Get Mystery Box with random crypto!

ውሎህ የት ነው? ሕይወት ሥነ ምህዳር ነው። የሰጠኸው ነገር ተመልሶ ይመጣል።የዘራውን ታጭዳለህ | ስብዕናችን #Humanity

ውሎህ የት ነው?

ሕይወት ሥነ ምህዳር ነው። የሰጠኸው ነገር ተመልሶ ይመጣል።የዘራውን ታጭዳለህ የምትሰጠውን ታገኛለህ በሌሎች ውስጥ የምታየውን በአንተ ውስጥ ታገኘዋለህ ፡፡ ሕይወት ሁሌ የሰጠሀትን መልሳ ትሰጠሀለች መልካም አድርግ መልካም ታገኛለህ እንደሚባለው ሁሉ።

ውሎህ አንተን ይገልፃል መልካም ቦታ ከተገኘህ በመልካም ይገለፃል በመጥፎ ቦታ ከዋልክ እንዲሁ ይሄንን የሚገልፅ ልናስተውለው የሚገባ አንድ ተረት አለ እንዲህ ይላል:-

አንድ ቀን ዝንብና ንብ እያወሩ በወሪያቸው መሀል ዝንብ ንብን እንዲህ ስትል ጠየቀቻት
ንብ ሆይ ለምንድነው የሰው ልጆች እኔን የሚጠሉኝ? ለምንስ ነው የሚጸየፉኝ ? ቤታቸው
ስገባ ያባርሩኛል ይገድሉኛል።
የሚጠጡት ነገር ላይ ከተገኘሁ ይደፉታል የሚበሉት ነገር ላይ ካረፍኩ ያረፍኩበትን ቦታ
ያለውን እህል ቆርሰው ይጥሉታል::

አንቺን ግን እንደ እኔ አይገፉሽም እንደውም ቤታቸው ስትገቢ ይንከባከቡሻል ደግሞም
መልካም ነገርን ተስፋ በማድረግ ደስታቸው እጥፍ ነው ለምንድነው?" ስትል ዝንብ ንብን
ጥያቄዋን አቀረበች
በዚህ ጊዜ ንብ እንዲህ አለቻት
ውሎሽ የት ነው?

ሰው ጠላን፣ ገፋን፣ ናቀን እያልን እንደ ዝንቧ ጥያቄን አዝለን ከምንጓዝ ውሏችንን በደንብ እንይ ወሏችን ተመልሶ እኛነታችንን ይገልፃል ውድቀታችንን ለማረምም ይሁን ብርታታችንን ለማብዛት ውሏችንን እንቃኝ ሀሳባችን ስራችንን፣ ስራችን ውጤታችንን፣ውጤታችን እኛነታችንን ይገልጽልናልና። የሰው መንገድ ሁሉ በዓይኑ ፊት የቀናች ትመስለዋለችና፣ራስን መፈተሽ መልካምም ነውና ወሎችን የት ነው?

   ውብ አሁን

@EthioHumanity
@EthioHumanity
     
@EthioHumanitybot