Get Mystery Box with random crypto!

ፍቅር ማለት በዚህ በምትመለከተው ጨለማ ውስጥ ከሚብለጨለጩት ቁጥር ስፍር የሌላቸው አምፓሎች መሀል | ስብዕናችን #Humanity

ፍቅር ማለት በዚህ በምትመለከተው ጨለማ ውስጥ ከሚብለጨለጩት ቁጥር ስፍር የሌላቸው አምፓሎች መሀል ፣ነፍስ አንዷን መርጣ በብርሃኗ ስትደምቅ ነው።ብርሀን ሁሉ የነፍስን ጨለማ አይገፍም ቢበዛ የራስህን ብርሃን ትፈልግ ዘንድ ያግዝህ ይሆናል።ሰው የቱንም ያህል በደማቅ ብርሀን ቢከበብ፣እውነተኛውን የራሱን ብርሃን እስካላገኘ ድረስ ነፍሱ ጨለማ ውስጥ ናት።

ፍቅርና ዝምታ መለኮታዊ ኃይሎች ናቸው።ፈጣሪን የምንፈራው ከተከታዮቹ ብዙ ጩኸት ይልቅ በጥልቅ ዝምታው ሳይሆን አይቀርም እናም በዝምታ ግርማ ሞገስ ውስጥ ባለ እውነተኛ ፍቅሩ።ዝምታን የሚያሸንፍ ጬኸት ፍቅርን የሚያንበረክክ  ብልጣ ብልጥነት የለም።   

አሌክስ አብርሀም

ውብ ምሽት !!

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot