Get Mystery Box with random crypto!

የምታቀው የውሃ ኩሬ ራቅ ብለህ ስትመለስ ደፍርሶ ቢጠብቅህ...ንጹህ ውሃን ለመጠጣት ያለህ አማራጭ | ስብዕናችን #Humanity

የምታቀው የውሃ ኩሬ ራቅ ብለህ ስትመለስ ደፍርሶ ቢጠብቅህ...ንጹህ ውሃን ለመጠጣት ያለህ አማራጭ ድፍርሱ እስከሚጠራ መጠበቅ ብቻ ይሆናል ። "አፈር የተቀላቀለበትን ውሃ እንዲጠራ ከፈለግክ፤ተወው አታማስለው" ይላል ፈላስፋው አለን ዋትስ። በመተው፤በመረጋጋት፤ በዝምታ፤ ለፍተን ያጣናቸውን ውድ የህይወት ስጦታዎች እናገኛለን።

ልክ እንደዚህ ሁሉ በህይወታችን የሚገጥሙንን ችግርና እንቅፋቶችን አንዳንዴ የምናጠራቸው መሃል ላይ እጃችንን ስለከተትን ብቻ ላይሆን ይችላል ። አንዳንዴ ዝምታችን እና ትእግስታችንም ብዙ ነገሮች በራሳቸው ጊዜና ሁኔታ እንዲስተካከሉልን እድል ይሰጡልናል ። እኛ ችግራችንን ለመፍታት የምናደርገው ጥረት ይበልጥ ችግር ውስጥ እንዳይዘፍቀን መጠንቀቅ ይኖርብናል ። አለዝያ የችግሩ አሳዳጊ እና አባባሽ እንጂ የችግሩ ፈቺ አንሆንም ።

ለተረጋጋ አይምሮ አለም ትገበራለች ብሏል ጥንታዊው ፈላስፋ። ምንም እንኳን ብዙ ነገሮች በጥረትና በሩጫ የሚገኙ ቢሆንም፤ አንዳንድ ወሳኝ ነገሮች ግን በእርጋትና በመተው እንዲሁም በዝምታ የሚገኙ ናቸው።

ውብ  ምሽት

@EthioHumanity
@EthioHumanity
     
@EthioHumanitybot