Get Mystery Box with random crypto!

ስብዕናችን #Humanity

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiohumanity — ስብዕናችን #Humanity
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiohumanity — ስብዕናችን #Humanity
የሰርጥ አድራሻ: @ethiohumanity
ምድቦች: ሳይኮሎጂ
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 30.73K
የሰርጥ መግለጫ

🔆እየጠየቁ መኖር መልስን፣
መልስን ፈልጎ ማግኘት ዕውቀትን፣
እውቀት ነፃነትን፣ ነፃነት ሙሉ ስብዕናን፣
ሙሉ ስብዕና ሠላምና እርካታን፣
እርካታ ደግሞ ደስተኛ ሆኖ መኖርን ያስገኛል፡፡
አብረን እንደግ !!
@EthioHumanity @Ethiohumanity
✍የተሰማቹን አጋሩን! ቤቱ ሁሌም ክፍት ነው፣ሃሳባቹን ፃፍፍ አርጉልን @EthioHumanitybot

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-03-13 21:09:47
መንቃት ህይወት ነው!

የነቁት ሰዎች ለመኖር የተለየ ትርጉም አላቸው፡፡ ትርጉማቸው ንቃትን የያዘ ነው:፣ እየተነፈሳችሁ ስለሆነ እየኖራችሁ  ነው ማለት አይደለም ፤ደማችሁ እየተዘዋወረ ስለሆነ እየኖራችሁ ነው ማለት አይደለም። በህይወት የምትኖሩት የነቃችሁ ከሆናችሁ እንደሆነ ነው::

ዝም ብለህ ራስህን በተመስጦ ስታነብ ውስጠትህ ረጥቦ ሕይወትህ ይለመልማል፣ ምስጠት ማለት መታዘብ ነው፣ ይቺን ሀሳብ በቀላሉ የምታስረዳ አንድ ምሳሌ አለች። የኩሬ ውሃ ጭቃ ሞልቶት ቢደፈርስ እየነካካን አናጠራውም፣ በነካካነው ቁጥር ይበልጥ እየደፈረሰ ነው የሚመጣው። መፍትሔው ኩሬውን አለመንካት ነው፤ መፍትሔው ኩሬው ዳር ተቀምጦ የተፈጥሮን ትንግርት ማስተዋል ነው። ኩሬው ለራሱ ሲተው እየጠራ ፣ እየጠራ ይመጣና ኩልል ያለ ንፁህ፣ የተጣራ ውሃ ይሆናል።

አእምሯችን እንደ ተንጣለለው ኩሬ በሃሳብ ጭቃ ደፍርሷል።ኩሬውን እየነካካን እንደማናጠራው ሁሉ አእምሮንም በሃሳብ ጉልበት መግራት አይቻልም። ኩሬው ራሱ በራሱ እንዲጠራ እንደምንተወው ሁሉ፣ አእምሮም ንቃት ላይ እንዲደርስ፣ ከሃሳብ ግርግር አሳርፎ ለራሱ ምትሃታዊ አርምሞ መተው አለበት። በጥልቅ አሰላሳዩም ተፈጥሮ በአእምሮ ላይ የራሱን ተአምር ሲሰራ በዝምታ ተውጦ ያስተውላል። በጥልቅ ማሰላሰል ሌላ ምንም ውስብስብ ነገር የለውም፣ በአጭሩ ከሃሳብ ነፃ ሆኖ ወደ መሆን ማእቀፍ [Consciousness] መሸጋገር ነው።

እናም የተረጋጋ ታዛቢ አመለካከት ይኑራችሁ ፣ በመመሰጥ ነፃነትን እና ደስታን ታገኛላችሁ። ንቁ፣ አንፀባርቁ ፣ ተመልከቱ ነገሮችን በእርጋታ ከውኑ በመንገዱ ውስጥ ኑሩ ፣ውስጣዊ ብርሃናችሁ በራሱ ጊዜ ያድጋል፡፡

ውብ አሁን

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot
1.5K viewsedited  18:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-10 20:26:15
ገበሬዉ ሁለቱን አህያዎች አንደኛዉን ጨዉ አንደኛዉን ባዶ በርሜል ጭኖ እየሄደ ነዉ።
ወገቡ ሊቆረጥ ደርሶ የሚንገዳገደዉ የጨዉ ኩንታሎችን የተሸከመዉ አህያ: ባዶ በርሜል የያዘዉ አህያ በፍጥነት ሲጓዝ ሲመለከት ጊዜ ከችግሩ ለመዉጣት አንድ ነገር ለማድረግ
ወሰነ።

"ወንዝ አካባቢ ሲደርሱ ዉሃ ዉስጥ በመዉደቅ ሸክሙን ማቃለል!" ከጥቂት ጉዞ በኋላ ወንዝ ጋር ደረሱና ጨዉን የተሸከመዉ አህያ እንዳቀደዉ አደረገ። እቅዱ ተሳክቶለትም ዉሃዉ በኩንታሉ ዉስጥ ያለዉን ጨዉ በከፊል አጥቦ ወሰደዉ፣ከቆይታ በኋላ ከወደቀበት ሲነሳ ከገመተዉ በላይ ሸክሙ ቀለለዉ። እንደ ጓደኛዉም ዘና ብሎ በፍጥነት መሄድ ቻለ።

ይህን የተመለከተዉ በርሜል ተሸካሚ አህያ ከመጀመሪያዉ የበለጠ እንዲቀለዉ በመሻት ልክ እንደጓደኛዉ ዉሃ ዉስጥ ተዘፈቀ።ግና ከቆይታዎች በኋላ ሲነሳ ወገብ ዛላዉ ሊቆረጥ ምንም አልቀረዉም።ነገሩ የተገላቢጦሽ ሆኖ በርሜሎቹ በዉሃ ተሞልተዉ ስለነበር የጉዞዉ እጣ-ፈንታ በብርክ፣ምጥና እንፉቅቅታ ወድቆ እየተነሳ መኳተን ሆነ።

ሌላዉ የጠቀመዉና የለወጠዉ የህይወት መንገድ እኛን ላይጠቅመን ይልቁንስ ሊጎዳን ይችላልና የሌላን ሰዉ እርምጃ ከመከተላችን በፊት ምክንያትና ዉጤቱን ማመዛዘን ይገባናል! ማንኛዉም ችግር ሲገጥመን ማንኛዉንም እርምጃ ከመዉሰዳችን በፊት አዕምሯችንን ማሰራትና ቆም ብለን ማሰላሰል ካልቻልን ለነጻነት ያሰብነዉ መንገድ የባሰ ጭንቅና መከራን ሊያመጣብን ይችላል!

በእጅ ያለ ወርቅ ከመዳብ ይቆጠራል እንዲሉ እኛ ዘንድ ያለዉን ጸጋ ማየት ተስኖን ዓይናችን የባተለበትን ሩቅ ማለም የነበረንን ሊያሳጣን ይችላልና ማመስገንን እልመድ! ጭፍን ተከታይነት ለራስም ሆነ ለሌላዉም እዳ እንጂ ትርፍ የለዉም!

ውብ ምሽት

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot
2.2K views17:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-07 21:32:28 ውሎህ የት ነው?

ሕይወት ሥነ ምህዳር ነው። የሰጠኸው ነገር ተመልሶ ይመጣል።የዘራውን ታጭዳለህ የምትሰጠውን ታገኛለህ በሌሎች ውስጥ የምታየውን በአንተ ውስጥ ታገኘዋለህ ፡፡ ሕይወት ሁሌ የሰጠሀትን መልሳ ትሰጠሀለች መልካም አድርግ መልካም ታገኛለህ እንደሚባለው ሁሉ።

ውሎህ አንተን ይገልፃል መልካም ቦታ ከተገኘህ በመልካም ይገለፃል በመጥፎ ቦታ ከዋልክ እንዲሁ ይሄንን የሚገልፅ ልናስተውለው የሚገባ አንድ ተረት አለ እንዲህ ይላል:-

አንድ ቀን ዝንብና ንብ እያወሩ በወሪያቸው መሀል ዝንብ ንብን እንዲህ ስትል ጠየቀቻት
ንብ ሆይ ለምንድነው የሰው ልጆች እኔን የሚጠሉኝ? ለምንስ ነው የሚጸየፉኝ ? ቤታቸው
ስገባ ያባርሩኛል ይገድሉኛል።
የሚጠጡት ነገር ላይ ከተገኘሁ ይደፉታል የሚበሉት ነገር ላይ ካረፍኩ ያረፍኩበትን ቦታ
ያለውን እህል ቆርሰው ይጥሉታል::

አንቺን ግን እንደ እኔ አይገፉሽም እንደውም ቤታቸው ስትገቢ ይንከባከቡሻል ደግሞም
መልካም ነገርን ተስፋ በማድረግ ደስታቸው እጥፍ ነው ለምንድነው?" ስትል ዝንብ ንብን
ጥያቄዋን አቀረበች
በዚህ ጊዜ ንብ እንዲህ አለቻት
ውሎሽ የት ነው?

ሰው ጠላን፣ ገፋን፣ ናቀን እያልን እንደ ዝንቧ ጥያቄን አዝለን ከምንጓዝ ውሏችንን በደንብ እንይ ወሏችን ተመልሶ እኛነታችንን ይገልፃል ውድቀታችንን ለማረምም ይሁን ብርታታችንን ለማብዛት ውሏችንን እንቃኝ ሀሳባችን ስራችንን፣ ስራችን ውጤታችንን፣ውጤታችን እኛነታችንን ይገልጽልናልና። የሰው መንገድ ሁሉ በዓይኑ ፊት የቀናች ትመስለዋለችና፣ራስን መፈተሽ መልካምም ነውና ወሎችን የት ነው?

   ውብ አሁን

@EthioHumanity
@EthioHumanity
     
@EthioHumanitybot
1.1K views18:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-07 21:31:39
1.1K views18:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-05 20:50:01      ወዳጄ ሆይ

ያለፈ ነገር አይቀዪርም ፣ ላወቀበት ሰው ግን ያለፈው ለወደፊቱ የራሱ የሆነ ትምህርት አለው ፣ ካለፈው ነገርህ ተማር እንጅ በፍፁም አታማርር ፣ ማማረር ነገህን በጎ አያደርገውም የሰዎች ሃሳብ የአንተን ማንነትአይገልፅም ፣ማንነትህ አንተ ውስጥ ነው ያለው ፣ መልካም አድርግ ሌላውን እርሳው የሁሉም ሰው የህይወት መንገድ (ጉዞ) ይለያያል ፣ጊዜው በደረሰ ሰው ሁኔታ አትቅና ለሁሉም ጊዜ አለው ።

በራስህ ላይ አተኩር ፣ ያለህ ነገር በቂ ነው ።በሰዎች ደስታ ደስ ይበልህ ፣ ክፉ አትመኝ ፣ በሃዘናቸውም አብረህ እዘን ሲያዝኑ አትደሰት ፣ ሰው ከሆንክ የሰው ነገር ይሰማህ ፣ይህ ማለት ግን ተንኮል እየሰሩ ከሚደሰቱ ሰዎች ተደሰት ማለት አይደለም ። ሰው እያስከፋ ብሎም እየገደለ የሚደሰት አለ ፣ አንተ ከተጎዳው ሰው ጋሁን ፣ አስተውል ።

ጊዜ የማይፈውሰውና የማይቀይረው ነገር የለም አንተም ጊዜው ይቀይርህ ዘንድ ፍቀድለት ፣በተሰጠህ ጊዜ ለመልካም ነገር ሱሰኛ ሁን ። የስራ ጉዳይ ውስጥህ የሚችለውናየሚያምንበት ተሰጥኦ ምን አለህ ? ምን አይነት ስራ መስራት ትችላለህ ? አስተውል ጓደኛህን አትመልከት ፣ ትለያያላችሁ ፤አለማችን በትምህርት ብቻ ወይም በጥበባት ብቻ ወይም በተወሰኑ ዘርፎች አይደለችም እየኖረች ያለችው፣ በጣም ብዙ ነገሮች ናቸው እየደገፏት ያቆሟት ፤ አንተም ጥቂትም ብትሆን ያለህን ችሎታ አውጣው ፣ ፈልገው አጎልብተው ጀምረው ፣ "ምን ይሻለኛል ?" እያልክ አታመንታ ጊዜህ እንዳያልቅ ፣በእርግጥ ጊዜህ ሳይሆን አንተ ነህ የምታልቀው ።

አስተውል ፣ መልካም ነገር ሁሉ ከፈጣሪ መጥፎ ነገር ሁሉ ደግሞ ከሰይጣን አይደለም ፣ ፈጣሪ መጥፎን ወደ መልካም የመቀዪር ብቃት አለው ። ሰይጣንም ያጠፋህ ዘንድ መልካም የሚመስል ነገር ሊያዘጋጅልህ ይችላል ፣አስተውል ። መልካም ማሰብና መልካም መሆን መልካም ነገር እንዲገጥምህ ማመቻቸት ነው ፣ መጥፎነት ከአንተ ይራቅ ፣ ለአንተም ሆነ ለሰዎች ጉዳት እንጅ ጥቅም የለውም ።

የሰራኸውና የምትሰራው ነገር የሆነ ጊዜ ላይ ዞሮ ያገኝሃል ፣ መጥፎ ከሰራህ እንደስራህ ፣ መልካም ከሰራህም እንደዚያው ይገጥምሃል ። "ሰው የዘራውን ያጭዳል" የሚለውን አስታውስ ፣
ክፉ ነገር እየዘራህ መልካም ነገር አትጠብቅ ፣ራስህን አትሸውድ ። ጤፍ ዘርተህ ባቄላ አትጠብቅ ። ጤፍ የዘራ ገበሬ ጤፍ እንደሚያጭድ ሁሉ ፣ አንተም የዘራኸውን በእጥፍ ታጭዳለህ።

ወዳጄ ሆይ!

ለራስህ ስትል መልካም ሁን ፣ በጎውንም አስብ። ለራስ ማሰብ ማስተዋል እንጅ ራስ ወዳድነት አይደለም። ራሱን የማይወድ ሰው ሌላውን አይወድም ። አትፍረድ ፣ የመፍረድ ሃላፊነት በፍፁም የለህም ። ፍርድ የፈጣሪ ነው፣ ለመፍረድ እንከን አልባ መሆን ያስፈልጋል ፣ ፍጥረት ሁሉ ፍጥረት በመሆኑ ብቻ እንከን አለበት ፣ ጎደሎ አለበት ። የተሻለ ሀሳብ አለኝ ብለህ ካሰብክና ከቻልክ ምከር ካልሆነ ዝም በል ።

ከጓደኛህ መልካም የሆነውን ነገሩን አውጣለት ፣አበረታታው፣እንደማይጠቅም አትንገረው ፣ ለሀዘኑ ሳይሆን ለደስታው ምክንያት ሁን ፣ ለስኬቱ እንጅ ለውድቀቱ መንስኤ አትሁን ። መልካም ጓደኛ ከፈጣሪ የሚሰጥ ጸጋ ነው ። መልካም ጓደኛ ፣ የማይቀና አሳቢና መካሪ ፣ ከእኔ ይልቅ ለአንተ የሚል ካለህ አንተ ተባርከሃል ታድለሃል ። ከሌለህ ደግሞ አንተ ራስህ መልካም በመሆን ጀምር ፣ ባህሪህንና ስራህን አይተው ይመጣሉ።

ያለ መጠን ማሰብ ጭንቀትን ፣ ሀዘንን ያስከትላል ።ከአቅምህ ከምትችለው በላይ አታስብ ፣መመለስ በማትችለው ነገር ላይ አትወጠር ፣ የተመለሱ ነገሮችህ ላይ ትኩረት አታድርግ። አንዳንድ መልሶች በድጋሚ ጥያቄወች ሆነው እንደሚመጡ አትዘንጋ ።

ባልገባን ሳይሆን በገባን ነገር ላይ እናተኩር ።ደግነት ዋጋ አያስከፍልም ነፃ ነው ፣ "ያስከፍላል"ብለህ ካሰብክም ምላሹ እጥፍ እንደሚሆንልህ አትዘንጋ። ደግ ሁኑ ፣ደግ ሆነው የተጎዱ የሉም ፣ ቢኖሩም ከጉዳታቸው ይልቅ በረከታቸው ሰላማቸው ልክ የለውም።

ደስታህንና ሰላምህን የሆነ ሰው ወይም ነገር ላይ አታስቀምጥ ፣ ያ ነገር ወይም ሰው ከአጠገብህ ሲርቅ ወይም
ሲጠፋ ደስታህም አብሮ ይጠፋል ። ደስታና ሰላም በአንተ ውስጥ ናቸው ። በራስህ በአፈጣጠርህ ደስ ይበልህ ፣ውለህ በመግባትህ ደስ ይበልህ ። በአለህ ትንሽ ነገር ደስ ይበልህ ።

ለፍቅር ለመውደድ እንጅ ለጥላቻ ለዛቻ ለምቀኝነት ጊዜ አይኑርህ ። በመውደድ የተጠመደ ሰው ለመጥላት ጊዜ የለውም።  እድሜህን በተመለከተ ፣ የፈጣሪ ፈቃድ ከሆነ ካለፈው ከተቃጠለው ጊዜህ ይልቅ ወደፊት የምትኖረው ብዙ ነው ። ዋናው ደግሞ የኖርክበት የእድሜ ብዛት ሳይሆን በኖርክበት ዘመን ያሳዪኸው መልካምነትና የሰራኸው ደግነት ነው።

የምናማርረው የተሰጠንንና የሆነልንን ’ረስተን ፣ ያልጎደለን ነገር ላይ "ጎደለን" ብለን በጥያቄ ስለምንሞላ ነው ፣ ባለው ነገር አመስጋኝ የሆነ ይጨመርለታል ። በማማረር መባረክ የለም ።

              ሰላምና ጤና ፣
ከመልካም አስተሳሰብና በጎ ህሊና ጋር ምንጊዜም ከዘመንህ አይለዪ።

            ውብ ምሽት

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
1.3K viewsedited  17:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-05 20:49:13
1.2K views17:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-02 12:00:04
እንኳን ለ127ኛው ለታሪካዊ ከኢትዮጵያ አልፎ ለአፍሪካ ነፃነት በር ለሆነው የጥቁር ህዝቦች ኩራት የአድዋ ድል በአል በሰላም አደረሰን።

@EthioHumanity
@EthioHumanity
1.5K views09:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-26 22:40:16 የማንን ግጥም ማንበብ ይፈልጋሉ?
1.3K views19:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-26 20:37:08
የምታቀው የውሃ ኩሬ ራቅ ብለህ ስትመለስ ደፍርሶ ቢጠብቅህ...ንጹህ ውሃን ለመጠጣት ያለህ አማራጭ ድፍርሱ እስከሚጠራ መጠበቅ ብቻ ይሆናል ። "አፈር የተቀላቀለበትን ውሃ እንዲጠራ ከፈለግክ፤ተወው አታማስለው" ይላል ፈላስፋው አለን ዋትስ። በመተው፤በመረጋጋት፤ በዝምታ፤ ለፍተን ያጣናቸውን ውድ የህይወት ስጦታዎች እናገኛለን።

ልክ እንደዚህ ሁሉ በህይወታችን የሚገጥሙንን ችግርና እንቅፋቶችን አንዳንዴ የምናጠራቸው መሃል ላይ እጃችንን ስለከተትን ብቻ ላይሆን ይችላል ። አንዳንዴ ዝምታችን እና ትእግስታችንም ብዙ ነገሮች በራሳቸው ጊዜና ሁኔታ እንዲስተካከሉልን እድል ይሰጡልናል ። እኛ ችግራችንን ለመፍታት የምናደርገው ጥረት ይበልጥ ችግር ውስጥ እንዳይዘፍቀን መጠንቀቅ ይኖርብናል ። አለዝያ የችግሩ አሳዳጊ እና አባባሽ እንጂ የችግሩ ፈቺ አንሆንም ።

ለተረጋጋ አይምሮ አለም ትገበራለች ብሏል ጥንታዊው ፈላስፋ። ምንም እንኳን ብዙ ነገሮች በጥረትና በሩጫ የሚገኙ ቢሆንም፤ አንዳንድ ወሳኝ ነገሮች ግን በእርጋትና በመተው እንዲሁም በዝምታ የሚገኙ ናቸው።

ውብ  ምሽት

@EthioHumanity
@EthioHumanity
     
@EthioHumanitybot
838 viewsedited  17:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-25 17:56:56
ሰዎች በየቦታው ፍጹም ትክክል መስለው ሲታዩ  ሰውኛ አይመስለኝም ። ከራሱ እየተቧቀሰ አካባቢው በቀረፀለት የትክክለኛነት ሳጥን ውስጥ የሚንፈራገጥ ሰው ራሱን ያጣ አሳዛኝ ይመስለኛል። ለእያንዳንዱ ነገሩ የሚጠነቀቅ ሰው ራሱን እየሆነ እንዳልሆነ ነው የሚገባኝ። ራስን መሆን እርማት አይጠይቅም። ራስን መሆን ጥንቃቄ አያሻም። መጠኑ ቢለያይም ሁላችንም ጋ ጥቂት እብደት፣ ጥቂትም ስህተት፣ ጥቂትም ፀፀት እና ጥቂትም ውድቀት አለ ብዬ አስባለሁ።

እውነታው ሰዎች ሊያወድሱህ ከፈለጉ ከፈጣሪ ታናሽ ያደርጉሃል ። ሊዘልፉህ ከፈለጉ ደግሞ ሳጥናኤል የሚቀናበት ክፉ ያደርጉሃል ። ከሰማሃቸው ደግሞ ራስህን የመሆን እድል አይሰጡህም ። ሁሉም በፈለጉት መንገድ ሊቀርፁህ መጥረቢያ ይስላሉ ። ልብህን ከከፈትክላቸው የየድርሻቸውን ጠርበው ቅርፅ አልባ ያደርጉሃል።

እኔና አንተ አንድ ቦታ ላይ በተለያየ አቅጣጫ ፊታችንን አዙረን ብንቆም የእኔ ቀኝ ያንተ ግራ ነው። 'ቀኝ ይሄ ነው ወይም ግራ ይሄ ነው' ብዬ ብከራከርህ ቂል ነኝ ። እንዳንተ አቋቋም ያንተ እውነት ይሆናል ። እንደ እኔ አቋቋም ደግሞ የእኔ እውነት ይሆናል ። ባንተ እውነት ለማመን ያንተን ጫማ መዋስ አለብኝ። የቆምኩበት ሆኜ ለስህተትህ ሒሳብ እየሰራሁ ስዳኝህ እቀሽማለሁ።


ጠበኛ እውነቶች
ሜሪ ፈለቀ

ውብ ቅዳሜ

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
2.2K views14:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ