05 21:17:19
ጨርሶ አይጨልምም። ፀሐይ ስትጠልቅ፣ ጨረቃና ከዋክብት ይወጣሉ። ዘጠኝ በሮች ሲዘጉ አንዱ ይከፈታል። ዘጠኝ ወዳጆች ሲሄዱ አንዱ ይተርፋል። ፀሐይ ባትጠልቅ ጨረቃ አትታይም። ፈተና ካልመጣም የማናውቃቸው ሰዎች አሉ። ፈተናው የሚሰጠን የመጨረሻ ውጤት የቅርብ ያልነው ሩቅ፣ የሩቅ ያልነው የቅርብ መሆኑን ነው።

ሁሌም ቢሆን ጥቁር ብቻ መስሎ ከሚታይህ ቀን ጀርባ የታዘለ ደማቅ ብርሃን አለ ሊገፈትሩህ ከበረቱ እልፍ ክንዶች ኋላ ሊያቀኑህ የቆሙ ልስልስ መዳፎች አሉ አንሸራትተው ከሚደፉህ ሃሳቦች ባሻገር በተስፋ ሞልተው የሚያቆሙህ ቅን ሀሳቦች ተሰልፈዋል ያላየኸው ነገ ብዙ አዲስ የህይወት ገፆችን ይዞ ይጠብቅሃል ካጎነበስክበት ቀና ትላለህ ሀዘንህ በሳቅ ይተካል ጉስቁልናህን ወዝ ይሽረዋል ይህ እንዲሆን ግን ነገን ጠብቀው ፣ ተስፋ አትቁረጥ ነገ ያንተ ሲሆን ብቻ አሸናፊ ነህ::

ፀሐይ ስትጠልቅ ያልጠበቅናቸው ጨረቃና ከዋክብት ይወጣሉ። የማታ ብርሃኖች ዙሪያውን በደንብ ባያሳዩንም ለእግራችን መርገጫ ያሳዩናል። ሰማዩን በውበት ይገልጡልናል። የብርሃንን ዋጋ እንድናስብና እንድንሰስት ያደርጉናል። እንደ ፀሐይ እርግጠኛ የሆንባቸው ወዳጆች ድንገት ሊጠልቁ ይችላሉ። ያልጠበቅናቸው ደግሞ ብቅ ይላሉ። ጨርሶ አይጨልምምና።

“ፀሐይ ስለ መጥለቋ ከተማረርክ ፣ ከዋክብትም ይሰወሩብሃል” ይባላል። ቢወጡም አታያቸውም ማለት ነው። ምሬት ዓይንን ያጨልማልና። "ከምንማረርባቸው ነገሮች ይልቅ..ልናመሰግንባቸው የሚገባን ብዙ ነገሮች አሉ።ሁሉም በግዜው ውብ ሆኖ መደረጉ አይቀርምና ፣ ለሆነልህ፣ ላለሆነልህ፣ ላለህ፣ ለሌለህ ዘወትር አመስግን ሁሌም ቢሆን ፈጣሪ ሁሉን በግዜው ውብ አድርጎ መስራት፣ ማከናወን ያውቅበታልና።

ውብ አሁን

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot
1.2K viewsedited  18:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ