Get Mystery Box with random crypto!

ደስታ የምኞት ውጤት፣ የማሳደድ ትርፍም አይደለም። ደስታን ተመኝቶ ያገኘ፣ አሳድዶ የያዘ የለም። | ስብዕናችን #Humanity

ደስታ የምኞት ውጤት፣ የማሳደድ ትርፍም አይደለም። ደስታን ተመኝቶ ያገኘ፣ አሳድዶ የያዘ የለም።

ደስታ ከገንዘብ ብዛት፣ከስልጣን ሹመት፣ ስጋዊ ስሜትን ከማርካት ወይም ከሳይንስ አይመነጭም፡፡ ደስታ በቁጥር አይመጠንም፡፡ መጋዘኖች አያከማቹትም፡፡ ዩሮ ወይም ዶላር አይገዛውም፡፡ ደስታ ከውስጥ የሚሰማ ነገር ነው፡፡ የነፍስ መስከን፣ የቀልብ መረጋጋት፣ የልቦና መስፋት፣ የሕሊና መርካት ውጤት ነው፡፡የአዕምሮአችንን ተፈጥሮ በትልቅ ተረድተን ከተጠቀምበት እውነተኛ ደስታ እና ነፃነት ማግኘት እንችላለን ፡፡

አትኩሮትህን በሌለህ ነገር ላይ ሳይሆን ባለህ ነገር ላይ አድርገው። ደስተኛ ለመሆን ሁሉም ነገር ሊኖርህ አይገባም። በደንብ ካስተዋልከው አሁን ያለህ ነገር ደስተኛ ለመሆን በቂ ነው።ምክንያቱም አንተ ያለህን ሙሉ ጤና የሚመኙ ምስኪኖች ብዙ ናቸውና።

ቁሉፉ ነን እኛ…የራሳችን ደስታ
ውብ አሁን!!

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot