Get Mystery Box with random crypto!

ስብዕናችን #Humanity

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiohumanity — ስብዕናችን #Humanity
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiohumanity — ስብዕናችን #Humanity
የሰርጥ አድራሻ: @ethiohumanity
ምድቦች: ሳይኮሎጂ
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 30.61K
የሰርጥ መግለጫ

🔆እየጠየቁ መኖር መልስን፣
መልስን ፈልጎ ማግኘት ዕውቀትን፣
እውቀት ነፃነትን፣ ነፃነት ሙሉ ስብዕናን፣
ሙሉ ስብዕና ሠላምና እርካታን፣
እርካታ ደግሞ ደስተኛ ሆኖ መኖርን ያስገኛል፡፡
አብረን እንደግ !!
@EthioHumanity @Ethiohumanity
✍የተሰማቹን አጋሩን! ቤቱ ሁሌም ክፍት ነው፣ሃሳባቹን ፃፍፍ አርጉልን @EthioHumanitybot

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 12

2022-10-22 14:42:02
ከተለመደው ወጣ በሉ!

አብዛኛው ሰው ለገጠመኙ የሚሰጠውን ምላሽ አትከተሉ፡፡ ከተለመደው ወጣ በሉ! ለየት በሉ!

ድክም ሲላችሁ ተስፋ መቁረጥን ሳይሆን ማረፍን ልመዱ፡፡

ሰዎች ትተዋችሁ ሲሄዱ እነሱን ሲከታተሉ መጦዝን ሳይሆን ለብቻችሁ ጊዜን መውሰድን ልመዱ፡፡

•  ስሜታችሁ ሲረበሽ “ለምን ስሜቴ ተረበሸ” ብላችሁ የበለጠ መረበሽን ሳይሆን ተረጋግታችሁ መንስኤውንና መፍትሄውን ማግኘትን ልመዱ፣ ስትሳሳቱ ራስን መውቀስና በጸጸት ታስሮ መኖርን ሳይሆን ራስን ይቅር በማለትና ከሁኔታው ትምህርትን በማግኘት እንደገና መሞከርን ልመዱ፡፡

አብዛኛውን ግዜ ሰዎች የሚረበሹት በሚያጋጥማቸው ችግር እውነተኛ ባህሪ ሳይሆን ለችግሩ በሰጡት የስሜት ትርጉም የተነሳ ነው ። ዋናው ችግር በሕይወትህ የሚያጋጥምህ ችግር ሳይሆን ስለችግሩ የምትሰጠው ስሜት ነው ። በሕይወትህ የሚያጋጥሙህ ችግሮች ሁሉ እውነተኛ ክስተቶች አይደሉም ።

አብዛኞቹ የስሜትህ ሁኔታ ናቸው ። ትልቁ ችግር ከክስተቶቹ በመነሳት በራስህ ስሜት የምትፈጥራቸው ችግሮች ናቸው ። "

በሁኔታዎች አትወሰዱ! ከሁኔታዎች ውስጥ መልካም ነገርን መውጣት ልመዱ! ይለመዳል!

ዶ/ር እዮብ ማሞ

ውብ ቅዳሜ
@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot
6.7K views11:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-19 20:07:25 እናንት ሁላችሁም፣ አንድ ላይ፣ የሕይወት ዛፍ ናችሁ፡፡ እናም ራሳችሁን ከመከፋፈል ተጠበቁ፡፡ ፍሬን ከፍሬ፣ ቅጠልን ከቅጠል፣ ቅርንጫፍን ከቅርንጫፍ አታስበልጡ፡፡ ግንዱን ከሥሮቹ፣ ዛፉን ከእናት አፈሩ ለይታችሁ አትውደዱ፡፡ ይህ ደግሞ … በዕርግጥም … አንዱን ከሌላኛው አስበልጦ፣ ሲከፋም ለይቶ ስትወድዱ የምታደርጉት ነው፡፡

አዎን … እናንት ሁላችሁም … አንድ ላይ … የሕይወት ዛፍ ናችሁ፡፡

ሥራችሁም የትም ነው፡፡ ቅርንጫፍና ቅጠሎቻችሁም በሁሉም ስፍራ፣ ፍሬዎቻችሁም በሁሉም አፍ ውስጥ ! በዛ ዛፍ ላይ ያለው የትኛውም ፍሬ፣ የትኛውም ቅርንጫፍ ሆነ ቅጠል፣ የትኛውም ሥሮች ይሁን ፍሬ፣ የእናንተው ፍሬ፣ የእናንተው ቅጠልና ቅርንጫፍ፣ የእናንተው ሥር ነው፡፡

ዛፉ ጣፋጭና ባለማራኪ መዓዛ ፍሬ ሲቸራችሁ ብታዩ፣ ጠንካራ እና ፍፁም አረንጓዴ ሆኖ ብታገኙት … ሥሮቹን ወደመገበው የሕይወት ወለላ አስተውሉ፡፡

ፍቅር የሕይወት ወለላ ነው፡፡ ጥላቻ ደግሞ የሞት መግል፡፡ ፍቅር ግን ልክ እንደ ደም ሳይታጎልና ሳይገደብ በሕይወት ሥሮች ውስጥ ሊፈስስ ይገባዋል፡፡ የደም ፍሰት መገደብ በሽታ እንደሚሆነው ጥላቻም እንዲሁ የተገደበ ወይም የታፈነ ፍቅር ነው፡፡ የታፈነ ፍቅር መመረዝ ደግሞ ጠይውንም ተጠይውንም፣ ሁለቱንም ይመርዛል፡፡

በሕይወት ዛፍ ላይ ያለች አንዲት ቢጫ ቅጠል ሌላም ሳትሆን ፍቅር የተነፈገች ቅጠል ነች፡፡ እናም ቢጫዋን ቅጠል አትውቀሷት፡፡ ተገንጥሎ የተዘነጠፈው ቅርንጫፍም ፍቅር የተራበ ቅርንጫፍ ነው፡፡ የተዘነጠፈውን ቅርንጫፍ አትርገሙት፡፡ መራራውም ፍሬ ቢሆን ሌላም ሳይሆን ጥላቻ የመረዘው ነውና አትኮንኑት፡፡ ይልቁንም የሕይወትን ወለላ፣ የፍቅርን በረከት ለጥቂቶች ብቻ አዝንቦ ለብዙዎች የነፈገውን፣ በዚህም ራሱን የካደውን፣ የታወረውን የራሳችሁን ተናዳፊ ልብ ውቀሱ፡፡

በልባችሁ ውስጥ የጥላቻ ዘር እስካለ ድረስ የፍቅርን ሐሴት አታውቋትም፡፡ የሕይወት ወለላን ለሁሉም መግባችሁ ለአንዲት ቅንጣት ነፍሳት ብትነፍጉ ያቺ የተነፈገችዋ ሕይወታችሁን ታመርረዋለች፡፡ የቱንም ወይንም ማንንም ስትወዱ እንደ እውነቱ ከሆነ የምትወዱት ራሳችሁን ነው፡፡ ስትጠሉም እንዲሁ ነው … የቱንም ወይንም ማንንም ብትጠሉ እንደ እውነቱ የምትጠሉት ራሳችሁን ነው፡፡

የምትወዱትና የምትጠሉት ልክ እንደ አንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ላይነጣጠሉ ተጣምረዋል፡፡ ለራሳችሁ ታማኝ ብትሆኑማ ኖሮ የምትወዱትንና የሚወድዳችሁን ከመውደዳችሁ በፊት የምትጠሉትንና የሚጠላችሁን ትወድዱ ነበር፣ፍቅር ቅንጦት አይደለም፡፡ ፍቅር መሰረታዊ ፍላጎት ነው፡፡ ከዳቦና ከውሃ፣ ከዓየርና ከብርሃን ይልቅ ፍቅር ያሻችኋል፡፡

ማንም ቢሆን በማፍቀሩ አይኩራራ ይልቁንም ነፃ ሆናችሁ እንዲሁ በዘፈቀደ ዓየሩን ወደ ውስጥ እንደምትስቡትና እንደምታስወጡት ሁሉ ፍቅርንም እንዲሁ በነፃነት ልብም ሳትሉ ተንፍሱት…ፍቅርን ማንም ከፍ ሊያደርገው፣ ሊቀድሰው የሚችል የለም፡፡ ይልቁንም ለፍቅር የሚገባ የተቀደሰ ልብ ሲያገኝ ፍቅር ራሱ ያን ልብ ይቀድሰዋል እንጂ፡፡

ፍቅር አያበድርም፣ አያውስምም፡፡ ፍቅር አይሸጥም፣ አይገዛምም፡፡ ሲሰጥ ግን ሁሉንም ይሰጣል፡፡ ሲወስድም ሁሉንም ይወስዳል፡፡ መቀበሉ በራሱ መስጠት ነው፡፡ መስጠቱም እንዲሁ መቀበል፡፡ እናም፣ ለዛሬ እንዲሁ እንደሆነው ሁሉ ለነገም ለከነገወዲያም እንዲሁ ነው፡፡

ራሱን ሳይሰስት ለባሕሩ የሚለግስ የትኛውም ወንዝ ዘወትር በባህሩ እንደሚሞላው ሁሉ እናንተም እንዲሁ ፍቅር መልሶ ይሞላችሁ ዘንድ ራሳችሁን አንጠፍጥፋችሁ ለፍቅር ተሰጡት፣አዎን … የባሕሩን ስጦታ ከባሕሩ የሚነፍግ ኩሬ መጨረሻው መበስበስም አይደል፡፡

በፍቅር … ትንሽ ወይም ትልቅ የሚሉት ነገር የለም፡፡ ፍቅርን መለካት፣ መመተር … ለፍቅር ደረጃ ማውጣት ስትጀምር፣ ፍቅር መራር ትዝታዎቹን አስታቅፎህ እብስ ብሎ ይጠፋል…

በፍቅር ዘንድ … ትላንት ወይም ዛሬ፣

ዛሬ ወይም ነገ…

እዚህ ወይም እዚያ ብሎ ነገር የለም፡፡

ሁሉም ወቅቶች የፍቅር ወቅቶች ናቸው፡፡ የትኛውም ቦታ ቢሆን ለፍቅር ቤተ መቅደስነት የተገባ ክቡር ነው፡፡ፍቅርን … ወሰንም ሆነ ዳር ድንበር፣ካቴናም ሆነ የተዘጋ በር አይገድበውም ፣ አዎን … ፍቅር ዓይናችሁን ሲያበራው … ያኔ … ሁሉም መልስ ፍቅር ዉስጥ እንደሚገኝ ትረዳላችሁ ፡፡

ግሩም ተበጀ
The Book of Mirdad

ውብ አሁን!!

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
7.0K views17:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-19 20:06:31
5.3K views17:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-17 21:54:38
አንዳንድ ውብ ልቦች ወደ ሕይወትህ ፍኖት ሲቀላቀሉ የቀድሞ አንተን አትሆንም... ትለያለህ... በጣም ትለያለህ!!

የሰው ሰውነቱ መታያው በልቡና ዉስጡ በሰነቀው ቅንነት ፣ ለሌላው በሚሰጠው እኩል ፍቅር ነው፡፡ይህ ልብ ውብ ነው፣ወበትንም በመላው ተፈጥሮ ላይ እነደከርቤ እጣን መአዛውን አግንኖ ያውዳል፡፡ይህ ውብ የደከመን ያበረታል፡፡ይህ ውብ ልብ ያዘነን ያፅናናል፣ይህ ውብ ልብ የወደቀን አንስቶ ያፀናል፡፡

ይህ ውብ ልብ በኑሮ ዝሎ የመጣበትን ዓላማ የዘነጋን ወደተፈጠረበት ዓላማ ይመልሰዋል፡፡ይህ ውብ ልብ ካጋጠመህ የድሮውን ቀርቶ የቅድሙን አንተ አትሆንም፡፡ይህ ውብ ልብ ይቀይርሀል፡፡ቅየራውም ለመልካም ነውና ራስህንም ውብ ያደርግሀል፡፡

ደምስ ሰይፉ

ውብ አሁን!!

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
6.3K views18:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-16 00:24:22 ሰዓት እላፊ!



አንዳንድ ነገሮች



“ሊነጋ ነው…”

በረጅሙ የጨለማ ዘመን ውስጥ ሊነጋ ነው ብለው የሰበኩን የተስፋ ነጋዴዎች ብዙ ናቸው። ይነጋ ይሆን ብለው የጓጉ ገበያተኞች በአይነትም በጠገራ ብርም ተስፋ ሲገዙ፣ በተስፋ ብርቱ ሰልፍ ተሰልፈው ከድቅድቅ ሲፋለሙ ባጅተው አልፈዋል።

ተስፋ ግን አሁንም ተፈላጊ ሸቀጥ ሆኖ ቀጥሏል። “ሊነጋ ነው” ይልሃል ጀምበሩ ደመቀ። “ሊነጋ ሲል ይጨልማል” ይልሃል ዘማሪው የአሁን ጨለማ አይርታህ ሲል። “በል በርታ ታጠቅ!” ይልሃል ሃይለ ቃል የሚያትት አፈ ቀላጢ ወቀሳጢ።

ድቅድቁ ግን አልተረታም። ነጋ ተብለን ነቅተን ነበር የዛሬ ሶስት አመት። ነጋልን እነሆ ደማቅ ጮራ ፈነጠቀ ብለን አረንጓዴ መስክና የሱፍ አበባ ልናይ ጓጉተን ተስፋ ሰነቅን። አይኖቻችንን በነጠላ ጫፍ አብሰን ብናይ ግን አይን ይወጋል ጨለማው። ከአይኖቻችን ቡኒ እዥ ፈሰሰ። ስንጨናበስ ከረምን። ተስፋ የጠበቁ አይኖች ዳፍንት ዳበረባቸው።

ተስፋ የሸጠልን ግን ከበረ።

ግድግዳዎቻችን ላይ “ሆፒንግ ኢዝ ሆፕለስ!”



አንዲት ታካሚ ለማነጋገር የተኛችበት ሄጄ ነበር። ሳይታወቀኝ ከሚገባው በላይ ተነጫነጭኩባት። እየወጣሁ ሳስበው የነበረው “ምን አድርጋኝ ነው እንዲህ የተቆናጠርኩባት?” ነበረ።

ሁሉም ሰው ይነጫነጫል ያለው። እኔም፣ ኮንሰልታንቱም፣ ሌሎች ሀኪሞችም ይቆናጠራሉ። ሆስፒታል ብቻ ሳይሆን ሁሉም ቦታ ነው። ሁሉም ሰው ነው። ምን ሆነን ነው?

ቀላል መልስ የለውም።

ወደቤቴ እያዘገምኩ እያሰብኩት ነበር።

ቀና መልስ የሚመልስ ሰው የለም። እንካ ስትለው ዓረፍተ ነገር፣ ሀይለ ቃል ይመልስልሃል ዘጠና ዘጠኝ።

መቼ ለት አንዱ ጀብራሬ መንገድ ላይ ያለምክንያት የአይን ቀለምህ አላማረኝም ብሎ ጥንብ እርኩሴን አወጣኝ። ደነቆርኩ ከስድቡ የተነሳ። ምን ሆነን ነው ይሄ ሁሉ tenderness አልኩ?

ቤቴ ስገባ አገኘሁት መልሱን።

አስቤዛ ስለመግዛት ማሰብ አለብኝ።



“Is your brain a vestigial organ?“

*insert Alfred Hitchcock's voice*

አንዱ በጥይት ጭንቅላቱን ተመትቶ መጥቶ የተጎዳውን አንጎሉን በቀዶ ህክምና ተወገደለትና ወደቤቱ ተመለሰ። debridement።

ከሳምንታት በኋላ በቀጠሮ ሲመጣ አስታማሚው “አሁንማ ተሽሎት ከበፊቱ የተሻለ ሰው ሆኗል” ብሎ ቀለደ።

አባባሉ አየር ላይ እየተንገዋለለች ቀረች።

“የተሻለ ሰው ሆኗል”፤ “አንጎሉ ጎድቶት ነበረንስ?” ፤“የማይጠቅም አንጎል ይዞ ይዞር ነበረን?”፤ “are we heading back to a fast track evolution where we don't need our frontal cortexes anymore?"

ባዮሎጂው ባያስኬድም አነዋወራችን ግን ይናገራል። የማንጠቀምበት የአንጎል ሸክም ግንባራችን ስር አለ።

አንቱ፥ ማጣፊያ አጥሮዎ ተቸግረዋል? እንኪያስ አንጎልዎን ያስቀንሱት። ህይወትዎን በተሻለ ያጣጥሙ።



“በሰማይ ላም አለኝ። በሬም ጭምር። ቤትና መኪናም። ድራፍት በማድጋ እጠጣለሁ፣ የተገኘውን ሁላ ፋክ አደርጋለሁ።”

— ወድቆ የተገኘ ዋሌት ውስጥ የነበረ ህልም።

yo Na

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity
@Nagayta
6.7K views21:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-16 00:22:45
4.9K views21:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-15 16:25:56 አንድ ዓይነት አስተሳሰብ እንዲኖር ከመጠበቅ ድርቅና ይልቅ መልካም አስተሳሰብ እንዲበዛ የመመኘቱ የዋህነት የበለጠ ይጠቅመን ይመስለኛል... በዚያው ልክ 'ልዩነትን' ከምንገልጽበት ስድብ ይልቅ ግንዛቤያችንን የምናኖርበት ስልጡን መንገድ ለአብሮ መኖር ትልማችን ብዙ ያዋጣ ይሆናል

ያልተዋጠልህ ነገር እንዳለ ስትገልጽ ሌሎች ያጣጣሙትን እንዲተፉልህ እየጠየቅህ ከሆነ በጎ አይደለም... አንተ ስትለው ትክክል ሌሎች ሲሉት ስህተት የሚባል ነገርም ያስተዛዝባል  ፣ ሁሉም ሰው ምንም የማለት ሰዋዊ ችሮታው ቢከበርለት እሻለሁ... "ዘንግህን ማወዛወዝ የምትችለው የሌሎችን አፍንጫ እስካልነካህ ድረስ ነው" የምትለው ደገኛ መርህ ብትጠበቅም ደስ ይለኛል... የማቻቻል ጉዳይ ነው.

The common ground of our humanity is greater and more enduring than the differences that divide us. It is so, and it must be so, because we share the same fateful human condition. We are creatures of blood and bone, idealism and suffering. Though we differ across cultures and faiths, and though history has divided rich from poor, free from un-free, powerful from powerless, and race from race, we are still all branches on the same tree of humanity". ~ Nelson Mandela

በጣም የሚያሳስበኝ ግን የ Common Ground እጦት ነው... እንዴት ሰው የጋራ አካፋይ ያጣል?... ስለምንስ በጋራ የሚቆምለትን ነገር ይሰዋል?... በየታዛህ ብትሸጎጥም ጉርብትና የምታጠነክርበትን ፈለግ ትሰራለህ እኮ... የቀዬው ሳር፣ ወንዙ፣ መስኩ ሁላ ለከብቶችህ ብቻ አይደለም... ለከብቶቻቸውም መድኅን ነው... አንድ ዓይነት ሐይማኖት ባትከተሉ መንፈሳዊነት አንድነታችሁ ነው... አንድ ቋንቋ ባይኖራችሁ ሰው መሆን የጋራችሁ ነው... የተለያዩ የብሔር ስያሜዎች ብትይዙ ዜግነት ንብረታችሁ ነው... "ልዩነት" የማይቋጠርበት ገመድ የለም!!!

የእኔና ያንት ገዢ መሬት /common ground/ ሰውነት ይባላል፡፡
ህግ የምናወጣውም፤ ህግ የምንሽረውም እሱ ላይ ቆመን ነው፡፡ ክፋት፣ ደግነት፣ ትክክል፣ ስህተት፣ ተበዳይ፣ በዳይ የምንባባለውም እሱ ላይ ቆመን ነው፡፡ ወደድንም ጠላንም፤ ከሳንም፣ ወፈርንም ሁላችንም ሰው በሚባል ቁና እኩል ተሰፍረናል፡፡

እስኪ እየሆነ ያለውን እንመርምር... የንፋሱን ከየት ወዴት እንፈትሽ... እያዋጣን ያለነውን ነገር እንጠይቅ... ምንም ከማለታችን በፊት ግን እንዲመጣ ለምንፈልገው በጎ ነገር ያለውን አስተዋጽዎ እንመዝን።

          ውብ ቅዳሜ

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
5.8K viewsedited  13:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-15 16:25:46
4.7K viewsedited  13:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-14 21:12:39
ለቤትዎ ለቢሮ እንዲሁም ለስጦታ የሚሆኑ የግድግዳ ምስሎች

- የቤቶን ውበት በዕጅጉ የሚጨምሩ
- የፎቶ ጥራታቸው HD የሆኑ
- ጠንካራ ወጥ MDF እንጨት ላይ የሚሰሩ
- መወልወል በሚችል ማቴሪያል ላሚኔት የተደረጉ
- ለሳሎን ፣ ለመኝታ ቤት እንዲሁም ለቢሮ የሚሆኑ
- ለወዳጅ ዘመድ እንደ ስጦታነት የሚሆኑ
- በራሶ ፎቶ መሰራት የሚችሉ

1 ሜትር ከ 50 ሴሜ በ 90 ሴሜ = 3000 ብር

የግድግዳ ምስሎቹን አሁኑኑ በሚፈልጉት ዲዛይን ይዘዙን በ 2 ቀን ውስጥ ሰርተን ያሉበት ድረስ አምጥትን እንገጥማለን፡፡

ብዙዋች ወደውታል እርሶም ይሞክሩት

ለማዘዝ ከፈለጉ በቴሌግራም ያናግሩን
t.me/natnaeladane

ወይም ይደውሉ
0922490744
5.7K views18:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-09 22:23:03
ዛሬ ከእንቅልፋችን ስንነሳ ብዙም አልተደነቅንም ነገር ግን እንዳሸለቡ በዛው የቀሩም አሉ !

ዛሬ ከዋልንበት በሰላም ወደቤታችን ስንገባ ብዙም አልተደነቅንም ነገር ግን እንደወጡ በዛው የቀሩም አሉ ! ዛሬ ሳናዝን መዋላችን ምንም አልደነቅንም ነገር ግን ሌሎች የሚወዱትን አጥተው ያዘኑ አሉ

እንደው ህይወታችንን ለደቂቃ ብናስተውል ከምንማረርባቸው ነገሮች ይልቅ ልናመሰግንባቸውየሚገባን ብዙ መልካም ነገሮች አሉ። ፤

ከጎደለን ነገር ይልቅ ያለንን እንይ። በሰላም ውሎ በሰላም ማደር እጅግ ትልቅ ነገር ነው። ነግቶ ለአዲስ ቀን መታጨት ደግሞ ትልቅ እድል ምክንያቱም አዲስ ቀን አዲስ ህይወት ነውና። ፤በአለም ላይ በየሰአቱ ለአዲስ ቀን የማይታደሉ ሞልተዋል። :

እናም አዲስ ቀን እንድናይ ስለተፈቀደልን ብቻ ትልቅ ምስጋና ይገባል።አመስጋኝ ነፍስ በስጦታዎች ትሞላለችና ፣ ሁልም በፈጣሪህ ደስ ይበልህ!

            ውብ አሁን!!

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
1.6K viewsedited  19:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ