Get Mystery Box with random crypto!

መዘግየትህን አትጥላው! ነገሮች በፍጥነት እንዲሳኩልህ አትፈልግ! መዘግየትህን አትጥላው! በትምህ | ስብዕናችን #Humanity

መዘግየትህን አትጥላው!

ነገሮች በፍጥነት እንዲሳኩልህ አትፈልግ! መዘግየትህን አትጥላው! በትምህርት፣ በስራ፣ በሀብት፣ በፍቅር ግንኙነት ወይ በትዳር አንተ እንዳሰብከው አለመሆኑ ለበጎ እንደሆነ አስብ።

ልብ እንበል!!

ጉንደን ካስበችው ለመድረስ ሺ ጊዜ ከምሰሶው ላይ ትወድቃለች።

ንብ ጣፋጩን ማር ለመጋገር ሚሊዮን ጊዜ አበቦች አካባቢ ትመላለሳለች:: ወዳጄ ስኬት ትኩረትንና ትእግስትን ይጠይቃል..

ወደ ኋላ የተንደረደረ ረጅም ርቀት እንደሚተኮስ አስብ፤ ወዳጄ ጥያቄህ ቶሎ ያልተመለሰው ጊዜው ስላልደረሰ ወይ ደግሞ ፈጣሪ የተሻለውን ሊሰጥህ ይሆናል። አንተ ብቻ ጥረትህን ሳታቋርጥ ታገስ፤ የህይወትህ ፀሀይ መውጣቷ አይቀርም!

ፋንዲሻ እንዴት አማርሽ ቢሏት እሳቱን ስለቻልኩት አለች ይባላል ፣ በህይወት መስመር ስኬትን ለማግኘት የግድ መከራውን ማለፍ አለብን!!

ውብ ምሽት!

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot