Get Mystery Box with random crypto!

ለጁምኣችን! ' መወደድም ሲሳይ ነው' አሉ ። ምነው ቢሉ ነብዩ ዩሱፍን ዓ.ሰ (ዮሴፍ | ስብዕናችን #Humanity

ለጁምኣችን!


" መወደድም ሲሳይ ነው" አሉ ። ምነው ቢሉ ነብዩ ዩሱፍን ዓ.ሰ (ዮሴፍን) አርቀው የጣሉት የገዛ ወንድሞቹ ፥ አንስተው ያከበሩት መኳንንት ባዶቹ ።

መውደቅ መጨረሻ አይሆንም ፥ ምነው ቢሉ ዮሴፍ ዓ.ሰ ለንግስና የታጨው እስር ቤት እያለ ነውና ፥ መነሳትም ተክትሎታልና ።

ሰው ኹሉን አወቅ ነኝ ይላል እንጂ ስለ ህልውናው በመተርጎም ፥ ውስጥ ውስጡን ትርጉምን ሁላ የምታስከነዳ ገራም የመለኮት ሥርዓት አለች ።መታገስ ነጃ ያወጣል ምነው ቢሉ የመለኮት ሥርዓት ኹሉን በገራምነት እንደምታስከነዳ ማመን ነውና ።

ሰለዲን አሊ

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity