Get Mystery Box with random crypto!

EMS Mereja

የቴሌግራም ቻናል አርማ emsmereja — EMS Mereja E
የቴሌግራም ቻናል አርማ emsmereja — EMS Mereja
የሰርጥ አድራሻ: @emsmereja
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 14.57K
የሰርጥ መግለጫ

👉 መረጃዎች፣ጥያቄዎች፣ አስተያየቶችና የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት ከፈለጉ በዚህ ያናግሩን👉 t.me/infoetrobot
👉 የዕለታዊ ዝግጅቶችና ዜናዎች በተባባሪ አቅራቢዎች እንዲደርሷችሁ👇👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@HAQMEDIA12
Subscribe ያድርጉ

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-06-01 19:53:58 ሐሙስ ምሽት! ግንቦት 24/2015 ዓ.ም የEMS ዐበይት ዜናዎች

1፤ ሂውማን ራይትስ ዎች የአማራ ክልል ኃይሎች በሚቆጣጠሩት የምዕራብ ትግራይ አካባቢ በትግራይ ተወላጆች ላይ የዘር ማጽዳት ድርጊቶችን እየፈጸሙ መኾኑን በምርመራ አረጋግጫለኹ ሲል ዛሬ ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል። ሪፖርቱ፣ ተበዳዮች "ለዘፈቀድ እስር፣ ድብደባና በእስር ቤት ለሕልፈት" መዳረጋቸውን ገልጧል። ድርጅቱ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈጻሚ የጸጥታ ኃይሎችና የጸጥታ ኃላፊዎችን "ከሥራ እንዲያግድና ምርመራ አድርጎ በሕግ እንዲጠይቅም" ጠይቋል። ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱና በላይ አያሌው የተባሉ ግለሰቦች "በዘፈቀደ እስር፣ ድብደባና በግዳጅ የማፈናቀል ድርጊታቸው ቀጥለውበታል" በማለትም ሪፖርቱ ከሷል። ድርጅቱ፣ የሪፖርቱን የመጀመሪያ ደረጃ ግኝት መንግሥት አስተያየት እንዲሰጥበት ልኮ ምላሽ አለማግኘቱንም ገልጧል።

2፤ ኢሰመጉ የአዲስ አበባ እና በኦሮሚያ ክልል በሸገር እና አዳማ ከትሞች መንግሥት 111 ሺህ 811 ቤቶችን "በግዳጅ" ማፍረሱን ትናንት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ድርጅቱ ይህን ያረጋገጠው፣ ከጥቅምት እስከ ግንቦት 2015 ዓ፣ም ባካሄደው ምርመራ መኾኑን ገልጧል። ኢሰመጉ፣ በአካል ምልከታና ተበዳዮችን በማናገር አጠናቀርኩት ያለው ሪፖርት፣ በቤት ፈረሳው ወቅት "ድብደባ"፣ "እስራት"፣ "የጥላቻ ንግግርን" ጨምሮ በተበዳዮች ላይ ተፈጽሙዋል ያላቸውን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ዘርዝሯል። በአዲስ አበባና ሸገር ከተሞች ቤቶች የፈረሱባቸው በርካታ ነዋሪዎች ከመንግሥት የመብራትና ውሃ አገልግሎት ያገኙ እንደነበር ሪፖርቱ ጠቅሷል። በአዲስ አበባ ከኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ብቻ ከ10 ሺህ በላይ ቤቶች ስለመፍረሳቸው አቤቱታ መቀበሉን ኢሰመጉ ገልጧል።

3፤ የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ለ5 ዓመታት አቋርጦት የቆየውን የመሬት ሊዝ ጨረታ ዛሬ በድጋሚ መጀመሩን አስታውቋል። አስተዳደሩ ባሁኑ ወቅት በሁሉም ክፍለ ከተሞች ከ14 ሄክታር በላይ በሊዝ ጨረታ ማዘጋጀቱን ቢሮው ገልጧል።
ቢሮው ለሊዝ ጨረታው 24 ሺህ የጨረታ ሰነዶችን ማዘጋጀቱን ገልጦ፣ ዛሬ የመጀመሪያው ዙር የሊዝ ጨረታ በቦሌ፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ ልደታ፣ አዲስ ከተማ፣ ቂርቆስ፣ ጉለሌ እና የካ ክፍለ ከተሞች እንደተጀመረ አስታውቋል።

4፤ ፌደራል ፖሊስ በፌደራል ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ መልካም ስም ላይ ያነጣጠረ "ሐሰተኛ መረጃ" በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች እየተሠራጨ ነው ሲል ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ፌደራል ፖሊስ፣ በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የሚሠራጨው ሐሰተኛ መረጃ የፌደራል ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ የወንጀል ተጠርጣሪዎችን "በኢሰብዓዊ አያያዝ" ይይዛል የሚል መኾኑን ገልጧል። ይህንኑ ሐሰተኛ መረጃ የሚያሠራጩት፣ "በአሸባሪነት ተጠርጥረው እንደሚፈለጉ ስም ዝርዝራቸው በይፋ ከተገለጹት መካከል" ናቸው ያለው ፖሊስ፣ ዓላማው የወንጀል ምርመራ መምሪያው በሽብር ተጠርጣሪዎች ላይ እያካሄደ ያለውን "የምርመራ ሂደት ማደናቀፍ" ነው ብሏል። ፌደራል ፖሊስ ጨምሮም፣ ሐሰተኛ መረጃ በሚያሠራጩ ግለሰቦች ላይ ርምጃ መውሰዱን እንደሚገፋበት ገልጧል።

5፤ የአሜሪካ ግምጃ ቤት ከሱዳን ጦር ሠራዊት እና ፈጥኖ ደራሽ ሠራዊት ጋር ግንኙነት ባላችሁ አራት ወታደራዊ ነክ ኩባንያዎች ላይ ማዕቀብ መጣሉን ዛሬ አስታውቋል። ማዕቀብ የተጣለባቸው፣ ከፈጥኖ ደራሹ ሠራዊት ጋር ግንኙነት ያላቸው ሁለት ኩባንያዎች እና ከጦር ሠራዊቱ ጋር ግንኙነት ያላቸው ሌሎች ሁለት ኩባንያዎች ናቸው። ማዕቀቡ፣ ኩባንያዎቹ በአሜሪካ ያላቸውን ገንዘብና ሃብት ማንቀሳቀስ እንዳይችሉና ሁለቱ ተዋጊ ኃይሎች ለጦርነቱ የሚኾናቸውን ገንዘብና ሌሎች ቁሳቁሶች እንዳያገኙ እንደሚያደርግ ግምጃ ቤቱ ገልጧል። የተኩስ አቁም ስምምነቶች እንዲጣሱና ግጭቱ እንዲቀጥል አድርገዋል በተባሉ የአገሪቱ መሪዎች ላይም የቪዛ ገደብ ተጥሎባቸዋል።

6፤ ንግድ ባንክ ዛሬ የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋ 54 ብር ከ3204 ሳንቲም እና መሸጫ ዋጋው 55 ብር ከ4068 ሳንቲም ሆኖ እንደዋለ በድረገጹ ገልጧል። የአንድ የእንግሊዝ ፓውንድ መግዣ ዋጋ ደሞ 64 ብር ከ1394 ሳንቲምና መሸጫው 65 ብር ከ4222 ሳንቲም ሆኗል። በተመሳሳይ አንድ ዩሮ በ57 ከ9870 ሳንቲም ተገዝቶ፣ በ59 ብር ከ1467 ሳንቲም ሲሸጥ መዋሉን ባንኩ ገልጧል። #ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                  
@emsmereja
4.9K views16:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-01 07:01:57 ሐሙስ ጠዋት! ግንቦት 24/2015 ዓ.ም የEMS ዐበይት ዜናዎች

1፤ በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ጢዮ ወረዳ ማንነታቸው ያልታወቀ ታጣቂዎች ባለፈው ዕሁድ ምሽት አራት ሰዎችን መግደላቸውን ዶይቸቨለ የዓይን እማኞችን ጠቅሶ ዘግቧል። በጥቃቱ ከተገደሉት ሰዎች መካከል፣ የጨፌ ሚስማ ደራ አማኑኤል ቤተ ክርስቲያን ሁለት ካህናት እንደሚገኙበት የዓይን እማኞች መናገራቸውን ዘገባው ጠቅሷል። ታጣቂዎቹ ሌሎች ሁለት ሰዎችን አግተው ከወሰዱ በኋላ፣ በከፍተኛ ገንዘብ ክፍያ እንደለቀቋቸው መስማቱንም ዘገባው አመልክቷል። የዓይን እማኞች ጥቃቱን የፈጸሙት የ"ኦነግ ሸኔ" ቡድን አባላት ናቸው ብለው እንደሚያምኑ ገልጸዋል ተብሏል።

2፤ የገዥው ብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ “የግል እና የቡድን ጥቅሞቻቸውን በሃይል ለማስከበር" የሚሞክሩ ኃይሎችን በቁርጠኝነት ለመታገል መወሰኑን ትናንት በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በመደበኛ ስብሰባው ማጠቃለያ ላይ በሰጠው መግለጫ፣ የሕግ የበላይነትን ለማስከበር፣ በነጻነት አጠቃቀምና አያያዝ ረገድ የሚታየውን መዛነፍ በአግባቡ ለመምራትና የመንግሥትን ኃይልን በብቸኝነት የመጠቀም መብትን በተገቢው መጠን ሥራ ላይ ለማዋል መወሰኑን ገልጧል። ፓርቲው፣ "የግልና የቡድን ፍላጎታቸውን በኃይል ማስፈጰም የሚፈልጉ" እና ሌ "ጽንፈኛ ኃይሎች ኅብረ ብሄራዊ አገራዊ አንድነትን በጠንካራ መሠረት ላይ ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ላይ ስጋት ፈጥረዋል” ብሏል። በሕዝቡ የነጻነት አጠቃቀምና አስተዳደር መካከል ያለውን ሚዛን በመጠበቅ ረገድ፣ ፓርቲው ውስንነቶች እንነበሩበትም በመግለጫው ላይ አመልክቷል።

3፤ በመጋቢት 2011 ዓ፣ም ከኢትዮጵያ ወደ ኬንያ ሲጓዝ ኢትዮጵያ ውስጥ በተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን የሞቱ ሰዎች ቤተሰቦች ሟቾቹ ከአደጋው በፊት ለደረሰባቸው "ሥቃይ" ካሳ መጠየቅ ይችላሉ ሲል አንድ የአሜሪካ ፍርድ ቤት ዳኛ መወሰናቸውን ሮይተርስ ዘግቧል። የፍርድ ቤቱ ዳኛ ውሳኔውን የሰጡት፣ ሟቾቹ አውሮፕላኑ መሬት ላይ ከመከስከሱ ቀደም ብሎ ባሉት ደቂቃዎች ሊሞቱ መኾኑን ተረድተው እንደነበር "ምክንያታዊ ድምዳሜ ላይ መድረስ ይቻላል" በማለት ነው። በአደጋው 157 መንገደኞች መሞታቸው ይታወሳል። ቦይንግ ኩባንያ ለአደጋው የወንጀል ተጠያቂነት እንዳይኖርበት ክአሜሪካ ፍትህ ሚንስቴር ጋር ቀደም ሲል ስምምነት ላይ የደረሰ ሲኾን፣ በምትኩ 2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ካሳ እና ቅጣት ለተጎጂዎች፣ ለአሜሪካ መንግሥትና ለተለያዩ አየር መንገዶች ለመክፈል ተስማምቷል።

4፤ የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ትናንት ሞስኮ ውስጥ እንደተወያዩ የኤርትራ መንግሥት ቃል አቀባይ የማነ ገ/መስቀል በትዊተር ገጻቸው አስታውቀዋል። የኢሳያስ እና ፑቲን ውይይት ያተኮረው፣ በሁለትዮሽ እና ዓለማቀፋዊ ጉዳዮች እንዲሁም ሁለቱ አገራት ትኩረት በሚሰጧቸው የጋራ ጉዳዮች ዙሪያ መኾኑን የማነ ገልጸዋል። ፕሬዝዳንት ፑቲን፣ ኢሳያስ ሩሲያ በነሐሴ በምታስተናግደው የአፍሪካና ሩሲያ የመሪዎች ጉባኤ ላይ እንዲሳተፉ እንደጋበዟቸው ተገልጧል። #ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                  
@emsmereja
4.9K views04:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-31 20:28:57 ረቡዕ ምሽት! ግንቦት 23/2015 ዓ.ም የEMS ዐበይት ዜናዎች

1፤ በአማራ ክልል ምሥራቅ ጎጃም ዞን ደብረ ኤሊያስ ወረዳ መልክዓ አንድነት በተባለ ገዳም ሰሞኑን ለአምስት ቀናት በተከታታይ በተፈጠረ ግጭት በርካታ ሰዎች እንደተገደሉ ዶይቸቨለ ዘግቧል። በግጭቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ምዕመናን እንደሞቱና እንደቆሰሉ እንዲኹም ከ200 በላይ የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች ጉዳት እንደደረሰባቸው የዓይን ምስክሮችና የሆስፒታል ምንጮች መናገራቸውን ዘገባው ጠቅሷል። በገዳሙ ምዕመን ላይ የተፈጸመው ጥቃት፣ "በከባድ መሳሪያ የታገዘ" እንደነበርና ከሞትና ከመቁሰል የተረፉት ከገዳሙ ወጥተው እንደተበታተኑ መስማቱን ዘገባው ገልጧል። ዜና ምንጩ፣ የግጭቱ መነሻ ምን እንደኾነ ግን የተጣራ መረጃ አለማግኘቱንና ግጭቱ ግን ትናንት ቆሟል መባሉን አመልክቷል።

2፤ በኢትዮጵያ መንግሥት እና በኦሮሞ ንጻነት ሠራዊት መካከል ታንዛኒያ ላይ ተጀምሮ የነበረው የሰላም ንግግር እስካኹን እንደተቋረጠ መኾኑን የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ መለስ ዓለም ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ መናገራቸውን የአገር ውስጥ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። መለስ በመንግሥትና በቡድኑ መካከል ሁለተኛ ዙር ንግግር የሚቀጥል ከኾነ፣ መንግሥት ለመገናኛ ብዙኀን ይፋ ያደርጋል ማለታቸውን ዘገባዎች ጠቅሰዋል። የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊትም፣ ባሁኑ ወቅት ከመንግሥት ጋር እየተካሄደ ያለ ወይም በእቅድ የተያዘ ንግግር የለም ሲል ትናንት በትዊተር ገጹ ባሠራጨው መረጃ ገልጦ ነበር።

3፤ ኢሰመጉ መንግሥት ግንቦት 18 ቀን በታላቁ አንዋር መስጅድ አካባቢ የመስጅዶችን መፍረስ በተቃወሙ ሙስሊሞች ላይ “የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በፈጸሙ" የጸጥታ አካላት ላይ ማጣራት አድርጎ ጥፋተኞችን በሕግ እንዲጠይቅ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ጠይቋል። ኢሰመጉ፣ በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ክልል በሸገር ከተማ አስተዳደር መንግሥታዊ አካላት መስጅዶችን እያፈረሱ ስለመኾኑ መረጃ እንዳገኘ ገልጧል። በአጠቃላይ ከ19 በላይ መስጅዶች እንዲፈርሱ እንደተደረገ ከኦሮሚያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት መስማቱን ኢሰመጉ በመግለጫው ጠቅሷል።

4፤ በኦሮሚያ ክልል የምሥራቅ ሸዋ ዞን ዱግዳ ወረዳ አርሶ አድሮች በቲማቲምና አትክልት የእርሻ ማሳችን ላይ የበጋ ስንዴ እንድናመርት መንግሥት አስገድዶናል ማለታቸውን ሪፖርተር ዘግቧል። በወረዳው ፍራፍሬ፣ ቃሪያ፣ ሽንኩርትና ቲማቲም እንዳይመረት የግብርና ተቆጣጣሪዎች እንደከለከሉ የገለጡት አርሶ አደሮች፣ ቲማቲምና ሽንኩርት የተከሉ አንዳንድ አርሶ አደሮች እንደታሠሩ መግለጣቸውን ዘገባው አመልክቷል። የወረዳው ግብርና ቢሮ በበኩሉ፣ አርሶ አደሮች ባንድ ማሳ ላይ በአንድ ዓመት የበጋ ስንዴንና አትክልቶችን በየተራ እንዲያመርቱ ከአርሶ አደሮቹ ጋር መግባባት ላይ ተደርሷል ማለቱን ዘገባው ጠቅሷል። ዘንድሮ በወረዳው በዘር ከተሸፈነው 25 ሺህ 771 ሄክታር መሬት ውስጥ 25 ሺህ 721 ሄክታር መሬት በበጋ ስንዴ እንደተሸፈነ ዜና ምንጩ የወረዳውን ግብርና ቢሮ በምንጭነት ጠቅሷል።

5፤ የሱዳን ጦር ሠራዊት ከፈጥኖ ደራሹ ሠራዊት ጋር በአሜሪካና ሳዑዲ ዓረቢያ አስተባባሪነት ከሚካሄደው ንግግር መውጣቱን ሮይተርስ ዲፕሎማቲክ ምንጮቻችን ጠቅሶ ዘግቧል። የአገሪቱ ጦር ሠራዊት ዋና አዛዥ ጀኔራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን፣ ፈጥኖ ደራሹ ሠራዊት ወደ ምክንያታዊነት የማይመለስ ከኾነ፣ ሙሉ ወታደራዊ አቅማችን እንጠቀማለን በማለት አስጠንቅቀዋል። ጦር ሠራዊቱ ከንግግሩ የወጣው፣ ፈጥኖ ደራሹ ሠራዊት ለእስካኹኖቹ የተኩስ አቁም ስምምነቶች ተገዢ አልኾነም በማለት እንደኾነ የተለያዩ ዘገባዎች ጠቅሰዋል። ጦር ሠራዊቱ ይህን ያለው፣ ከሰኞ ምሽት ጀምሮ ለአምስት ቀናት የተራዘመው ተኩስ አቁም ሳይጠናቀቅ ነው።

6፤ የተመድ ጸጥታው ምክር ቤት በደቡብ ሱዳን ላይ የጣለውን የጦር መሳሪያ ማዕቀብ በድጋሚ አራዝሟል። ጸጥታው ምክር ቤት የሰላም ስምምነቱን አደናቅፈዋል በተባሉ አንዳንድ ባለሥልጣናትና ወታደራዊ ባለሥልጣናት ላይ የጣለውን የጉዞና የገንዘብ ዝውውር ማዕቀብ ጭምር ማራዘሙን ገልጧል። ጸጥታው ምክር ቤት የጦር መሳሪያ ማዕቀቡን ያራዘመው፣ በመንግሥት ጦር ሠራዊት እና በተቃዋሚው ቡድን ተዋጊዎች መካከል የተደረሰው የሰላም ስምምነት ገና ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ባለመኾኑ እንደኾነ ተገልጧል።

7፤ ንግድ ባንክ ዛሬ የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋ 54 ብር ከ3041 ሳንቲም እና መሸጫ ዋጋው 55 ብር ከ3902 ሳንቲም ሆኖ እንደዋለ በድረገጹ ገልጧል። የአንድ የእንግሊዝ ፓውንድ መግዣ ዋጋ ደሞ 64 ብር ከ4469 ሳንቲምና መሸጫው 65 ብር ከ7358 ሳንቲም ሆኗል። በተመሳሳይ አንድ ዩሮ በ58 ከ2683 ሳንቲም ተገዝቶ፣ በ59 ብር ከ4337 ሳንቲም ሲሸጥ መዋሉን ባንኩ ገልጧል። #ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                  
@emsmereja
4.9K views17:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-31 07:16:56 አስደንጋጭ ዜና
99 ካህናት ተገደሉ፣
እንዴት?
በማን?
መቼ?
የከንቲባው ጋርድ የጠለፋትን ልጅ ይዞ የትውልድ ሀገሩ ሲገባ የተደረገለት ደማቅ አቀባበል፣
ደብረፂዮን ገ/ሚካኤል ጌታቸው ረዳን ለምን አስጠነቀቁት፤
በጎንደር የሞቱት 4 ሰዎች ዝርዝር መረጃ፣
ሙሉ መረጃውን ከስር ባለው ሊንክ ተመልከቱት









5.2K views04:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-31 07:10:01 ረቡዕ ጠዋት! ግንቦት 23/2015 ዓ.ም የEMS ዐበይት ዜናዎች

1፤ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ቧሁኑ ወቅት ከፌደራል መንግሥቱ ጋር "የተጀመረ ወይም የታቀደ የሰላም ንግግር የለም" ሲል በትዊተር ገጹ ባሰራጨው መረጃ አስታውቋል። በኦሮሚያ ክልል የቀጠለው ግጭት እንዲፈታ ቁርጠኛ መኾኑን በድጋሚ ያረጋገጠው ቡድኑ፣ ከመንግሥት ጋር ሁለተኛ ዙር ንግግር ለመጀመር የተያዘ ቀጠሮ እንደሌለ ገልጧል። ቡድኑ፣ ሌላ ዙር ንግግር ከተጀመረ ወዲያውኑ ይፋ አደርጋለኹ ብሏል።

2፤ የደቡብ ክልል ጸጥታ ኃይሎች በሃዲያ ዞን ደመወዝ በወቅቱ እንዲከፈላቸው የጠየቁ በርካታ የመንግሥት ሠራተኞችን ከአንድ ወር በላይ እንዳሠሩ መስማቱን ጠቅሶ ቪኦኤ ዘግቧል። በዞኑ በምሥራቅ ባዳዎቾ ወረዳ የመንግሥት ሠራተኞችን ጨምሮ 40 ሰዎች እንደታሠሩ ዘገባው አመልክቷል። በወረዳው ከመምህራን በስተቀር አብዛኞቹ የመንግሥት ሠራተኞች ላለፉት ሦስት ወራት ደመወዝ እንዳልተከፈላቸው አንዳንድ የመንግሥት ሠራተኞች ለዜና ምንጩ ተናግረዋል።

3፤ በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኢምባሲ ከዓለማቀፉ የፍልሰት ድርጅት ጋር በመተባበር 86 "ለጉዳት ተጋላጭ የኾኑ" ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞችን ወደ አገራቸው መመለሱን በትዊተር ገጹ ባሰራጨው መረጃ አስታውቋል። ወደ አገራቸው ከተመለሱት ፍልሰተኞች መካከል፣ 30ዎቹ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ከነበሩባት የመን ወደ ጅቡቲ የገቡ መኾናቸውን ኢምባሲው ጠቅሷል። ቀሪዎቹ ፍልሰተኞች ግን በሕገወጥ ሰው አዘዋዋሪዎች አማካኝነት ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ሊያደርጉት የነበረውን የጉዞ እቅዳቸውን የተው እንደኾኑ ተገልጧል።

4፤ ከ10 ዓመት በኋላ እንደገና በረራ ለማስጀመር የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓርብ'ለት ወደ ናይጀሪያ የላከው ቦይንግ 737 አውሮፕላን ወደ አዲስ አበባ እንደተመለሰ የናይጀሪያ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። አውሮፕላኑ የተመለሰው፣ የናይጀሪያ አየር መንገድን ሰኞ'ለት በራራ ለማስጀመር የተያዘው እቅድ ባለመሳካቱ እንደኾነ ተገልጧል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ በተደራጀው የናይጀሪያ አየር መንገድ ውስጥ የ49 በመቶ ድርሻ አለው። የአገሪቱ ሲቪል አቬሽን ባለሥልጣን ግን፣ የአየር መንገዱ የበራራ ደኅንነት በአስተማማኝ ሁኔታ አለመረጋገጡንና በረራ እንዳይጀምር በአገሪቱ ፍርድ ቤት የተጣለበትን እገዳ በመጥቀስ ፍቃድ ሳይሰጠው መቅረቱን ዘገባዎች አመልክተዋል። አየር መንገዱ በረራ የሚጀምርበት አዲስ ቀን አልተቆረጠለትም።

5፤ የሱማሊያ ፌደራል መንግሥትና አብዛኞቹ የፌደራል ግዛቶች መንግሥታት የአገሪቱን መንግሥታዊ ሥርዓት ፕሬዝዳንታዊ ብቻ ለማድረግ የደረሱበት ስምምነት ጠንካራ ተቃውሞ እንደገጠመው የሱማሊያ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ተቃውሟቸውን ካሰሙት መካከል፣ የቀድሞ የአገሪቱ መሪዎችና የስምምነት ሰነዱን ባለመፈረም ብቸኛ የኾነው የፑንትላንድ ራስ ገዝ መንግሥት ይገኙበታል። ፑንትላንድ፣ የጠቅላይ ሚንስትርነትን ሥልጣን ሙሉ በሙሉ አስወግዶሁሉንም ሥልጣኖች ለፕሬዝዳንቱ መስጠት "ለአምባገነንነት በር ይከፍታል" ብላለች። ስምምነቱ፣ ወደፊት የሚካሄዱት ምርጫዎች በሙሉ ቀጥተኛ ምርጫ እንዲኾኑ ማድረግን ይጨምራል።

6፤ የሱዳን ጦር ሠራዊትና ፈጥኖ ደራሽ ሠራዊት ለአምስት ቀናት ያረዘሙትን ተኩስ አቁም አሁንም ሳያከብሩት መቅረታቸውን ዓለማቀፍ የዜና ምንጮች ዘግበዋል። ሁለቱ ተፋላሚ ወገኖች እስከ ትናንት ሌሊት ድረስ በካርቱም ውጊያቸውን እንደቀጠሉ ዘገባዎቹ አመልክተዋል።

7፤ ደቡብ አፍሪካ በ"ብሪክስ" አገራት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለሚገኙ የውጭ አገራት ተሳታፊዎች "የዲፕሎማሲ የመብት ከለላ" እንደምትሰጥ ገልጣለች። ውሳኔው፣ የዓለማቀፉ ወንጀል ፍርድ ቤት መመስረቻ ስምምነት ፈራሚ የኾነችው ደቡብ አፍሪካ፣ ፍርድ ቤቱ የእስር ማዘዣ ያወጣባቸውንና በጉባኤው የሚሳተፉትን የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንን ለማሰር እንዳትገደድ ያስችላታል። ደቡብ አፍሪካ፣ የዲፕሎማቲክ መብት ከለላውን ነገ እና ዓርብ ለምታስተናግደው የብሪክስ አገራት ውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች ስብሰባ ተሳታፊዎች ጭምር መስጠቷን ገልጣለች። #ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                  
@emsmereja
5.1K views04:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-30 21:11:01

4.1K views18:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-30 06:49:45 ማክሰኞ ጠዋት! ግንቦት 22/2015 ዓ.ም የEMS ዐበይት ዜናዎች

1፤ ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በጦርነቱ ትምህርት ያቋረጡ የትግራይ ሕጻናት የትምህርት ቁሳቁሶችን ለማሰባሰብና የወደሙ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት በአዲስ አበባ እርዳታ ማሰባሰብ ሊጀምር መኾኑን ዋዜማ ሰምታለች። ፓርቲው ይህንኑ እንቅስቃሴ የሚጀምረው ነገ ሲኾን፣ ዕቅዱ በክልሉ ከ10 ሺህ በላይ የተዘጉ ትምህርት ቤቶችን እንደገና ትምህርት ለማስጀመር ያለመ መኾኑን ዋዜማ ተረድታለች። በክልሉ ከ2.3 ሚሊየን በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ውጭ መኾናቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ በቅርቡ ገልጦ ነበር።

2፤ ብሄራዊ የምክክር ኮሚሽን ዛሬ በሲዳማ ክልል የምክክር ጉባኤ ተሳታፊዎችን መለየትና አጀንዳ መሰብሰብ እንደሚጀምር ትናንት ሀዋሳ ላይ በሰጠው መግለጫ መናገሩን ዶይቸቨለ ዘግቧል። ኮሚሽኑ የመጀመሪያውን ዙር የተሳታፊ ልየታና አጀንዳ የመሰብሰብ ሥራ የሚያካሂደው፣ በሲዳማ፣ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያና ሐረሬ ክልሎችና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር እንደኾነ መግለጡን ዘገባው ጠቅሷል። ኮሚሽኑ ትግራይ ክልልን ጭምር በብሄራዊ የምክክር ሂደቱ ለማካተት፣ ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር በቅርቡ መወያየቱን ገልጧል ተብሏል።

3፤ በኢትዮ-ጅቡቲ መስመር የሚመላለሱ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ታጣቂዎች የሚያደርሱባቸው ጥቃት እየተባባሰ ስለመሄዱ መናገራቸውን ቪኦኤ ዘግቧል። አሽከርካሪዎቹ ታጣቂዎች አግተው ከፍተኛ ገንዘብ ከመጠየቅ ጀምሮ እስከ ግድያ የሚደርስ ጥቃት እንደሚፈጽሙባቸው መግለጣቸውን ዘገባው ጠቅሷል። ትራንስፖርት ሚንስቴር ግን፣ ለችግሩ መፍትሄ እንደሚፈልግ ቀደም ሲል ቃል ገብቶ ነበር።

4፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተወሰኑ አገልግሎት ሰጪ ተቋማቱን ሥራ ለግል ተቋማት በውክልና ሊያስተላልፍ መኾኑን "ኢትዮጵያ ኢንሳይደር" ዘግቧል። ሥራቸውን ለግል ተቋማት የሚያስተላልፉ ሠራተኞች ወደሌላ መስሪያ ቤት ይዛወራሉ መባሉን ዘገባው አመልክቷል። የከተማዋ ፐብሊክ ሰርቪስ ኮሚሽን በውክልና ከሚያስተላልፋቸው አምስት ተቋማት መካከል፣ የንግድ፣ ትራንስፖርት፣ ገቢዎችና የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮዎች ይገኙበታል ተብሏል። የካቲት 12፣ ዳግማዊ ምኒሊክና ዘውዲቱን ጨምሮ ስድስት ሆስፒታሎችም ለግል ተቋማት በውክልና እንደሚተላለፉ ዘገባው አመልክቷል። #ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                  
@emsmereja
5.1K views03:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-29 23:19:59
መኖር እየፈለኩኝ በብር እጦት እንዳልሞት ድረሱልኝ እባካችሁ ሼር አድርጉልኝ

እናትና አባቴ በሕይወት የሉም!

| ቤተልሄም ማናዬ ትባላለች። የድሬዳዋ ልጅ ስትሆን የ 21 ዓመት ወጣት ናት። በድንገት ባጋጠማት ከፍተኛ የሆነ የልብ ህመም እየተሰቃየች ትገኛለች

በአጭር ጊዜ ውስጥም የልብ ቀዶ ጥገና ማድረግ እንዳለባት የህክምና ዶክተሮች ወስነዋል። ለህክምናውም ከአንድ ሚሊዮን ( 1,000,000.00 ) ብር በላይ እንደሚያስፈልጋት ተነግሯታል።

ለወገን ደራሽ ወገን ነውና
ወጣት ቤቴልሄምን መርዳትም ሆነ ማገዝ የምትፈልጉ

ቤተልሄም ማናዬ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
የቁጠባ ሂሳብ ቁጥር
1000286844751

ቤተልሄም ማናዬ
አዋሽ ባንክ
የቁጠባ ሂሳብ ቁጥር
01336719848400

ስልክ
+251-946-024735 ቤተልሄም

በገንዘብ እንኳን መርዳት ባትችሉ ለጓደኛችሁና ለሌሎች ሰዎች ሼር በማድረግ እንርዳት

#ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                  
@emsmereja
4.6K views20:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 20:02:15 ሐሙስ ምሽት! ግንቦት 3/2015 ዓ.ም የEMS ዐበይት ዜናዎች

1፤ ብሄራዊ ባንክ ለሳፋሪኮም ኩባንያ አካል ለኾነው ሳፋሪኮም ኤምፔሳ የሞባይል የፋይናንስ አገልግሎት ንዑስ ኩባንያ የገንዘብ መገበያያና መላላኪያ አገልግሎት "ኤምፔሳ" እንዲጀምር ፍቃድ ሰጥቷል። ሳፋሪኮም ኩባንያ በኢትዮጵያ የሞባይል ገንዘብ መገበያና መላላኪያ አገልግሎት ፍቃድ በማግኘት የመጀመሪያው የውጭ ኩባንያ ኾኗል። ኩባንያው የ"ኤምፔሳ" አገልግሎቱን ከተያዘው የአውሮፓዊያን ዓመት በፊት እንደሚጀምር የኬንያው ቢዝነስ ደይሊ ኩባንያውን ጠቅሶ ዘግቧል። ሳፋሪኮም ኬንያ ውስጥ "ኤምፔሳ" የጀመረው ከ15 ዓመታት በፊት ሲኾን፣ ባሁኑ ወቅት በኬንያና ሌሎች የአፍሪካ አገራት ከ50 ሚሊዮን በላይ ደንበኞች አሉት።

2፤ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ለሚያስገነቡት አዲስ ቤተመንግሥት ተጨማሪ ሦስት ተቋራጮች መቅጠራቸውን ዋዜማ ከምንጮቿ ሰምታለች። የ"ጫካ" ፕሮጀክት አጠቃላይ ወጪው 49 ቢሊዮን ብር እንደሚደርስ ሲገለጽ የቆየ ሲኾን፣ የምዕራባዊያን ዲፕሎማቲክ ምንጮች ግን ወጪው 850 ቢሊዮን ብር ሊደርስ እንደሚችል በመናገር ላይ ናቸው። ፕሮጀክቱ በ503 ሔክታር ላይ የቅንጡ መኖሪያና መዝናኛ መንደሮችንና ሦስት ሰው ሠራሽ ሐይቆች ግንባታ ያካተተ ሲኾን፣ ግንባታው የሚካሄደው በየካ ክፍለ ከተማ የካ ተራራ ግርጌ ነው። የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን እስካኹን የ29 ኪሎ ሜትር የውስጥ ለውስጥ መንገድ ግንባታ አካሂዷል።

3፤ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የተወሰኑ የግል ትምህርት ቤቶች በቀጣዩ ዓመት እናደርገዋለን ባሉት የተማሪዎች የትምህርት ክፍያ ዙሪያ ከወላጆች ጋርመግባባት ላይ መድረስ እንዳልቻሉ ሪፖርተር ዘግቧል። የትምህርት ክፍያ ጭማሪ ለማድረግ ከወሰኑት 1 ሺህ 253 ትምህርት ቤቶች መካከል፣ 1 ሺህ 31 ትምህርት ቤቶች ከወላጆች ጋር ባደረጉት ውይይት 20 በመቶ ጭማሪ ብቻ ለማድረግ መግባባት ላይ እንደደረሱ የከተማዋ የትምህርት ሥልጠናና ቁጥጥር ባለሥልጣን ዛሬ በሰጠው መግለጫ መናገሩን ዘገባው አመልክቷል። ባለሥልጣኑ የግል ትምህርት ቤቶች በቀጣዩ ዓመት ከወርሃዊ ክፍያ ውጭ በዓይነትም ኾነ በገንዘብ የክፍያ ጭማሪ ማድረግ አይችሉም ማለቱ ተገልጧል። የግል ትምህርት ቤቶች ከወላጆች ጋር የተወያዩት፣ ከ20 እስከ 100 ፐርሰን የሚደርስ ጭማሪ ለማድረግ መወሰናቸውን ለባለሥልጣኑ ማሳወቃቸውን ተከትሎ ነው።

4፤ የደቡብ ክልል ምክር ቤት የቁጫ ሕዝቦች ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ተወካዮች የኾኑ ሦስት የክልሉ ምክር ቤት አባላትን ከግንቦት 1 ጀምሮ ከአባልነት መሰረዙን የጋሞ ዞን ኮምንኬሽን ቢሮ አስታውቋል። ሦስቱ የፓርቲው ተወካዮች ከምክር ቤቱ አባልነት የተሰረዙት፣ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ እና ምርጫ ቦርድ በፍርድ ቤት ሲያካሂዱት የቆዩትን ክርክር መሠረት በማድረግ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በቁጫ ምርጫ ክልሎች በድጋሚ ምርጫ እንዲካሄድ በወሰነው መሠረት መኾኑን ቢሮው ገልጧል። ከክልሉ ምክር ቤት አባልነት የተሰናበቱት የፓርቲው ተወካዮች፣ ጌዲዮን ጌታቸው፣ ማሳሞ ማዳልቾ እና ሊዲያ በለጠ ናቸው። በጋሞ ዞን በሁለት ወረዳዎች የሚኖረው የቁጫ ሕዝብ ለዓመታት ሲያነሳው የቆየውን የማንነትና ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ ለፌደሬሽን ምክር ቤት ያስገባ ሲኾን፣ ምክር ቤቱ ግን እስካኹን በጥያቄው ላይ ውሳኔ አልሰጠም።

5፤ የተመድ ሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ልዩ ስብሰባ የሱዳኑ ግጭት ባስከተለው ሰብዓዊ መብት ተጽዕኖ ዙሪያ መክሯል። የተመድ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽነር ቮልከር ተርክ በምክር ቤቱ ልዩ ስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ የታጠቁ ኃይሎች በሰላማዊ ሰዎች ላይ "ጾታዊ ጥቃትና ግድያ" እንደሚፈጽሙ ገልጸው፣ ተፋላሚዎች የጦርነት ሕግጋትን እንዲያከብሩ ጠይቀዋል። ተርክ፣ የሱዳን ጦር ሠራዊት በሰላማዊው ሕዝብ መኖሪያዎች ላይ የአየር ድብደባዎችን መፈጸሙንና ፈጥኖ ደራሽ ሠራዊቱም በሲቪሎች ሠፈሮች መሸጎ እየተዋጋ መኾኑንም ገልጸዋል። በተፋላሚ ወገኖች ላይ ተጽዕኖ መፍጠር የሚችሉ አገራት ሀሉ ግጭቱ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ጥረት እንዲያደርጉ ተርክ ተማጽነዋል።

6፤ ሁለቱ የሱዳን ተፋላሚ ወገኖች ሳዑዲ ዓረቢያ ጅዳ ውስጥ ሲያደርጉት የሰነበቱት የቅድመ-ድርድር ንግግር አበረታች ውጤት ማሳየት መጀመሩን ሮይተርስ አደራዳሪዎችን ጠቅሶ ዘግቧል። ተፋላሚዎቹ ወገኖች በቅርቡ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ይደርሳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ዘገባው አመልክቷል። የጅዳውን ንግግር የሚመሩት፣ ሳዑዲ ዓረቢያ እና አሜሪካ ናቸው።

7፤ ንግድ ባንክ ዛሬ የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋ 54 ብር ከ2167 ሳንቲም እና መሸጫ ዋጋው 55 ብር ከ3010 ሳንቲም ሆኖ እንደዋለ በድረገጹ ገልጧል። የአንድ የእንግሊዝ ፓውንድ መግዣ ዋጋ ደሞ 65 ብር ከ3270 ሳንቲም እና መሸጫው 66 ብር ከ6335 ሳንቲም ሆኗል። በተመሳሳይ አንድ ዩሮ በ59 ብር ከ3890 ሳንቲም ተገዝቶ፣ በ60 ብር ከ5768 ሳንቲም ሲሸጥ መዋሉን ባንኩ ገልጧል። #ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                  
@emsmereja
1.6K views17:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 13:46:01 ጥንቃቄ

የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን በገበያ ላይ ባደረገው ቁጥጥር የኢትዮጵያ አስገዳጅ ደረጃንና የገላጭ ጽሑፍ መስፈርቶች ሳያሟሉ ተመርተው እየቀረቡ ያሉ ምርቶችን ህብረተሰቡ እንዳይጠቀም አሳስቧል፡፡

የተከለከሉት በአጠቃላይ 91 የተለያዩ የምግብ ምርት ዓይነቶች መሆናቸውን የባለስልጣኑ የሕዝብ የኮሙንኬሽ ዳሬክቶሬት ዳሬክተር አበራ ደመቀ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

46 ዓይነት አይኦዳይዝድ ጨው፣ 27 ዓይነት የምግብ ዘይት፣ 10 ዓይነት ከረሜላ ፣5 ዓይነት አቼቶ 2 ዓይነት የለውዝ ቅቤ እና 1 የቫኔላ ፍሌቨር ምርቶችን  እንደሚገኙበትም ገልጸዋል፡፡

ባለስልጣን በገበያ ላይ ባደረገው ቁጥጥር የኢትዮጵያ አስገዳጅ ደረጃንና የገላጭ ጽሑፍ መስፈርቶች ስለማያሟሉ በተጨማሪም በቁጥጥር ወቅት የተገኙ ግኝቶች እንደሚያሳዩት ምርቶቹ በአብዛኛው በሚባል መልኩ የመጠቀሚያ ጊዜ፣ የአምራች ድርጅታቸው ሥም፣ አስገዳጅ ደረጃ ምልክት፣ መለያ ቁጥርም ሆነ አድራሻቸው ምርቱ ላይ ያልተገለጸና የሌላቸው በመሆኑ የተነሳ ነዉ፡፡

ምርቱ ሊይዛቸው የሚገቡ ንጥረ ነገሮች በውል ለማይታወቅ በተጨማሪም ከሚመለከታቸው የጤና  ተቆጣጣሪ አካላት ፍቃድ የሌላቸው በመሆኑ ህብረተሰቡ ጥቅም ላይ እንዳያውላቸው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አሳስቧል፡፡

ለጥንቃቄ የምርቱ ዓይነትና የተገኙትን ክፍተቶች ይፋ በማድረግ ህብረተሰቡ በትኩረት ተመልክቶ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ባለስልጣን መስሪያቤቱ አሳስቧል፡፡

በዚህም መሠረት፦

የምርት ዓይነቶች እና ብራንድ ሥማቸው

  የምግብ ጨዉ

1.  ሳባ የገበታ ጨው(Saba IODIZED Salt)
2.  ንጋት የገበታ  ጨው(Nigat IODIZED SALT)
3.  አዲስ ብርሃን የገበታ ጨው  ADDIS BERHAN IODIZED SALT
4.  ሙና የገበታ ጨው(MUNA TABLE SALT)
5.  ቤዝ የገበታ ጨው/BASE IODIZED SALT
6.  ጉስቶ የገበታ ጨው/GUSTO IODIZED SALT
7.  ማክ የገበታ ጨው/MAK IODIZED SALT
8.  አባይ የገበታ ጨው/ABAY TABLE SALT
9.  መስቱራ ባለ አዮዲን የተፈጨ ጨው MESTURA REFINED & IODIZED SALT
10.  መነስ ጨው /MENES IODIZED SALT
11.  ሙሉ የገበታ ጨው /Mulu Table Salt
12.  ኢርኮ  አዮዳይዝድ  ጨው ERKO IODIZED SALT
13.  አርዲ የገበታ ጨው/ARDI IODIZED SALT
14.  ዘመን የገበታጨው/ZEMEN IODIZED SALT
15.  ዘመን የገበታጨው/ZEMEN IODIZED SALT
16.  ጨረቃ የገበታ ጨው/IODIZED SALT
17.  ፋና የገበታጨው/Fana Table Salt
18.  ዳናት የገበታጨው
19.  ሶም የገበታጨው/som iodized salt
20.  ጉግሳ በአዮዲን የበለፀገ የገበታጨው/GUGSA Iodised Salt
21.  ሸጋ ጨው/SHEGA Iodized SALT
22.  ፍዳክ የገበታ ጨው/FDAK IODIZED SALT
23.  ኡሚ የገበታ ጨው/UMI IODIZED SALT
24.  ጊዜ አዮዳይዝድ ጨው/GIZE IODIZED SALT
25.  ባማክ የገበታ ጨው/bamak Iodized Salt
26.  ማዚ የገበታ ጨዉ/MAZI IODIZED SALT
27.  አዲስ የገበታ ጨዉ/ADDIS Iodized Salt
28.  የገበታ ጨው/Iodized salt
29.  TANA TABLE SALT/ጣና የገበታ ጨው
30.  ጣና የገበታ ጨው
31.  ማኢዳ የገበታ ጨው/MAEEDA IODIZED SALT
32.  አሚን ጨው/Amin iodized salt
33.  ሆም የገበታ ጨው/HOME IODIZED SALT
34.  ጂኤም የገበታ ጨው/GM IODIZED SALT
35.  ገዳ አዮዳይዝድ የታጠበ የገበታ ጨው/ GEDA IODIZED SALT
36.  ዛማ አዮዳይዝድ የታጠበ ባለ አዮዲን ጨው /ZAMA SALT
37.  ሶሲ የአዮዲን ጨው/Sosi Iodized Salt
38.  ብቁ የገበታ ጨው/Biku iodized salt
39.  H.T.F TABLE SALT /ኤች.ቲ.ኤፍ
40.  AFRAN Iodized Salt
41.  ኤምሬት ጨው/Emirate IODIZED SALT
42.  ስፔሻል የገበታ ጨው/Special Iodized Salt
43.  ሊያ የገበታ ጨው/ LIYA IODIZED SALT
44.  አፊ ጨው/AFI IODIZED SALT
45.  ዩስራ ጨው/ YUSERA  SALT
46.  ቡዜ የገበታጨው/BUZE IODIZED SALT

የምግብ ዘይት

1.  ነጃ ንጹህ የምግብ ዘይት/ NEJA Pure Edible Oil
2.  ረና ንጹህ የምግብ ዘይት/ Rina Edible Pure Food Oil
3.  የኛ ንጹህ የምግብ ዘይት/Yegna Pure Edible Oil
4.  ኑራ  ንጹህ የምግብ ዘይት /Nura Pure Edible oil
5.  ሕይወት ንጹህ የምግብ ዘይት /HIWOT Edible Cooking Oil
6.  ሚድ ንጹህ የምግብ ዘይት /MID Pure Edible Oil
7.  ጉና ንጹህ የኑግ  የምግብ ዘይት/GUNA Pure Niger Edible Oil
8.  አዲስ  ንጹህ የምግብ  ዘይት
9.  ኑር ንጹህ የምግብ ዘይት/Nur Pure Edible Oil
10.  ኑራ ንጹህ የምግብ ዘይት/NuraPure Edible Oil
11.  ሶፊ ንጹህ የምግብ ዘይት/Sofi Pure Edible Oil
12.  ደሴት ንጹህ የምግብ ዘይት/Deset Pure Food Oil
13.  HADI COOKING OIL
14.  Arif cooking oil
15.  ሰነዓ ንፁህ የምግብ ዘይት /Senea pure food oil
16.  ቃል ንፁህ የምግብ ዘይት/Kale Pure Food Oil
17.  ናዲ የተጣራ ንጹህ የምግብ ዘይት/ Nadi pure food oil
18.  ሰላም ንፁህ የምግብ ዘይት/Selam pure food oil
19.  ኑኑ ንፁህ የምግብ ዘይት /Nunu pure food oil
20.  MIFTAH pure food oil
21.  ቤላ የተጣራ የኑግ ዘይት/BELLA Pure Niger Oil
22.  ጣዝማ ንፁህ የምግብ ዘይት
23.  ሚና ንፁህ የምግብ ዘይት
24.  ብሌን ንፁህ የምግብ ዘይት/Blen Pure  Edible Oil
25.  ደስታ የተጣራ የኑግ  ዘይት
26.  ሐዲ የተጣራ የምግብ ዘይት
27.  ሳራ የኑግ የምግብ ዘይት/Sara Niger Oil

የከረሜላ ምርቶች

1.  ማሂ ከረሚላ/Mahi candy
2.  ኢላላ ጣፋጭ  ከረሚላ/Elaala sweet candy
3.  ፋፊ  ሎሊፖፐ/Fafi lolipop
4.  ኢላላ  ሎሊፖፕ  ቢግ  ጃር/Elaala lolypop big jar
5.  ኮከብ ከረሚላ/KOKEB candy
6.  ከረሚላ
7.  ከረሚላ
8.  ኤም ቲ  ሎሊፖፕ/MT Loliipop
9.  ኤ.ኤ ከረሚላ/A.A candy
10.  ምንም ገለጭ ፁሑፍ የሌለው ከረሜላ

የአቼቶ ምርቶች

1.  ሮያል አቼቶ/Royal VINEGAR
2.  ዋልታ አቼቶ
3.  ሮያል  አቼቶ/ROYAL Vinegar
4.  ሌመን  አቼቶ/LEMEN ACETO
5.  ሸገር  አቼቶ/SHEGER ACETO

  የለዉዝ ቅቤ

#ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                  
@emsmereja
2.8K views10:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ