Get Mystery Box with random crypto!

ሰዎች በየቦታው ፍጹም ትክክል መስለው ሲታዩ  ሰውኛ አይመስለኝም ። ከራሱ እየተቧቀሰ አካባቢው በቀ | ስብዕናችን #Humanity

ሰዎች በየቦታው ፍጹም ትክክል መስለው ሲታዩ  ሰውኛ አይመስለኝም ። ከራሱ እየተቧቀሰ አካባቢው በቀረፀለት የትክክለኛነት ሳጥን ውስጥ የሚንፈራገጥ ሰው ራሱን ያጣ አሳዛኝ ይመስለኛል። ለእያንዳንዱ ነገሩ የሚጠነቀቅ ሰው ራሱን እየሆነ እንዳልሆነ ነው የሚገባኝ። ራስን መሆን እርማት አይጠይቅም። ራስን መሆን ጥንቃቄ አያሻም። መጠኑ ቢለያይም ሁላችንም ጋ ጥቂት እብደት፣ ጥቂትም ስህተት፣ ጥቂትም ፀፀት እና ጥቂትም ውድቀት አለ ብዬ አስባለሁ።

እውነታው ሰዎች ሊያወድሱህ ከፈለጉ ከፈጣሪ ታናሽ ያደርጉሃል ። ሊዘልፉህ ከፈለጉ ደግሞ ሳጥናኤል የሚቀናበት ክፉ ያደርጉሃል ። ከሰማሃቸው ደግሞ ራስህን የመሆን እድል አይሰጡህም ። ሁሉም በፈለጉት መንገድ ሊቀርፁህ መጥረቢያ ይስላሉ ። ልብህን ከከፈትክላቸው የየድርሻቸውን ጠርበው ቅርፅ አልባ ያደርጉሃል።

እኔና አንተ አንድ ቦታ ላይ በተለያየ አቅጣጫ ፊታችንን አዙረን ብንቆም የእኔ ቀኝ ያንተ ግራ ነው። 'ቀኝ ይሄ ነው ወይም ግራ ይሄ ነው' ብዬ ብከራከርህ ቂል ነኝ ። እንዳንተ አቋቋም ያንተ እውነት ይሆናል ። እንደ እኔ አቋቋም ደግሞ የእኔ እውነት ይሆናል ። ባንተ እውነት ለማመን ያንተን ጫማ መዋስ አለብኝ። የቆምኩበት ሆኜ ለስህተትህ ሒሳብ እየሰራሁ ስዳኝህ እቀሽማለሁ።


ጠበኛ እውነቶች
ሜሪ ፈለቀ

ውብ ቅዳሜ

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot