Get Mystery Box with random crypto!

ስብዕናችን #Humanity

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiohumanity — ስብዕናችን #Humanity
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiohumanity — ስብዕናችን #Humanity
የሰርጥ አድራሻ: @ethiohumanity
ምድቦች: ሳይኮሎጂ
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 30.61K
የሰርጥ መግለጫ

🔆እየጠየቁ መኖር መልስን፣
መልስን ፈልጎ ማግኘት ዕውቀትን፣
እውቀት ነፃነትን፣ ነፃነት ሙሉ ስብዕናን፣
ሙሉ ስብዕና ሠላምና እርካታን፣
እርካታ ደግሞ ደስተኛ ሆኖ መኖርን ያስገኛል፡፡
አብረን እንደግ !!
@EthioHumanity @Ethiohumanity
✍የተሰማቹን አጋሩን! ቤቱ ሁሌም ክፍት ነው፣ሃሳባቹን ፃፍፍ አርጉልን @EthioHumanitybot

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 11

2022-11-01 18:06:34
2.2K views15:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-01 18:05:53 Fua Event Organizer is the company which plans & organizes full wedding , Graduation, Birthday, festival, Bridal shower, Baby shower packages & other social events and it is the best in Ethiopia.

OUR SERVICES

*Consulting the Budget

*Selecting Venues

*Selecting Vendors

-Photographers

-Videographers

-Decors

-Bands

-Cakes

-Singers/Amukligns and

-Wedding day Coordinators/Protocols

*Coordinating Events
2.3K views15:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-31 21:33:22 ሰዓት እላፊ! (ፀዴ ቀደዳ ነው ሳትሰለች አንብበው)



. [Restoring Faith in Humanity]

. ∞ ∞ ∞ ∞

እነሱም ይላሉ፣
ተኩሰን አንስትም፣
እኛም እንላለን፣
ቃታ አናስከፍትም።
እንዲህ ተባብለን፣ የተገናኘን 'ለት፣
ተሰብሰብ አሞራ ትበላለህ ዱለት።

-

የአዲስ አበባ ሠው ሆይ።

ይሄ የተጣድንበት እሳት፣ ይሄ እቶን፣ ይሄ ነበልባል፣ ይሄ ድውይ ጦርነት ስሙ የርስ በራስ ጦርነት (Civil War) ነው። በቀላል አማርኛ - የቀድሞው ኢህአዴግ ግንባር በስልጣን እና በሪሶርስ መስማማት አቅቶት #እርስ_በራሱ ስለተጣላና ስለተከፋፈለ ያወደቀብን ዳፋ፣ ያመጣብን ሲቪል ዋር ነው። የሲቪል ዋር ደግሞ ጀግና የለውም። ፈሪም የለውም። ፀጉረ ልውጥ - ባዳና ባንዳ የለውም። ድሉም ችንፈቱም፣ ገድሉም ውርደቱም የኔና ያንተ ነው። #የኛው ገመና፣ የኛው ነውር ነው።

እውነት ነው።

ት*ግሬዎቹ ላመኑበት ባመኑበት በታላቅ ጀግንነት ተዋግተዋል። እኛም ላመንንበት ባመንንበት በታላቅ ጀግንነት ገጥመናቸዋል። እነሱም ዘራችንን ሊያጠፉ ወጉን ብለዋል። እኛም አገር ሊያፈርሱ ወጉን ብለናል። ሁሉም የየራሱን Narrative ይዞ አውደ ውጊያ ወርዷል። አፋፍ ለአፋፍ፣ ምሽግ ለምሽግ፣ ጢሻ ለጢሻ፣ ቆረንጦ ለቆረንጦ በታላቅ ወንዳ ወንድነት ገጥሟል። ታላቅ ገድልን ተጋድሏል። አቸናፊም ተቸናፊም ታሪክ አስጽፏል። ታሪክ ሰርቷል።

የሸገር ሰው ሆይ።

አሁን በቀጣይ ሳምንታት አቸነፍን ብለን፣ መቀሌ ገባን ብለን። ምናልባትም የህወሃት አመራሮችና የጦር ጄነራሎች በወንድ ልጅ/ በማርያም መንገድ እንዲሼሹ ተደረጉ ብለን። አልያም አይበለውና ተማርከው ወታደራዊ ፍርድ ቤት ቀረቡ ብለን የት*ግሬውን ቅስም የመስበርና የማሳጣት ፕሮፓጋንዳ ውስጥ ከገባን #ትልቁን ስእል (The Big Picture) እንስታለን። የቅሽምናን Cycle እናስቀጥላለን።

አትርሳ።

ት*ግሬው እኮ የአገርህ ልጅ ነው። በደም፣ በባህል፣ በእምነት፣ በአኗኗር፣ በወኔ በኑሮ አንተን መሳይ ነው። ቢያኮርፍም፣ በቃኝ ካንተ ጋራ አብሮ መኖር፣ ፍታኝ ልፋታህ ቢልም ዘመድህ ነው። በሕግ በዜግነት ያንተ አይነት መብትና ግዴታ ያለው ኢትዮጵያዊ ነው። በታሪክ ደግሞ ሃገር ግንባታ ላይ፣ ዳር ድንበር ማስጠበቅ ላይ፣ ኢትዮጵያን ማቅናት ላይ አኩሪ ገድል ያለው፣ ታላቅ አስተዋጽኦን ካበረከቱ ጥቂት ነገዶች ውስጥ #ከላይ የሚመደብ ነው።

በዚህ።

ወደ ገደለው - አሁን በዚህ አስቀያሚ ጦርነት ሳቢያ Average ኢትዮጵያዊ ከተጋፈጠው መከራ በላይ ት*ግሬው ተጋፍጧል። ከየትኛውም ክልል በላይ የትግራይ ክልል የፈርኦን ዘመን ዳፋዎችን ተቀብሎ ኖሯል።

አስበው።

ለሁለት አመት ልጆቹን ት/ቤትና ኮሌጅ አልላከም። ብሩን አውጥቶ አስቤዛ እንዳይገዛ ባንክ ተዘግቶበታል። ስልክ ኢንተርኔት ተቋርጦበታል። እንዳይነግድ፣ እንዳይወጣ እንዳይገባ መንገድ ተዘግቶበታል። ደሞዝ አልተሰጠውም። ባጀት አልተለቀቀለትም። አልዘራም፣ አልነገደም። እዚህ ግባ የሚባል ምርጥ ዘር፣ ማዳበሪያና መድሃኒት አላገኘም፤ አልተሰራጨለትም። በላዩ ላይ ህወሃት አልዋጋ ያላትን ወጣት በሙሉ በግድም በውድም በአፈሣ ወስዳ ማግዳዋለች።

እና።

እናማ ጦርነትን እና ረሃብን አንድ ላይ ሲያስተናግድ የነበረ ክልል ሕዝብ ተቸነፈ፣ ጊዜ ጣለው ብለን የቅስም ሰበራና የማቅለል፣ የማዋረድ (Humiliation) ፕሮጀክት ውስጥ ከገባን ነግ በኔን የማናውቅ፣ ያልበሰልን፣ ከታሪክ የማንማር ጉፋያዎች ነን ማለት ነው።

እኔ ልፍረድ።

ወደ ኋላ እንይ። መላውን የትግራይ ስፍራ አጠቃላዩን የትግራይ 52 ወረዳዎችና አራት ዞኖች በተደጋጋሚ ጎቦኝቻለሁ። በስራ የአለም አቀፍ NGO የResearch ጥናት ሃላፊ ሆኜ አጥንቻለሁ። ዞሬ ሰርቼበታለሁ። ሕዝቡን፣ ኑሮውን፣ ባህሉን፣ ውሎውን፣ ደግነቱን፣ አዲስ ሰው ወዳጅነቱን፣ በትክክል አውቀዋለሁ። ከእጁ በልቻለሁ - ጠጥቻለሁ። እንደ ሠው ተከብሬ ተስተናግጃለሁ። ዘርህ ሐማሴን፣ ዘመዶችህ ኤርትራ ናቸው ነው ብሎ የጠላኝ የገፋኝ አልነበረም።

ትግሬውን የማውቀው 22 ላይ ሲጨስ፣ ሲጨፍርና ብር ሲበትን ሳይሆን ትግራይ ላይ ሠርክ ኑሮን ሲገፋና ሲጋፋ ነው።

አንተ ፍረድ።

ከሌላው ክልል #በተለየ መልኩ ከትግ*ሬዎቹ ክልል ሄዶ የሰራ ሠው። መቀሌ/አክሱም/አዲግራት ዩንቨርሲቲ የተማረ ሠው፣ ከትግሬዎቹ ጋራ በክልላቸው የኖረ ሠው፣ ሰዎቹንና ባህሪያቸውን ሲወድዳቸው እንጂ ሲጠላቸው አጋጥሞኝ አያውቅም። ሲናፍቅ እንጂ ሲያማርር ሰምቼ አላውቅም። እንግዳን መውደድ፣ የመሃል አገርን ሰው ማክበር ጥጉና ማሳያው ናቸው። ያያቸው የሚመሰክርላቸው ጥሬ ሐቃቸው ነው። ካየህ ከኖርክ፣ ከተማርክ ከነበርክ ምስክር ነህ አንተ።

ስማኝ የሸገር ልጅ።

አገርህን የምትወድድ ከሆነ፣ ኢትዮጵያን የምታፈቅር ከሆነ፣ ሕዝቦቿ ወገኖቼ ናቸው የምትል ከሆነ፣ በት*ግሬ ዘመድህ ችንፈትና ውድቀት አትደሰትም። አትፈነጥዝም። በቀል እያሰብክ የመጨረሻውን ሳቅ ልገልፍጥ አትልም።

ሞክር።

የድርሻህን ሞክር። የአቅምህን ወርውር። DO Something.

. . . ደውል።

በቅርብህ የምታውቀው የትግራዋይ ወዳጅህ፣ ጓደኛህ፣ ባልደረባህ፣ ጎረቤትህ፣ ደንበኛህ ጋራ አሁኑኑ ደውል። ወይንም ቴክስት ጻፍለት። ጠፋሁበት ብለህ፣ እስከዛሬ የት ነበርኩ ብለህ ሼም #አይያዝህ።

ዝም አትበለው።

አዋራው፣ ጠይቀው። ዘመድ አዝማድ፣ ቤተሰቦችህ እንዴት ናቸው ብለህ ጠይቀው። ስራ ላጣ፣ ተሰድዶ ለመጣ፣ ለተፈናቀለ፣ እዚህ ለተቸገረ፣ ቤት ኪራይ ለጎደለው፣ ወይንም እዛ ላለ ሰው ምን ልርዳ ምን ላግዝ ብለህ ጠይቀው። ያቅሜን ልወርውር በለው። እሱ ሼም #ይሉኝታ ስለሚቆልፈው፣ አንተው አደፋፍረው። ከድባቴው አውጣው። አበረታታው። ያልፋል ይሄም በለው። መጣላት መታረቅ በኛ አልተጀመረም ብለህ አስረዳው። . . . ዘር ብሔር ሳትቆጥር መከታ ሁነው።

¤

. [ይሄ መልካምነትህ #ላንተ ሶስት ጥቅም አለው]

1 - የምታምንበት ፈጣሪ ብድራትህን ይከፍልሃል።
2 - የምትወዳት አገርህ ላይ ቂምና ቁርሾ ትቀንሳለህ።
3 - ህሊናህ፣ አእምሮህ ሰላም ያገኛል።

-

. . . ማን ያውቃል - ነገ የዚህ ገበሬ ስድራ ገዛ፤ የዚህችን ምንም የማታውቅ ንጽህት ትግራወይቲ ህጻን የወደፊት እጣፈንታ ላይ የተስፋ ጭላንጭል ያበራኸው አንተ ትሆን ይሆናል።

¤

“Love and kindness are never wasted. They always make a difference. They bless the one who receives them, and they bless you, the giver.”

– Barbara De Angelis

Eyob Mihreteab

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity
3.3K views18:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-31 21:32:04
2.9K views18:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-30 17:56:48
ፍቅር ማለት በዚህ በምትመለከተው ጨለማ ውስጥ ከሚብለጨለጩት ቁጥር ስፍር የሌላቸው አምፓሎች መሀል ፣ነፍስ አንዷን መርጣ በብርሃኗ ስትደምቅ ነው።ብርሀን ሁሉ የነፍስን ጨለማ አይገፍም ቢበዛ የራስህን ብርሃን ትፈልግ ዘንድ ያግዝህ ይሆናል።ሰው የቱንም ያህል በደማቅ ብርሀን ቢከበብ፣እውነተኛውን የራሱን ብርሃን እስካላገኘ ድረስ ነፍሱ ጨለማ ውስጥ ናት።

ፍቅርና ዝምታ መለኮታዊ ኃይሎች ናቸው።ፈጣሪን የምንፈራው ከተከታዮቹ ብዙ ጩኸት ይልቅ በጥልቅ ዝምታው ሳይሆን አይቀርም እናም በዝምታ ግርማ ሞገስ ውስጥ ባለ እውነተኛ ፍቅሩ።ዝምታን የሚያሸንፍ ጬኸት ፍቅርን የሚያንበረክክ  ብልጣ ብልጥነት የለም።   

አሌክስ አብርሀም

ውብ ምሽት !!

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
4.0K views14:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-29 07:56:52
ሸጋ ቅዳሜ!
4.8K views04:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-24 21:05:51 በዚህ ምድር ላይ ሰው ሁሉ የዘራውን ያጭዳል። ይህ ህገ ተፈጥሮ ነው። በየትኛውም የዓለም ክፍል የሚሰራ ህግ ነው። እንደ ህገ-መንግስት በአንድ ሉአላዊ ሀገር ብቻ የተገደበ አይሆንም። በምድር ላይ ለሰራው ደግነት ይሁን ክፋት ብድራት መከፈሉ የማይቀር ይሆናል።በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ የቻልከውን ያህል መልካም ውለታ ብትውል ብድራት ተከፋይ ትሆናለህ። ካለህ ላይ መስጠት ማለት ነው። … የምትሰጠው ነገር ባይኖርህ ጥሩ ፈገግታ ስጥ። ምናልባት ይህች ፈገግታ አንተ ባታውቅ እንጂ አንዲት የጨነቃት ነፍስ ትታደጋለች ።

ያንተ መልካም ስነምግባር ሌላውን ተመልካች ከተኛበት የመቀሰቀስ መግነጢሳዊ የስበት ኃይል እንዳላት አንተ አታውቅም ይሆናል። በዚህ ምድር ላይ የተዘራ ማንኛውም ነገር እንዲሁ ወድቆ የሚቀር ላይሆን ይችላል።

መልካም ገበሬ ለነፍሱም ለቤተሰቦቹም ብሎም ለሃገር ለህዝብ የሚተርፍ ዘር ዘርቶ ፍሬውን ይመግባል።  በየትኛውም የህይወት ሜዳ ላይ የሚገኝ እያንዳንዱ ግለሰብ መልካም ገበሬ ለመሆን የሚያግደው የለም።

ሁሌም በጎ በጎውን ማሰብ ስትለማመድ መልካም ገበሬ ትሆናለህ።  ከራስህ አልፎ ተርፎ ለሌላው የሚጠቅም መልካም ሐሳብ ወደ ዓለም ብትልክ መልካምነት ዞሮ ይከፍልሃል። ብድራቱን ታገኛለህ። የጣልከው አልያም ያካፈልከው ሁሉ መልሶ ብድራቱን ይከፍልሃልም። …መልካም መሆን ኪሳራ ከሌለው ክፉ መሆን ምንም ትርፍ የለውም። … ወዲህም ባንተ ላይ እንዲሆንየማትፈልገውን ነገር በሌላው ላይ አታድርግ። …ፍቅር ትሻ እንደሆን ፥ ቀድመህ አንተ ፍቅር ስጥ።  ያልሰጡትን ለማግኘት ማሰብ ፥ ስንዴ ዘርቶ የጤፍ ምርት እንደመጠበቅ እንዳይሆን። … ከመስተዋት የተሰራ ቤት ውስጥ የሚኖር ሰው ከቤቱ ሆኖ  ወደ ውጭ ድንጋይ መወርወር የለበትም። 

ጋን በጠጠር ይደገፋል እንዲሉ ፤ እያንዳንዱ ሰው በሌላው ህይወት በቀጥታም ይሆን በተዘዋዋሪ  ተፅእኖ ማሳደሩ ህገ-ተፈጥሮ ነው።አይመለከተኝም፥ አይደርስብኝም የምትለው ነገር ላይሆን ይችላል። … ጉንፋን የያዘው ሰው አጠገብህ ተቀምጦ ቫዮረሱ አንተ ዘንድ እንዳይደርስ ለማድረግ አትችልም። በአንድም በሌላ መልክ ኢንተርአክሽን ይኖራል።

            ውብ ምሽት
@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot
8.1K views18:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-24 21:05:31
6.3K views18:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-23 21:29:55 "ባለቤቴ ምጧ እንደመጣ ወደ ሆስፒታል አመራን ፣ ልጃችን እንደተወለደ ነርሷ የልጃችንን ፆታ ወንድ ወይም ሴት ናት ብላ ልትነግረን አልፈለገችም። ከዛ በኋላ የልጃችንን ፆታ ለምን ልትነግረን እንዳልፈለገች አጥብቄ ጠየቅኳት። ነርሷም "ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሆስፒታሉ ፆታን በተመለከተ ምንም አይነት መረጃ መስጠት እንደማንችል ስልጠና ተሰጥቶናል። የልጃቸውን ፆታ ይሄ ነው ብለህ ስትነግራቸው ሆስፒታሉን እና የጤና ባለሙያዎቹን በታላቅ ቁጣ በአንድ እግራቸው የሚያቆሙ ሞገደኛ ወላጆች አሉ " ብላ መለሰችልኝ። አሁን የገባኝ ነገር የምንኖርበት አለም የዕብደት ሆኗል!"

ሌላኛዋ አስተያየት ሰጪ የገጠማትን ጨመረች " በቅርቡ ወንድ ልጄን ስወልድ የሞላሁት የልደት ሰርተፍኬት ፎርም የፆታ ማሳወቂያ ሶስት አማራጮች ነበሩት። ወንድ_ ሴት__ እና ያልተወሰነ_.....! አስቡት የምንወልዳቸው ህፃናት በአንድ ጊዜ ወንድ ወይም ሴት ከመሆን የዘለለ ምርጫ ባይኖራቸውም ሶስተኛው አማራጭ የተተወው ህፃናቱ ሲያድጉ በራሳቸው ምርጫ ፆታቸውን እንዲመርጡ ታስቦ ነው"

እነዚህን አስተያየቶች What is a woman? ከሚለው የ Matt Walsh አስደናቂ ዘጋቢ ፊልም ስር ያስቀመጡት በሃገራቸው ስር ሰዶ በተንሰራፋው ፆታን ከመረዳት እስከ መቀየር በደረሰው ማህበረሰባዊ ጤንነታቸው ግራ የተጋቡ አሜሪካዊያን ወላጆች ናቸው።

የሶስት ሴት ልጆችና የአንድ ወንድ ልጅ አባት የሆነው ማት ዎሽ What is a Woman? ( ሴት ምንድናት?) የሚለውን ቀላል ጥያቄውን ይዞ ከአሜሪካ ጎዳናዎች አንስቶ ግዙፍ ዩኒቨርስቲዎቿን አስከሚመሩት ምሁራን " ሴት ምንድናት" እያለ ቢጠይቅም የሚያገኘው መልስ የራሱን ጤንነት እስኪጠራጠር ድረስ አስደንጋጭ ነበር።

ማት አንዲት ፆታዋን ቀይራ ወንድ ነኝ ከምትል ቆንጆ ጋር ቁጭ ብሎ "ሴት ምንድናት?" ብሎ ጠየቃት። ይህቺው ቆንጆ "እስኪ ሴቶቹን ጠይቃቸው። እኔኮ ሴት አይደለሁም" ትለዋለች። ወንዶቹም ከፆታቸው ተካክደው ሴት ሆነው ያወሩታል። ማት ለመሞገት ቢሞክርም ኋላ ቀር የዳይኖሰር ዘመን ሰው መስሎ ይታያቸዋል።

ማት በመንገድ የሚያገኛቸውን የተለያዩ ወጣቶችን ይጠይቃል " እኔ እንደምታዩኝ በእውነታው ወንድ ነኝ። እራሴን ሴት ነኝ ብዬ ብገልፅና ብቀርብ ምላሻችሁ ምንድነው?" ታዲያ ለዚህ ጥያቄ ከወጣቶቹ የሚያገኘው አብዛኛው መልስ " ምርጫህ ያንተ ነው። ሴት ነኝ ብትለኝም ችግር የለብኝም። ሁሉም ሰው ነኝ ብሎ የሚያምነውን ነው። ያን ያህል የሚያስጨንቀኝ ጉዳይ አይደለም " የሚል ነበር።

ማት ወደ ዩኒቨርስቲዎች አምርቶ በስነ ፆታ ማህበራዊና ቤተሰባዊ ጉዳዮች ጥርሳቸውን የነቀሉ አንቱ የተባሉ ምሁራንና ባለሙያዎችን በሴት ምንነት ፣ የፆታ ክፍፍልና ብየናችን በተፈጥሮ መሰረቶችና በእውነታው መመዘን እንዳለበት ቢሞግትም የአብዛኞቹ ትንተናና አረዳድ እንደሚከተለው ነው .... 'የሰው ልጆች ፆታቸው በመራቢያ አካላቸው ማለትም በብልቶቻቸው ምክንያት ሊወሰን እንደማይችልና ፆታቸውን በውስጣቸው ከሚሰማቸው ስሜት ተነስተው መምረጥ እንደሚችሉ በምርጫቸውም ላይ የዘረመል ተዋፅኦዋቸው ያለውን የምናልባት ድርሻ በመተንተን ይህም ማለት ሴት ወይም ሴትነት ጡት ስላንጠለጠለችና Vagina ስላላት የሚገኝ እንዳልሆነ ያስረዳሉ። ለወንዶችም ወሸላ ማንጠልጠላቸው ፆታቸውን ወንድ ነው ለማለት ብቁ አይደለም። ሴትም ሆነ ወንድ ፆታቸውን ውስጣቸው እንደሚሰማቸው ስሜት መምረጥና መቀየር መብታቸው እንደሆነ የአብዛኛው ምሁራንና ባለሙያዎች አቋም ነው።

ታዲያ ይህንን ፆታን በተመለከተ የተዛባው አመለካከት ፆታን በመበየን አላቆመም። ወንዶችን እንደፍላጎታቸው ሴት ለማድረግ ሴቶችንም ወደ ወንድነት ለመቀየር ሆስፒታሎች ተቋቁመው የፆታ ቅየራ gender transplant ይሰራላቸዋል። ወንዶች ቀዳዳ ያበጃሉ ሴቶችም ያንጀለጅላሉ። ፆታ መቀየሩ የሚያስከትለውን የሆርሞን መዛባት ለማስተካከል በፋብሪካ እንደ መድሃኒት የተመረቱ ሆርሞኖች የፆታ ቅየራውን ተከትለው ጥቅም ላይ ይውላሉ። ኢንዱስትሪው በቪሊየን ዶላሮች እየዘወረ ትውልዱ ከማይቀር የማንነት ቀውስ ውስጥ ይወድቃል።

ህፃናት በጨቅላ እድሜያቸውና ባልበሰለ አዕምሯቸው በዚህ ውዝግብ ውስጥ ገብተው በየ ሆስፒታሉ ፆታቸውን ለመቀየር ላይና ታች ይቀደዳሉ። አብዛኞቹ ፆታቸውን ያስነካኩ ወይም gender transplant ያሰሩ ህፃናት
ከሚገጥማቸው የማንነት ቀውስ የሚያወጣቸው አጥተው አብዛኞቹ ራሳቸውን ያጠፋሉ።

ማት በዚሁ ዘጋቢ ፊልም እንዳሳየን ፆታቸውን ወደ ሴትነት የቀየሩ ወንዶች በተለያዩ የስፖርት ውድድሮች ከሴቶች ጋር ሴት ነን ብለው እየተወዳደሩ ውድድሮችን ያሸንፋሉ። የካዱት ተፈጥሯዊ ማንነታቸውና ፆታቸው ውድድሩን ለማሸነፍ እንደረዳቸው ቢጠየቁም ማሸነፋቸው ከስራና ከጥረት ጋር እንጂ ከፆታ ጋር እንደማይገናኝ አጥብቀው ይሞግታሉ። በነሱ አለም ሴት ነኝ ያለ ሴት ወንድ ነኝ ያለም ወንድ ነው።

ፆታቸውን ያስቀየሩ ወይም ሴት ነን ብለው የሚያምኑ ወንዶች የሴቶች ሽንት ቤት ካልተጠቀምን ፣ ሴቶች የሚጠቀሙበት ስፓ ውስጥ ገብተን ካልታሸን በሚል የአደባባይ አንባጓሮ ይፈጥራሉ። አስቡት... ልብም በሉ አንድ ወንድ ወሸላውን እንጠልጥሎ ከሴቶች ጋር ካልሸናው ከሴቶች ጋር ካልታጠብኩ ይላል። በዚሁ ፆታቸውን በቀየሩ ሰዎች የሽንት ቤት አጠቃቀም ዙሪያ ከማት ጠንከር ያለ ጥያቄና ክርክር የገጠማቸው የኮንግረስ አባል ጥያቄውን ለመመለስ ከመጨነቃቸው የተነሳ ከፍተኛ ፍርሃት እየተነበባቸው ቃለ መጠይቁን እስከማቋረጥ ደርሰዋል። ከምሁራኑ እስከፖለቲከኞቹ የሚያስፈራቸው አንዳች ሃይል ምን እንደሆነ ግራ ያጋባል።

በዚህና መሰል ጉዳዮች ላይ ለተቃውሞ መንቀሳቀስና አጥብቆ መጠየቅ በኋላ ቀርነት አስፈርጆ የዳይኖሰር ዘመን ሰው ያስብላል። ሚዲያውም ሆነ ምሁራኑ በግላቸው ያመኑበት አቋም እንዳለ ሆኖ በጉዳዩ ላይ የሰላ ትችትን ማቅረብ ይፈራሉ።

በዚህ ሁሉ መከራ ውስጥ Hollywood Netflix እና ግዙፍ የፊልም ኢንዱስትሪዎች ፆታን መርጦ ስለመቀየርና የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻን በተመለከተ በፊልሞቻቸው ይሰብካሉ። በአሜሪካ ተደማጭነት ያላቸው ፖለቲከኞችና የህዝብ ተወካይ ሴናተሮች ወገባቸውን አስረው ፆታን መርጦ ስለመቀየር ያልተገደቡ መብቶች ይሞግታሉ።

ማት ቢጨንቀውና ሃገሩን አሜሪካን ቢጠራጠር ሴት ምንድናት የሚለውን ጥያቄውን ይዞ የኬንያ የገጠር መንደሮች ውስጥ ተገኘ። የማሳይ ጎሳ አባላትን አጊንቶ ሴት ምንድናት አላቸው? ማሳዮች የጠራ ተፈጥሮአዊ መልስ ነበራቸው "ሴት የምትወልድ ናት ፣ ሴት ጡት ያላት ፣ ሴት የመራቢያ አካል ያላት ወልዳ የምታጠባ ናት። ሴትና ወንድን ለመለየት አንቸገርም" አሉት። ማት ለማሳይ ጎሳ አባላት በሃገሩ ያለውን ፆታን የመረዳትና የመቀየር ዝብርቅርቅ አስረዳቸው። ማሳዮች ሳቁ ተገረሙም። ማት ወደ ማሳይ ሄደ እንጂ ወደ ሃገሬ ኢትዮጵያ ቢመጣ በመስቀለኛ ማማተብን ይለምድ ነበር።

ማት በስተመጨረሻ "ሴት ምንድናት?" ብሎ ጥያቄ ያቀረበላቸው ምሁር በትዕቢት ተሞልተው "ሚስትህን ጠይቃት" ባሉት መሰረት አለምን የዞረበትን ጥያቄ ይዞ ወደ ሚስቱ ተመልሷል።

ሚስቱ ምን ትመልስለት ይሆን ?

ዘጋቢ ፊልሙን ከማየት ብዙ መረዳትና መልሶች ያገኛሉ!

ሙሉቃል ቃል

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity
7.2K views18:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-23 21:29:21
4.9K views18:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ