Get Mystery Box with random crypto!

አንድ ዓይነት አስተሳሰብ እንዲኖር ከመጠበቅ ድርቅና ይልቅ መልካም አስተሳሰብ እንዲበዛ የመመኘቱ የ | ስብዕናችን #Humanity

አንድ ዓይነት አስተሳሰብ እንዲኖር ከመጠበቅ ድርቅና ይልቅ መልካም አስተሳሰብ እንዲበዛ የመመኘቱ የዋህነት የበለጠ ይጠቅመን ይመስለኛል... በዚያው ልክ 'ልዩነትን' ከምንገልጽበት ስድብ ይልቅ ግንዛቤያችንን የምናኖርበት ስልጡን መንገድ ለአብሮ መኖር ትልማችን ብዙ ያዋጣ ይሆናል

ያልተዋጠልህ ነገር እንዳለ ስትገልጽ ሌሎች ያጣጣሙትን እንዲተፉልህ እየጠየቅህ ከሆነ በጎ አይደለም... አንተ ስትለው ትክክል ሌሎች ሲሉት ስህተት የሚባል ነገርም ያስተዛዝባል  ፣ ሁሉም ሰው ምንም የማለት ሰዋዊ ችሮታው ቢከበርለት እሻለሁ... "ዘንግህን ማወዛወዝ የምትችለው የሌሎችን አፍንጫ እስካልነካህ ድረስ ነው" የምትለው ደገኛ መርህ ብትጠበቅም ደስ ይለኛል... የማቻቻል ጉዳይ ነው.

The common ground of our humanity is greater and more enduring than the differences that divide us. It is so, and it must be so, because we share the same fateful human condition. We are creatures of blood and bone, idealism and suffering. Though we differ across cultures and faiths, and though history has divided rich from poor, free from un-free, powerful from powerless, and race from race, we are still all branches on the same tree of humanity". ~ Nelson Mandela

በጣም የሚያሳስበኝ ግን የ Common Ground እጦት ነው... እንዴት ሰው የጋራ አካፋይ ያጣል?... ስለምንስ በጋራ የሚቆምለትን ነገር ይሰዋል?... በየታዛህ ብትሸጎጥም ጉርብትና የምታጠነክርበትን ፈለግ ትሰራለህ እኮ... የቀዬው ሳር፣ ወንዙ፣ መስኩ ሁላ ለከብቶችህ ብቻ አይደለም... ለከብቶቻቸውም መድኅን ነው... አንድ ዓይነት ሐይማኖት ባትከተሉ መንፈሳዊነት አንድነታችሁ ነው... አንድ ቋንቋ ባይኖራችሁ ሰው መሆን የጋራችሁ ነው... የተለያዩ የብሔር ስያሜዎች ብትይዙ ዜግነት ንብረታችሁ ነው... "ልዩነት" የማይቋጠርበት ገመድ የለም!!!

የእኔና ያንት ገዢ መሬት /common ground/ ሰውነት ይባላል፡፡
ህግ የምናወጣውም፤ ህግ የምንሽረውም እሱ ላይ ቆመን ነው፡፡ ክፋት፣ ደግነት፣ ትክክል፣ ስህተት፣ ተበዳይ፣ በዳይ የምንባባለውም እሱ ላይ ቆመን ነው፡፡ ወደድንም ጠላንም፤ ከሳንም፣ ወፈርንም ሁላችንም ሰው በሚባል ቁና እኩል ተሰፍረናል፡፡

እስኪ እየሆነ ያለውን እንመርምር... የንፋሱን ከየት ወዴት እንፈትሽ... እያዋጣን ያለነውን ነገር እንጠይቅ... ምንም ከማለታችን በፊት ግን እንዲመጣ ለምንፈልገው በጎ ነገር ያለውን አስተዋጽዎ እንመዝን።

          ውብ ቅዳሜ

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot