Get Mystery Box with random crypto!

ሕይወት ከሁሉም ነገር በፊት የነበረች ናት ። ቆነጃጅት ምድር ላይ ከመወለዳቸው በፊት ቁንጅና ነበረ | ስብዕናችን #Humanity

ሕይወት ከሁሉም ነገር በፊት የነበረች ናት ። ቆነጃጅት ምድር ላይ ከመወለዳቸው በፊት ቁንጅና ነበረች። ስለ እውነት ከመነገሩ ቀድማ እውነት ነበረች።

ሕይዎት በዝምታችን ውስጥ ታዜማለች ፣ በእንቅልፋችን ውስጥ ታልማለች። በዝቅታ በወደቅንበት ጊዜ እንኳን ቢሆን ሕይወት ከፍ ባለ ዙፋን ላይ ትቀመጣለች። እኛ ስናለቅስ እርሷ በቀኑ ላይ ፈገግ ትልበታለች። የእሥራት ሰንሰለታችንን በምንጎትትበት ወቅት እርሷ ነፃ ናት።

ብዙ ጊዜ ሕይወትን እንማራለን። ሆኖም ግን መራራና ጨለማ እኞው እንጂ እርሷ አይደለችም። ሕይዎትን ባዶ ናት እንላለን። ሆኖም ግን ነብሳችን በምድረበዳ የተቅበዘበዘችና ስለራሷ ብቻ እያሰበች መሆኗን ልብ አንልም

ሕይዎት ትልቅ ከፍ ያለችና ሩቅም ናት። ሰፊው የእይታ አድማሳችሁ እግሯ ስር አይደርስም ፣ ሆኖም ደግሞ ቅርብ ናት ፣ እስትንፋሳችሁ ከእርሱ ልብ ባይጠጋም የጥላችሁ ጥላ ግን ፊቷ ላይ ያርፋል። የጩኸታችሁ ማስተጋባት ለእርሷ እንደ መኸርና ፀደይ ንፋስ ነው።

እንደ ነብሳችሁ ሁሉ ሕይወት ሕይወት ደግሞ ድብቅና ስውር ናት። ሕይወት ስትናገር ሁሉም ነፍሶች ቃላት ይሆናሉ ፣ ሕይዎት ስትናገር የከናፍራችሁ ፈገግታና የአይኖቻችሁ እንባ ሳይቀር ድምፆች ይሆናሉ። ሕይወት ስታዜም መስማት የማይችል ሲቀር ጆሮ ይሰጣታል ፣ ሕይወት ስትራመድ አይነስውራን እጆቿን ይዘው በአድናቆት ይከተሏታል።

( The Prophet )
ካህሊል ጂብራን

ውብ ምሽት

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot