Get Mystery Box with random crypto!

በዚህ ምድር ላይ ሰው ሁሉ የዘራውን ያጭዳል። ይህ ህገ ተፈጥሮ ነው። በየትኛውም የዓለም ክፍል የሚ | ስብዕናችን #Humanity

በዚህ ምድር ላይ ሰው ሁሉ የዘራውን ያጭዳል። ይህ ህገ ተፈጥሮ ነው። በየትኛውም የዓለም ክፍል የሚሰራ ህግ ነው። እንደ ህገ-መንግስት በአንድ ሉአላዊ ሀገር ብቻ የተገደበ አይሆንም። በምድር ላይ ለሰራው ደግነት ይሁን ክፋት ብድራት መከፈሉ የማይቀር ይሆናል።በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ የቻልከውን ያህል መልካም ውለታ ብትውል ብድራት ተከፋይ ትሆናለህ። ካለህ ላይ መስጠት ማለት ነው። … የምትሰጠው ነገር ባይኖርህ ጥሩ ፈገግታ ስጥ። ምናልባት ይህች ፈገግታ አንተ ባታውቅ እንጂ አንዲት የጨነቃት ነፍስ ትታደጋለች ።

ያንተ መልካም ስነምግባር ሌላውን ተመልካች ከተኛበት የመቀሰቀስ መግነጢሳዊ የስበት ኃይል እንዳላት አንተ አታውቅም ይሆናል። በዚህ ምድር ላይ የተዘራ ማንኛውም ነገር እንዲሁ ወድቆ የሚቀር ላይሆን ይችላል።

መልካም ገበሬ ለነፍሱም ለቤተሰቦቹም ብሎም ለሃገር ለህዝብ የሚተርፍ ዘር ዘርቶ ፍሬውን ይመግባል።  በየትኛውም የህይወት ሜዳ ላይ የሚገኝ እያንዳንዱ ግለሰብ መልካም ገበሬ ለመሆን የሚያግደው የለም።

ሁሌም በጎ በጎውን ማሰብ ስትለማመድ መልካም ገበሬ ትሆናለህ።  ከራስህ አልፎ ተርፎ ለሌላው የሚጠቅም መልካም ሐሳብ ወደ ዓለም ብትልክ መልካምነት ዞሮ ይከፍልሃል። ብድራቱን ታገኛለህ። የጣልከው አልያም ያካፈልከው ሁሉ መልሶ ብድራቱን ይከፍልሃልም። …መልካም መሆን ኪሳራ ከሌለው ክፉ መሆን ምንም ትርፍ የለውም። … ወዲህም ባንተ ላይ እንዲሆንየማትፈልገውን ነገር በሌላው ላይ አታድርግ። …ፍቅር ትሻ እንደሆን ፥ ቀድመህ አንተ ፍቅር ስጥ።  ያልሰጡትን ለማግኘት ማሰብ ፥ ስንዴ ዘርቶ የጤፍ ምርት እንደመጠበቅ እንዳይሆን። … ከመስተዋት የተሰራ ቤት ውስጥ የሚኖር ሰው ከቤቱ ሆኖ  ወደ ውጭ ድንጋይ መወርወር የለበትም። 

ጋን በጠጠር ይደገፋል እንዲሉ ፤ እያንዳንዱ ሰው በሌላው ህይወት በቀጥታም ይሆን በተዘዋዋሪ  ተፅእኖ ማሳደሩ ህገ-ተፈጥሮ ነው።አይመለከተኝም፥ አይደርስብኝም የምትለው ነገር ላይሆን ይችላል። … ጉንፋን የያዘው ሰው አጠገብህ ተቀምጦ ቫዮረሱ አንተ ዘንድ እንዳይደርስ ለማድረግ አትችልም። በአንድም በሌላ መልክ ኢንተርአክሽን ይኖራል።

            ውብ ምሽት
@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot