Get Mystery Box with random crypto!

EMS Mereja

የቴሌግራም ቻናል አርማ emsmereja — EMS Mereja E
የቴሌግራም ቻናል አርማ emsmereja — EMS Mereja
የሰርጥ አድራሻ: @emsmereja
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 14.57K
የሰርጥ መግለጫ

👉 መረጃዎች፣ጥያቄዎች፣ አስተያየቶችና የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት ከፈለጉ በዚህ ያናግሩን👉 t.me/infoetrobot
👉 የዕለታዊ ዝግጅቶችና ዜናዎች በተባባሪ አቅራቢዎች እንዲደርሷችሁ👇👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@HAQMEDIA12
Subscribe ያድርጉ

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2023-05-07 10:12:08
ተቀበሩ

የቤት ሰራተኛዋ አልተያዘችም እንድትያዝ ሼር አድርጉ እባካችሁ ተባበሩ



በቤት ሰራተኛ በጭካኔ ታርደው እና በእሳት ተቃጥለው ህይወታቸው አለፈ!!

በቡራዩ ቄራ አካባቢ የተሰማው መርዶ ለጆሮ ሰቅጣጭ ነበር

በፎቶው ላይ የምታይዋቸው የ12 አመቱ

* ናሖል ጌቱ እና
* የ5 አመቷ ታናሽ እህቱ ናኑ ጌቱ

ወላጅ እናታቸውን በሞት ያጡት የዛሬ ሁለት አመት ገደማ ነበር

አባታቸው ጌቱ የቡራዩ ቄራ ሰራተኛ በመሆኑ የስራው ባህሪይ ሌሊት ሌሊት ነው እንደተለመደው ትናንትም ልጆቹን ለቤት ሰራተኛዋ ትቶ ስራ ያነጋል

ይህቺ ሰራተኛ ግን ልጆቹን በጭካኔ አርዳ እና በእሳት ጭምር አቃጥላ ህይወታቸው እንዲያልፍ አድርጋለች

የቤት ስራተኛ ስሟ :- ነጋሴ ከበደ ነው

አልተያዘችም

እባካችሁ እንድትያዝ በሼር ተባበሩ እባካችሁ

ልጅ ያለው የልጁ፣ወንድምና እህት ያለው፣ የወንድሙና እህትን ነገር መቼም ትረዳላችሁና በእባካችሁ ገዳይ እንድትያዝ ለጓደኞቻችሁም ቢሆን #ሼር ብቻ እንድታደርጉልን ተብላቹሃል አደራ

ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                  
@emsmereja
5.3K views07:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-06 22:25:23
ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ በፌዴራል ፖሊስ በቁጥጥር ስር ዋለ
ጋዜጠኛው ጅቡቲ ከገባ በኋላ ወደሌላ አገር ሊሻገር ሲል ከዓለም አቀፉ ፖሊስ እና ከጅቡቲ ብሔራዊ ፖሊስ ጋር በመተባበር በቁጥጥር ስር እንዲውልና ተላልፎ ለኢትዮጵያ እንዲሰጥ ተደርጎ ዛሬ ምሽት አዲስ አበባ መግባቱን የፌደራል ፖሊስ በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ አስነብቧል።

#ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                  
@emsmereja
5.2K views19:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-06 19:36:50 የዲቪ 2024 እድለኛ አሸናፊዎች ይፋ ሆኑ!

አሜሪካ ኢትዮጵያ በሚገኘው ኢምባሲዋ በኩል ከሰሞኑ አመልካቾች ከአጭበርባሪዎች እንዲጠነቀቁ ማሳሰቧ ይታወሳል
የዲቪ 2024 እድለኛ አሸናፊዎች ይፋ ሆኑ።
ባሳለፍነው ጥቅምት እና ህዳር ወራት ላይ በበይነ መረብ አማካኝነት የተሞላው የ2024 ዲቪ ሎተሪ አሸናፊዎች መታወቃቸው ተገልጿል።
በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኢምባሲ የዲቪ 2024 ማመልከቻ የሞሉ ዜጎችም መመረጣቸውን እና አለመመረጣቸውን የፊታችን ቅዳሜ ማለትም ከሚያዚያ 28 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ማወቅ እንደሚችሉ ከሰሞኑ ማሳሰቡ ይታወሳል።
በዚህ መሰረትም አመልካቾች https://dvprogram.state.gov/ESC/ በዚህ ሊንክ በመግባት የዲቪ 2024 እድለኛ መሆን አለመሆናቸውን ማረጋገጥ እንደሚችሉ ተገልጿል።
ይህ በዚህ እንዳለም የድቪ ሎተሪ አሸንፋችኋል፣ ከአሜሪካ ኢምባሲ ነው እምንደውለው በሚል የሚያጭበረብሩ አካላት ስለሚኖሩ አመልካቾች እንዲጠነቀቁ ኢምባሲው ማሳሰቡ ይታወሳል።
አመልካቾች ዲቪ ሎተሪ ስለማሸነፋቸው በራሳቸው እና እጃቸው ላይ ባለው ሚስጢራዊ ቁጥር ብቻ ማረጋገጥ እንደሚችሉም ተገልጿል።
የ2023 ዲቪ ሎተሪ አሸናፊዎች እስከ ቀጣዩ መስከረም 2016 ዓ.ም ድረስ ብቻ ባሉት ቀናት ውስጥ እንደሚስተናገዱም ኢምባሲው በመግለጫው ላይ ጠቁሟል።
የ2022 ዲቪ ሎተሪ አሸናፊዎች በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት መከሰቱን ተከትሎ የአሜሪካ እና ኢትዮጵያ ግንኙነት በመሻከሩ ተጎድተናል ማለታቸው ይታወሳል።
ዲቪ ከደረሳቸው ኢትዮጵያዊያን መካከል አስተያየታቸውን ለአልዐይን የሰጡ የድቪ 2022 አሸናፊዎች በሁለቱ ሀገራት ግንኙነት መሻከር ምክንያት እድሉን ተጠቅመን ወደ አሜሪካ እንዳንሄድ ተደርገናል ብለውም ነበር።
በኢትዮጵያ ያለው የአሜሪካ ኢምባሲ በበኩሉ " የዲቪ ሎተሪ እድለኛ ተሆነ ማለት ቪዛ ይገኛል፣ ለቪዛ ቃለ መጠይቅም ይጠራል ወይም ቪዛ ይሰጣል ማለት አይደለም" ሲል በወቅቱ ምላሽ ሰጥቷል።
ነገር ግን የዲቪ ሎተሪ እድለኛ መሆን የቪዛ ጥያቄ ለማቅረብ የመጀመሪያው መስፈርት ነው ያለው ኢምባሲው እድለኞቹ አሁን ላይ የቪዛ አገልግሎት ሂደት ውስጥ ሳይገቡ ከቀረ በቀጣይ በሚደረጉ ተመሳሳይ የቪዛ አገልግሎት ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ ሲልም አክሎ ነበር።
አሜሪካ በየዓመቱ ከአፍሪካ፣ እስያ፣ አውሮፓ፣ ሰሜን አሜሪካ፣ ደቡብ አሜሪካ እና አውስትራሊያ 50 ሺህ ሰዎችን በድቪ ሎተሪ ወደ ሀገሯ ታስገባለች።
አፍሪካ የዚህ እድል ትልቁን ኮታ የምትሸፍን ሲሆን በዲቪ 2022 ፕሮግራም ግብጽ፣ አልጀሪያ እና ሱዳን እያንዳንዳቸው 6 ሺህ ሰዎች እድለኞች ሲሆኑ ሞሮኮ 4 ሺህ 138 ፣ ዲሞክራቲክ ኮንጎ 3 ሺህ 347 ፣ጋና 3 ሺህ 145 ፣ ኢትዮጵያ ደግሞ 2 ሺህ 988 ሰዎች የዲቪ እድለኛ እንደሆኑ ከተቋሙ ድረገጽ ያገኘነው መረጃ ያስረዳል። መረጃውን #ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                  
@emsmereja
5.2K viewsedited  16:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-04 07:08:15 ለቸኮለ ማለዳ! ሐሙስ ሚያዝያ 26/2015 ዓ.ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች

1፤ የአሜሪካ ተራድዖ ድርጅት ዩኤስአይዲ ኃላፊ ሳማንታ ፓወር በድርጅታቸው ድጋፍ ትግራይ ውስጥ የሚካሄደው የምግብ ዕርዳታ ሥርጭት ላልተወሰነ ጊዜ እንደቆመ ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል። ድርጅቱ በክልሉ የዕርዳታ ሥርጭት ያቋረጠው፣ የዕርዳታ እህል ከመጋዘን ተዘርፎ ገበያ ውስጥ እየተሸጠ መኾኑን መረዳቱን ተከትሎ ምርመራ በመጀመሩ እንደኾነ ፓዎር ገልጸዋል። የአሜሪካ መንግሥት ጉዳዩን ለፌደራልና ለክልሉ መንግሥት ማሳወቁንና ኹለቱም በምርመራውና ጥፋተኞችን ተጠያቂ በማድረግ ዙሪያ ከድርጅቱ ጋር ለመተባበር ፍቃደኛ መኾናቸው ተገልጧል። ዩኤስአይዲ የዕርዳታ አቅርቦቱን እንደገና የሚጀምረው፣ በክልሉ ጠንካራ የቁጥጥር ሥርዓት እንደተዘረጋ ካረጋገጠ ብቻ መኾኑን መግለጫው አውስቷል።

2፤ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ በክልሉ ተፈጸመ በተባለው የዕርዳታ እህል ዝርፊያ ዙሪያ አስተዳደራቸው ምርመራ መጀመሩን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል። ከዓለማቀፍ የረድዔት ድርጅቶች፣ ዲፕሎማቶችና ከክልሉ ማኅበረሰብ መሪዎች የዕርዳታ እህል ላልታሰበለት ዓላማ እየዋለ ስለመኾኑ ጥቆማ እንደደረሳቸውና ድርጊቱቱ እንደተፈጸመ "በርካታ መረጃ" መኖሩን የገለጡት ጌታቸው፣ ጥፋተኛው ማንም ይኹን ማን ተጠያቂ እናደርጋለን ብለዋል። ኾኖም ኹሉም ረድኤት ድርጅቶች በክልሉ የዕርዳታ አቅርቦታቸውን እንዲቀጥሉ ጌታቸው ጠይቀዋል።

3፤ የትግራይ ክልል የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በክልሉ ውስጥ የተሠረቀ የዕርዳታ እህል ገዢዎችንና ሻጮችን ለመቆጣጠር ጥረት እንደሚያደርግ መግለጡን ቪኦኤ ዘግቧል። ኾኖም ኮሚሽኑ የክልሉ መንግሥት በሚቆጣጠራቸው አካባቢዎች የተዘረፈ የዕርዳታ እህል የለም በማላት ማስተባበሉን ዘገባው አመልክቷል። የዓለም ምግብ ድርጅት፣ ከሽራሮ መጋዘኑ ለ100 ሺህ ተረጂዎች የሚበቃ ዕርዳታ እንደተዘረፈበትና በዝርፊያው ላይ ምርመራ እያደረገ እንደኾነ በቅርቡ አሶሴትድ ፕሬስ መዘገቡ ይታወሳል። ዝርፊያው ከሽራሮ መጋዘን መቼ እንደተፈጸመ ግን ዘገባው በትክክል አልገለጸም።

4፤ የጀርመኑ ጠቅላይ ሚንስትር ኦላፍ ሾልት ዛሬ በኢትዮጵያ ይፋዊ ጉብኝት ለማድረግ አዲስ አበባ ይገባሉ። ሾልት በአዲስ አበባ ቆይታቸው፣ ከፕሬዝዳንት ሳሕለወርቅ፣ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ፣ ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ እና ከአፍሪካ ኅብረት ባለሥልጣናት ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚነጋገሩ የአገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቀደም ሲል ማስታወቁ ይታወሳል። ጠቅላይ ሚንስትር ሾልት ከኢትዮጵያ ጉብኝታቸው በኋላ ወደ ኬንያ እንደሚያቀኑ ተገልጧል።

5፤ "ኤን ቢሲ ኢትዮጵያ" የተሰኘ አዲስ ቴሌቪዥን ጣቢያ ትናንት በይፋ ሥራ መጀመሩን መንግሥታዊው ቴሌቪዥን ጣቢያ ዘግቧል። የጣቢያው ባለቤት "ናሽናል ሜዲያ አክሲዮን ማኅበር" እንደኾነ ዘገባው ጠቅሷል። በአማርኛ ቋንቋ የ24 ሰዓት ሥርጭት የጀመረው ጣቢያው፣ በግል ባለሃብቶች አማካኝነት በግማሽ ቢሊዮን ብር ካፒታል የተጀመረ መኾኑን ዘገባው አመልክቷል። የአዲሱ ቴሌቪዥን ጣቢያ መስራች አባልና ዋና ሥራ አስኪያጅ የቀድሞው የፋና ብሮድካስት ሥራ አስኪያጅ ብሩክ ከበደ መኾናቸው ተገልጧል። #ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                  
@emsmereja
2.7K views04:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 21:07:15 ቆቦና የሸዋሮቢት አሁን የተፈጠረውን በሊንኩ ይመልከቱ



3.8K views18:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 20:48:48

3.4K views17:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 17:26:23
መንግሥት ወደ ቀልቡ ተመልሶ ሰላማዊውን መንገድ ካልተከተ: ከባድ ደም መፋሰስ በሸዋሮቢትና አካባቢው መከሰቱ አይቀርም:: የሚደርሱን መረጃዎች ጥሩ አይደሉም:: የአማራ ክልል ባለስልጣት የንጹሃን ዜጎች ደም በገፍ እንዳይፈስ መፍጠን አለባችሁ:: ትዕግስት : ትዕግስት: ስክነት: ስክነት:: መረጃውን #share በማድረግ ተባበረኝ

ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                  
@emsmereja
4.3K viewsedited  14:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 13:01:51 አማኞች በረሃብ እንዲሞቱ አድርጓል የተባለው ኬንያዊ ፓስተር ፍርድ ቤት ቀረበ!
ይህን አስተምሮውን ተከትለው በጫካ ውስጥ ከምግብ ርቀው የተደበቁ ሰዎች ፍለጋ ሲካሄድ ሰንብቷል
በኬንያ በረሃብ ከጸናችሁ “ኢየሱስን ታዩታላችሁ፤ ገነትም ትገባላችሁ” በሚል አስተምሮው ከ100 በላይ ሰዎች ህይወት እንዲጠፋ ምክንያት የሆነው ፓስተር ፍርድ ቤት ቀረበ።
"ገነት አስገባችኋለሁ" በሚል ከአማኞች ገንዘብ የተቀበለው ናይጄሪያዊ ፓስተር ተከሰሰ
በናይጀሪያ ለደህንነቱ የሰጋ ፓስተር ክላሽ ይዞ መስበኩ አነጋጋሪ ሆኗል
የ“ጉድ ኒውስ ኢንተርናሽናል ቸርች” መስራቹ ፓስተር ፖል ማኬንዚ በምስራቃዊ ኬንያ ማሊንዲ በተሰኘችው ከተማ ፍርድ ቤት መቅረቡን የኬንያው ሲቲዝን ቴሌቪዥን ዘግቧል።
ፓስተር ፖል ማኬንዚ በፈረንጆቹ ሚያዚያ 15 የአለም ፍጻሜ እንደሚሆን በመግለጽ ተከታዮቹ በረሃብ ራሳቸውን ገድለው ገነት ይገቡ ዘንድ መስበኩ ተጠቅሷል።
ይህን አስተምሮውን ተከትሎም በርካታ ተከታዮቹ ሻካሆላ ወደተባለ ጫካ መግባታቸውንና እስካሁን የ101 ሰዎች አስከሬን መገኘቱን (አብዛኞቹ ህጻናት ናቸው) የኬንያ ባለስልጣናት ገልጸዋል።
ከ400 በላይ ሰዎችም የገቡበት አይታወቅም ያለው የኬንያ የሀገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስቴር በጫካው ውስጥ ለቀናት አሰሳ ሲያደርግ መቆየቱን አስታውቋል።
በዚህም 8 ሰዎችን ማግኘት ቢቻልም ረሃብ አዳክሟቸው ብዙም ሳይቆዩ ህይወታቸው አልፏል ነው ያለው።
325 ሄክታር በሚሸፍነው ሻካሆላ ጫካ እጅግ ሰፊ ከመሆኑ አንጻር አሁንም በርካቶች በረሃብ ህይወታቸውን ሰውተው ፈጣሪያቸውን ለማየት እየተጠባበቁ እንደሚሆን ይገመታል።
በህይወት የተገኙትና ረሃብ ክፉኛ የጎዳቸው ሰዎችም ምግብ እንዲበሉ ለማድረግ የተደረገው ሙከራ ሳይሳካ መቅረቱ ተነግሯል።
በፖሊስ ቁጥጥር ስር ያለውና ከዚህ ቀደምም በተለያየ ወንጀል ተይዞ በጉቦ የወጣው ማኬንዚ ስለቀረበበት ክስ እስካሁን ምንም አይነት ምላሽ አልሰጠም።
ሮይተርስ ግን ፓስተሩ ተከታዮቹን እንዲጾሙ አለማዘዙን መናገሩን የክስ ሂደቱን መርማሪዎች ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።
ትናንት ፍርድ ቤት የቀረበው ፖል ማኬንዚ በጅምላ ተቀብረው በተገኙት ከ100 በላይ ሰዎች እና በሌሎች ከባድ ወንጀሎች ክስ ይመሰረትበታል ተብሏል። #ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                  
@emsmereja
4.4K views10:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 12:55:59
የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ

በኦሮሚያ ክልል ያለውን ግጭት በማስወገድ ሰላምን ለማምጣት ያለመውና በታንዛኒያ ሲካሄድ የቆው የሰላም ውይይት የመጀመሪያ ምዕራፍ ዛሬ ተጠናቋል።

ውይይቱ በአብዛኛው በአዎንታዊ መልኩ የተከናወነ ቢሆንም በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ ግን በዚህኛው የውይይት ምዕራፍ ስምምነት ላይ ለመድረስ አልተቻለም።

ግቱን በዘላቂነትና ሰላማዊ በሆነ መንገድ ለማስቆም እንዲቻል ሁለቱም አካላት የሰላም ውይይቱን መቀጠል አስፈላጊ መሆኑ ላይ ተግባብተዋል፡፡

በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥትና እስካሁን ሲመራባቸው በነበሩ መሠረታዊ ርሆች መሠረት ግጭቱን በሰላማዊ መልኩ ለመፍታት መንግስት የጸና አቋም አለው።

ይህንን መልካም አጋሚና በውይይት ችግሮችን የመፍታት በጎ ጅምር በጠቀም ጉዳዩ እልባት እንዲያገኝ የኢትዮጵያ መንግሥት ያለውን ፅኑ አቋም ዳግም ያረጋግጣል።

የሰላም ውይይቱን ላመቻቹና ላስተናገዱ አካላት የኢፌዴሪ መንግሥት ምስጋናውን ያቀርባል።

ሚያዝያ 25 ቀን 2015 ዓ.ም

አዲስ አበባ

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

#ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                  
@emsmereja
3.8K viewsedited  09:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 12:34:48 የ2024 ዲቪ ሎተሪ እድለኞች ከመጪው ቅዳሜ ጀምሮ ይፋ እንደሚደረጉ አሜሪካ አስታወቀች
የዲቪ 2024 ማመልከቻ የሞሉ ዜጎች መመረጣቸውን እና አለመመረጣቸውን ከፊታችን ቅዳሜ ሚያዚያ 28/2015 ጀምሮ ማወቅ እንደሚችሉ አሜሪካ አስታውቃለች
አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኢምባሲ በትዊተር ገጹ ባሰፈረው መልዕክት፤ ባሳለፍነው ጥቅምት እና ህዳር ወራት በበይነ መረብ አማካኝነት የተሞላው የ2024 ዲቪ ሎተሪ አሸናፊዎች መታወቃቸው ገልጿል።
በዚህም መሰረት፤ አመልካቾች በዲቪ ሎተሪ ድረገጽ ላይ በመግባት ያመለከቱበትን ልዩ ቁጥር ወይም ኮድ በማስገባት አሸናፊ መሆናቸውንና አለመሆናቸውን ማረጋገጥ ይችላሉ ተብሏል።
ኤምባሲው አክሎም፤ የዲቪ ሎተሪ አሸንፋችኋል፣ ከአሜሪካ ኢምባሲ ነው የምንደውለው በሚል የሚያጭበረብሩ አካላት ስለሚኖሩ አመልካቾች እንዲጠነቀቁ ያሳሰበ ሲሆን፤ የዕድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ስለመመረጣቸውና ስላለመረጣቸው አመልካቾች በራሳቸው እጃቸው ላይ ባለው ሚስጢራዊ ቁጥር ማረጋገጥ ብቸኛው መንገድ እንደሆነም አመላክቷል።
በተጨማሪም የ2023 ድቪ ሎተሪ አሸናፊዎች፤ እስከ ቀጣዩ መስከረም 2016 ድረስ ብቻ እንደሚስተናገዱ ኢምባሲው አስታውቋል።
አሜሪካ በዓለም ላይ በየዓመቱ 50 ሺሕ ሰዎችን በ”ዳይቨርሲቲ ቪዛ“ ወይም ድቪ ሎተሪ አማካኝነት ወደ አገሯ የምታስገባ ሲሆን፤ ከእነዚህም ውስጥ የአፍሪካ፣ እስያ፣ አውሮፓ፣ ሰሜን አሜሪካ፣ ደቡብ አሜሪካ እና አውስትራሊያ ዜጎች ይገኙበታል።
#ሼር በማድረግ መረጃውን ለብዙ ሰው አድርሱ


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                  
@emsmereja
3.5K views09:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ