Get Mystery Box with random crypto!

ሰዓት እላፊ! (ፀዴ ቀደዳ ነው ሳትሰለች አንብበው) . [Res | ስብዕናችን #Humanity

ሰዓት እላፊ! (ፀዴ ቀደዳ ነው ሳትሰለች አንብበው)



. [Restoring Faith in Humanity]

. ∞ ∞ ∞ ∞

እነሱም ይላሉ፣
ተኩሰን አንስትም፣
እኛም እንላለን፣
ቃታ አናስከፍትም።
እንዲህ ተባብለን፣ የተገናኘን 'ለት፣
ተሰብሰብ አሞራ ትበላለህ ዱለት።

-

የአዲስ አበባ ሠው ሆይ።

ይሄ የተጣድንበት እሳት፣ ይሄ እቶን፣ ይሄ ነበልባል፣ ይሄ ድውይ ጦርነት ስሙ የርስ በራስ ጦርነት (Civil War) ነው። በቀላል አማርኛ - የቀድሞው ኢህአዴግ ግንባር በስልጣን እና በሪሶርስ መስማማት አቅቶት #እርስ_በራሱ ስለተጣላና ስለተከፋፈለ ያወደቀብን ዳፋ፣ ያመጣብን ሲቪል ዋር ነው። የሲቪል ዋር ደግሞ ጀግና የለውም። ፈሪም የለውም። ፀጉረ ልውጥ - ባዳና ባንዳ የለውም። ድሉም ችንፈቱም፣ ገድሉም ውርደቱም የኔና ያንተ ነው። #የኛው ገመና፣ የኛው ነውር ነው።

እውነት ነው።

ት*ግሬዎቹ ላመኑበት ባመኑበት በታላቅ ጀግንነት ተዋግተዋል። እኛም ላመንንበት ባመንንበት በታላቅ ጀግንነት ገጥመናቸዋል። እነሱም ዘራችንን ሊያጠፉ ወጉን ብለዋል። እኛም አገር ሊያፈርሱ ወጉን ብለናል። ሁሉም የየራሱን Narrative ይዞ አውደ ውጊያ ወርዷል። አፋፍ ለአፋፍ፣ ምሽግ ለምሽግ፣ ጢሻ ለጢሻ፣ ቆረንጦ ለቆረንጦ በታላቅ ወንዳ ወንድነት ገጥሟል። ታላቅ ገድልን ተጋድሏል። አቸናፊም ተቸናፊም ታሪክ አስጽፏል። ታሪክ ሰርቷል።

የሸገር ሰው ሆይ።

አሁን በቀጣይ ሳምንታት አቸነፍን ብለን፣ መቀሌ ገባን ብለን። ምናልባትም የህወሃት አመራሮችና የጦር ጄነራሎች በወንድ ልጅ/ በማርያም መንገድ እንዲሼሹ ተደረጉ ብለን። አልያም አይበለውና ተማርከው ወታደራዊ ፍርድ ቤት ቀረቡ ብለን የት*ግሬውን ቅስም የመስበርና የማሳጣት ፕሮፓጋንዳ ውስጥ ከገባን #ትልቁን ስእል (The Big Picture) እንስታለን። የቅሽምናን Cycle እናስቀጥላለን።

አትርሳ።

ት*ግሬው እኮ የአገርህ ልጅ ነው። በደም፣ በባህል፣ በእምነት፣ በአኗኗር፣ በወኔ በኑሮ አንተን መሳይ ነው። ቢያኮርፍም፣ በቃኝ ካንተ ጋራ አብሮ መኖር፣ ፍታኝ ልፋታህ ቢልም ዘመድህ ነው። በሕግ በዜግነት ያንተ አይነት መብትና ግዴታ ያለው ኢትዮጵያዊ ነው። በታሪክ ደግሞ ሃገር ግንባታ ላይ፣ ዳር ድንበር ማስጠበቅ ላይ፣ ኢትዮጵያን ማቅናት ላይ አኩሪ ገድል ያለው፣ ታላቅ አስተዋጽኦን ካበረከቱ ጥቂት ነገዶች ውስጥ #ከላይ የሚመደብ ነው።

በዚህ።

ወደ ገደለው - አሁን በዚህ አስቀያሚ ጦርነት ሳቢያ Average ኢትዮጵያዊ ከተጋፈጠው መከራ በላይ ት*ግሬው ተጋፍጧል። ከየትኛውም ክልል በላይ የትግራይ ክልል የፈርኦን ዘመን ዳፋዎችን ተቀብሎ ኖሯል።

አስበው።

ለሁለት አመት ልጆቹን ት/ቤትና ኮሌጅ አልላከም። ብሩን አውጥቶ አስቤዛ እንዳይገዛ ባንክ ተዘግቶበታል። ስልክ ኢንተርኔት ተቋርጦበታል። እንዳይነግድ፣ እንዳይወጣ እንዳይገባ መንገድ ተዘግቶበታል። ደሞዝ አልተሰጠውም። ባጀት አልተለቀቀለትም። አልዘራም፣ አልነገደም። እዚህ ግባ የሚባል ምርጥ ዘር፣ ማዳበሪያና መድሃኒት አላገኘም፤ አልተሰራጨለትም። በላዩ ላይ ህወሃት አልዋጋ ያላትን ወጣት በሙሉ በግድም በውድም በአፈሣ ወስዳ ማግዳዋለች።

እና።

እናማ ጦርነትን እና ረሃብን አንድ ላይ ሲያስተናግድ የነበረ ክልል ሕዝብ ተቸነፈ፣ ጊዜ ጣለው ብለን የቅስም ሰበራና የማቅለል፣ የማዋረድ (Humiliation) ፕሮጀክት ውስጥ ከገባን ነግ በኔን የማናውቅ፣ ያልበሰልን፣ ከታሪክ የማንማር ጉፋያዎች ነን ማለት ነው።

እኔ ልፍረድ።

ወደ ኋላ እንይ። መላውን የትግራይ ስፍራ አጠቃላዩን የትግራይ 52 ወረዳዎችና አራት ዞኖች በተደጋጋሚ ጎቦኝቻለሁ። በስራ የአለም አቀፍ NGO የResearch ጥናት ሃላፊ ሆኜ አጥንቻለሁ። ዞሬ ሰርቼበታለሁ። ሕዝቡን፣ ኑሮውን፣ ባህሉን፣ ውሎውን፣ ደግነቱን፣ አዲስ ሰው ወዳጅነቱን፣ በትክክል አውቀዋለሁ። ከእጁ በልቻለሁ - ጠጥቻለሁ። እንደ ሠው ተከብሬ ተስተናግጃለሁ። ዘርህ ሐማሴን፣ ዘመዶችህ ኤርትራ ናቸው ነው ብሎ የጠላኝ የገፋኝ አልነበረም።

ትግሬውን የማውቀው 22 ላይ ሲጨስ፣ ሲጨፍርና ብር ሲበትን ሳይሆን ትግራይ ላይ ሠርክ ኑሮን ሲገፋና ሲጋፋ ነው።

አንተ ፍረድ።

ከሌላው ክልል #በተለየ መልኩ ከትግ*ሬዎቹ ክልል ሄዶ የሰራ ሠው። መቀሌ/አክሱም/አዲግራት ዩንቨርሲቲ የተማረ ሠው፣ ከትግሬዎቹ ጋራ በክልላቸው የኖረ ሠው፣ ሰዎቹንና ባህሪያቸውን ሲወድዳቸው እንጂ ሲጠላቸው አጋጥሞኝ አያውቅም። ሲናፍቅ እንጂ ሲያማርር ሰምቼ አላውቅም። እንግዳን መውደድ፣ የመሃል አገርን ሰው ማክበር ጥጉና ማሳያው ናቸው። ያያቸው የሚመሰክርላቸው ጥሬ ሐቃቸው ነው። ካየህ ከኖርክ፣ ከተማርክ ከነበርክ ምስክር ነህ አንተ።

ስማኝ የሸገር ልጅ።

አገርህን የምትወድድ ከሆነ፣ ኢትዮጵያን የምታፈቅር ከሆነ፣ ሕዝቦቿ ወገኖቼ ናቸው የምትል ከሆነ፣ በት*ግሬ ዘመድህ ችንፈትና ውድቀት አትደሰትም። አትፈነጥዝም። በቀል እያሰብክ የመጨረሻውን ሳቅ ልገልፍጥ አትልም።

ሞክር።

የድርሻህን ሞክር። የአቅምህን ወርውር። DO Something.

. . . ደውል።

በቅርብህ የምታውቀው የትግራዋይ ወዳጅህ፣ ጓደኛህ፣ ባልደረባህ፣ ጎረቤትህ፣ ደንበኛህ ጋራ አሁኑኑ ደውል። ወይንም ቴክስት ጻፍለት። ጠፋሁበት ብለህ፣ እስከዛሬ የት ነበርኩ ብለህ ሼም #አይያዝህ።

ዝም አትበለው።

አዋራው፣ ጠይቀው። ዘመድ አዝማድ፣ ቤተሰቦችህ እንዴት ናቸው ብለህ ጠይቀው። ስራ ላጣ፣ ተሰድዶ ለመጣ፣ ለተፈናቀለ፣ እዚህ ለተቸገረ፣ ቤት ኪራይ ለጎደለው፣ ወይንም እዛ ላለ ሰው ምን ልርዳ ምን ላግዝ ብለህ ጠይቀው። ያቅሜን ልወርውር በለው። እሱ ሼም #ይሉኝታ ስለሚቆልፈው፣ አንተው አደፋፍረው። ከድባቴው አውጣው። አበረታታው። ያልፋል ይሄም በለው። መጣላት መታረቅ በኛ አልተጀመረም ብለህ አስረዳው። . . . ዘር ብሔር ሳትቆጥር መከታ ሁነው።

¤

. [ይሄ መልካምነትህ #ላንተ ሶስት ጥቅም አለው]

1 - የምታምንበት ፈጣሪ ብድራትህን ይከፍልሃል።
2 - የምትወዳት አገርህ ላይ ቂምና ቁርሾ ትቀንሳለህ።
3 - ህሊናህ፣ አእምሮህ ሰላም ያገኛል።

-

. . . ማን ያውቃል - ነገ የዚህ ገበሬ ስድራ ገዛ፤ የዚህችን ምንም የማታውቅ ንጽህት ትግራወይቲ ህጻን የወደፊት እጣፈንታ ላይ የተስፋ ጭላንጭል ያበራኸው አንተ ትሆን ይሆናል።

¤

“Love and kindness are never wasted. They always make a difference. They bless the one who receives them, and they bless you, the giver.”

– Barbara De Angelis

Eyob Mihreteab

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity