Get Mystery Box with random crypto!

EMS Mereja

የቴሌግራም ቻናል አርማ emsmereja — EMS Mereja E
የቴሌግራም ቻናል አርማ emsmereja — EMS Mereja
የሰርጥ አድራሻ: @emsmereja
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 14.57K
የሰርጥ መግለጫ

👉 መረጃዎች፣ጥያቄዎች፣ አስተያየቶችና የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት ከፈለጉ በዚህ ያናግሩን👉 t.me/infoetrobot
👉 የዕለታዊ ዝግጅቶችና ዜናዎች በተባባሪ አቅራቢዎች እንዲደርሷችሁ👇👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@HAQMEDIA12
Subscribe ያድርጉ

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2023-05-03 07:10:23 ረቡዕ ማለዳ! ሚያዝያ 25/2015 ዓ.ም የEMS ዐበይት ዜናዎች

1፤ አሜሪካ በትግራይ ክልል ዘላቂ ሰላም ለማስፈን "የኤርትራ ወታደሮችንና ከፌደራል መንግሥቱ ጸጥታ ኃይል ውጭ የኾኑ ኃይሎችን ከትግራይ ሙሉ በሙሉ ማስወጣትና ተዓማኒ የሽግግር ፍትህ ሂደት ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው" ስትል በውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቷ በኩል ባወጣችው መግለጫ አሳስባለች። መንግሥትና ሕወሃት የፕሪቶሪያውን ሰላም ስምምነት ተግባራዊ በማድረግ ረግድ ያሳዩትን ስኬት ያደነቀችው አሜሪካ፣ የሲቪሎችን ደኅንነት ለማስጠበቅና የተሟላ የትጥቅ ማስፈታትና መልሶ ማዋሃድ ሂደት ለማከናወን "ተጨማሪ የሰላም ስምምነት አፈጻጸም ተቆጣጣሪዎች" እንዲሠማሩ ጠይቃለች። የኢትዮጵያ መንግሥትና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታንዛኒያ ውስጥ የጀመሩት ድርድር በቅን መንፈስ እንዲካሄድም አሜሪካ ጨምራ ጥሪ አድርጋለች።

2፤ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደመቀ ከተመድ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽነር ቮከር ተርክ ጋር ትናንት በጽሕፈት ቤታቸው መወያየታቸውን ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አስታውቋል። ደመቀ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ከሕወሃት ጋር በደረሰበት የሰላም ስምምነት አፈጻጸም ረገድ የታዩ ርምጃዎችን ለኮሚሽነሩ እንዳብራሩላቸው ሚንስቴሩ ገልጧል። ሚንስቴሩ፣ ደመቀ እና ተርክ የኢትዮጵያ መንግሥትና ኮሚሽኑ በሽግግር ፍትህ ዙሪያ በትብብር ለመስራት በሚችሉበት ኹኔታ ዙሪያ ጭምር ተወያይተዋል ተብሏል።

3፤ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን በዳንጉር እና ጉባ ወረዳዎች አዋሳኝ አካባቢዎች ሲንቀሳቀሱ የቆዩ 90 ያህል ታጣቂዎች ወደ ሰላማዊ ኑሮ መመለሳቸው የዞኑ ኮምንኬሽን ቢሮ ባሰራጨው መረጃ አስታውቋል። ታጣቂዎቹ ከእነ ሙሉ ትጥቃቸው ወደ ሰላማዊ ኑሮ የተመለሱት፣ መንግሥት ባደረገው ጥሪ መሠረት እንደኾነ ቢሮው ገልጧል።

4፤ ንግድ ሚንስቴር በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ላንድ ወር የሚቆይ ማሻሻያ ማድረጉን ትናንት ማምሻውን አስታውቋል። በአዲሱ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ቤንዚን በሊትር 69 ነጥብ 43 ብር፣ ነጭ ናፍጣ በሊትር 71 ነጥብ 08 ብር፣ ኪሮዚን በሊትር 71 ነጥብ 08 ብር፣ ቀላል ጥቁር ናፍጣ በሊትር 57 ነጥብ 84 ብር፣ ከባድ ጥቁር ናፍጣ በሊትር 56 ነጥብ 50 ብር እንዲኹም የአውሮፕላን ነዳጅ በሊትር 66 ነጥብ 60 ብር መኾኑን ሚንስቴሩ ገልጧል። ከአውሮፕላን ነዳጅ ውጭ፣ ሌሎቹ ምርቶች ላይ በማስተካከያው መሠረት የዋጋ ጭማሪ ተደርጎባቸዋል።

5፤ ዓለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት አሜሪካ፣ ቻይና እና አውሮፓ ኅብረት የንግድ ጎራ ለይተው ዓለማቀፍ ፉክክር ውስጥ ከገቡ ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪካ አገራት በእጅጉ ተጎጂ ይኾናሉ በማለት አስጠንቅቋል። ድርጅቱ፣ እንዲህ ባለው ኹኔታ ውስጥ አፍሪካ ከ10 ዓመታት በኋላ እስከ አራት በመቶ የሚደርስ የዓመታዊ የምርት መጠን ማሽቆልቆል ሊገጥማት ይችላል ብሏል። በኃያላን መካከል በሚደረግ ዓለማቀፍ የጅዖፖለቲካ ፉክክር ሳቢያ የካፒታል ፍሰቶች ከተገደቡ፣ የአፍሪካ አገራት ከውጭ የሚያስገቧቸው ምርቶች ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ እንደሚጨምርና ለወጭ ምርቶቻቸው አንዳንድ የገበያ መዳረሻዎችን ሊያጡ እንደሚችሉ ድርጅቱ ገልጧል። ድርጅቱ፣ አፍሪካ 10 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ቀጥተኛ የውጭ ኢንቨስትመንትና የልማት ድጋፍ ልትጣ ትችላለች በማለትም አስጠንቅቋል። #ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                  
@emsmereja
4.0K views04:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-02 20:03:34 ማክሰኞ ሚያዝያ 24/2015 ዓ.ም የEMS ዐበይት ዜናዎች

1፤ የተመድ ምግብ ፕሮግራም በትግራይ ክልል "በዕርዳታ ምግብ ዝርፊያ" ሳቢያ ሥራውን ለጊዜው ማቋረጡን አሶሴትድ ፕሬስ ከረድኤት ሠራተኞች መስማቱን ጠቅሶ ዘግቧል። ድርጅቱ፣ በክልሉ የምግብ ዕርዳታ ሥርጭት ማቆሙን ከ10 ቀናት በፊት ለአጋሮቹ ማሳወቁን ዘገባው አመልክቷል። ዜና ምንጩ በጉዳዩ ዙሪያ ለድርጅቱ ላቀረብኩት ጥያቄ ምላሽ አላገኘኹም ብሏል። ድርጅቱ በክልሉ ከሽራሮ ከተማ መጋዘኑ ላይ በተፈጸመ ለ100 ሺህ ተረጂዎች የሚበቃ የሰብዓዊ ዕርዳታ ዝርፊያ ዙሪያ ምርመራ ስለመጀመሩ ከሦስት ሳምንታት በፊት ተዘግቦ እንደነበር ይታወሳል።

2፤ 47 የመብት ተሟጋች ድርጅቶች የኢትዮጵያ መንግሥት "ያልተገደበ የኢንተርኔት አገልግሎትን እንዲያረጋግጥና የበይነ መረብ መገናኛ ዘዴዎችን ተደራሽ እንዲያደርግ" ለጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ደብዳቤ መጻፋቸውን ዓለማቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቹ ኮሚቴ (ሲፒጄ) ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ድርጅቶቹ መንግሥት ኢንተርኔት መዝጋትን በመሳሪያነት መጠቀሙ እንዳሳሰባቸው በደብዳቤያቸው መግለጣቸውን ሲፒጄ ገልጧል። መንግሥት በተያዘው ወር በአማራ ክልል ተቃውሞ ሲቀሰቀስ የኢንተርኔት አገልግሎቶትን መዝጋቱንና ባለፈው የካቲት ደሞ የተወሰኑ የበይነ መረብ መገናኛ ዘዴዎችን መገደቡን የጠቀሱት ድርጅቶቹ፣ የኢንተርኔትን ማቋረጥ መሠረታዊ መብቶችን የሚጥስና የጋዜጠኞችን የሥራ ነጻነት የሚያሳጣ መኾኑን ማውሳታቸውን ሲፒጄ ገልጧል።

3፤ አብን አማራ ክልልን "የጦርነት ቀጠና ማድረግ የሚፈልጉ አካላት በአስቸኳይ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ" ዛሬ ባወጣው መግለጫ አሳስቧል። የክልሉ የፋኖ ታጣቂዎች ከመከላከያ ሠራዊትና የፌደራል ጸጥታ ኃይሎች ጋር በአኹኑ ወቅት የገቡበትን መካረር ለማርገብ፣ ከጸጥታ አካላቱ ጋር ንግግር እንዲጀምሩም ፓርቲው ጥሪ አድርጓል። ፓርቲው፣ ከፌደራልና ክልል መንግሥታት፣ ከምሁራን፣ ከተቃዋሚ ፓርቲዎችና ከአገር ሽማግሌዎች የተውጣጣ አካል ከክልሉ ሕዝብ ጋር "በአንገብጋቢ አጀንዳዎች" ዙሪያ እንዲወያይ፣ መንግሥት የውይይት በሩን እንዲከፍትና በክልሉ ውስጥ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ "ያላግባብ የታሠሩ" አካላት እንዲፈቱም ጠይቋል።

4፤ ኢዜማ መንግሥት ከኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ጋር በታንዛኒያ በሚያደርገው የሰላም ድርድር "እነማን እየተሳተፉ" እንደኾነ ለሕዝብ ግልጽ መረጃ እንዲሰጥ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ጠይቋል። ፓርቲው፣ መንግሥት ወደፊትም ከቡድኑ ጋር በድርድሩ የሚደርስበትን "የስምምነት ይዘት" እና ስምምነቱ "እንዴት እንደሚፈጸም" ግልጽ መረጃ በመስጠት ሕዝቡን "ከውዥንብርና ትርምስ እንዲጠብቅ" አሳስቧል። ገዥው ፓርቲ ከተለያዩ ቡድኖች ጋር የሚያደርጋቸው የሰላም ድርድሮች "ግልጽነት ሲጎድላቸውና አፈጻጸማቸው በተገቢው ኹኔታ ሳይከናወን" ሲቀር ታዝቤያለሁ ያለው ኢዜማ፣ ይህንኑ ማሳሰቢያ ያወጣው መንግሥት ኤርትራ ውስጥ ይንቀሳቀስ ከነበረው ኦነግና ሕወሃት ጋር ቀደም ሲል ያደረጋቸው ድርድሮች ግልጽነት የጎደላቸው እንደነበሩ በማስታወስ መኾኑን ጠቅሷል።

5፤ ሚድሮክ ኩባንያ የለገደምቢ ወርቅ ማዕድን ማውጫው በነዋሪዎችና በአካባቢው ላይ ብክለት አስከትሏል በማለት ሂውማን ራይትስ ዎች ያቀረበበትን ውንጀላ "መሠረተ ቢስ" በማለት ማስተባበሉን ሪፖርተር አስነብቧል። ሂውማን ራይትስ ዎች ከለገደምቢ ማዕድን ማውጫ የሚወጡ መርዛማ ንጥረ ነገሮች ጉዳት እያስከተሉ ነው በማለት፣ መንግሥት ፍቃዱን እንዲሰርዝበት መጠየቁ ይታወሳል። የኦሮሚያ ክልል ማዕድን ባለሥልጣንም፣ ሂውማን ራይትስ ዎች መንግሥት ማዕድን ማውጫውን ቀደም ሲል ለምን እንደዘጋውና ለምን በድጋሚ ሥራ እንዲጀምር እንደፈቀደ "የሚያውቀው አንዳችም ነገር የለም" ማለቱን ዜና ምንጩ ጠቅሷል። ባለሥልጣኑ፣ በነዋሪዎች የሚታየው የጤና ችግር ሚድሮክ ማዕድን ማውጫውን ከመረከቡ ከ20 ዓመት በፊት ተያይዞ የመጣ ችግር ሊኾን ይችላል ማለቱንም ዘገባው ገልጧል።

6፤ የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የሱዳኑ ግጭት "ባስቸኳይ ሊቆም ይገባዋል" ሲሉ ትናንት ለአገራቸው ቴሌቪዥን በሰጡት ቃለ ምልልስ ላይ ተናግረዋል። የሱዳን ግጭት ሊፈታ የሚችለው በራሳቸው በሱዳናዊያን መኾኑን ያሰመሩበት ኢሳያስ፣ ጎረቤት አገራት ለሱዳናዊያን ጥረት ድጋፍ ሊያደርጉ እንደሚችሉ ጠቁመዋል። ፕሬዝዳንት ኢሳያስ፣ ኤርትራ፣ ከውጊያ የሚሸሹ ኤርትራዊያን ዜጎችን፣ ሲቪል ሱዳናዊያን ስደተኞችንና ሌሎች የውጭ ዜጎችን በደስታ እንደምትቀበልም በመግለጫቸው ገልጸዋል።

7፤ የሱዳን ጦር ሠራዊት ዋና አዛዥ ጀኔራል ቡርሃን እና የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሠራዊት ዋና አዛዥ ጀኔራል ደጋሎ የሰባት ቀናት ተኩስ አቁም ለማድረግ በመርህ ደረጃ መስማማታቸውን የደቡብ ሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ኹለቱ ባላንጣዎች ከመጭው ሐሙስ ጀምሮ ለሰባት ቀናት የሚቆይ ተኩስ አቁም ለማድረግ መስማማታቸውን የገለጡት፣ የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ዛሬ ኹለቱንም በስልክ ካግባቧቸው በኋላ መኾኑን መግለጫው አመልክቷል። ኹለቱ ተፋላሚ ወገኖች ፕሬዝዳንት ኪር ባቀረቡላቸው ሃሳብ መሠረት፣ ወደፊት በሚወሰን ቦታ ግጭቱን ለማስቆም ለሚያደርጉት ንግግር ተወካዮቻቸውን ለመሰየም እንደተስማሙ ተገልጧል።

8፤ ንግድ ባንክ ዛሬ የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋ 54 ብር ከ1793 ሳንቲም እና መሸጫ ዋጋው 55 ብር ከ2629 ሳንቲም ሆኖ እንደዋለ በድረገጹ ገልጧል። የአንድ የእንግሊዝ ፓውንድ መግዣ ዋጋ ደሞ 64 ብር ከ4799 ሳንቲም እና መሸጫው 65 ብር ከ7695 ሳንቲም ሆኗል። በተመሳሳይ አንድ ዩሮ በ59 ብር ከ4997 ሳንቲም ተገዝቶ፣ በ60 ብር ከ6897 ሳንቲም ሲሸጥ መዋሉን ባንኩ ገልጧል። #ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                  
@emsmereja
4.2K views17:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-02 07:10:42 ማክሰኞ ማለዳ! ሚያዝያ 24/2015 ዓ.ም የEMS ዐበይት ዜናዎች

1፤ በግጭት በምትታመሰው ሱዳን የሚኖሩ በተለይ ከትግራይ ክልል የተሰደዱ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች መንግሥት እንዲረዳቸው መጠየቃቸውን ቪኦኤ ዘግቧል። መንግሥት ወደ አገራቸው እንዲመልሳቸው የጠየቁት፣ በሰሜኑ ጦርነት ሳቢያ ወደ ሱዳን የተሰደዱና በምሥራቃዊ ሱዳን ዑምራኩባ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ስደተኞች እንደኾኑ ዘገባው አመልክቷል። ስደተኞቹ የሱዳኑ ግጭት መቀስቀሱን ተከትሎ፣ በስደተኛ ጣቢያው የተለያዩ አገልግሎቶችን ሲሰጡ የነበሩ የረድኤት ድርጅቶች ጣቢያውን ለቀው መውጣታቸውን መናገራቸውን ዘገባው ጠቅሷል።

2፤ በትግራይ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ትምህርት ቤቶች ትናንት እንደገና መከፈት እንደጀመሩ የክልሉ ትምህርት ቢሮ መግለጡን ጠቅሶ የክልሉ ቴሌቪዥን ዘግቧል። በክልሉ በኮሮና ወረርሽኝና ከዚያም በሰሜኑ ጦርነት ሳቢያ ኹሉም ትምህርት ቤቶች ከሦስት ዓመታት በላይ ተዘግተው ነበር። በክልሉ የሚገኙ አብዛኞቹ ትምህርት ቤቶች በጦርነቱ ከባድ ወይም ከፊል ጉዳት እንደደረሰባቸው ሲገለጽ ቆይቷል።

3፤ ኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና ጅቡቲ በቅርቡ በአልሸባብ ላይ ለሦስት ወራት የሚቆይ የጋራ ልዩ ወታደራዊ ርምጃ እንደሚወስዱ የሱማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሞሐመድ ትናንት መናገራቸውን የአገሪቱ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ሱማሊያ በጋራ ወታደራዊ ዘመቻው ዙሪያ ከሦስቱ አገራት ጋር ስምምነት ላይ መድረሷን ፕሬዝዳንቱ ማረጋገጣቸውን ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል። ፕሬዝዳንቱ የጋራ ወታደራዊ ዘመቻውን በበላይነት የምትመራው ሱማሊያ እንደኾነችና ዘመቻውን የሚያስተባብር ወታደራዊ ዕዝ ሞቃዲሾ ውስጥ እንደሚቋቋም መግለጣቸውን ዘገባዎቹ አመልክተዋል።

4፤ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒ ብሊንከን ለሱዳኑ ውጊያ ሰላማዊ መፍትሄ ማፈላለግ ቀጥለዋል። ብሊንከን፣ የሱዳን ጦር ሠራዊትና ፈጥኖ ደራሹ ሠራዊት ግጭቱን ባስቸኳይ እንዲያቆሙና ያልተገደበ ሰብዓዊ ዕርዳታ እንዲገባ እንዲፈቅዱ ዓለማቀፍ ግፊት በማድረግ አስፈላጊነት ዙሪያ ከኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ እና ከአፍሪካ ኅብረት የወቅቱ ሊቀመንበርና ከኮሞሮሱ ፕሬዝዳንት አዛሊ አሶማኒ ጋር በስልክ መነጋገራቸውን መስሪያ ቤታቸው ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ብሊንከን፣ ኹለቱ ተፋላሚ ወገኖች የተኩስ አቁም ቃል ኪዳኖችን እንዲያከብሩና ድርድር እንዲጀምሩ ግፊት በማድረግ አስፈላጊነት ዙሪያ ከኹለቱ መሪዎች ጋር ሃሳብ መለዋወጣቸውን መግለጫው ጠቅሷል። አሜሪካ ግጭቱን ለማስቆም አፍሪካ ኅብረት መር የኾነ አፋጣኝ ዕቅድ እንዲነደፍ እንደምትደግፍ በመግለጫዋ ገልጣለች። #ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                  
@emsmereja
4.5K views04:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-01 19:54:30 ሰኞ ምሽት! ሚያዝያ 23/2015 ዓ.ም የEMS ዐበይት ዜናዎች

1፤ እናት ፓርቲ ፌደራል መንግሥቱ በአማራ ክልል ውስጥ የጀመረውን "የጅምላ እስር፣ የትጥቅ ማስፈታት ዘመቻ፣ የድርጅቶችና ግለሰቦችን የገንዘብ እንቅስቃሴ የማገድ ሂደት" እንዲያቆም ዛሬ ባወጣው መግለጫ ጠይቋል። ፓርቲው፣ መንግሥት "በማንአለብኝነት አካሄዱ ቀጥሎ በአገርና በሕዝብ ላይ ለሚደርሰው ማንኛውም ዓይነት ጥፋትና ውድመት ከተጠያቂነት አያመልጥም" በማለት አስጠንቅቋል። ፓርቲው፣ በአንዳንድ ክልሎች በገዥው ፓርቲ ባለሥልጣናት ላይ በተፈጸሙ ግድያዎች ላይ "ምርምራ ባልተካሄደበትና ጥፋተኞች ባልተለዩበት ኹኔታ" ይደረጋሉ ያላቸው ፍረጃዎች "የፍትህ አሰጣጡን እንደሚያዛቡ" በመግለጽም በመግለጫው ተችቷል።

2፤ ፌደራል ፖሊስ የቀድሞውን የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋዜጠኛ አክሊሉ አበበን በአደገኛ ዕጽ አዘዋዋሪነት ጠርጥሬ ትናንት በቁጥጥር ስር አውየዋለኹ ማለቱን የመንግሥት ዜና አውታሮች ዘግበዋል። ተጠርጣሪው በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለው፣ ኹለት ነጥብ 10 ኪሎ ግራም ኮኬን በጉዞ ሻንጣው ውስጥ በመያዝ ከቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ወደ ዱባይ በአውሮፕላን ሊጓዝ ሲል እንደኾነ ተገልጧል። ተጠርጣሪው ከአራት ወራት በፊት "በስነ ምግባር ጉድለት" ከጣቢያው ሲባረር የጋዜጠኝነት መታወቂያውን እንዳልመለሰና በቁጥጥር ስር በዋለበት ወቅት የቀድሞ መስሪያ ቤቱ የሰጠውን የጋዜጠኝነት መታወቂያ ይዞ እንደተገኘ ዘገባዎቹ አመልክተዋል።

3፤ ጅቡቲ "ሕገወጥ ፍልሰተኞች" ናቸው ያለቻቸውን ሦስት ሺህ የውጭ ዜጎች በቁጥጥር ስር ማዋሏን የፈረንሳዩ ዜና ወኪል ዘግቧል። የአገሪቱ መንግሥት በቁጥጥር ስር ያዋላቸውን ከጎረቤት አገራት የሄዱ "ሕገወጥ ፍልሰተኞች" ወደየአገራቸው ለመመለስ መወሰኑንና ፍልሰተኞቹ በገዛ ፍቃዳቸው በ30 ቀናት ውስጥ ለመንግሥት ሪፖርት እንዲያደርጉ የጊዜ ገደብ መስጠቱን ዘገባው አመልክቷል። ባለፈው ዓመት ብቻ 22 ሺህ ሕገወጥ ፍልሰተኞች ወደ አገሪቱ መግባታቸውን የአገሪቱ ደኅንነት ሚንስቴር መናገሩን ዘገባው ጨምሮ ጠቅሷል።

4፤ የሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች ከትናንት እኩለ ሌሊት ጀምሮ ያራዘሙትን የ72 ሰዓታት ተኩስ አቁም በድጋሚ በመጣስ ዛሬም ውጊያውን እንደቀጠሉ ዓለማቀፍ የዜና ወኪሎች ዘግበዋል። የአገሪቱ ጦር ሠራዊት ዋና አዛዥ ጀኔራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን በግጭቱ ዙሪያ የሚነጋገሩ መልዕክተኛቸውን ወደ ሪያድ የላኩ ሲሆን፣ ግብጽ በበኩሏ ኹለቱ ወገኖች "አስቸኳይ የግጭት ማቆም" ስምምነት ላይ እንዲደርሱ የሚጠይቅ ረቂቅ የውሳኔ ሃሳብ ዛሬ ለዓረብ ሊግ አስቸኳይ ስብሰባ ማቅረቧን ገልጣለች። ተመድ በውጊያው ሳቢያ ከ800 ሺህ በላይ ሱዳናዊያን ወደ ጎረቤት አገራት ሊሰደዱ ይችላሉ ሲል አስጠንቅቋል።

5፤ አንጋፋው የኬንያ ተቃዋሚ መሪ ራይላ ኦዱንጋ ኬንያዊያን ከነገ ጀምሮ በፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ መንግሥት ላይ እንደገና የአደባባይ ተቃውሞ ለማድረግ ሰልፍ እንዲወጡ ጥሪ ማድረጋቸውን የአገሪቱ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ኦዲንጋ ኬንያዊያን በድጋሚ ወደ አደባባይ ለተቃውሞ እንዲወጡ ጥሪ ያደረጉት፣ ፕሬዝዳንት ሩቶ ጥያቄያቸውን በፓርላማዊ አሠራር ለመፍታት ቁርጠኛ አልኾኑም በማለት ነው። ኦዲንጋ፣ መንግሥት የአገሪቱን የዋጋ ንረት እንዲቀንስና የብሄራዊ ምርጫ ኮሚሽኑን በብቸኝነት እንደገና ከማዋቀር እንዲቆጠብ ለመጠየቅ ባለፈው ወር በጠሯቸው ተከታታይ የተቃውሞ ሰልፎች ላይ ሰልፈኞች ከጸጥታ ኃይሎች ጋር መጋጨታቸው ይታወሳል።

6፤ ንግድ ባንክ ዛሬ የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋ 54 ብር ከ1696 ሳንቲም እና መሸጫ ዋጋው 55 ብር ከ2530 ሳንቲም ሆኖ እንደዋለ በድረገጹ ገልጧል። የአንድ የእንግሊዝ ፓውንድ መግዣ ዋጋ ደሞ 64 ብር ከ4115 ሳንቲም እና መሸጫው 65 ብር ከ6997 ሳንቲም ሆኗል። በተመሳሳይ አንድ ዩሮ በ59 ብር ከ7978 ሳንቲም ተገዝቶ፣ በ60 ብር ከ9938 ሳንቲም ሲሸጥ መዋሉን ባንኩ ገልጧል። #ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                  
@emsmereja
4.7K views16:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-01 08:49:17 ሰኞ ጠዋት! ሚያዝያ 23/2015 ዓ.ም የEMS ዐበይት ዜናዎች

1፤ የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌደሬሽን "በዝቅተኛ እርከን ላይ የሚገኙ ሠራተኞች የደመወዝ እንዲሻሻል" መንግሥትን ለመጠየቅ ዛሬ በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ እንዳያካሂድ እንደተከለከለ አስታውቋል። ኮንፌደሬሽኑ ዛሬ የሚከበረውን ዓለማቀፍ የወዛደሮች ቀን ታሳቢ በማድረግ በመስቀል አደባባይ የጠራውን ሰልፍ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እንዳልፈቀደ ገልጧል። የኮንፌደሬሽኑ ፕሬዝዳንት ካሳሁን ፎሎ የሠራተኛው የደሞዝ እንዲስተካከል ከሦስት ዓመታት በላይ ከመንግሥት ጋር ቢደራደሩም ውጤት እንዳላገኙ ባለፈው ወር ለዋዜማ ተናግረው ነበር።

2፤ የጸጥታና ደኅንነት ግብረ ኃይል በአማራ ክልል የሽብር ተግባራትን ሲፈጽሙ አገኘኋቸው ያላቸውን 47 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል። ግብረ ኃይሉ ከተጠርጣሪዎቹ የነፍስ ወከፍና የቡድን ጦር መሳሪያዎችን መያዙንና፣ የተጠርጣሪዎቹ ዓላማ በክልሉ ሕገመንግሥታዊ ሥርዓቱን በማፍረስ ክልላዊ ሥልጣን በኋይል መቆጣጠርና ፌደራል መንግሥቱን ለመጣል ነበር ብሏል። የኅቡዕ ቡድኑ ከ16 የዲያስፖራ ጽንፈኛ አካላት ጋር ግንኙነት ነበረው ያለው ግብረ ኃይሉ፣ ቡድኑ በክልሉ ውስጥ ታጣቂዎችን የመመልመልና ማሰልጠን እንቅስቃሴ ሲያደርግ እንደነበር ጠቅሷል። በዚሁ እንቅስቃሴ ውስጥ ተሳትፈዋል ከተባሉት ውስጥ፣ አንጋፋው ፖለቲከኛ ልደቱ አያሌው እና የኢትዮ- 360 የዩትዩብ ጣቢያ ባልደረቦች ይገኙበታል።

3፤ ኢትዮጵያ ያሰለጠነቻቸው የሱማሊያ ምልምል ወታደሮች ሥልጠናቸው በሳምንቱ መጨረሻ ማጠናቀቃቸውን የሱማሊያ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ሰልጣኞቹ በቅርቡ የመንግሥት ወታደሮች ከአልሸባብ ጋር የሚያደርጉትን ውጊያ እንደሚቀላቀሉ ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል። ኢትዮጵያ አሰልጥና ያስመረቀቻቸው ሱማሊያዊያኑ ምልምሎች ብዛታቸው ስንት እንደኾነ ግን አልተገለጠም። ባለፈው መጋቢት ኡጋንዳ 3 ሺህ ምልምሎችን ለሱማሊያ አሰልጥና ማስረከቧ የሚታወስ ሲሆን፣ ኤርትራም ለኹለተኛ ዙር ሥልጠና ሱማሊያዊያን ምልምሎችን ለማሰልጠን እንደወሰደች ከጥቂት ወራት በፊት ተዘግቦ ነበር።

4፤ የሱዳን ጦር ሠራዊት እና ፈጥኖ ደራሽ ሠራዊት ትናንት እኩለ ሌሊት ያበቃውን የ72 ሰዓታት ተኩስ አቁም ለኹለተኛ ጊዜ ለማራዘም መስማማታቸውን አስታውቀዋል። ኾኖም ኹለቱ ተፋላሚ ወገኖች ተኩስ አቁሙ ከመራዘሙ በፊትም ካርቱም ውስጥ ውጊያ እንዳላቆሙ የውጭ ዜና ምንጮች ዘግበዋል።
#ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                  
@emsmereja
552 views05:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-01 08:47:05 ሰኞ ጠዋት! ሚያዝያ 23/2015 ዓ.ም የEMS ዐበይት ዜናዎች

1፤ የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌደሬሽን "በዝቅተኛ እርከን ላይ የሚገኙ ሠራተኞች የደመወዝ እንዲሻሻል" መንግሥትን ለመጠየቅ ዛሬ በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ እንዳያካሂድ እንደተከለከለ አስታውቋል። ኮንፌደሬሽኑ ዛሬ የሚከበረውን ዓለማቀፍ የወዛደሮች ቀን ታሳቢ በማድረግ በመስቀል አደባባይ የጠራውን ሰልፍ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እንዳልፈቀደ ገልጧል። የኮንፌደሬሽኑ ፕሬዝዳንት ካሳሁን ፎሎ የሠራተኛው የደሞዝ እንዲስተካከል ከሦስት ዓመታት በላይ ከመንግሥት ጋር ቢደራደሩም ውጤት እንዳላገኙ ባለፈው ወር ለዋዜማ ተናግረው ነበር።

2፤ የጸጥታና ደኅንነት ግብረ ኃይል በአማራ ክልል የሽብር ተግባራትን ሲፈጽሙ አገኘኋቸው ያላቸውን 47 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል። ግብረ ኃይሉ ከተጠርጣሪዎቹ የነፍስ ወከፍና የቡድን ጦር መሳሪያዎችን መያዙንና፣ የተጠርጣሪዎቹ ዓላማ በክልሉ ሕገመንግሥታዊ ሥርዓቱን በማፍረስ ክልላዊ ሥልጣን በኋይል መቆጣጠርና ፌደራል መንግሥቱን ለመጣል ነበር ብሏል። የኅቡዕ ቡድኑ ከ16 የዲያስፖራ ጽንፈኛ አካላት ጋር ግንኙነት ነበረው ያለው ግብረ ኃይሉ፣ ቡድኑ በክልሉ ውስጥ ታጣቂዎችን የመመልመልና ማሰልጠን እንቅስቃሴ ሲያደርግ እንደነበር ጠቅሷል። በዚሁ እንቅስቃሴ ውስጥ ተሳትፈዋል ከተባሉት ውስጥ፣ አንጋፋው ፖለቲከኛ ልደቱ አያሌው እና የኢትዮ- 360 የዩትዩብ ጣቢያ ባልደረቦች ይገኙበታል።

3፤ ኢትዮጵያ ያሰለጠነቻቸው የሱማሊያ ምልምል ወታደሮች ሥልጠናቸው በሳምንቱ መጨረሻ ማጠናቀቃቸውን የሱማሊያ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ሰልጣኞቹ በቅርቡ የመንግሥት ወታደሮች ከአልሸባብ ጋር የሚያደርጉትን ውጊያ እንደሚቀላቀሉ ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል። ኢትዮጵያ አሰልጥና ያስመረቀቻቸው ሱማሊያዊያኑ ምልምሎች ብዛታቸው ስንት እንደኾነ ግን አልተገለጠም። ባለፈው መጋቢት ኡጋንዳ 3 ሺህ ምልምሎችን ለሱማሊያ አሰልጥና ማስረከቧ የሚታወስ ሲሆን፣ ኤርትራም ለኹለተኛ ዙር ሥልጠና ሱማሊያዊያን ምልምሎችን ለማሰልጠን እንደወሰደች ከጥቂት ወራት በፊት ተዘግቦ ነበር።

4፤ የሱዳን ጦር ሠራዊት እና ፈጥኖ ደራሽ ሠራዊት ትናንት እኩለ ሌሊት ያበቃውን የ72 ሰዓታት ተኩስ አቁም ለኹለተኛ ጊዜ ለማራዘም መስማማታቸውን አስታውቀዋል። ኾኖም ኹለቱ ተፋላሚ ወገኖች ተኩስ አቁሙ ከመራዘሙ በፊትም ካርቱም ውስጥ ውጊያ እንዳላቆሙ የውጭ ዜና ምንጮች ዘግበዋል።
#ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                  
@emsmereja
2.0K views05:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 22:00:31 ኢሠማኮ የሠራተኞች ቀንን እንዳያከብር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መከልከሉን አስታወቀ
የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) ነገ ሰኞ ሚያዚያ 22/2015 በመስቀል አደባባይ የሠራተኞች ቀንን በማስመልከት ለማክበር የያዘው ፕሮግራም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መከልከሉን ገለጸ።

ኮንፌዴሬሽኑ በየዓመቱ ሚያዝያ 23 የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የሠራተኞች ቀን፣ በመስቀል አደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ ለማክበር ፕሮግራም መያዙን አስታውቆ ነበር።

ይሁን እንጂ በዓሉን በሰላማዊ ሰልፍ ለማክበር ዝግጅት ከጨረሰ በኋላ፣ ፕሮግራሙ እንዳይከናወን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ ቢሮ መከልከሉን አዲስ ማለዳ ያገኘችው መረጃ ያመላክታል።

የዘንድሮው የሠራተኞች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ134ኛ፣ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ48ኛ ጊዜ የሚከበር ሲሆን፣ ኢሠማኮ በ ዓሉን "ለሠራተኞች መሠረታዊ ጥያቄዎች አፋጣኝ መፍትሄ" በሚል መሪ ቃል ለማክበር መዘጋጀቱን በሰጠው መግለጫ ገልጾ ነበር።

መሪ ቃሉ የተመረጠው በአሁኑ ወቅት የተከሰተዉ የኑሮ ዉድነትና የሠራተኞች መብት መጣስን በተመለከተ ለመንግሥት በማቅረብ መፍትሔ እንዲያገኙ ለማድረግ መሆኑም ተመልክቷል።

የኢሠማኮ ጠቅላይ ምክር ቤት መጋቢት 28/2015 ባካሄደዉ መደበኛ ስብሰባ በሠራተኞች ዋና ዋና ችግሮች ላይ ተወያይቶ፣ የዘንድሮው በዓል በሰላማዊ ሰልፍ በአደባባይ እንዲከበርና የሠራተኛው ጥያቄዎች ለሚመለከታቸዉ የመንግሥት አካላት እዲቀርብ ወስኖ ነበር።

ኢሠማኮ የሠራተኛ መብቶች እንዳከበሩ በተደጋጋሚ ለሚመለከታቸው አካላት ጥሪ ሲያቀርብ የነበረ ሲሆን፤ በተለይ የዋጋ ንረት ተከትሎ የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝ እንዲሻሻል መጠየቁም የሚታወስ ነው። #ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                  
@emsmereja
3.0K views19:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 18:49:58
ከፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል የተሰጠ መግለጫ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ በአማራ ክልል ሕገ-መንግስታዊ ሥርዓቱን በማፍረስ ክልላዊ ስልጣንን በኃይል ለመያዝ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት በህቡዕ ተደራጅተውና ተቀናጅተው በሚንቀሳቀሱ ጽንፈኛ ኃይሎች ላይ የማያዳግም ህጋዊ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል ሚያዚያ 20 ቀን 2015 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ…
3.7K views15:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 18:48:02 የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል
ሚያዝያ 22 ቀን 2015 ዓ.ም
#ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                  
@emsmereja
3.4K views15:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 18:48:02 ከፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል የተሰጠ መግለጫ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
በአማራ ክልል ሕገ-መንግስታዊ ሥርዓቱን በማፍረስ ክልላዊ ስልጣንን በኃይል ለመያዝ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት በህቡዕ ተደራጅተውና ተቀናጅተው በሚንቀሳቀሱ ጽንፈኛ ኃይሎች ላይ የማያዳግም ህጋዊ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል ሚያዚያ 20 ቀን 2015 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ማስታወቁ ይታወሳል።

በመሆኑም የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ- ኃይል እየወሰደ ባለው እርምጃ በዚህ ህቡዕ አደረጃጀት ውስጥ ሲንቀሳቀሱና የሽብር ተግባር ሲፈጽሙ የተገኙ 47 ተጠርጣሪዎችን ከበርካታ የነፍስ ወከፍና የቡድን መሣሪያዎች፣ ቦንቦችና ተቀጣጣይ ፈንጂዎች እንዲሁም ከሳተላይት መገናኛ መሣሪያዎች እና የተለያዩ መረጃዎችን ከያዙ ላፕቶፖች ጋር በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ለመገናኛ ብዙኃን በላከው መግለጫ አመልክቷል።ተጠርጣሪዎቹ የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮችን የግድያ ዒላማ በማድረግ፤ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል በመናድ የክልሉን መንግሥታዊ መዋቅር በመቆጣጠር የፌደራል መንግሥትን ለመጣል በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት ተደራጅተው እና ተቀናጅተው በህቡዕ ሲንቀሳቀሱ እንደተደረሰባቸው አስታውቋል።

ግብረ-ኃይሉ ለመገናኛ ብዙኃን በላከው መግለጫ፤ መንግስት የዴሞክራሲ ምህዳሩን ለማስፋት እና ለሐሳብ ትግል ሰፊ ዕድል በመስጠቱ እንዲሁም ችግሮች በውይይት እንዲፈቱ ባደረገው ጥረት ብዙዎች ይሄንን ዕድል መጠቀማቸውን አስታውሷል። ይሁንና የአማራን ህዝብ የማይወክሉ እነዚህ ጽንፈኛ ኃይሎች የመንግሥትን ሰላማዊ አማራጭ በመግፋት በውጭ ከሚገኙ ግብረ-አባሮቻቸው ጋር በህቡዕ በመገናኘት የፖለቲካ፣ የወታደራዊ፣ የኢንተለጀንስ፣ የሚዲያ እና የፋይናንስ ክንፍ ማቋቋምቸው እንደተደረሰበት መግለጫው አመልክቷል።

የጋራ ግብረ-ኃይሉ መግለጫ እንዳመለከተው፤ የጽንፈኛ ኃይሎችን የፖለቲካ፣ የወታደራዊ፣ የኢንተለጀንስ፣ የፋይናንስ እና የሚዲያ ክንፍ የሚመራው ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ የተባለ ግለሰብ ሲሆን፤ ይህ ክንፍ በተለያዩ የውጭ ሀገራት ከሚገኙ 16 ጽንፈኛ የዲያስፖራ አባላት ጋር ትስስር በመፍጠር በሚያገኛቸው የሎጀስቲክስ እና የፋይናንስ ድጋፎች በአማራ ክልል ከባህርዳር ከተማ ጀምሮ በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች ታጣቂዎችን የመመልመል፣ የማሰልጠን፣ የማስታጠቅና የማሠማራት ተግባር በማከናወን በክልልና በፌደራል ደረጃ ሽብር እና ግድያ እንዲፈጽሙ ተልዕኮ ሲሰጥ እንደነበር በተደረገ ክትትል እና ምርመራ ተደርሶበታል ብሏል መግለጫው። ለዚህም በለጠ ሸጋው እና ምሕረት ወዳጆ ወይም በቅጽል ስሙ ምሬ ወዳጆ በተባሉት የጽንፈኛ ኃይሉ ታጣቂ መሪዎች እና ግብረ-አባሮቻቸው ሰሞኑን በትውልድ በቀኤአቸው ግፍና ጭካኔ በተሞለበት አኳሃን የተገደሉት የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አባልና የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ግርማ የሺጥላ እና የጥቃት ሰለባ የሆኑ የሥራ ባልደረቦቻቸው ማሳያ ናቸው ብሏል የጋራ ግብረ-ኃይሉ መግለጫ።

የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል መግለጫ አክሎም፤ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት የሚገኙ እነዚህ ጽንፈኛ ኃይሎች በፈጠሩት ህቡዕ አደረጃጀት እኩይ ዓላማቸውን ለማስፈጸም በአማራና በሌሎች አካባቢዎች በሚገኙ 130 ወረዳዎች የመለመላቸውንና በህቡዕ ያዘጋጇቸውን 450 ግለሰቦች የአማራ ክልል ህዝብ የመረጣቸውንና በተለያዩ የአመራር እርከኖች ላይ ያስቀመጣቸውን በኃይል በማስወገድ በራሳቸው መዋቅር የመተካት ሥራ ሲሰሩ እንደነበር በክትትል እና በምርመራ የተደረሰባቸው መሆኑን አስታውቋል።በተጨማሪም ጽንፈኛ ኃይሎች የክልሉን የፀጥታ ኃይልንም በራሳቸው ታጣቂዎች ለመቀየር ተዘጋጅተው እንደነበር የተገኛው መረጃ ማመላከቱን ገልጿል።

ዶ/ር መሥፍን ኃ/ማርያም፣ ዶ/ር ግሩም ላቀውና ሌሎችም በተለያዩ የውጭ ሀገራት የሚኖሩ የጽንፈኛ ኃይሉ ተባባሪዎች ከውጭ ሆነው የፖለቲካ ክንፉን እንደሚያስተባብሩ፤ አንተነህ ብርሃን፣ ወርቁ ጓዴና ሌሎችም ከሀገር ውስጥና ከውጭ የሚላከውን ገንዘብ እንዲቀበሉና ለሽብር ተልዕኮ ማስፈፀሚያ እንዲያውሉ የባንክ አካውንት እንደተከፈተላቸው በክትትልና በተደረገው ምርመራ መረጋገጡን የገለፀው የጋራ ግብረ-ኃይሉ መግለጫ፤ ቴዎድሮስ አስፋውን ጨምሮ ሌሎችም በዚሁ የሽብር እንቅስቃሴ ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን መግለጫው አስታውቋል።

መግለጫው አያይዞም የእነዚህ ጽንፈኛ ኃይሎችን የሚዲያና ፕሮፓጋንዳ ክንፍ የሚመራው መስከርም አበራ በተባለች ግለሰብ መሆኑን ጠቅሶ፤ በዚህ ህቡዕ አደረጃጀት ውስጥ ከሀገር ውስጥ ዳዊት በጋሻው የተባለ ግለሰብ እንዲሁም ከተለያዩ የውጭ ሀገራት ደግሞ ከኢትዮ 360 እና መረጃ ቲቪ ሀብታሙ አያሌው፣ ምንአላቸው ስማቸው፣ ብሩክ ይባስ እና እየሩሳሌም ተ/ፃዲቅ በተጨማሪም ዘመድኩን በቀለ እና ልደቱ አያሌው ከአንከር ሚዲያ መሳይ መኮንን እንዲሁም ሌሎች ግለሰቦች የዚህ እኩይ ዓላማ አስፈፃሚ አባላት መሆናቸውን በምርመራ መረጋገጡን ገልጿል።

እነዚህ ጽንፈኛ ኃይሎች የሀሰት ወሬዎችን በመፍጠር እና ከፍተኛ የሽብር ፕሮፓጋንዳ በመንዛት ህዝቡን በብሄር እና በሀይማኖት በመከፋፈልና በማጋጨት የክልል እና የፌደራል መንግሥትን በኃይል ለመጣል እንዲሁም ሀገሪቱ ከጀመረችው የለውጥና የልማት መንገድ ወጥታ ወደ ለየለት ሁከትና ትርምስ እንድትገባ በህቡዕ ተደራጅተው እየሠሩ መሆናቸውን የገለፀው የጋራ ግብረ ኃይሉ፤ በሀገር ውስጥና በውጭ ሆነው በሀሰት ሀገር ለማፍረስ የሚሰሩ እነዚህን ጨምሮ ሌሎችም በህቡዕ አደረጃጀቱ ውስጥ ያሉ ግለሰቦችም ጭምር በሽብርተኝነት ምርመራ እየተጣራባቸው መሆኑን መግለጫው አመልክቷል።

እነዚህ የሽብር ኃይሎች ከሚኖሩባቸው ሀገራት በአለም አቀፍ የፖሊስ ድርጅት (ኢንተርፖል) እንዲሁም እነሱ ከሚኖሩባቸው ሀገራት መንግሥት የፀጥታ እና የደኅንነት ተቋማት ጋር በተመሠረቱ የትብብር ማዕቀፎች አማካኝነት ወደ ሀገር ቤት ተላልፈው እንዲሰጡ በህግም እንዲጠየቁ እየሰራ መሆኑን እና ይህንኑ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።

የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል መግለጫ አክሎም፤ እነዚህ ውጭ ሀገር የሚኖሩ ተፈላጊዎች ከውጭ ሀገር በሚያገኙት እና በሀገር ውስጥ ያላቸውን ሀብት ተጠቅመው ለዚህ እኩይ ተግባር እያዋሉ መሆኑን በምርመራ የተደረሰበት ስለሆነ በሀገር ውስጥ ያላቸውን ሀብት የመለየት እና በህግ የመቆጣጠር ስራ እየተሰራ መሆኑንም ጭምር አስታውቋል።

ሕገ-መንግሥቱንና ሕገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለማፍረስ እየተንቀሳቀሱ የነበሩ እነዚህ ጽንፈኛ ኃይሎች የኢትዮጵያን አንድነት ከማይፈልጉ የውጭ ፀረ ሰላም ኃይሎች ጋር ተቀናጅተው መንግሥትን በኃይል ለማስወገድ ሲሰሩ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው የሚገኝ መሆኑን ያመለከተው የጋራ ግብረኃይሉ መግለጫ፤ ኅብረተሰቡ የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የሚወሰደውን እርምጃ ከትጥቅ ማስፈታት ጋር በማያያዝ ውዥንብር ለመፍጠርና የተሳሳተ መረጃ ለማሰራጨት ከሚጥሩ አካላት ራሱን እንዲጠብቅ በጋራ እንዲታገል ጥሪ አቅርቧል።

በመጨረሻም የተጀመረው ህጋዊ ኦፕሬሽን ከግቡ እንዲደርስ ህብረተሰቡ እያደረገ ላለው ከፍተኛ ተሳትፎ የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል ምስጋና እያቀረበ፤ በህግ ቁጥጥር ሥር እንዲውሉ ጥብቅ ክትትል እየተደረገባቸው ያሉ ተፈላጊዎችን ካሉበት ጠቁሞ እንዲያሲዝ በዚህ አጋጣሚ ጥሪውን እያቀረበ በቀጣይ የምንደርስበትን ውጤት ለህዝብ እየገለፀ እንደሚሄድ ያስታውቃል።
3.4K views15:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ