Get Mystery Box with random crypto!

እኛ ሻማዎች ነን እርካብና መንበር [ 117-118 ] | ስብዕናችን #Humanity

እኛ ሻማዎች ነን

<<...ባንድ ምሽት ሰውዬው በባሕር ዳርቻ ባለው የወደብ ከፍታ ቦታ ትንሽ ሻማ ይዞ መውጣት ይጀምራል። በዚህ ጊዜ 'ወዴት ነው እየሄድን ያለንው?' ሲል ሻማው ጥያቄ አቀረበለት።
"እየሄድን ያለነው ከቤቱ ባሻገር ከፍ ብሎ ወደሚታየው ቦታ ነው። በዚህም ለመርከቡ የወደቡን አቅጣጫ ማሳየት እንችላለን" አለው።
"እንደምታየው የእኔ ብርሃን በጣም ውስን ናት። እንዴትስ ከርቀት ያለ መርከብ በእኔ ብርሃን ተመርቶ ወደቡ ጋር መድረስ ይችላል?" አለ ሻማው።

"ምንም እንኳ ያንተ ብርሃን ትንሽ ብትሆንም የምትችለውን ያህል ማብራትህን አታቋርጥ፣ የቀረውን ነገር ለእኔ ተውው" አለው ሰውየው። በዚህ ንግግራቸው መሀል እያሉ ከከፍታ ቦታው ደረሱና ሰውዬው ትልቁን የፋኖስ ብርጭቆ እያሳየው ሻማውን በማስጠጋት ፋኖሱን ለኮሰው። ወዲያውኑም የተለኮሰው ፋኖስ የባሕሩን አካባቢ በብርሃን ጸዳል ሞላው።

እኛ ሻማዎች ነን። ከእኛ የሚጠበቀውም የሻማነታችንን ያህል ማብራት ነው። ቀሪው የሥራችን ስኬት ላይ ፈጣሪ ይታከልበታል። የአንዲት ትንሽ ሻማ መብራት ወይም ክብሪት ጫካ ሙሉ እሳት እንደምትፈጥር ሁሉ በእያንዳችን ያለች የብርሃን ምሳሌ ስናውቅም ሳናውቅም ለሌሎች ሕይወት መለወጥ ምክንያት ትሆናለችና ብርሃናችንን ሳንሳሳላት እንድትበራ እድል እንስጣት።

ዕድገትም ቅብብሎሽ ነው። እኛ ማድረግ የምንችለውን ሰርተን ለተገቢውና ለሚጠበቅብን ስናስረክበው እሱም በፈንታው ዳር ያደርሰዋል። ሻማዋ ለፋኖሱ እንዳቀበለችው ማለት ነው። ይህ ነው፣ ለዕድገት የድርሻን መወጣት ማለት፤ ሻማነታችንን ማበርከት የሚጠበቅብንን መወጣት። >>

እርካብና መንበር [ 117-118 ]
ዲራአዝ

ውብ  አዳር

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot