Get Mystery Box with random crypto!

ስብዕናችን #Humanity

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiohumanity — ስብዕናችን #Humanity
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiohumanity — ስብዕናችን #Humanity
የሰርጥ አድራሻ: @ethiohumanity
ምድቦች: ሳይኮሎጂ
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 30.61K
የሰርጥ መግለጫ

🔆እየጠየቁ መኖር መልስን፣
መልስን ፈልጎ ማግኘት ዕውቀትን፣
እውቀት ነፃነትን፣ ነፃነት ሙሉ ስብዕናን፣
ሙሉ ስብዕና ሠላምና እርካታን፣
እርካታ ደግሞ ደስተኛ ሆኖ መኖርን ያስገኛል፡፡
አብረን እንደግ !!
@EthioHumanity @Ethiohumanity
✍የተሰማቹን አጋሩን! ቤቱ ሁሌም ክፍት ነው፣ሃሳባቹን ፃፍፍ አርጉልን @EthioHumanitybot

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 13

2022-10-09 11:52:55 ሰብዓዊነት የገዘፈበት የፍትህ ኮከብ!

ምንም እንኳን የአርጀንቲናዊ ተወላጅ ቢሆንም እሱ ለኔ ሐገር አልባ የዓለም ነው። እሱ ብዙ ነው ፊዚስት፣ፀሀፊ፣አስተማሪ፣ዲፕሎማት፣
የጦርሀይል አዛዥ እና የመብት ተሟጋች ነው ። ይህ ሰው ማነው ስመ ገናናው ዓለማቀፋዊው የነጻነት ፋኖ ተዋጊ .....ኤርኔስቶ ቼ ጉቬራ
ያላደለው በቀበሌ ፤ በወረዳ ፤በብሄር ፤በሃይማኖት ተሰባጣጥሮ በጎጥ ተተብትቦ ይጣመዳል ይቧቀሳል የኔ ጀግና ኤርኔስቶ ቼ ጉቬራ ለዘመዶቹ ለሰው ልጆች ዘብ ይቆማል ይህ ሰው ቅዱስ ነው።ቅድስና ማለት ህይወትቱን ሙሉ ለሰው ልጆች ነፃነት መታገል ብሎም አንድያ ነፍሱን መገበር አይደለምን ?ካለምንም ስስት ማንነትን ዘርን ሳይቆጥር ሰው መሆን ክብር ነው ብሎ ለሰው ልጆች ነፃነትን ሊለግስ አቅም አልባዎችን አለሁላቹ እሚል ለኔ ይህ አለማቀፍ የነፃነት አርበኛ ቅዱሴ ነው።

ዓለም ህዝቦቿ ሁሉም ሰዎች በእኩልነት እና በሰላም ይኖሩ ዘንድ ለማየት ተመኘ
ህልሙንም እውን ለማድረግ ጣረ ይህ ክንፍ አልባ በምድር የተመላለሰ መልአክ ነው።
እውነተኛ ኮሚኒስት ነው ኮሚንዝም የአለም ማህበረሰብን ወደፊት እሚያስጉዝ እና አዲስ
ማህበረሰብን ለመፍጠር ያስችላል ብሎ ለሰው ልጆች እኩልነት ለማምጣት ከጨቋኞች ጋ ታገለ ማን ?....ዶክተር ኤርኔስቶ ቼ ጉቬራ የአለም ሰዎች በሰላም የመኖር እና ያለመኖር እጣ ፈንታ በልእለ ሃያል አገሮች መውደቅ ፍትሃዊነት የገደለው ነው ያለው ኤርኔስቶ ቼ ጉቬራ ወደ ሰሜን አፍሪካ አቀና በአልጄርያ እርእሰ ከተማ በአልጀርስ ንግግር አደረገ ቋንቋው ሁሉ ጭቆና ፤ ግፍ ፤በደል ይቁም ነው ።

ይህ ፍትሃዊ የፍትህ ተወርዋሪ ኮኮብ
በምድር እነሆ ላይፈዝ በሰው ልቦች ደሞቆ እና ህያው ሆኖ አልፏል።

# ስለአለማቀፍ ! ስለ ሰውነት ጥግ ሳስብ አእምሮዬን ላይ ድቅን የሚልበኝ አንድ ሰው
ነው. ....Che Guevara ገፁ ሰውነትን የሚያገዝፍልኝ አርማ ነው!!! አለማቀፋዊነት ዜማ የሚያቀነቅን ሰንደቄ አድራጓቱ ከመረዳት አቅም በላይ ጥልቅ የሰውነት ትርጉምን ተሸክሞል።
ህልመኛም ጭምር ነው 1956 ስምንት ሆነው ከሜክሲኮ ተነስተው የገዜው አንባገነኑን
የባቲስታ መንግሥት ለመገልበጥ ወደ ኩባ አቀኑ ለስምንት በኩባ ጫካዎችም የጉሬላ ውጊያ ጀመሩ አምባገነኑ የባቲስታ መንግሥት የመጣል ትግሉም ቼ ወሳኝ ሚና ተጫውቶ በድል
ተጠናቀቀ።

ይህ ጀግናዬ ማለም ብቻ ሳይሆን መተግበርም ይችልበታል።በተተኪው የካስትሮ አስተዳደርም የካስትሮ ቀኝ እጅ ሆኖ እስከ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴርነት ድረስ ላልወለደው የኩባ ህዝብ አገለገለ።ምከንያት እሱ ዘመዶቹ የሰው ልጆች ናቸውና ።ቼኮ ከጨቋኝ ሃያላን ጋ ሲታገል ከተጨቆኝ ጋ ሲያብር ኖሯል የእውነት!!እንደምን ሰው ከተሸናፊ ጋር በፍቅር ይወድቃል ??
ቼ!! መለክያው እኩልነት ነበር ተጨቆኝና ጨቆኝ የሌለበት ምድር ለመፍጠር ።
ዛሬ የERNESTO CHE GUEVERA መፅሀፍ በአሜሪካ ሳይቀር በአለም መፅሀፍት ቤቶች
ይገኛል የቼ ምስል ያረፈበት ሰአቶችን ቲሸርቶች በሺዎች ይቸበቸባሉ የላቲን አሜሪካ ተማሪዎች ጠዋት ጠዋት እንደ ብሄራዊ መዝሙር ቼ እንወድሀለን ቼ አንተን እንወርስሀለን
እያሉ ያዜማሉ።

ቼ የፍትህ ተወርዋሪ ኮኮብ ነው !!


ልክ የዛሬ 55 አመት! በዛሬው ቀን የፍትህ ቀንዲል፤ የጭቁኖች አባት፤ የአርነት አርማ ቼ! ወደቀ።

ለገንዘብ በተገዙ ሴረኞች፤ ነፃነትን በጥቅም በሸጡ መደዴዎች፤ በደል በእጃቸው በተነባበረ ወለፈንዲዎች ቼ ከሞተ ድፍን 55 አመት።

ቼ ሰው ነበር! የሰውነት ውሀ ልክ ነበር። ከራስ ይልቅ ለሰው መኖርን፤ መስዋዕትነትን እና ፍቅርን አስተምሯል!
°°
Your eternal flame
Has shown us the light of dawn
[ማሪያ ማኬባ - አሉታ ኮንቲኒዋ]
°°
You can kill a revolutionary but you can't kill the revolution.
Aluta Continua
°°
55th anvarsary day of the heroic Guerrilla.
Che ♡

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity
945 views08:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-09 11:51:18
925 views08:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-08 08:58:38 ለቅዳሚታችን!


ምርጥ 50 ፊልሞች ከዓለም ዙሪያ
============================

ከዚህ በታች ያስቀመጥኳቸው 50 ፊልሞች (movies) በተለያዩ ወቅቶች ተመልክቼያቸው እጅግ ግሩም ቁምነገር ያገኘሁባቸው፣ ያዝናኑኝና፣ ለየት ብለው ያስደመሙኝ ምርጥ ፊልሞች ናቸው።

ምርጥ የምላቸውን ፊልሞች ሳካፍል ይህ ለ3ኛ ጊዜ ነው። ፊልም የማየት ፍቅሩና የተመቻቸ አጋጣሚው ያላችሁ፣ እነዚህን ፊልሞች ጊዜ ሰጥታችሁ ተመልከቷቸው።

በበኩሌ ፊልሞች ከመፅሐፎች ባልተናነሰ ብዙ ግርምትንና ትምህርትን ይሰጡኛል። ከፊልሞች ተለይቼ አላውቅም። እና ዓለምን ካጥለቀለቁ ከሺህዎች መሐል አይተን ያደነቅናቸውን ምርጦቹን እየቀዳን እንካፈል።

አሉኝ የምትሏቸው ምርጥ ፊልሞች ካሉ በcomment ላይ አክሉልኝ። ቀጣዩ 4ኛ ዙር የምርጥ ፊልሞች ዝርዝር ደግሞ ከተወሰኑ ሳምንታት በኋላ ይቀጥላል።

በተለየ ለማስታወስ ያህል፦ እንደ ከዚህ በፊቶቹ የፊልም ዝርዝሮቼ ሁሉ፣ በዚህ በ3ኛው ዙር ዝርዝር ውስጥም ሶስት የአማርኛ ሙቪዎች ተካተዋል። ከሶስቱም ላይ የተለየ ግሩም ለዛ አግኝቼባቸዋለሁ።

Lucy የሚለው ድንቅ የmind evolution ፅንሰ ሀሳብ ይዞ የተነሳው ፊልምም መነሻውና መድረሻው የእኛዋ ሉሲ (ድንቅነሽ) ነች። የሀገርኛዎቹንም ሌሎቹንም ልክ እንደ እኔ ያያቸው ሰው ሁሉ አድናቆቱን ሳይቸራቸው እንደማያልፍ፣ የኳኮሜዲ ይዘት ባላቸውም ፈገግ ሳይል እንደማይጨርስ እርግጠኛ ነኝ።

እስቲ ለማንኛውም አረፍ እንበል። እና በፊልሞቻችን ዘና እያልን መንፈሳችንን እናዝናና። እንደነቅ። እና ራሳችንን በሌሎች ተሞክሮ እናበልፅግ።

መልካም የዕረፍት ቀናት ለሁላችን በያለንበት ይሆንልን ዘንድ ተመኘሁ። ፊልሞቹ እነዚሁና፦

1) A Beautiful Mind (2001)
2) A Fortunate Man (2018)
3) A Thin Red Line (2014)
4) Cold Mountain (2003)
5) Darkest Hour (2017)
6) Defiance (2008)
7) Emperor (2012)
8) First They Killed My Father (2017)
9) Free State of Jones (2016)
10) Glory (1989)
11) Green Book (2018)
12) In Love and War (1996)
13) In the Land of Blood and Honey (2011)
14) Léon: the Professional (1994)
15) La Borena (ላ ቦረና) (2013)
16) Lucy (2014)
17) Milada (2017)
18) Mission of Honor (2018)
19) Mosul (2020)
20) No Direction Home: Bob Dylan (2005)
21) Official Secrets (2019)
22) On the Basis of Sex (2018)
23) On the Road to Berlin (2015)
24) Rebuni (ረቡኒ) (2014)
25) Riphagen the Untouchable (2016)
26) Road Trip (2000)
27) Schindler's List (1993)
28) Second in Command (2006)
29) Selma (2015)
30) The Angel (2018)
31) The Aviator (2004)
32) The Butler (2013)
33) The Devil's Mistress (2016)
34) The Dig (2021)
35) The Exception (2016)
36) The Great Debaters (2007)
37) The Green Mile (1999)
38) The Guernsey Literary & Potato Peel Pie Society (2018)
39) The Notebook (2004)
40) The Photographer of Mauthausen (2018)
41) The Railway Man (2013)
42) The Theory of Everything (2014)
43) The Two Popes (2019)
44) The Wolf's Call (2019)
45) The Zookeeper's Wife (2017)
46) Wonder (2017)
47) Yearbegnaw Lij (የአርበኛው ልጅ) (2015)
48) You Don't Mess with the Zohan (2008)
49) 12 Years a Slave (2013)
50) 22 July (2018)


ሸጋ ቅዳሚት!

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity
1.6K viewsedited  05:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-08 08:57:48
1.5K views05:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-07 21:51:38
እኔ ነኝ ተጠያቂው በል

ለምታገኘው ደስታም ሆነ ለሚደርስብህ ችግር ተጠያቂው አንተና አንተ ብቻ ነህ ማንም ላንተ ህይወት ሃላፊነቱን አይወስድም...

የራስህን ገነት የምትገነባውም ሆነ እራስህን በገሃነም እሳት የምትጥለው አንተ እና አንተ ብቻ ነህ ።

ውብ አሁን

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@Ethiohumanitybot
2.5K viewsedited  18:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-06 23:36:12 ድሬዳዋ የሚኖር ሰው ካለ እዚህ ቻናል ውስጥ ሊተባበረኝ የሚችል ፍቃደኛ ካለ በዚህ ሊንክ ቢያወራኝ @Nagayta
1.4K viewsedited  20:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-05 21:46:59
Invest in yourself

" ለሰው ልጅ ሁሉ እኩልና ያለስስት የተሰጠ ሀብት ቢኖር ጊዜ ነው ። ጊዜህን መጠቀም ስትችል እራስህን ትለውጥበታለህ...ራሥህን መለወጥ ሥትችል ሌሎችንም ትለውጣለህ ። ራስህን ለመለወጥ ጊዜን ካልወሰድህ ሌላን መለወጥ አትችልም ። ( Invest in your self )ራስህ ላይ ፈሰስ አድርግ መጀመርያ ራስህን ለውጥ ።

አስተሳሰብህን ሞርድ ፣ እይታህን አጥራ ፣ ንግግርና እርምጃህን ገምግም ነገ የሚኖርህ ዛሬን ስትጠቀምበት ነው ። ከዛሬም ያለህ ጊዜ አሁን ነው...አሁን ደግሞ እያለፈ ነው! ጥያቄው እንዴት እያለፈ ነው የሚለው ነው ። ለዚህ ጥያቄ የምትመልሰው መልስ #ነገ በምትለው ምናባዊው ቀን ላይ ያለህን አንተነት ይወስነዋል ። "

ዛሬህን ተጠቀምበት...

ዉብ አዳር
@EthioHumanity
@EthioHumanity
986 views18:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-05 07:13:06 የሴት የቦንዳ ልብሶችን በቅናሽ ዋጋ መረከብ የሚፈልግ ካለ ከታች ባለው ሊንክ ማናገር ይችላል።

@Selina_3ts
1.2K views04:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-30 23:20:58
Baga ittiin isin gahe, nu gahe !
እንኳን አደረሳችሁ፤ አደረሰን !

Ayyaana Gaarii !
መልካም በዓል !
#Irreecha2015
2.4K views20:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-30 09:30:58
ለጁምኣችን!


'ጦርነት' ማለት ምን ማለት ነው? (እውነተኛ ፍቺው?)

ጦርነት ማለት፦

"አሳምረው የሚተዋወቁ፣ የሚጠላሉና ቅራኔያቸውን በሠላም መፍታት ያልቻሉ፣ ዕድሜያቸውን ያመነዠኩ ሰዎች - የማይተዋወቀውን፣ የማይጠላላውንና ቅራኔውን በሠላም ለመፍታት የማይገደውን ወጣት፣ በሠላም ከተቀመጠበት ከሞቀ ቤቱ ጠርተው፣ እርስበርሱ የሚያጨፋጭፉበት የተረገመ መንገድ ነው"

"War is an abominable situation in which old people, who knew each other, hate each other, and failed to solve their problems peacefully, would drag the young people, who do not know each other, who do not hate each other, and who are willing to make peace with each other, to kill each other."

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity
3.3K views06:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ