የማንፈልገው ነገር ባይኖር የምንፈልገውም አይኖርም ! ልዩነት የምንወደው ሳይሆን የምንቀበለው ነው ። ማንም ለራሱ ሀሳብ ቅድሚያ ቢሰጥ ፣ ተቃራኒውን ለመቀበል ደስታ ባይታይበት አይገርምም ። " የእኔ ሀሳብ ወይም ሞት ! " ማለት ግን ራስን ማስቀደም ሳይሆን ልዩነትን ማጥፋት ነው ። ይህ እውነትን ለመስቀል ገመድ ማዘጋጀት ይሆናል የወደድነውን ያገኘነው ካልወደድነው መሀል መርጠን መሆኑን ልብ ማለት ያሻል ። እኛ የወደድነው ብቻ ቢኖር ፣ የምንጠላው ወይም የማንወደው ባይኖር የምንወደውን መውደዳችንን በምን እናውቀው ነበር ? የምንጠላውን የሚወዱት እንዳሉ መረዳት ብቻ ሳይሆን ለምንወደው ነገር ማነፃፀሪያ እንዲሆነንም ያስፈልገናል ። የማንወደውን ነገር ከማጥፋት ለሚወዱት መተው ያስፈልገናል ። የምንፈልገው ነገር መኖሩን ያወቅነው የማንፈልገው በመኖሩም ጭምር ነው ። ቴዎድሮስ ተ/አረጋይ ውብ አዳር @EthioHumanity @EthioHumanity @EthioHumanitybot 823 views18:58