Get Mystery Box with random crypto!

መስጠት ካልቻልኩ መቀበል አይሆንልኝም ' ደግነት ልቤ ውስጥ በተዘራ ጊዜ ፍሬውን አጭጄ እሰበስ | ስብዕናችን #Humanity

መስጠት ካልቻልኩ መቀበል አይሆንልኝም "

ደግነት ልቤ ውስጥ በተዘራ ጊዜ ፍሬውን አጭጄ እሰበስብና ለተራቡት እሰጣቸዋለሁ . . .ነፍሴ የወይን ፍሬ ባበቀለች ጊዜ ፍሬዎቹን ጨምቄ የተጠሙትን አጠጣቸዋለሁ ::

ውስጤ በብርሃን በተሞላች ጊዜ የውስጤን ፋኖስ የመስኮቴ ጫፍ ላይ አስቀምጣትና በጨለማ ለሚጉዋዙት ብርሃን እሆናቸዋለሁ :: ጥላቻን ከልቤ ያጠፋልኝ ዘንድ ሁልጊዜም የፍቅርን ችቦ መጨበጥ እሻለሁ ::

ሰዎች በዘርና በቀለም ተለያይተው በተለያዩ አህጉራትና ሀገራት ይኖራሉ ,,,,, እኔ ግን ለሁሉም ማህበረሰቦች እንግዳ ነኝ ከየትኛውም ሀገር አልወግንም። መላው ዓለም ሀገሬ ነው፣
የሰው ልጅ ሁሉ ወገኔ ነው ።

የአዳም/አደም ልጆች ደካማ ሆነው በተለያዩ ጉዳዮች መከፋፈላቸው የሚያሳዝን ነው , ዓለም ሳትከፋፈልም ጥብብ ያለች ናት ይህችን ጠባብ ዓለም በግዛት ፣ በሰፈር፣በአውራጃ መከፋፈሉ በአላዋቂነት የታጀበ ሞኝነት ይመስለኛል . . . . !

"ካህሊል ጂብራን"

ውብ ምሽት

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot