Get Mystery Box with random crypto!

ደግነትን ፣ ርህራሄን ፣ አዛኝነት ፣ ቅንነት እና በጎ አሳቢነት በተፈጥሮ ለሰው ልጅ የተቸረ ነው። | ስብዕናችን #Humanity

ደግነትን ፣ ርህራሄን ፣ አዛኝነት ፣ ቅንነት እና በጎ አሳቢነት በተፈጥሮ ለሰው ልጅ የተቸረ ነው።

ከትሕትና የበለጠ መልካም ነገር የለም። የደካማነት መገለጫ አይደለም።
የዋህነት ደካማነት ሳይሆን የለስስት የመኖር ችሎታ ነው፣ ደግነት የመልካም ሰው የህይወት መምርያ ነው። ደጎች የፍቅር ልብ ያላቸው፣የሰው ችግር የሚገባቸው ።ከራሳቸው ሰውን የሚስቀድሙ ፣በሰው ላይ የማይፈርዱ ና ሩህረሩህ ናቸው ።ውስጣቸው ከክፋት የጠራ ብዙ ደስታ ና ፍቅር የሚገኝባቸው ጥበበኞች ናቸው።

ሰው በውስጡ በመልካም እና ሰናይ ምግባራት የተሞላ ፍጥረት ነው።
እኩይ ተግባር ግን የልምምድ ወጫዊ ተፅእኖ ተግባር ነው።በውጫዊ ተጽእኖ ሳይደናቀፉ እና ሳይቀየሩ ይህን የተፈጥሮ ጸጋ መጠቀም ደግሞ ታላቅነት ነው ሰብአዊነት ነው አርቆ አሳቢነት ነው አስተዋይነት ነው።

በአስተዋይነት ከተጓዝን ደስታ ፣ ፍቅር ፣ እርካታ እና ነጻነት ደግሞ የህይወት ሽልማት ናቸው።

           ውብ አዳር

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot