Get Mystery Box with random crypto!

ስብዕናችን #Humanity

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiohumanity — ስብዕናችን #Humanity
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiohumanity — ስብዕናችን #Humanity
የሰርጥ አድራሻ: @ethiohumanity
ምድቦች: ሳይኮሎጂ
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 30.73K
የሰርጥ መግለጫ

🔆እየጠየቁ መኖር መልስን፣
መልስን ፈልጎ ማግኘት ዕውቀትን፣
እውቀት ነፃነትን፣ ነፃነት ሙሉ ስብዕናን፣
ሙሉ ስብዕና ሠላምና እርካታን፣
እርካታ ደግሞ ደስተኛ ሆኖ መኖርን ያስገኛል፡፡
አብረን እንደግ !!
@EthioHumanity @Ethiohumanity
✍የተሰማቹን አጋሩን! ቤቱ ሁሌም ክፍት ነው፣ሃሳባቹን ፃፍፍ አርጉልን @EthioHumanitybot

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2022-12-11 22:04:16 ምክር ለወዳጅ

በወጣትነት ሁሉም ነገር ትክክል ነው ከሚል መመሪያ ውጣ ፤ ሁሉንም ካላየሁ አላምንም አትበል ። ሰምቶ ማመን ፣ ከተጎዱት መማር አስተዋይነት መሆኑን አትርሳ ። የሰማንያ ዓመት ዕውቀትን ለመገብየት ግድ ሰማንያ ዓመት መኖር የለብህም ። ሰማንያ ዓመት ከኖሩት በትሕትና መጠየቅ ይገባሃል ።

ምክርን ብትሰማ በነጻ ትማራለህ ። ምክርን አልሰማ ብትል ግን በዋጋ እንደምትማር እወቀው ። በዋጋ መማር ግን አድካሚ ደግሞም የሚያስመርር ነው ። ብልህ ከሆንህ በሰው ከደረሰው ትማራለህ ፣ ሞኝ ከሆንህ ግን በራስህ ሲደርስ ትማራለህ ።

የታየህን አሳይ ፣ ያልታየህን አጥራው ። በደንብ ያልተረዳኸውን አታስተምረው። ያልቀመስከውን ለሰው አትጋብዝ ። የሰማኸውን ሁሉ አትመን ። ያየኸውን ሁሉ ስጡኝ ፣ የተናገርከውን ሁሉ ፈፅሙ አትበል ። የሰጠኽውን እርሳ እንጂ አታውራ። ፍፃሜውን ሳታይ ምስጋና አታብዛ ። ቀኑ ሳይመሽ ቀኑ ጥሩ ነው አትበል ።

ዓይንህ የፊቱን ቢያይ ልብህ የኋላውን ያስብ ። ነገ ላይ እንድትደርስ የትናንቱን አትርሳ ። የምትሄድበት እናዳይጠፋህ የመጣህበትን አትዘንጋ ።

የአባቶችህን መልካም ሥራ አብነት አድርግ ። ካሳለፉት ሕይወት ተማር እንጂ አወዳሽና ወቃሽ አትሁን ። ሌሎች መሆን ያለባቸውን ስታውቅ አንተ መሆን ያለብህ እንዳይጠፋህ ተጠንቀቅ ። ደግሞም አንተም በታሪክ ፊት መሆንህን እወቀው ።

ክፋት አይሙቅህ ፣ መልካም ነገርም ብርድ ብርድ አይበልህ ። ለክፋት አቅም ካለህ ለበጎ ነገርም አቅም አለህና ተግባርህ የምርጫ ውጤት ነውና አስብበት ።

ገንዘብ የሚመልሰው የገንዘብን ጥያቄ ብቻ ነውና ሁሉንም ነገር ገንዘብ ያስገኝልኛል ብለህ አታስብ ። ላለው አትሩጥ ፣ ምጽዋትህና ተግባርህ በአቅምህ መጠን ይሁን እንጂ ከአቅምህ አትነስ ። ድሃም ሆነህ ተበድረህ ስጦታ አትስጥ ። በጣም ካልቸገረህ ለቅንጦት አትበደር ። ያንተን ድርሻ ከጨረስህ ያልተጨረሰ የሌሎችን ድርሻ ፈፅምላቸው ።

ለሀብታም አትሳቅ ፣ የደሀ ጉልበት አይለፍብህ ፣ ያለ ሰው ሰው አልሆንክምና ሰው አትጥላ ፣ የወጣህበትን መሰላል አትገፍትር ፣ ለመውረድም ያስፈልግሃልና ፣ ያየኽውን ሴት ሁሉ የመውደድ ጠባይህ ካለቀቀህ ትዳር አትያዝ ፣ ካልጋበዙህ በቀር አማካሪ አትሁን ፣ ባልጠሩህ ሥፍራ አቤት አትበል ፣ ካልሾሙህ መሪ አትሁን ፣ ጉድለት በሌለበት ቦታ ጊዜህን አታባክን ፣ የሰው ፊት ጥገኛ ሁነህ ሲስቁልህ የምትስቅ ሲቆጡህ የምታለቅስ አትሁን ፣ ነገርህን በልክ ፣ ቃልህን በጣዕም ፣ ድምፅህን በዝግታ ፈፅመው ።

እውር እንዳይሉህ ያልታየኽን አያለሁ አትበል ። ጨካኝ እንዳይሉህ ያልተሰማህን ጩኸት እሰማለሁ አትበል ። ንፉግ እንዳይሉህ ያለ አቅምህ እረዳለሁ አትበል ። ነገር አይገባውም እንዳይሉህ ያልገባህን እንደገባህ አድርገህ አትለፍ ። አንድ በጎ ዕውቀት ሳትጨብጥ የዋልክበትን ቀን እንደ ኖርክበት አትቁጠረው ፣ ስለዚህ መፅሐፍትን አንብብ ፣ አዋቂዎችን ጠይቅ ፣ ሁሉን ሳትንቅ ስማ ።

ሥልጣን ሲሰጥህ መሪ እንጂ አለቃ አትሁን ፤ ከፊት እየቀደምህ አስከትል እንጂ ከኋላ ሆነህ አትቅደም ።

በዓላማ ኑር ፤ እንቅፋቶች የሚያጸኑህ እንጂ ተግባርህን የሚያስተውህ አይሁኑ ። ሕይወት ትምህርት ቤት መሆኑና ባለማወቅ ብዙ ትህምርቶች እንዳያመልጡህ ተጠንቀቅ ።
:
የመከራ ቀን ወዳጆችህን አትርሳ ፤ የዛሬ ሰው ብቻ አትሁን ፤ የትላንቱንም አስብ ፤ አንገት የተፈጠረው ዞሮ ለማየት ነውና ።

ዓለም ዋዣቂ ናት ። ከፍና ዝቅ ስትል አትደናገጥ ፤ ፀሐይ ዝናብን ተከትላ ትፈነጥቃለች ። ከመከፋትም በኋላ ትልቅ መፅናናት ይሆናል ። ከሌሊት በኋላም ሌሊት አይመጣም ። ከሀዘን በኋላ ደስታ ይሆናልና በርታ!

መነቀፍን አትፍራ ፤ ነቀፋህን ግን አጥራው ፤ ስለ ሀሰት ሳይሆን ስለ እውነት ተገፋ ፤ ሌሎችን ውደድ ፍቅር ስጦታ እንጂ ብድር አይደለምና አልወደዱኝም ብለህ በአበዳሪዎች አንቀጽ አትካሰስ ፤ የገባህን አድርግ የዚህ ዓለም ሰው ሲወድህም ሲጠላህም ባለማወቅ ነው ። ብዙዎች ስለወደዱህ ይወድሃል ፤ ብዙዎች ስለጠሉህ ይጠላሃል ።

ሁልጊዜ የበላዮችህን አትመልከት ፤ የበታቾችህንም ተመልከት ። ለድምፅ አልባዎች ጩህላቸው ፣ ለተጠቁት ተሟገትላቸው ። እውነት እውነት በማለትህ የምታጣው ሀሰተኛ ወዳጅህን ብቻ ነው ። እውነት እውነት በማለትህ የምታተርፈው ግን እውነተኛ ወዳጅን ነው ።

ደጋፊዎች ተከታዮች አይደሉም ። ሰዎች ስለደገፉህም የያዝኩት እውነት ነው ብለህ መንቻካ አትሁን ፤ ምናልባት ዛሬ የሚጮሁልህ ዛሬን ሊረሱብህ ሊሆን ይችላልና ። ሲያለቅሱልህም ቃልህ ማርኳቸው ሳይሆን የሞተ ዘመዳቸው ትዝ ብሏቸው ሊሆን ይችላልና አለቀሱ ብለህ ንግግርህን ድንበር አታሳጣው ። እውነትንም በደጋፊ ብዛት እንዳትመዝናት ተጠንቀቅ ።

ለእውነታ እንጂ ለይሉኝታ አትኑር ፤ ያን ስልህ የምትኖርበት ሕዝብና ባሕል ከእውነት ጋር እስካልተጋጨ መጋፋት የለብህም። ሠዎች የሚቀበሉህ ባሕላቸውን ስታውቅና ስታከብርላቸው ነው ።

ልጅነት የለሰለሰ መሬት ፣ ወጣትነት የአዝመራ ዘመን ፣ ሽምግልና ደግሞ የአጨዳ ዘመን መሆኑን አስተውል ። በሽምግልናህ የምታጭደው የወጣትነትህን አዝመራ ነውና ዛሬ ለምትዘራው ተጠንቀቅ ።

የሰዎችን ያለማወቅ አግዝ ፤ ዕውቀትህ ባላወቁት ላይ እንድትኮራና እንድትፈርድ አያድርግህ የአዋቂ ኩሩ ቁጥሩ ካላዋቂዎች ነውና ማወቅ ባለዕዳነት እንዳይሆን አላዋቂዎችን እርዳቸው ።

ዛሬ የመዝራት ዘመንህ ነገ መከርህ ነውና በእምነት እውነትን ዝራ ፤ በምታውቀው ቦታ ላይ አገልጋይ በማታውቀው መልካም ተግባር ላይ ደጀን ሁን ፤ በቦታህ መምህር ያለቦታህ ተማሪ ሁን ፤ ክብሩ እንዳይቀንስብህ ከዕቃ ትምክህት ፣ ከዕውቀት ሙግት ራቅ ።

ሁሉን ወሬ ላውራ አትበል ፣ የደበቁህን ምስጢር አታውጣጣ ፣ የሰማኽውን ወሬና የተገለጠልህን ምስጢር ምን መፍትሔ ሰጠኸውና ? ያየህውን ሥራ ሁሉ እሰራለሁ የሰማኸውን ትምህርት ሁሉ እማራለሁ አትበል ። ይህ የተሰወረው የቅንዓት ጠባይ ነውና ሁሉን ልያዝ ማለትም ዝንጉ አድረጎ እንዳያስቀርህ ሁሉም ውስጥ ልኑር አትበል ።

ቆንጆዎች ቁንጅናቸው ሁሉን የሚተካ እየመሰላቸው ከዕውቀትና ከትሕትና ይርቃሉ ። ሁሉንም ሰው በመልካቸው የሚማርኩት ስለሚመስላቸው ኩሩና ተንኮለኞች ይሆናሉ ። አንተ ግን ቆንጆ ወዳጅን እንጂ ቆንጆ ቁመናን አትሻ ፤ ቆንጆ ትዳርን እንጂ ቆንጆ ሴትን አትመኝ ፤ የላይ ነገር ከንቱና ኀላፊ ነውና በሚፈርስ አካል ፣ ኑሮ በሚለውጠው መልክ አትደለል ።

እወድሃለሁ ብለህ የምትናገረውን ቃል ውለታ አታድርገው ፣ መውደድህን የምትናገረው እንወድሃለን እንዲሉህ አይሁን ፣ ሠላም ያለው አፍቃሪ የራሱን ፍቅር ያለ ምክንያት መፈፀም የሚችል ብቻ እንደሆነ እወቅ ። መወደድህን ለመስማት አትጠብቅ ።

የሰዎችን ያለማወቅ አግዝ ፤ ዕውቀትህ ባላወቁት ላይ እንድትኮራና እንድትፈርድ አያድርግህ የአዋቂ ኩሩ ቁጥሩ ካላዋቂዎች ነውና ማወቅ ባለዕዳነት እንዳይሆን አላዋቂዎችን እርዳቸው ።

ዛሬ የመዝራት ዘመንህ ነገ መከርህ ነውና በእምነት እውነትን ዝራ ፤ በምታውቀው ቦታ ላይ አገልጋይ በማታውቀው መልካም ተግባር ላይ ደጀን ሁን ፤ በቦታህ መምህር ያለቦታህ ተማሪ ሁን።

        ውብ አዳር

@Ethiohumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot
1.3K views19:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-11 22:04:09
1.3K views19:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-04 19:08:05
ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ

@Ultrabonda ከዚህ በታች ያለውን መስፈርት የምታሟላ የሽያጭ ባለሙያ ይፈልጋል

የሽያጭ ባለሙያ ( Sales )

ከዚህ በፊት ልብስ ቤት ሰርታ የምታውቅ እና ስለ ልብሶች በቂ እውቀት ያላት

የስራ መደብ:- የልብስ ሽያጭ

ፆታ:- ሴት

የስራ ቦታ:- አዲስ አበባ (መገናኛ)


ደሞዝ በስምምነት

ፍላጎት ያላቹ @Nagayta በዚህ ሊንክ መምጣት ትችላላችሁ
1.7K views16:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-03 21:48:34
ሕይወት በ’የኔ’ እና ‘የኛ’ የምናሳንሰው ነገር የላትም… ከጽንፍ አልባው ምልዓት ላይ በተገለጸልን ልክ የገባንን ሁሉ የእኔ/ኛ አንልም… እኛ ራሳችንን ያንን ምልዓት አይደለን? “You are not a drop in the ocean; you are the entire ocean in a drop” ይላል Rumi

ይህን ሁለንተና በግላዊነት መያዝ አይቻልም… የኔ ብሎ ማሳነስ አይቻልም… እኛው ራሳችን ሁለንተናውን ነንና ፣ ብዙ የአለማችን እሳቤዎች ከሕይወት በተናጥሎ የመኖርን ቅዠት ይሰብካሉ… ውቅያኖሱን ሆነህ ሳለ የውቅያኖሱን ‘አንድ ጠብታ ወስደህ’ የኔ ማለት ከራስም ያሳንሳል…ከራስህ ተነጥለህ ‘የራስህ’ ሊኖርህ አይችልም።

የግዙፍ ውቅያኖስ አካል ነን ፣ከኔ ቤት ላይ የረጨኸው እሳት ከሆነ ነበልባሉ ያንተን ቤት ይነካል ሽቶ ስትረጨኝ የመዓዛው ቅንጣቶች ለአፍንጫህ ውብ ጠረን ይለግሳል ሰው የዘራውን ያንኑ ደግሞ ያጭዳል ይህን ምስራቃውያኑ Karma ሲሉት ሌሎች ደግሞ Boomerang ይሉታል Boomerang አውስትራሊያኖቹ አቦርጂኒስቶች ከእንጨት የሚሰሩት ደጋን ቅርጽ ያለው የአደን መሳሪያ ሲሆን ወርዋሪው ዘንድ ተመልሶ እንዲመጣ ተደርጎ የሚነደፍ ነው… ለሃሳብ፣ ለስሜትና ድርጊትህ መጠንቀቅ የሚኖርብህ ወላፈኑ ‘ለእኔም’፣ ‘ለእርሷም’፣ ‘ለእነርሱም’ እንደሚተርፍ በማሰብ ነው ምክንያቱም We are all One!

በረከት በላይነህ "የመንፈስ ከፍታ" ላይ እንዲህ ይለናል
“የግልህ ወንዝ ስለሌለህ ብቻህን የምትሰራው ድልድይ የለም! የሰማዩ ርቀት፣ የምድሪቱ ስፋት በ’እኛ’ እንጂ በ’እኔ’ አይለካም፡፡ ውዱ ‘እኔ’ ከ’እኛ’ የተሰራው ነውና!”

ደምስ ሰይፉ

           ውብ አሁን!!

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
938 viewsedited  18:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-01 21:39:19
ለባለ ሱቆች በብዛት መረከብ የምትፈልጉ

0991208847 ወይም @Nagayta
2.0K views18:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-26 16:52:51
ሁሉም ሰው ዋጋ አለው!

ሰው የሚሰጥህ ክብር አንተ ለራስህ በምትሰጠው ሚዛንና መጠን ነውና ለራስህ ትልቅ ዋጋና ብዙ ክብር ይኑርህ፣ ማንኛውም ሰው በማንኛውም አይነት ስራ ዘርፍ ቢሰማራ የተወሰነ ቀናት እስኪለምደው ይቸገራል እንጂ ስራውን የማይወጣበት ምንም አይነት ምክንያት የለም !

ዕድሉን ስላላገኘ እንጂ ሰው ሁሉ ወሳኝ ጠቃሚ ነው ነገር ግን በሌሎች ዘንድ ቦታውን ባለመግኘቱ እና ተቀባይ ባለመኖሩ ሊወድቅ ይችላል !ሰው ቦታን ይለምዳል እንጅ ቦታ ሰውን አይለምድም !ከደካማ ስር ብትሆን ማንነትህ አይወርድም እንዲውም ምርኩዝ ትሆነዋለህ !ከጠንካራ ጎን ብትቆም በሱ ወንበር አትመራም በራስህ ህሊና እንጅ !

ሰውን በአስተሳሰቡ እንጅ በፍፁም በአለባበሱ አትመዝነው፡፡ ምክንያቱም ሰው ቦታን ይቀይራል እንጅ ቦታ ሰውን አይቀይርም! ጠንካራ ሰዎች ሌሎችን ከፍ እንጅ ዝቅ አያደርጉም እና  ጠንካራ ከሆንክ ለሰው ትልቅ ቦታ ስጥ ብዙ ዋጋም ይኑርህ።

Bee A Good Human

Our life can be translated into love,We can color our whole life with kindness, transforming our everyday activities and ejoying our everyday ways of being with human warmth. Our Life Can Be Translated into Love.

እራስህን በሰላም ፣ በብርሃን ፣ በጥበብ ፣በንቃተ-ህሊና ሸፍነው፡፡የአንተ ሃላፊነት ይህ ነው ፡፡ደስታ እና ርህራሄ በህይወት መንገድህ አይለዩህ፣ ከተፈጥሮ ጋር እጅ ለእጅ ተያይዘህ ኑር  ፡፡ይህን ለማድረግ ሁሌም ከልብህ ጀምር።ሁሌም ይህን አድርግ፣ሁሌም ይህንን ሁን ፡፡

  ፏፏቴ የሆነች ቅዳሜን ተመኘን

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot
834 viewsedited  13:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-25 09:23:08 ለጁምኣችን!


" መወደድም ሲሳይ ነው" አሉ ። ምነው ቢሉ ነብዩ ዩሱፍን ዓ.ሰ (ዮሴፍን) አርቀው የጣሉት የገዛ ወንድሞቹ ፥ አንስተው ያከበሩት መኳንንት ባዶቹ ።

መውደቅ መጨረሻ አይሆንም ፥ ምነው ቢሉ ዮሴፍ ዓ.ሰ ለንግስና የታጨው እስር ቤት እያለ ነውና ፥ መነሳትም ተክትሎታልና ።

ሰው ኹሉን አወቅ ነኝ ይላል እንጂ ስለ ህልውናው በመተርጎም ፥ ውስጥ ውስጡን ትርጉምን ሁላ የምታስከነዳ ገራም የመለኮት ሥርዓት አለች ።መታገስ ነጃ ያወጣል ምነው ቢሉ የመለኮት ሥርዓት ኹሉን በገራምነት እንደምታስከነዳ ማመን ነውና ።

ሰለዲን አሊ

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity
1.1K views06:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-23 21:58:58
የማንፈልገው ነገር ባይኖር የምንፈልገውም አይኖርም !

ልዩነት የምንወደው ሳይሆን የምንቀበለው ነው ። ማንም ለራሱ ሀሳብ ቅድሚያ ቢሰጥ ፣ ተቃራኒውን ለመቀበል ደስታ ባይታይበት አይገርምም ። " የእኔ ሀሳብ ወይም ሞት ! " ማለት ግን ራስን ማስቀደም ሳይሆን ልዩነትን ማጥፋት ነው ። ይህ እውነትን ለመስቀል ገመድ ማዘጋጀት ይሆናል   የወደድነውን ያገኘነው ካልወደድነው መሀል መርጠን መሆኑን ልብ ማለት ያሻል ።

እኛ የወደድነው ብቻ ቢኖር ፣ የምንጠላው ወይም የማንወደው ባይኖር የምንወደውን መውደዳችንን በምን እናውቀው ነበር  ? የምንጠላውን የሚወዱት እንዳሉ መረዳት ብቻ ሳይሆን ለምንወደው ነገር ማነፃፀሪያ እንዲሆነንም ያስፈልገናል ። የማንወደውን ነገር ከማጥፋት ለሚወዱት መተው ያስፈልገናል ።  የምንፈልገው ነገር መኖሩን ያወቅነው የማንፈልገው በመኖሩም ጭምር ነው ።

                ቴዎድሮስ ተ/አረጋይ

           ውብ አዳር

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot
823 views18:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-16 20:33:20
መስጠት ካልቻልኩ መቀበል አይሆንልኝም "

ደግነት ልቤ ውስጥ በተዘራ ጊዜ ፍሬውን አጭጄ እሰበስብና ለተራቡት እሰጣቸዋለሁ . . .ነፍሴ የወይን ፍሬ ባበቀለች ጊዜ ፍሬዎቹን ጨምቄ የተጠሙትን አጠጣቸዋለሁ ::

ውስጤ በብርሃን በተሞላች ጊዜ የውስጤን ፋኖስ የመስኮቴ ጫፍ ላይ አስቀምጣትና በጨለማ ለሚጉዋዙት ብርሃን እሆናቸዋለሁ :: ጥላቻን ከልቤ ያጠፋልኝ ዘንድ ሁልጊዜም የፍቅርን ችቦ መጨበጥ እሻለሁ ::

ሰዎች በዘርና በቀለም ተለያይተው በተለያዩ አህጉራትና ሀገራት ይኖራሉ ,,,,, እኔ ግን ለሁሉም ማህበረሰቦች እንግዳ ነኝ ከየትኛውም ሀገር አልወግንም። መላው ዓለም ሀገሬ ነው፣
የሰው ልጅ ሁሉ ወገኔ ነው ።

የአዳም/አደም ልጆች ደካማ ሆነው በተለያዩ ጉዳዮች መከፋፈላቸው የሚያሳዝን ነው , ዓለም ሳትከፋፈልም ጥብብ ያለች ናት ይህችን ጠባብ ዓለም በግዛት ፣ በሰፈር፣በአውራጃ መከፋፈሉ በአላዋቂነት የታጀበ ሞኝነት ይመስለኛል . . . . !

"ካህሊል ጂብራን"

ውብ ምሽት

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
2.9K views17:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-15 21:56:34
'እኔ ማን እንደሆንኩኝ አታውቅም, ግን እኔ ማን እንደሆነች አውቃለሁ'

'She doesn't know who I am, but I know who she is

የ85 አመት አዛውንት ናቸው ከ 60 ዓመት በላይ ከባለቤታቸው ጋር በትዳር ኖረዋል, ባለቤታቸውን በሄዱበት ሁሉ እጃቸውን አጥብቃ እንድትይዛቸው ባለመሰልቸት ይጠይቋታል, ስትቆም ቆመው ስትቀመጥ ተቀምጠው ስታስቸግር አብረው ተቸግረው . . . ሳይሰለቹ የድሮ ፍቅራቸውን ሳይቀንሱ በ 85 ዓመት የአዛውንት ጉልበታቸው አሁንም በትዕግስት አብረዋት አሉ :: ሰዎች ሚስታቸው ምን ሆና እንዲህ እንደሆነች ይጠይቃሉ “አልዛይመርስ' የመርሳት በሽታ አለባት” ሲሉ ይመልሱላቸዋል

እና ምንም አታስታውስም ? ምንም !ያን ሁሉ ዓመት የሕይወት ውጣውረዳችንን,ደስታችንን ሀዘናችንን ወልደን ኩለን መዳራችንን ዘመድ አዝማድን ኧረ እኔንም ዘንግታኛለች
እናም "ሚስትህ እጅህን ብትለቅህ ትጨነቃለህ ማለት ነው ?" ለምን አልጨነቅም ምንም ነገር ማንንም አታስታውስም እኮ በዚህ ዓለም ያላትን ነገሮች ሁሉ ረስታለች እኔንም ጭምር , ለብዙ አመታት አላወቀችኝም እና ያለኔ ማን አላትና ነው የማልጨነቀው ?!

"እናም አንተን ባታውቅህም በየቀኑ መንገድ ላይ እየመራሃት ትቀጥላለህ" ማለት ነው ,
ፈገግ አሉና አይኖቼን እምባ ባቀረሩ አይናቸው እየተመለከቱ . "እኔ ማን እንደ ሆንኩኝ አታውቅም ግን እኔ ማን እንደሆነች አውቃለሁ " ውዷ ከ 60 ዓመት በላይ ብዙ ነገር የሰጠችኝ ሕይወቴ ናት " እናም ሕይወቴን ሙሉ በሄደችበት ሁሉ አብሪያት አለሁ , ሰው ካለ ህይወቱ ምን ሕይወት አለው ... እከተላታለሁ።

መልካሞችን ሁሌም ያብዛልን።

ውብ አዳር

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot
3.6K views18:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ