Get Mystery Box with random crypto!

ገበሬዉ ሁለቱን አህያዎች አንደኛዉን ጨዉ አንደኛዉን ባዶ በርሜል ጭኖ እየሄደ ነዉ። ወገቡ ሊቆረጥ | ስብዕናችን #Humanity

ገበሬዉ ሁለቱን አህያዎች አንደኛዉን ጨዉ አንደኛዉን ባዶ በርሜል ጭኖ እየሄደ ነዉ።
ወገቡ ሊቆረጥ ደርሶ የሚንገዳገደዉ የጨዉ ኩንታሎችን የተሸከመዉ አህያ: ባዶ በርሜል የያዘዉ አህያ በፍጥነት ሲጓዝ ሲመለከት ጊዜ ከችግሩ ለመዉጣት አንድ ነገር ለማድረግ
ወሰነ።

"ወንዝ አካባቢ ሲደርሱ ዉሃ ዉስጥ በመዉደቅ ሸክሙን ማቃለል!" ከጥቂት ጉዞ በኋላ ወንዝ ጋር ደረሱና ጨዉን የተሸከመዉ አህያ እንዳቀደዉ አደረገ። እቅዱ ተሳክቶለትም ዉሃዉ በኩንታሉ ዉስጥ ያለዉን ጨዉ በከፊል አጥቦ ወሰደዉ፣ከቆይታ በኋላ ከወደቀበት ሲነሳ ከገመተዉ በላይ ሸክሙ ቀለለዉ። እንደ ጓደኛዉም ዘና ብሎ በፍጥነት መሄድ ቻለ።

ይህን የተመለከተዉ በርሜል ተሸካሚ አህያ ከመጀመሪያዉ የበለጠ እንዲቀለዉ በመሻት ልክ እንደጓደኛዉ ዉሃ ዉስጥ ተዘፈቀ።ግና ከቆይታዎች በኋላ ሲነሳ ወገብ ዛላዉ ሊቆረጥ ምንም አልቀረዉም።ነገሩ የተገላቢጦሽ ሆኖ በርሜሎቹ በዉሃ ተሞልተዉ ስለነበር የጉዞዉ እጣ-ፈንታ በብርክ፣ምጥና እንፉቅቅታ ወድቆ እየተነሳ መኳተን ሆነ።

ሌላዉ የጠቀመዉና የለወጠዉ የህይወት መንገድ እኛን ላይጠቅመን ይልቁንስ ሊጎዳን ይችላልና የሌላን ሰዉ እርምጃ ከመከተላችን በፊት ምክንያትና ዉጤቱን ማመዛዘን ይገባናል! ማንኛዉም ችግር ሲገጥመን ማንኛዉንም እርምጃ ከመዉሰዳችን በፊት አዕምሯችንን ማሰራትና ቆም ብለን ማሰላሰል ካልቻልን ለነጻነት ያሰብነዉ መንገድ የባሰ ጭንቅና መከራን ሊያመጣብን ይችላል!

በእጅ ያለ ወርቅ ከመዳብ ይቆጠራል እንዲሉ እኛ ዘንድ ያለዉን ጸጋ ማየት ተስኖን ዓይናችን የባተለበትን ሩቅ ማለም የነበረንን ሊያሳጣን ይችላልና ማመስገንን እልመድ! ጭፍን ተከታይነት ለራስም ሆነ ለሌላዉም እዳ እንጂ ትርፍ የለዉም!

ውብ ምሽት

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot