Get Mystery Box with random crypto!

ትላንት አልፏል ስለዚህ ሞቷል። እከሌ ህይወቱ አለፈ ስንል፡ ሞተ ከአሁን ቡሃላ እዚ ምድር ላይ አይ | ስብዕናችን #Humanity

ትላንት አልፏል ስለዚህ ሞቷል።
እከሌ ህይወቱ አለፈ ስንል፡ ሞተ ከአሁን ቡሃላ እዚ ምድር ላይ አይኖርም እያልን ነው። በተመሳሳይ ሁኔታ ትላንት አልፏል (አለፈ) ስንል ሞቷል በህይወታችንም ዋጋ የለውም እያልን ነው። ነገ ደሞ ሚስጥር ነው ካልደረስንበት አናውቀውም።እንዲሁም ነገ ስጦታ ነው ካልተሰጠን አንደርስበትም።ዛሬ ግን በእጃችን ላይ ነው። ስለዚህ ስለ ትላንት በማሰብ ስለነገም በመጨነቅ ዛሬን አናበላሽዉ። ትልቅ ጥበብ ዛሬን መኖር ነው ከዛሬም ደሞ አሁን። ወዳጄ ትላንት ስላሳለፍከው ነገም ስለምትሆነው አትጨነቅ። ነገን ስትደርስበት ህይወት እራሷ ትገልፅልሀለች።

የህይወት ትልቁ ስጦታ በህይወት
መኖር ነው። ትዳር የምትመሰርተው ሀብት ንብረት የምታፈራው በህይወት ስላለክ ነው። ህይወት ደግሞ የሚኖሯት እንጂ የሚመልስዋት ጥያቄ ፣የሚፈቷት እንቆቅልሽ አይደለችም።የሆነው ሁሉ መሆን የኖረበት ነው ፣ የሚሆነውም መሆን ያለበት ነው። ለምን ሆነ ? ህይወት ምንድነች ? የመሳሰሉትን በመጠየቅ እራስህን አታድክም። የህይወት ጥያቄዎች ሁሉ መልስ ያለው እራስዋ ህይወት ውስጥ እንጂ አይምሮህ ውስጥ አይደለም።

አንተ ያስከፋህን ነገር አይደለህም ፡አንተ ያስደሰተህንም ነገር አይደለህም አንተ የሁለቱም መውረጃ ቦይ ነህ የሚያስደስትህም የሚያስከፋህም ነገር በአንተ ውስጥ ያልፉል አንተግን ሁለቱንም አይደለህም። ይህ የህይወት ህግ ነው።

ከ24 ሰአት ውስጥ 12ቱ ብርሀን 12ቱ ጨለማ ነው፣1አመትም በጋና ክረምት ነው ። አየህ በህይወት ብርሀንና ጨለማ በጋና ክረምትም ይፈራረቃሉ።ባንተም በተመሳሳይ መልኩ ማግኘትና ማጣት ፣ማዘንና መደሰት ይፈራረቃሉ ይህ ይሆን ዘንድ ግድ ነው ። በሌላው ከሆነው ይልቅ ባንተ ብቻ የሆነ ምንም የለም። ካንተ በፊትም አሁን በሚኖሩትም የሆነ ነው አንተ ላይም እየሆነ ያለዉ። የሚሟሽ የሚከለስ እንጂ አዲስ መከራ የለም። ፀደይ፣ መኸር፣በልግ እያሉ ወቅቶች እንደሚፈራረቁ ስሜቶችም አንተ ላይ ይፈራረቃሉ።ንዴት ፣ ቁጣ ፣ መረጋጋት፣ መስከን እያሉ ማለት ነው። አስታዉስ አንተ ግን ስሜቶችህን አይደለህም አንተ ከዛ በላይ ነህ።

ሰለዚህ ህይወት ምንድናት እያልክ አትጨነቅ ።እስዋ የህፃን ልጅ ሳቅና ለቅሶ፣ የወጣት ድንፋታ ፣የሽማግሌ ስክነት፣ አለቶች ከውሀ ጋር ሲጋጩ የሚያሰሙት ድምፅ፣ ንፋስ የሚያወዛውዘው ቅጠል ይህ ሁሉ ናት። አንተ ግን የህይወትን ሚስጥር በቃላት ለመግለፅ በመሞከር እና ስለትላንት በማሰብ እንዲሁም ስለነገ በመጨነቅ ዛሬን ታበላሻለህ።እውነት ዛሬ ነው! ። ስለዚህ ዛሬን ኑር !

ውብ አሁን

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity

@Ethiohumanitybot