Get Mystery Box with random crypto!

የሚያልፍ ዝናብ አይምታህ!! እዚህች ምድር ላይ ስንኖር በትንሹም ይሁን በትልቁ በየደቂቃው እንለ | ስብዕናችን #Humanity

የሚያልፍ ዝናብ አይምታህ!!

እዚህች ምድር ላይ ስንኖር በትንሹም ይሁን በትልቁ በየደቂቃው እንለዋወጣለን። ቢታወቀንም ባይታወቀንም ነው እንግዲህ ቢያንስ ገላችን የበላውን ያንሸራሽራል፣ ሕዋሳት ይሞታሉ ይወለዳሉ። ቢያንስ አንዲት ፀጉር ትበቅላለች ወይም ትረግፋለች። ፊኛችን ሳያቋረጥ በፈሳሽ ይሞላል። ጊዜው ሲደርስም ይጎላል።

ሕይወት እንግዲህ እንዲህ ነው፤ ይሄ ዑደትና የዝግመት ለውጥ አይበቃንምና ደሞ አንዳንድ ጊዜ እጅግ የሚለውጠን ቀውስ ይመጣብናል ገላችን፣አዕምሮአችን ይታመማል እንረበሻለን፣እንጨነቃለን።ሕይወት እንግዲህ ይሄ ነው ሰው በግሉ፣ ሕብረተሰብም ተፈጥሮው ይመስሉኛል።

ይሄን ደጋግሜ መገንዘቤ፣ደጋግሜም በነዚህ ሁኔታዎች ውስጥ ማለፌ ያስተማረኝ ነገር አለ።መረባበሽ ፋይዳ እንደሌለው የተረጋጋ ታዛቢ፣ የመነኩሴ አመለካከት አለኝ። ከፍ ዝቅ ያለ ነገር ሲያጋጥመኝ በረጉ ዓይኖቼ አያለሁ። በቀዘቀዘ መንፈስና አካል እቀበለዋለሁ እንደሚለወጥ ስለማውቅ!"የሚያልፍ ዝናብ አይምታህ" ሲሉ አዛውንት ዝናቡን ፍራው ማለታቸው አይደለም። ዝናቡን ማወቃቸው ነው። የተወሰነለት ዕድሜ አለው፣ ያውም አጭር ማለታቸው ነው። ሰው ቢያንስ በተስፋ የችግሮቹን ዘመን ያልፋል ማለታቸው ነው።

/ከአዳም ረታ አንደበት/

በእርግጥም የሚገጥሙንና የሚያጋጥሙንን ክስተቶችና ፈተናዎች መወሰን ባንችል እንኳን፣ ምላሻችንንና ግብረ-መልሳችንን መወሰን እንችላለንና ዘወትር የመጣው እስኪያልፍ፣ የቀለጠው እስኪ ረጋ፣ የነደደው እስኪ ከስል፣ በሰከነ አዕምሮ፣ በተረጋጋ መንፈስ፣ በአንድ ልብ መቀበሉንና ማሳለፋን እንወቅበት።

       ሰናይ ምሽት ይሁንልን

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot