Get Mystery Box with random crypto!

በአንዲት ትንሽየ ከተማ ውስጥ ለብዙ ዘመናት ማራኪ ስዕሎችን በመሳል ለከተማዋ ነዋሪዎች እና ከሩቅ | ስብዕናችን #Humanity

በአንዲት ትንሽየ ከተማ ውስጥ ለብዙ ዘመናት ማራኪ ስዕሎችን በመሳል ለከተማዋ ነዋሪዎች እና ከሩቅ አካባቢ ለሚመጡ እንግዶች በጥሩ ዋጋ እየሸጠ ደስታ የተሞላበት ሕይወት የሚኖር አዛውንት ነበር። ከዕለታት አንድ ቀን በከተማዋ ውስጥ ከሚገኙ ድሃዎች
መካከል አንዱ መጣና ሰዓሊውን «በሥራህ ብዙ ገቢ እያገኘህ ለምንድን ነው በከተማዋ ያሉ የኔ ቢጤ ደሃዎችን ለመርዳት ንፉግ ያደረገህ ??...

የዚያ ልኳንዳ ቤት ባለቤት እዚህ ግባ የሚባል ገንዘብ ሳይኖረው ለድሃዎች በየቀኑ ስጋ ያድላል፤ በተመሳሳይ ሁኔታ የዚያ ዳቦቤት ባለቤት ዘወትር በየቀኑ በነፍስ ወከፍ ለድሃዎች ዳቦ ይሰጣል» በማለት ጠየቀው። ሰዓሊው ምንም መልስ ሳይሰጠው በሰከነ መንፈስ ታጅቦ በስሱ ፈገግ አለ።

ድሃው በሰዓሊው ዝምታ ተበሳጭቶ ከቤቱ ውስጥ ተስፈንጥሮ ወጣ። ወደ መሃል ከተማ በመገስገስ አላፊ አግዳሚውን እያስቆመ «ሰዓሊው ብዙ ኃብት ቢያከማችም ድሃወችን
ለመርዳት ፍላጎት የሌለውና ስስታም ነው» በማለት ወሬ መንዛት ጀመረ። የአካባቢው ነዋሪዎች በሰዓሊው ላይ ጥርስ ነከሱበት። ማህበራዊ መገለል ደረሰበት። የሚያናግረው አንድ ሰው እንኳ አጣ።

ከተወሰኑ ቀናት በኋላ አዛውንቱ ሰዓሊ ክፉኛ ታመመ። ከአካቢቢው ነዋሪዎች መካከል አንድም ሰው ትኩረት የሰጠው አልነበረም። ከጎኑ ማንም ሳይኖር ብቻውን ሞተ።

ቀናት በንፋስ ፍጥነት ነጎዱ። የከተማዋ ነዋሪዎች የልኳንዳ ቤቱ ባለቤት ለድሃዎች በነጻ የሚያድለውን ስጋ እንዳቆመ አስተዋሉ። የዳቦ ቤቱ ባለቤትም ለሚስኪኖች በነጻ
የሚያከፋፍለውን ዳቦ እንዳቋረጠ ተገነዘቡ። ድሃዎቹ በልኳንዳ ቤቱ በር ፊት ለፊት ቆመው የለመዱትን ስጋ ለማግኘት ቢማጸኑም ሰሚ አጡ። በዳቦ ቤቱ መስኮት ዙሪያ ቢያንዣብቡም
ለስም እንኳ የሚያዳምጣቸው አንድ ሰው አጡ።

የከተማዋ ነዋሪዎች ተሰብስበው የልኳንዳ እና ዳቦ ቤቶቹን ባለቤቶች «ዘወትር በየቀኑ ለድሃዎች ትሰጡ የነበረውን ስጋ እና ዳቦ ለምን
አቆማችሁ» ብለው ሲጠይቋቸው «በየቀኑ ለከተማዋ ድሃዎች በነጻ የምንሰጠውን የስጋና ዳቦ ዋጋ በየወሩ የሚከፍለን አዛውንቱ ሰዓሊ ነበር። ከሱ ህልፈት በኋላ ክፍያ የሚፈጽምልን
ሰው ባለመኖሩ በነጻ ማደሉን አቋርጠነዋል» በማለት ወሽመጥ ቆራጭ ምላሽ ሰጧቸው።

የተወሰኑ ሰዎች ባንተ ላይ ክፉ ጥርጣሬ ሊያሳድሩ ይችላሉ። አንዳዶች ደግም እንደ ሐጫ በረዶ የጠራህ አድርገው ሊስሉህ ይችላሉ። ሁለቱም አይጠቅሙህም። አይጎዱህምም።
ቁም ነገሩ ያለው ፈጣሪ ስላንተ የሚያውቀው ትክክለኛ ማንነትህ ላይ ነው። ለክፉ አሳቢዎች ክፋ ምላሽ ላለመስጠት ጥረት አድርግ።

ደግነትህ ለብዙዎች የዕድሜ ማራዘሚያ ሰበብ ስለሆነ እንዳይከስም ጠብቀው። ለጋስ በመሆንህ በምላሹ ከሌሎች ምንም ነገር አትጠብቅ። የጊዜ ጉዳይ ቢሆን እንጂ መልካም ነገር ሁሌም ከፈጣሪህ በጎ ምላሽ አለው።
ህሊናህ ይረካ ዘንድ ከመቀበል ይልቅ ሰጪ ሁን። በምግባርህ ፈጣሪህን ለማስደሰት ሁሌም ጥረት አድርግ። እርሱ ከወደደህ ደስታ በእጅህ ትገባለች።በመልካም ስነ ምግባር ሽቶ የተርከፈከፈ ስብዕና ከመሬት በታች አፈር ለብሶ እንኳ መዓዛው ያውዳል።
               
ውብ  አሁን
@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot