Get Mystery Box with random crypto!

እውነትን ፣ቅንነትን ፣ ገንዘብ ከማድረግ በላይ ኮተትን ብቻ  ገንዘብ አድርጎ ህይወቱን በክህደት፣ | ስብዕናችን #Humanity

እውነትን ፣ቅንነትን ፣ ገንዘብ ከማድረግ በላይ ኮተትን ብቻ  ገንዘብ አድርጎ ህይወቱን በክህደት፣ በውሸት ፣በጥቅመኝነት ፣በአስመሳይነት በብልጣብልጥነት እየኖረ ኑሮ የበራለት የሚመስለው ሰውነት እንዴት ያልታደለ ነው።

የህሊና ፣ የቤተሰብ ሰላምና ደስታ በብልጣብልጥነት አይመጣም። ፈጣሪ ባህሪና ተግባራችንን ያያል። ከሰው የወሰድነውን ከሰውየው ብንደብቅ ከአምላክ አንደብቅም። የምናተርፈው ነገር ቢኖር የሆነ ጊዜ ላይ የሚመጣ መጥፎ ስቃይን ነው። ያውም ለልጅ የሚተርፍ የበደል ክፍያን ነው፣የቆምን መስሎን የዘነጋን…. ሰው የዘራውን ያጭዳልና እናስተውል።

መልካምነት ከማንም በላይ ላራስ ነው ጥቅምና ፍይዳው፣ ቅን ሀሳብ አሳቢውን ይባርካል። ከአንተ የመነጨና ተንደርድሮ የተተኮሰ ኃይል በእኩል መጠን እና ልክ አጥፊ እንደሆነ ሁሉ ራስህንም ያጠፍል፤ ሀሳብህን አልሚ ከአደረከው ደግሞ ቅድሚያ አንተን እና የእኔ የምትለውን ሁሉ ባርኮ ለሌሎች ይተርፋል።

መጥፎ ነገራችንን ሁሉ በመልካም ይቀየርልን

                              ሄለን ካሳ

ውብ አሁን

@EthioHumanity
@EthioHumanity
     
@EthioHumanitybot