Get Mystery Box with random crypto!

EMS Mereja

የቴሌግራም ቻናል አርማ emsmereja — EMS Mereja E
የቴሌግራም ቻናል አርማ emsmereja — EMS Mereja
የሰርጥ አድራሻ: @emsmereja
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 14.57K
የሰርጥ መግለጫ

👉 መረጃዎች፣ጥያቄዎች፣ አስተያየቶችና የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት ከፈለጉ በዚህ ያናግሩን👉 t.me/infoetrobot
👉 የዕለታዊ ዝግጅቶችና ዜናዎች በተባባሪ አቅራቢዎች እንዲደርሷችሁ👇👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@HAQMEDIA12
Subscribe ያድርጉ

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-06-10 10:24:57 ከጎንደር ዩንቨርስቲ
ከትናንት በስተያ ምሽት በጎንደር ዩኒቨርሲቲ አንድ ተማሪ አንገቱ ላይ እንዲሁም ደረቱ አካባቢ በጩቤ መውጋቱን በዛም ላይ ከርሱ ጋር የነበረችው ልጅ መደፈሩዋን መረጃ ደርሶኛል። ተጎጂ ተማሪውም በጎንደር ዩንቨርስቲ ሪፈራል ሆስፒታል ህክምና ላይ ነው ብለዋል።
ለጊዜው ይህን ማን እደፈፀመው በውል የታወቀ ነገር የለም።
መረጃ ህይወት ነው፣ ይህንንም መረጃ ለጓደኞቻችሁ#Share በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ


t.me/emsmereja
t.me/emsmereja
t.me/emsmereja
2.4K viewsedited  07:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-10 10:17:14
ታሰረ
#Ethiopia | የጉማ አዋርድ መሥራችና አዘጋጅ ፤ ዳይሬክተር ዮናስ ብርሃነ መዋ መርኃ ግብሩን ሳያጠናቅቅ ትናንት ምሽት ታሰረ።

9ኛው የጉማ የሽልማት ዝግጅት በስካይላይት በደመቀ ሁኔታ ተከናውኖ ከምሽቱ 5:20 ሰዓት ላይ ተጠናቆ ነበር።
ወ/ሮ ሳምራዊት ከሰተ (ሊሊ) እንደተናገራቸው "አንቺን አንፈልግሸም ! ... እርሱን ግን ለጥያቄ እፈልገዋለን " በማለት ቦሌ ትራፊክ መምሪያ በተለምዶ ስሙ አንበሳ ጋራዥ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ መታሰሩን ተናግራለች።

***

[ ትውስታ : አምና፣ ካቻምና መድረክ ላይ ]

[ ልጅ አባቱን በመድረክ፣ በሕዝብ ፊት የሰጠው ማስጠንቀቂያ ]

እኔ አስራሃለሁ!"

"ፖለቲካ ውስጥ ተመልሰህ ብትገባ መንግሥት ሳይሆን እኔ አስራሃለሁ!"

"አንዳንድ ሰው እድለ ቢስ ሆኖ በልጅነቱ ሀገሩን እየጠላ አድጎ ሲያድግም ሀገሩን ለማፍረስ ይጥራል። አንዳንድ እድለኞች ደግሞ የሀገራቸውን ታላቅነት ተሰብከው አድገው ሀገራቸውን ለመገንባት ደፋ ቀና ሲሉ ህይወታቸውን ይጨርሳሉ። እንደዚህ ስለሀገር መልካምነት ተሰብከው ሀገር ለመገንባት ከባጁ እድለኞች መካከል አንዱ ወላጅ አባቴ ነው!"

ዮናስ ብርሀነ መዋ፣ የጉማ አዋርድ መሥራች እና ሥራ አስኪያጅ በፕሮግራሙ ላይ የተናገረው

"በሕይወት መቆየት እና በሕይወት መኖር ይለያያል። እኔ በሕይወት መኖር የጀመርኩት ዛሬ ነው። ይሁንና ልጄ፣ አባቱ የተነጠቀውን ሕይወት ለማኖር ዮናስ ብርሃነ መዋ ሲል አኑሮኛል። ልጄን በእናንተ ፊት በክብር እንዳመሰግነው ፍቀዱልኝ"
ብርሃነ መዋ

መረጃ ህይወት ነው፣ ይህንንም መረጃ ለጓደኞቻችሁ#Share በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ


t.me/emsmereja
t.me/emsmereja
t.me/emsmereja
2.5K views07:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-10 10:12:09 ሰሞኑን ኹለት ሰዎች በጸጥታ ኃይሎች ተመትተው ሲገደሉ የሚያሳየው ተንቀሳቃሻ ምስል ባለፈው ዓመት ጥር ወር ላይ የተፈጸመ መሆኑ ተገለጸ 

ከሰሞኑ በማህበራዊ ሚዲያ ሲሰራጭ የነበረውንና ኹለት ሰዎች በጸጥታ ኃይሎች ተመትተው ሲገደሉ የሚያሳየውን ተንቀሳቃሽ ምስል አስመልክቶ ዶይቸ ቬለ የሟች ቤተሰቦችን ጠቅሶ ባወጣው ዘገባ፤ ግድያው የተፈጸመው በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ድባጤ ወረዳ ውስጥ ባለፈው ዓመት ጥር ወር ላይ ነው ብሏል።

የሟች ቤተሰቦች "ባለፈው ዓመት ለተለያዩ ተቋማት፣ ሰብአዊ መብትን ጨምሮ አቤቱታ ብናቀርብም ፍትህ ማግኘት አልቻልንም፣" ሲሉ መናገራቸውም ነው የተገለጸው።

በዚህ ጉዳይ ላይ የኢትየጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የማጣራት ሥራ እየሰራ እንደሚገኝ የተጠቀሰ ሲሆን፤ ኮሚሸኑ ለጊዜው ማብራሪያ እንደማይሰጥ መግለጹም ተጠቁሟል፡፡

ከሰሞኑ በማኅበራዊ መገናኛ ዜደዎች ላይ ሲዘዋወር የነበረው የመከላከያ ሠራዊት የደንብ ልብስ የለበሱ ወታደሮች በጫካ ውስጥ ኹለት ግሰለቦችን ሲገድሉ የሚያሳየው የአንድ ደቂቃ ከአስራ ስድስት ሴኮንድ ተንቀሳቃሽ ምስል አነጋጋሪ የነበረ ሲሆን፤ ድርጊቱ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ድባጤ ወረዳ ጊጶ በሚባል ቀበሌ ውስጥ መፈጸሙ ነው የተገለጸው። ከገዳዮቹ ወታደሮች መካከል የአንዱ ወታደራዊ የደንብ ልብስ ላይ የታተመ የሲዳማ ክልል ባንዲራ ይታያል።

ከተገደሉት ኹለት ሰዎች መካከል አንዱ ታከለ መንገሻ ዱጉማ  እንደሚባሉ እና በዚያው ድባጤ ወረዳ ጫንጮ ቀበሌ ነዋሪ መሆናቸው እንዲሁም ሌላኛው ሀብታሙ አያና የተባሉ ግለሠብ መሆናቸው ተገልጿል።

በጉዳዩ ላይ ከመንግሥት በኩል እስካሁን ምንም ያልተባለ ሲሆን፤ ዶይቼ ቬለ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ማብራሪያ ማግኘት አለመቻሉን ጠቅሷል።
መረጃ ህይወት ነው፣ ይህንንም መረጃ ለጓደኞቻችሁ#Share በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ


t.me/emsmereja
t.me/emsmereja
t.me/emsmereja
2.9K viewsedited  07:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-09 16:58:21 ኮንዶሚኒየም ደርሷቸው “በቀበሌ ቤቶች” ውስጥ የሚኖሩ ግለሰቦች፤ በአንድ ወር ውስጥ ቤቶቹን እንዲያስረከቡ ቀነ ገደብ ተሰጣቸው
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፤ ኮንዶሚኒየም ደርሷቸው “በቀበሌ ቤቶች” ውስጥ የሚኖሩ የከተማዋ ነዋሪዎች እስከ ሰኔ 30 ድረስ የተከራዩዋቸውን ቤቶች እንዲያስረክቡ ቀነ ገደብ አስቀመጠ። የከተማ አስተዳደሩ የሚረከባቸውን እነዚህን የቀበሌ ቤቶች “የደሀ ደሀ” ተብለው ለተለዩ ነዋሪዎች ለማከፋፈል እቅድ መያዙን አስታውቋል።

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የግንባታ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ቶማስ ደበሌ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” እንደተናገሩት፤ የቀበሌ ቤቶቻቸውን አስረክበው ወደ ኮንዶሚኒየም ቤት እንዲገቡ ደብዳቤ የተሰጣቸው የከተማይቱ ነዋሪዎች፤ በየካቲት 2011 ዓ.ም እና በዘንድሮ ዓመት ህዳር ወር ላይ ዕጣ የወጣላቸው ዕድለኞች ናቸው። በቀድሞ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ የሚመራው አስተዳደር፤ በየካቲት 2011 ዓ.ም. ዕጣ ያወጣባቸው የኮንዶሚኒየም ቤቶች ብዛት 51,200 ገደማ ነበር።

በወቅቱ ለነዋሪዎች ሊተላለፉ በዝግጅት ላይ እያሉ በተነሳባቸው ተቃውሞ ምክንያት ከባለ እድለኞች ጋር ርክክብ ሳይፈጸምባቸው የዘገዩት እነዚህ የኮንዶሚኒየም ቤቶች፤ የቁልፍ ርክክብ የተፈጸመባቸው ግን ባለፈው ዓመት ነው። የከተማ አስተዳደሩ በዚህ ዓመት ህዳር ወር በ25,791 ቤቶች ላይ ዕጣ ያወጣ ሲሆን፤ ከዕድለኞች ጋር ውል የመዋዋል ስራው የተከናወነው ደግሞ ካለፈው ጥር እስከ ግንቦት ወር ባሉት  አምስት ወራት ውስጥ ነበር።

በከተማ አስተዳደሩ የሚገነቡ የኮንዶሚኒየም ቤቶችን የመከታተል ኃላፊነት ያለበት የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን፤ የኮንዶሚኒየም ዕጣ ወጥቶባቸው ነገር ግን እስካሁን ድረስ ያላለቁ 139 ሺህ ቤቶች ላይ የማጠናቀቂያ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን የኮርፖሬሽኑ የግንባታ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጸዋል። ኮርፖሬሽኑ በ32 የግንባታ ሳይቶች ላይ የሚገኙትን እነዚህ ቤቶች ሙሉ ለሙሉ ለማጠናቀቅ፤ ባለፉት አራት ወራት ሲሰራ መቆየቱን አስረድተዋል።
መረጃ ህይወት ነው፣ ይህንንም መረጃ ለጓደኞቻችሁ#Share በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ


t.me/emsmereja
t.me/emsmereja
t.me/emsmereja
3.7K views13:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-09 16:55:09
ጋዜጠኛ ቴድሮስ አስፋውን ጨምሮ 4 ግለሰቦች የዋስትና መብት ተፈቀደላቸው

አርብ ሰኔ 2 ቀን 2015 (EMS) የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት፤ ጋዜጠኛ ቴድሮስ አስፋውን ጨምሮ በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው ምርመራ ሲደረግባቸው የቆዩ አራት ግለሰቦችን የዋስትና መብት ፈቅዷል።

የዋስትና መብት የተፈቀደላቸው ግለሰቦች፤ ጋዜጣኛ ቴድሮስ አስፋው፣ ሳሮን ቀባው፣ ጌታቸው ወርቄ እና ጌታዎይ አለሙ ናቸው።

የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤሕግ፤ በተጠርጣሪዎች ላይ ምርመራ የቀጠለ ቢሆንም ዋስትና ቢፈቀድላቸው እንደማይቃወም አመልክቷል።

በዚህም መሠረት ፍርድ ቤቱ፤ ለቴድሮስ አስፋው የ15 ሺሕ ብር፣ ለሳሮን ቀባው የ3 ሺሕ ብር እንዲሁም ጌታቸው ወርቄ እና ጌታዎይ አለሙ እያንዳንዳቸው የ10 ሺሕ ብር ዋስ አስይዘው ከእሥር እንዲፈቱ ማዘዙን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

ዐቃቤ ሕግ በአጠቃላይ 51 በሽብር ወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦች ላይ ክስ የመሰረተ ሲሆን፤ 24 ተጠርጣሪዎች ላይ ባሉበት፣ በቀሪዎቹ 27 ተጠርጣሪዎች ላይ ደግሞ በሌሉበት ክስ እንደተመሰረተባቸው ተገልጿል።
መረጃ ህይወት ነው፣ ይህንንም መረጃ ለጓደኞቻችሁ#Share በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ


t.me/emsmereja
t.me/emsmereja
t.me/emsmereja
3.4K viewsedited  13:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-09 16:32:19 በባህሬን በአሰሪዋ ተደብድባና ተደፍራ ያረገዘችው ኢትዮጵያዊ ወጣት ፍትህ እንድታገኝ መደረጉ ተገለጸ

ወጣቷ የስድስት ወር እርጉዝ መሆኗ ተረጋግጧል
=======#=======
አርብ ሰኔ 2 ቀን 2015 (EMS) በባህሬን አንዲት ወጣት 4 ዓመት ሙሉ ስትሰራበት የነበረበት ቤት ውስጥ በአሰሪዋ በመደፈር፣ በመደብደብ እና የመግደል ዛቻ ሲደርስባት በመቆየቱና የድረሱልኝ ጥሪዋን በማሰማቷ ምክንያት፤ በባህሬን የኢፌዲሪ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት እና በባህሬን የኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ በጋራ በመሆን ለሚመለከተው የሕግ አካል በማመልከት ፍትሕ እንድታገኝ መደረጉ ተገልጿል።

ይሁን እንጂ አሰሪዋ “አልደፈርኩም” ብሎ የሕክምና ወረቀት በማቅረብ ጉዳዩ ትኩረት እንዳያገኝ በማድረግ ወጣቷን ወደ ኢትዮጵያ ለመላክ ሙከራ ያደረገ ቢሆንም፤ ጽ/ቤቱና በባህሬን የኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ ከ6 ወራት በላይ በመከራከርና የDNA ምርመራ በማስደረግ በተገኘው የምርመራ ውጤት መሰረት፤ ወጣቷ የስድስት ወር እርጉዝ መሆኗና የእርሱም ልጅ እንደሆነ ፍርድ ቤት መወሰኑ ተነግሯል።

በዚህም መሠረት፤ የወጣቷን እና የልጇንና መብት በማስከበር 64 ሺሕ 800 የባህሬን ዲናር (9 ሚሊዮን 344 ሺሕ 886 ብር) በየአራት ዓመት ክፍያ እንዲከፍል አሰሪው የተስማማ ሲሆን፤ ለመጀመሪያ አራት ዓመት የሚሆን ቅድመ ክፍያ 14 ሺሕ 200 የባህሬን ዲናር (2 ሚሊዮን 47 ሺሕ 799 ብር) በመቀበል ፍርድ ቤት ፈርሞበት ወጣቷ ፍትህ እንድታገኝ መደረጉን በባህሬን የኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ አስታውቋል።
መረጃ ህይወት ነው፣ ይህንንም መረጃ ለጓደኞቻችሁ#Share በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ


t.me/emsmereja
t.me/emsmereja
t.me/emsmereja
3.3K viewsedited  13:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-09 13:25:36 ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር የሚያዋሳናትን ድንበር መዝጋቷ ተገለጸ

አርብ ሰኔ 2 ቀን 2015 (EMS) ኤርትራ ከኢትዮጵያ እና ጅቡቲ ጋር የሚያዋሳናትን ድንበር መዝጋቷን የእንግሊዝ መንግሥት አስታውቋል።

የእንግሊዝ መንግሥት ኤርትራ የኢትዮጵያ እና ጅቡቲ ድንበሯን የዘጋችበትን ምክንያት ያልገለጸ ሲሆን፤ በኤርትራ ግን የሽብር ጥቃት ሊፈጸም ይችላል የሚል ስጋት እንደሌለዉ ገልጿል።

የእንግሊዝ የውጭ የጋራ ደህንነትና እድገት ቢሮ፤ የብሪታኒያ ዜጎች ከኤርትራ ድንበር 25 ኪሎ ሜትር እርቀት ባላቸዉ ማንኛውም አካባቢዎች እንዳይንቀሳቀሱ፣ በኤርትራ የሚገኙ የእንግሊዝ ዲፕሎማቶችና ዜጎች አገሪቱን በቶሎ ለቅቀዉ እንዲወጡ እንዲሁም ወደ ኤርትራ ለመጓዝ ያሰቡ ጉዟቸዉን እንዲሰርዙ አሳስቧል።

በተጫማሪም በኤርትራ የሚገኙ የእንግሊዝ ዜጎች ከታሰሩ፣ ጥቃት ከደረሰባቸው ወይም ከተገደሉ በአስመራ ለሚገኘው የእንግሊዝ ኤምባሲ ደውለው እንዲያሳውቁ አስገንዝቧል።

በኤርትራ የሚገኙ ቤተሰቦቻቸው ሁኔታ ያሳሰባቸው የእንግሊዝ ዜጎችም ለመንግሥት እንዲያሳውቁ ተነግሯቸዋል።

በአንጻሩ ኤርትራ ከሱዳን ጋር የሚያዋስናት ድንበር ክፍት መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ የሱዳን ግጭት ከመጀመሩ አስቀድሞ ፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና የሱዳን ፈጥኖ ደራሸ ሃይሎች መሪ ጄኔራል መሃመድ ሃምዳን ዳጋሎ ውይይት ማድረጋቸው ይታወሳል።

ለሦስት አስርት ዓመታት ድንበር ዘግተው የኖሩት ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ግንኙነታቸው መሻሻል አሳይቷል።

በሰሜኑ ጦርነት ወቅትም የኤርትራ ጦር አባላት ከኢትዮጵያ መከላካያ ሰራዊት ጋር በመሆኑ በትግራይ ክልል ከህወሓት ታጣቂዎች ጋር ሲዋጉ እንደነበር ሲነገር ቆይቷል።
በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሰረት የኤርትራ ሃይሎች ከኢትዮጵያ ትግራራይ ክልል ሙሉ በሙሉ መውጣት ያለባቸው ሲሆን፣ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አሁንም ብዙ አካባቢዎች በኤርትራ ሃይሎች መያዛቸውን ይገልጻል።

ከቀናት በፊት የኤርትራ መንግሥት የኢትዮጵያና ኤርትራን ግንኙነት ለማበላሸት የሚጥሩ ሃይሎች መኖራቸውን ጠቅሶ፤ “ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ” ሲል ማሳሰቡ ይታወሳል።

ከሰሜኑ ጦርነት ማብቃት ወዲህ ኢትዮጵያ ከአሜሪካ እና ምዕራባውያን አገራት ጋር ያላት ግንኙነት መሻሻል ማሳየቱ የሚገለጽ ሲሆን፤ ኤርትራም ከቻይናና ሩስያ ጋር ያላትን ግንኙንት ማጣናክሯ ይጠቀሳል።

በሌላ በኩል፤ በሱዳን ጥገኝነት ጠይቀው ከሚገኙ 130 ሺሕ በላይ ኤርትራውያን ስደተኞች “ታግተን ወደ ኤርትራ እንወሰዳለን” የሚል ከፍተኛ ስጋት ውስጥ መሆናቸው ተገልጿል።

በዚህም ብዙዎቹ ከዚህ ስጋት ለማምለጥ እንዲሁም በሱዳን ያለውን ቀውስ ሸሽተው በጎንደር በኩል ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ መሆናቸው ተመላክቷል።
መረጃ ህይወት ነው፣ ይህንንም መረጃ ለጓደኞቻችሁ#Share በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ


t.me/emsmereja
t.me/emsmereja
t.me/emsmereja
3.5K viewsedited  10:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-09 13:13:16 በሱሉልታ ከተማ በሸኔ ታጣቂዎች ቁጥራቸው በውል ያልታውቁ ሰዎች ታፍነው መወሰዳቸው ተገለጸ

በቅርቡ በተዋቀረው የሸገር ከተማ አስተዳደር ሥር በሚገኘው የሱሉልታ ክፍለ ከተማ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎች በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ታፍነው መወሰዳቸውን ነዋሪዎች ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል።

ነዋሪዎቹ እንደገለጹት፤ በሱሉልታ ክፍለ ከተማ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት በማለት በሚጠራው እና በመንግሥት “ኦነግ ሸኔ” በመባል በአሸባሪነት በተፈረጀው ታጣቂ ቡድን የሚፈጸሙ መሰል ድርጊቶች እየተበራከቱ መምጣታቸውን አስረድተዋል፡፡

በዚህም “ከአንድ ሳምንት በፊት በአንድ ምሽት ብቻ ከሱሉልታ ክፍለ ከተማ ኪዳነምሕረት ቤተክርስቲያን አካባቢ ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ላይ ቁጥራቸው ከ20 በላይ የሚሆኑ ሰዎች በሸኔ ታጣቂዎች ታፍነው ተወስደዋል፡፡” ሲሉ ነው የገለጹት።

ሰዎቹ በተወሰዱበት ዕለትም ምንም አይነት የመሳሪያ ድምጽ ባለመሰማቱ የጸጥታ አካላት ደርሰው ሊያስጥሏቸው እንዳልዳቻሉ ጠቅሰዋል።

ረቡዕ ግንቦት 30/2015 እንዲሁ ቁጥራቸው ያልታወቁ ሰዎች ምሽት ላይ ታግተው መወሰዳቸውን ተናግረዋል፡፡

የተወሰዱት ሰዎችም እስካሁን ድረስ ያሉበት አይታወቅም የተባለ ሲሆን፤ አጋቾችም ይህን ያህል ብር አምጡና እንለቃቸዋለን በማለት እየተደራደሩ እንደሚገኙ ተገልጿል።

ነዋሪዎቹ ታጣቂ ቡድኑ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በአካባቢው እና በሌሎች አዋሳኝ ወረዳዎች በስፋት እንደሚንቀሳቀስ የተናገሩ ሲሆን፤ ትግሉም ከሌላ አካል ጋር ሳይሆን ንጹሃን ዜጎችን እያፈነ ገንዘብ መጠየቅ ነው ሲሉ አብራርተዋል፡፡

አዲስ ማለዳ በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ ለማግኘት ለሱሉልታ ክፍለ ከተማ የሰላም እና ጸጥታ ዘርፍ ኃላፊ ታገል መለሠ በተደጋጋሚ ብትደውልም፤ ስልክ ባለማንሳታቸው ምላሻቸውን ማካተት አልቻለችም፡፡
መረጃ ህይወት ነው፣ ይህንንም መረጃ ለጓደኞቻችሁ#Share በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ


t.me/emsmereja
t.me/emsmereja
t.me/emsmereja
3.4K viewsedited  10:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-09 07:41:05 ዓርብ ጠዋት! ሰኔ 2/2015 ዓ.ም የEMS ዕለታዊ ዜናዎች

1፤ የኢትዮጵያ መንግሥት እና የአሜሪካ ዓለማቀፍ ተራድዖ ድርጅት ዩኤስአይዲ "እጅግ አሳሳቢ" የኾነውን የዕርዳታ ምግብ ላልተፈለገለት ዓላማ ማዋልን እየመረመሩ መኾኑን ትናንት ማምሻውን ባወጡት የጋራ መግለጫ አስታውቀዋል። ኢትዮጵያና አሜሪካ የወንጀሉን ፈጻሚዎች ተጠያቂ ለማድረግ እንደሚሠሩና፣ ወደፊት "አስተማማኝ የዕርዳታ ምግብ ሥርጭት ሥርዓት" ለመዘርጋት እንደሚተባበሩ ገልጠዋል። ሁለቱ መንግሥታት እዚህ ስምምነት ላይ የደረሱት፣ የተራድዖ ድርጅቱ ከፍተኛ ምግብ ዕርዳታ ዝርፊያ በአገሪቱ ስለመፈጸሙ በምርመራ ማረጋገጡና ለኢትዮጵያዊያን ተረጂዎች የሚሰጠውን ዕርዳታ ማቋረጡ ከተዘገበ በኋላ ነው።

2፤ የኢትዮጵያ መንግሥት በቀጣዩ በጀት ዓመት ለመከላከያ 50 ቢሊዮን ብር መመደቡን የበጀት ዝርዝሩን የተመለከቱ የዜና ምንጮች ዘግበዋል። መንግሥት በጦርነቱ የወደሙ መሠረተ ልማቶችን መልሶ ለመገንባት ደሞ፣ ለቀጣዩ ዓመት 20 ቢሊዮን ብር መመደቡ ተገልጧል። ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው ረቂቅ በጀት ለትግራይ ክልል 12 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር የፌደራል ድጎማ የመደብ ሲኾን፣ ለአማራ 45 ነጥብ 1 እንዲኹም ለአፋር ክልል 6 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር መድቧል ተብሏል። ትግራይ ላለፉት ሁለት ዓመታት የፌደራል ድጎማ አለማግኘቷ ይታወሳል።

3፤ የሱዳን ተፋላሚ ወገኖች ካርቱም ውስጥ የሚያካሂዱት ውጊያ ተባብሶ መቀጠሉን የውጭ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ባለፉት ቀናት በደቡባዊ ካርቱም ውጊያ የተካሄደው፣ "ያርሙክ" የተሰኘውን ግዙፍ የጦር መሳሪያ ፋብሪካ ለመቆጣጠር እንደኾነ ዘገባዎች አመልክተዋል። ፈጥኖ ደራሽ ሠራዊቱ ረቡዕ'ለት የጦር መሳሪያ ፋብሪካውን መቆጣጠሩን ገልጦ የነበረ ሲኾን፣ ሱዳን ትሪቡን ግን ጦር ሠራዊቱ መልሶ ፋብሪካውን መቆጣጠሩን ዓይን እማኞችን ጠቅሶ ዘግቧል። ጦር ሠራዊቱ ከካርቱም ውጭ ተጨማሪ ሠራዊት እየገባለት እንደኾነ ተሰምቷል።

4፤ ተመድ በምሥራቃዊ ኮንጎ ያሠማራውን ሰላም አስከባሪ ጦር "ባስቸኳይ" ከአገሪቱ እንደሚያስወጣ ማስታወቁን የፈረንሳይ ዜና ወኪል ዘግቧል። የተመድ የሰላም ማስከበር ሃላፊ፣ ሰላም አስከባሪ ሠራዊቱ በኮንጎ መንግሥት ጥያቄ መሠረት ባስቸኳይና ኃላፊነት በተሞላበት መንገድ እንደሚወጣ መናገራቸውን ዘገባው ጠቅሷል። ባለሥልጣኑ፣ የተመድ ጦር ሲወጣ፣ ኮንጎ አማጺ ቡድኖች የደቀኑባትን ስጋት ራሷ ለመመከት መዘጋጀት አለባት ማለታቸውን ዘገባው አመልክቷል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሰላም አስከባሪው ኃይል ሰላማዊ ዜጎችን ከአማጺዎች ጥቃት መከላከል አልቻለም በሚል ከነዋሪዎች ጋር ተደጋጋሚ ግጭት ውስጥ ሲገባ ቆይቷል። መረጃ ህይወት ነው፣ ይህንንም መረጃ ለጓደኞቻችሁ#Share በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ


t.me/emsmereja
t.me/emsmereja
t.me/emsmereja
3.8K views04:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-08 22:20:22 አሜሪካ በአማራ እና ኦሮሚያ ክልል ያለው ውጥረት እንዲረግብ ጠየቀች

ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነቷን ይበልጥ ማሳደግ እንደምትፈልግም ነው ያስታወቀችው።

የአሜሪካና የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በሳኡዲ ውይይት አድርገዋል።
መረጃ ህይወት ነው፣ ይህንንም መረጃ ለጓደኞቻችሁ#Share በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ


t.me/emsmereja
t.me/emsmereja
t.me/emsmereja
4.1K views19:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ