Get Mystery Box with random crypto!

አንዳንድ ውብ ልቦች ወደ ሕይወትህ ፍኖት ሲቀላቀሉ የቀድሞ አንተን አትሆንም... ትለያለህ... በጣ | ስብዕናችን #Humanity

አንዳንድ ውብ ልቦች ወደ ሕይወትህ ፍኖት ሲቀላቀሉ የቀድሞ አንተን አትሆንም... ትለያለህ... በጣም ትለያለህ!!

የሰው ሰውነቱ መታያው በልቡና ዉስጡ በሰነቀው ቅንነት ፣ ለሌላው በሚሰጠው እኩል ፍቅር ነው፡፡ይህ ልብ ውብ ነው፣ወበትንም በመላው ተፈጥሮ ላይ እነደከርቤ እጣን መአዛውን አግንኖ ያውዳል፡፡ይህ ውብ የደከመን ያበረታል፡፡ይህ ውብ ልብ ያዘነን ያፅናናል፣ይህ ውብ ልብ የወደቀን አንስቶ ያፀናል፡፡

ይህ ውብ ልብ በኑሮ ዝሎ የመጣበትን ዓላማ የዘነጋን ወደተፈጠረበት ዓላማ ይመልሰዋል፡፡ይህ ውብ ልብ ካጋጠመህ የድሮውን ቀርቶ የቅድሙን አንተ አትሆንም፡፡ይህ ውብ ልብ ይቀይርሀል፡፡ቅየራውም ለመልካም ነውና ራስህንም ውብ ያደርግሀል፡፡

ደምስ ሰይፉ

ውብ አሁን!!

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot