Get Mystery Box with random crypto!

EMS Mereja

የቴሌግራም ቻናል አርማ emsmereja — EMS Mereja E
የቴሌግራም ቻናል አርማ emsmereja — EMS Mereja
የሰርጥ አድራሻ: @emsmereja
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 14.57K
የሰርጥ መግለጫ

👉 መረጃዎች፣ጥያቄዎች፣ አስተያየቶችና የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት ከፈለጉ በዚህ ያናግሩን👉 t.me/infoetrobot
👉 የዕለታዊ ዝግጅቶችና ዜናዎች በተባባሪ አቅራቢዎች እንዲደርሷችሁ👇👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@HAQMEDIA12
Subscribe ያድርጉ

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-07-01 12:02:41 የአገራዊ ቀውሱ ዋና ምክንያት የኦሮሞን ሕዝብ የፖለቲካ ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ መመለስ አለመቻሉ ነው ሲል ኦነግ ገለጸ

ኢትዮጵያ ለገባችበት ውጥንቅጥ ዋናው ምክንያት የኦሮሞን ሕዝብ የዘመናት የፖለቲካ ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ ከመመለስ ይልቅ ኃይል ለመጠቀም መሞከር ነው ሲል የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ገለጸ።

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) 50ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በማስመልከት ባወጣው ልዩ መግለጫ፤ በኦሮሚያ ክልል ያለው ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል ያለ ሲሆን፤ በጊዜ መፍትሔ ካልተፈለገለት አገሪቷን ጭምር ወዳልተፈለገ አቅጣጫ እንዳያመራት ያሰጋል ሲል ገልጿል።

በመላው ኦሮሚያ ክልል በሚባል ደረጃ ሰላም ጠፍቷል፣ ሕዝቡም መሰረታዊ አገልግሎት የማያገኝበት ደረጃ ላይ ደርሷል ብሏል፡፡

በክልሉ እየተካሄዱ ባሉ ግጭቶችም በሚሊዮን የሚቆጭሩ ዜጎች ከቀዬያቸው ተፈናቅለዋል ያለው ግንባሩ፤ በሠላም ወጥቶ መግባትም ጥያቄ ምልክት ውስጥ ከገባ ዓመታት ተቆጥረዋል ሲል አብራርቷል፡፡

ከዕለት ዕለት እያሻቀበ ያለው የኑሮ ውድነትም ከገጠር እስከ ከተማ ያለውን ማሕበረሰብ በእጅጉ አማሯል ሲል ገልጾ፤ የአገሪቷ ችግር በእጅጉ እየተወሳሰበ መምጣቱንም ጠቅሷል፡፡

መንግሥት የማህበረሰቡን ጥያቄዎችን በአግባቡ በመመርመር እና ተገቢውን ምላሽ በመስጠት ተረጋቶ በሰላም እንዲኖር ማድረግ እንዳለበት በማሳስብም፤ የኦሮሞም ሆነ በአገሪቷ የሚኖሩ ብሔር ብሔረሰቦች ጥያቄ መልስ ሊያገኝ የሚችለው በዚህ መንገድ ብቻ ነው ብሏል።

በተጨማሪም የራስን ዕድል በራስ የመወሰን፣ የአገር ባለቤትነት ጥያቄ፣ የዴሞክራሲ እና የመሳሰሉ የሕዝቡ የዘመናት ጥያቄዎች መልስ እስኪያገኙ ግንባሩ ትግሉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስረድቷል፡፡

በተጨማሪም የኦሮሞን ሕዝብ ጥያቄ ከባድ መስዋዕትነት እየከፈለ ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ ይዞ እዚህ እንዳደረሰ ኹሉ አሁንም አስፈላጊውን መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ እንደሆነም ነው የጠቆመው።

በመጨረሻም እንደ ኦሮም ነጻነት ግንባር ኹሉ ለመብታቸው እና የሕዝብ ጥያቄ እንዲመለስ ከሚታገሉ ተቋማት ጋር ለመስራት ቃል ኪዳናችንን እናድሳለን ብሏል።

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ሊቀ መንበር ዳውድ ኢብሳ በቅርቡ በሰጡት ማብራሪያ "አገሪቷን እየመራ ያለው መንግሥት ሰዎችን ወደ እስር ቤት በማጋዝ እና በማፈን የሚያመጣው ለውጥ ስለማይኖር፤ ይህን ድርጊቱን የማያቆም ከሆነ የጀመርነውን ትግል አጠናክረን እንቀጥላለን።" ማለታቸው የሚታወስ ነው፡፡  ሼር ያድርጉ
ለትክክለኛ ወቅታዊ መረጃዎች ቻናላችንን join በማድረግ ተከታተሉ
http://t.me/emsmereja
http://t.me/emsmereja
4.7K views09:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-01 09:52:37 ፊንጫ ስኳር ፋብሪካ የህልውና አደጋ ውስጥ መግባቱን ሠራተኞች ተናገሩ

በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን የሚገኘው የፊንጫ ስኳር ፋብሪካ ከፍተኛ የህልውና አደጋ ውስጥ መግባቱን የፋብሪካው ሠራተኞች ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል፡፡

ሥማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የፋብሪካው ሠራተኞች ፋብሪካው ከጊዜ ወደ ጊዜ የማምረት አቅሙ በከፍተኛ መጠን እያሽቆለቆለ መሄዱን ገልጸው፤ አሁን ላይ የህልውና አደጋ ውስጥ መግባቱን ተናግረዋል፡፡

ፋብሪካው ከዚህ ቀደም በዓመት ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ስኳር ያመርት ነበር ያሉት ሠራተኞች፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን በዓመት ከ200 ሺሕ ኩንታል ያነሰ የስኳር ምርት ብቻ እያመረተ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡

ለዚህም እንደ ዋና ምክንያት የተጠቀሰው ለምርት ሂደቱ የሚያስፈልጉ ማሽነሪዎች አለመሟላታቸው እና ያሉትም ዕድሳት ከተደረገላቸው ረዥም ጊዜ ማስቆጠሩ ነው ተብሏል።

እንዲሁም በአካባቢው ባለው ከፍተኛ የጸጥታ ችግር ለስኳር ምርት ግብዓት የሚሆን የሸንኮራ አገዳ እንደ ልብ ተንቀሳቅሶ ማቅረብ አለመቻሉ ተጠቅሷል።

የሸንኮራ አገዳውን ለማምጣት ቢያንስ ከፋብሪካው ከ 35 እስከ 40 ኪሎ ሜትር እርቀት መጓዝ እንደሚያስፈልግ የጠቀሱት ሠራተኞቹ፤ በዚህ ወቅት ይህን ለማድረግ በፍጹም የማይታሰብ መሆኑን ተናግረዋል።

በተጨማሪም ለፋብሪካው ቋሚ ሰራተኞች የኹለት ወር፣ ለቀን ሠራተኞች ደግሞ የሦስት ወራት ደመወዝ እስካሁን እንዳልተከፈላቸው በማስረዳት፤ ከአስር ዓመት ወዲህም ለሠራተኞች ምንም አይነት የደምወዝ ጭማሪ አለመደረጉንም ጠቅሰዋል፡፡

በዚህም ከሦስት ዓመት ወዲህ ከ1 ሺሕ በላይ የሚሆኑ የፋብሪካው ቋሚ ሠራተኞች ሥራ ለቀዋል የተባለ ሲሆን፤ አሁን ላይ 2 ሺሕ ገደማ ሠራኞች መኖራቸው ተመላክቷል።

በአካባቢው በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች መካከል ተደጋጋሚ ውጊያ እንደሚደረግም ተገልጿል።

ይህም የፋብሪካው ማሽነሪዎች፣ ተሸከርካሪዎች እንዲሁም የተለያዩ ቁሳቁሶች ከፍተኛ ውድመት እንዲደርስባቸው ማድረጉ ነው የተነገረው።

ሠራተኞቹ አክለውም፤ ስለደሞዝ እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች የአስተዳደር ክፍሉን በምንጠይቅበት ወቅት የሚሰጠን ምላሽ "ፋብሪካው ይቀጥል አይቀጥል ባልታወቀበት ወቅት ስለ ደሞዝ ለማውራት ያስቸግራል" የሚል ነው ሲሉ ተደምጠዋል።

"ይህ ኹሉ ችግር የተጋረጠው መንግሥት ለፋብሪካው በሰጠው ዝቅተኛ ትኩረት የተነሳ ነው።" ያሉት ሠራተኞች፤ በዚሁ ከቀጠለ እስከወዲያኛው ሊዘጋ እና ሥራ ሊያቆም እንደሚችል ስጋታቸውን ገልጸዋል።

ስኳር ኮርፖሬሽን ለእንደዚህ ዓይነት ጉዳዮች ራሱ ተቋሙ መልስ እንዲሰጥ አቅጣጫ ተቀምጧል በማለት በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥቧል።

ሆኖም አዲስ ማለዳ ከፋብሪካው አስተዳደር ክፍል ምላሽ ለማግኘት ያደረገችው ሙከራ ሳይሳካ ቀርቷል።

በትናንትናው ዕለት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ11 ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱን ያቀረበው የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በጸጥታ፣ ግብዓት እጥረትና ሌሎች ችግሮች ከፋብሪካዎች የሚቀርበው የስኳር ምርት ካለው ፍላጎት አንጻር ከ10 በመቶ የማይበልጥ ነው ብሏል።
ለትክክለኛ ወቅታዊ መረጃዎች ቻናላችንን join በማድረግ ተከታተሉ
http://t.me/emsmereja
http://t.me/emsmereja
4.0K views06:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-01 09:08:43 ቅዳሜ ጠዋት! ሰኔ 24/2015 ዓ.ም የEMS ዐበይት ዜናዎች

1፤ የኢትዮጵያ ኮምንኬሽን ባለሥልጣን ኩባንያዎች በአገሪቷ ለሁለተኛው ሙሉ የቴሌኮምኒኬሽን አገልግሎት ፍቃድ የብቃት ማረጋገጫ እንዲያቀርቡ ጥሪ ትናንት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ አድርጓል። የብቃት ማረጋገጫ ሰነዱ ማቅረቢያ ቀነ ገደብ በቀጣዩ ዓመት መስከረም የመጀመሪያ ሳምንት እንደኾነ ባለሥልጣኑ ገልጧል። ተቋሙ ይፋ ያደረገው የብቃት ማረጋገጫ ሰነድ፣ የሰነድ ማቅረቢያ መስፈርቶችንና የብቃት መመዘኛዎችን የያዘ እንደኾነ ተገልጧል።

2፤ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ትምህርት ሚንስቴር ሕገመንግሥቱን ጥሷል ሲል ትናንት ማምሻውን በወጣው መግለጫ ከሷል። ሚንስቴሩ የሕገ መንግሥት ጥሰት የፈጸመው፣ በምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ እና ደቡባዊ ትግራይ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችን ወደ አማራ ክልል በማጠቃለሉ እንደኾነ አስተዳደሩ ገልጧል። የሚንስቴሩ ድርጊት "ኾን ተብሎ የተፈጸመ"፣ "ተቀባይነት የሌለው" እና "የሰላም ሂደቱን የሚያደናቅፍ" መኾኑን የገለጸው አስተዳደሩ፣ ሚንስቴሩ ድርጊቱን "ባስቸኳይ እንዲያስተካክል" አሳስቧል። ፌደራል መንግሥቱም ለተፈጸመው ድርጊት በሚንስቴሩ አመራሮች ላይ ርምጃ እንዲወስድ አስተዳደሩ ጨምሮ ጠይቋል።

3፤ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን የሚገኘው ፊንጫ ስኳር ፋብሪካ ካለፉት ኹለት ወራት ወዲህ ሥራ እንዳቆመ ነው። የፋብሪካው ሠራተኞች የኹለት ወር ደመወዛቸው ስላልተከፈላቸው ከእነ ቤተሰባቸው ለከፍተኛ ችግር መጋለጣቸውን መናገራቸውን ቪኦኤ ዘግቧል። ፋብሪካው ሥራ ያቆመው፣ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ባደረሰበት ጥቃት ሳቢያ እንደኾነ በወቅቱ እንደተገለጠ ይታወሳል።

4፤ የኢትዮጵያ የውጭ ምርት ገቢ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር ባለፉት 11 ወራት በ11 ነጥብ 8 በመቶ ቅናሽ ማስመዝገቡን ንግድ ሚንስቴር ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረበው ሪፖርት እንደገለጠ "ኢትዮጵያ ኢንሳይደር" ዘግቧል። በተጠቀሰው ወቅት መንግሥት አገኘዋለኹ ብሎ ያቀደው የወጪ ንግድ ገቢ 4 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር እንደነበር የጠቀሰው ዘገባው፣ ከዘርፉ የተገኘው ገቢ ግን የ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ጉድለት ማሳየቱን ሚንስቴሩ መናገሩን ዘገባው አመልክቷል። የጥራጥሬ የወጪ ንግድ ግን ከዕቅድ በላይ ገቢ ማስመዝገቡ ተገልጧል ተብሏል። ሚንስቴሩ ለወጪ ንግድ መቀዛቀዝ በምክንያትነት ከጠቀሳቸው መካከል፣ ኮንትሮባንድና የዓለም ንግድ እንቅስቃሴ መቀዛቀዝ እንደሚገኙበት ዘገባው ጠቅሷል።
ለትክክለኛ ወቅታዊ መረጃዎች ቻናላችንን join በማድረግ ተከታተሉ
http://t.me/emsmereja
http://t.me/emsmereja
3.7K views06:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-30 20:05:18 ዓርብ ምሽት! ሰኔ 23/2015 ዓ.ም የEMS ዐበይት ዜናዎች

1፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ መስፋፋት ሳቢያ "ሕጋዊ ካሳ አላገኙም" ላላቸው አርሶ አደሮች የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ እንደሰጠ የከተማዋ ኮምንኬሽን ቢሮ አስታውቋል። ከንቲባ አዳነች አቤቤ ዛሬ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ የሰጧቸው በከተማዋ አስተዳደር ስር የሚገኙ አርሶ አደሮች 3 ሺህ 451 እንደኾኑ ቢሮው ገልጧል። ከንቲባዋ የይዞታ ማረጋገጫውን በሰጡበት ስነ ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር፣ አስተዳደሩ የመሬት ባለይዞታ አርሶ አደሮችን መብት ለማስጠበቅ ቀደም ሲል የወሰዳቸውን ሕጋዊና አስተዳደራዊ ርምጃዎች አብራርተዋል ተብሏል።

2፤ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ያቋቋሙት ገለልተኛ የኢኮኖሚ አማካሪዎች ምክር ቤት ዛሬ ከመንግሥት የብሄራዊ ማክሮ ኢኮኖሚ ዐቢይ ኮሚቴ ጋር ውይይት ማድረጉን የመንግሥት ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ገለልተኛው አማካሪ ምክር ቤቱ በመድረኩ ላይ፣ መንግሥት እያዘጋጀው ባለው ኹለተኛው ምዕራፍ የአገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሃ ግብር ረቂቅ ሰነድ ላይ አስተያየቱን እንደሰጠ ዘገባው አመልክቷል። የማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴው፣ ሰነዱ ተጠናቆ ተግባራዊ ከመኾኑ በፊት በድጋሚ ገለልተኛ አማካሪ ምክር ቤቱ አስተያየት እንዲሰጥበት አደርጋለኹ ብሏል ተብሏል።

3፤ የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በአገራዊ ምክክር የሚሳተፉ ተወክዮችን መምረጥ ጀምሬያለኹ ማለቱን ዶይቸቨለ ዘግቧል። በክልሉ በሚካሄደው ምክክር በወረዳ ደረጃ ከ12 ሺህ በላይ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተወካዮች እንደሚሳተፉ ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ዛሬ አሶሳ ውስጥ በሰጡት መግለጫ መናገራቸውን ዘገባው ጠቅሷል። ኮሚሽኑ በክልሉ ለሚካሄደው ምክክር ዘጠኝ የማኅበረሰብ አደረጃጀቶችን ላይቷል ተብሏል።

5፤ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግና ፍትህ ቋሚ ኮሚቴ ኢትዮጵያ ከ51 ሺህ በላይ ከሱዳኑ ግጭት የሸሹ ሱዳናዊያን ስደተኞችን እያስተናገደች መኾኗን መረዳቱን አስታውቋል። ቋሚ ኮሚቴው ይህን የገለጠው፣ በአማራ ክልል፣ ምዕራብ ጎንደር ዞን በመተማ እና ገንዳ ውሃ ከተሞች የሚገኙ የሱዳናዊያን ስደተኞች መጠለያዎችን በጎበኘበት ወቅት እንደኾነ ምክር ቤቱ ጠቅሷል። ፌደራል ፖሊስ ለሱዳናዊያኑ ስደተኛ መጠለያዎች አስፈላጊውን ጥበቃ እያደረገ እንደኾነ መመልከቱን ቋሚ ኮሚቴው ገልጧል።

5፤ ንግድ ባንክ ዛሬ የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋ 54 ብር ከ5943 ሳንቲም እና መሸጫ ዋጋው 55 ብር ከ6862 ሳንቲም ሆኖ እንደዋለ በድረገጹ ገልጧል። የአንድ የእንግሊዝ ፓውንድ መግዣ ዋጋ ደሞ 66 ብር ከ0009 ሳንቲምና መሸጫው 67 ብር ከ3209 ሳንቲም ሆኗል። በተመሳሳይ አንድ ዩሮ በ59 ከ7043 ሳንቲም ተገዝቶ፣ በ60 ብር ከ8984 ሳንቲም ሲሸጥ መዋሉን ባንኩ ገልጧል።
ለትክክለኛ ወቅታዊ መረጃዎች ቻናላችንን join በማድረግ ተከታተሉ
http://t.me/emsmereja
http://t.me/emsmereja
4.0K views17:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-30 13:34:31
" የሃጫሉን ግድያ የፈጸሙትን ታውቃለችሁ አውጡልን " - ወ/ሮ ፋንቱ ደምሴ

ትላንት በ " አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ፋውንዴሽን " አዘጋጅነት የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ የተሰዋበት ዝክር እና የሃጫሉ አዋርድ ተካሂዷል።

በዚሁ ዝግጅት ላይ የአርቲስት ሃጫሉ ባለቤትና የሃጫሉ ፋውንዴሽን ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሮ ፋንቱ ደምሴ ንግግር ያደረገች ሲሆን በንግግሯም ከባለቤቷ ግድያ ጋር በተያያዘ ዛሬም ድረስ ፍትሕ እንዳልተገኘ በመግለፅ ቅሬታ አቅርባለች።

ወ/ሮ ፋንቱ ፤ " አንተ ከተለየን ጊዜ ጀምሮ ለሦስት ዓመታት ያህል  ያንተን እውነታ ወይም ያንተን ፍትህ አላየሁም " ብላለች።

" በአካል ጥለን ከሄድክ ጀምሮ እኔና ልጆቻችን ያላንተ ሀሳብ፣ ናፍቆት እና ፍቅር በስተቀር እውነትንና የሰውን ደም በምትመጠው ሀገር ላይ እየኖርን ይሀው ሶስት አመታትን አስቆጥረናል " ስትል በሀዘን ስሜት ተናግራለች።

ወይዘሮ ፋንቱ በአርቲስት ሃጫሉ ሞት ጋር በተያያዘ ተጠርጥራ በህግ ቁጥጥር ስር ከዋለች በኋላ ነፃ የተለቀቀችው ሴት ላይ ያላትን ቅሬታ አሰምታለች።

በተጨማሪ ፤ " መንግስትም ሆነ ሌላው አካላት የሃጫሉን ግድያ የፈጸሙትን ታውቃለችሁ አውጡልን " ስትል ጠይቃለች።

" አሁንም፣ ወደፊትም ከፈጣሪ በታች ያንተ እውነት የገደሉህ ፣ ያስገደሉህን እና ከአንተ ጋር የነበረችው ልጅ ጋር ነው ያለው። ለኔ ማንም ንፁህ አይደለም " ብላለች።

ወ/ሮ ፋንቱ በሃጫሉ ግድያ እጃቸው ያለበት ብዙ መሆናቸውን በመግለፅ " እውነታውን አውጡልኝ  " ስትል ጥሪ አቅርባለች።

" ለሃጫሉ ፍትህ አልሰፈነችም " ያለችው ወ/ሮ ፋንቱ " የእሱ እውነታ አለመውጣቱን ሁላችሁም ታውቃላችሁ፤ በሀይማኖታችሁ ፀልዩልን " ብላለች። ሼር ይደረግ
ለትክክለኛ ወቅታዊ መረጃዎች ቻናላችንን join በማድረግ ተከታተሉ
http://t.me/emsmereja
4.0K viewsedited  10:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-10 22:31:45
የትግራይ ክልል ፕሬዚደንት ጌታቸው ረዳ ነገ ወደ ባህርዳር እንደሚሄድ ተሰምቷል።
ሰሞኑን በነበረ ስብሰባ ላይ ዶክተር ይልቃል ከፋለ የአመራር ግንኙነት መጀመር አለበት ማለታቸውን መዘገቤ ይታወሳል።
መረጃ ህይወት ነው፣ ይህንንም መረጃ ለጓደኞቻችሁ#Share በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ


t.me/emsmereja
t.me/emsmereja
t.me/emsmerej
2.8K viewsedited  19:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-10 19:50:29 ቅዳሜ ምሽት! ሰኔ 3/2015 ዓ.ም የEMS ዕለታዊ ዜናዎች

1፤ የመንግሥት ቃል አቀባይ ለገሠ ቱሉ የአሜሪካው ዓለማቀፍ ተራድዖ ድርጅት ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ ዕርዳታ መስጠት ማቋረጡ "ፖለቲካዊ ውሳኔ" ነው በማለት ዛሬ በሰጡት መግለጫ ላይ መናገራቸውን የአገር ውስጥ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ለገሠ የድርጅቱ "የጅምላ ውሳኔ" በመንግሥት ዘንድ ተቀባይነት እንደሌለው ገልጠው፣ ውሳኔው ሰብዓዊ ገጽታ የለውም ማለታቸውን ዘገባዎች አመልክተዋል። ድርጅቱ በምግብ ዕርዳታ ዝርፊያ ዙሪያ በመገናኛ ብዙኀን በኩል ባወጣው መረጃ፣ የፌደራል፣ የክልልና መንግሥታትንና የመከላከያ ሠራዊትን ስም አጉድፏል ሲሉ ቃል አቀባዩ ወቅሰዋል ተብሏል። መንግሥትና ድርጅቱ በምግብ ዕርዳታ ዝርፊያው ላይ የጋራ ምርመራ ለማድረግ ከትናንት በስቲያ መስማማታቸው ይታወሳል።

2፤ የፌደራል የይቅርታና ምኅረት ቦርድ እስካኹን ባለው ሕግ ምኅረት በማይፈቀድባቸው አንዳንድ ከባድ ወንጀሎች የተፈረደባቸው ፍርደኞች የምኅረትና ይቅርታ ጥያቄ እንዲያቀርቡ የሚፈቅድ አዲስ መመሪያ ማዘጋጀቱን ሪፖርተር ዘግቧል። መመሪያው የምኅረት ጥያቄ እንዲያቀርቡ የፈቀደላቸው፣ በሽብር፣ በአስገድዶ መድፈር፣ በሙስና፣ በተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት፣ በሕገወጥ ሰው ዝውውር፣ በሕገወጥ የጦር መሳሪያና አደንዛዥ ዕጽ ዝውውርና መሠረተ ልማቶችን በማውደም የተፈረደባቸው ፍርደኞች ናቸው። ቦርዱ ውሳኔ ለመስጠት፣ ፍርደኞች በማረሚያ ቤት ያሳዩትን ባሕሪ፣ የወንጀላቸውን ክብደት እና የእስር ጊዜያቸውን ግማሹን ማጠናቀቃቸውን ግምት ውስጥ እንደሚያስገባ በመምሪያው ላይ እንደተገለጠ ዘገባው ጠቅሷል።

3፤ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሕገወጥ የወርቅ ምርትና ግብይት ተሠማርተዋል ተብለው የተጠረጠሩ 29 የውጭ አገር ዜጎች በቁጥጥር ስር መዋለቸውን ፋና ብሮድካስት ዘግቧል። በቁጥጥር ስር የዋሉት የውጭ ዜጎች "ከታጠቁ ኃይሎችና አሸባሪ ቡድኖች" ጋር በመመሳጠር የወርቅ ማዕድን ዝርፊያ ሲፈጽሙ እንደነበር ብሄራዊ መረጃና ደኅንነት ማስታወቁን ዘገባው ጠቅሷል። የውጭ ዜጎቹ የየት አገር ዜጎች እንደኾኑ ዘገባው አላመለከተም። መንግሥት በወርቅ ማዕድን ላይ የሚፈጸመውን ሕገወጥ ንግድ ለመቆጣጠር በቅርቡ አገር ዓቀፍ ግብረ ኃይል ማቋቋሙ ይታወሳል።

4፤ የሱዳን ተፋላሚ ወገኖች የደረሱበት የ24 ሰዓታት ተኩስ አቁም ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ ኾኗል። የተኩስ አቁሙን ተከትሎ ካርቱም ውስጥ ውጊያው ጋብ ማለቱን ዓለማቀፍ የዜና ወኪሎች ዘግበዋል። በሌላ ዜና፣ ሱዳን የተመድ ልዐክ ቮልከር ፐርቴስን የዲፕሎማቲክ እውቅና መንፈጓ በተመድ ቻርተር ያለባትን ግዴታ ይጥሳል በማለት ተመድ ውሳኔውን ውድቅ ማድረጉን ሮይተርስ ዘግቧል። በአገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ውስጥ የአገራትን መብቶች ግዴታዎችን የሚደነግገው የቬይና ኮንቬንሽን፣ አገራት በግዛታቸው የተወከሉ የሌላ አገራት ዲፕሎማቶችን እውቅና ነፍገው ከአገር የማባረር መብት ይሰጣል። ኾኖም የተመድ ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ፣ ይህ ድንጋጌ ዓለማቀፍ ድርጅት የኾነውን ተመድን አይመለከትም ማለታቸው ተገልጧል።

5፤ የሱማሊያ ጸጥታ ኃይሎች የአልሸባብ ታጣቂዎች ትናንት ምሽት በኃይል የተቆጣጠሩትን ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት የሚያዘወትሩትን የሞቃዲሾውን "ፐርል ቢች" ሆቴል ማስለቀቃቸውን የሱማሊያ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። በታጣቂዎቹ ጥቃትና በተኩስ ልውውጡ ሦስት ወታደሮችን ጨምሮ ዘጠኝ ሰዎች እንደተገደሉና ሌሎች 10 ሰዎች እንደቆሰሉ ዘገባዎች አመልክተዋል። ጸጥታ ኃይሎች ሌሊቱን 84 ሰዎችን ከታጣቂዎቹ እገታ በደኅና አስለቅቀዋል ተብሏል። እገታውን የፈጸሙት የቡድኑ ታጣቂዎች እንደተገደሉ ተገልጧል።

6፤ በኬንያ የሩማኒያ አምባሳደር ድራጎስ ቲጋው አፍሪካዊያንን ከዝንጀሮ ጋር አመሳስለው አስተያየት በመስጠታቸው ወደ አገራቸው እንደተጠሩ የኬንያ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። የሩማኒያ አምባሳደር ባለፈው ሚያዝያ ላይ ይህንኑ ዘረኛ አስተያየት የሰጠት፣ ኒውዮርክ ውስጥ በተካሄደ አንድ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ስብሰባ ላይ እንደነበር ተገልጧል። የአገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር የአምባሳደሩ ንግግር አገሪቱን እንደማይወክል ገልጦ፣ አፍሪካዊያንን ይቅርታ ጠይቋል ተብሏል። መረጃ ህይወት ነው፣ ይህንንም መረጃ ለጓደኞቻችሁ#Share በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ


t.me/emsmereja
t.me/emsmereja
t.me/emsmereja
3.1K views16:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-10 14:44:06
አምቡላንስ ላይ በተፈጸመ ጥቃት የሰው ሕይወት አለፈ
የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ አጠቃላይ ስፔሻላይዝ ሆስፒታል ጤና ባለሙያ ገመቹ ጀቤሣ በታጣቂዎች በተከፈተ ተኩስ ሕይወታቸው ማለፉ ተነገረ።

ጤና ባለሙያው ትናንት ሰኔ 2/2015 ከአዲስ አበባ ወደ ደምቢዶሎ በመመለስ ላይ እያሉ እናንጎ አካባቢ በአምቡላንስ ላይ በተከፈተው ተኩስ ሕይወታቸው ማለፉን አዲስ ማለዳ ከዩኒቨርሲቲው ያገኘችው መረጃ ያመላክታል።
መረጃ ህይወት ነው፣ ይህንንም መረጃ ለጓደኞቻችሁ#Share በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ


t.me/emsmereja
t.me/emsmereja
t.me/emsmereja
2.9K viewsedited  11:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-10 10:26:58 የልጆቼ አባት የት እንዳለ አላውቅም የምትለን ይህች አስተያየት ሰጪ ሰዎች የተለያዩ ቦታዎች እንዳዩት ነግረውኛል፣ አንዳንዶቹ ተማርኳል፣ ቆስሏል፣ ተሰውቷል ሌሎቹ ደግሞ በህይወት አለ ይሉኛል ብላለች፡፡

ለምን ወደ ቀድሞ ቤትሽ አልተመለስሽም? በሚል ላቀረብንላት ጥያቄም “ለደህንነቴ እሰጋለሁ፣ የመንግስት አካላትም ቅድሚያ መሰራት ያለበት ስራ አለ እንዳትሄዱ ብለውናል፣ እኔ ግን የባሌ ጉዳይ ያሳስበኛል፣ ልጆቼም ጥያቄያቸው አላባራም ቢሆንልኝ ወደቤቴ ገብቼ ኑሮዬን ብመራ ደስታዬ ነው“ ብላላች፡፡

መረጃ ህይወት ነው፣ ይህንንም መረጃ ለጓደኞቻችሁ#Share በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ


t.me/emsmereja
t.me/emsmereja
t.me/emsmereja
3.3K views07:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-10 10:26:57 ከጦርነትና የሰላም ስምምነት በኋላ ህይወት በትግራይ ምን ይመስላል?

የትግራይ ክልል ነዋሪዎች ተስፋቸውን እና ስጋታቸውን ነግረውናል


ከጦርነትና የሰላም ስምምነት በኋላ ህይወት በትግራይ ምን ይመስላል?

የትግራይ ክልል ነዋሪዎች ተስፋቸውን እና ስጋታቸውን ነግረውናል

የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት እንዲቆም ምክንያት የሆነው የሰላም ስምምነት ከተፈረመ ስድስት ወር አልፎታል

ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በሀገር መከላከያ ሰራዊት የሰሜን እዝ በሕወሃት ታጣቂዎች መጠቃቱን ተከትሎ ነበር በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት የተጀመረው።

ለሁለት ዓመት ገደማ በተካሄደው በዚህ ጦርነት በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ህይወታቸውን ሲያጡ የ28 ቢሊዮን ዶላር የኢኮኖሚ ውድመትም አድርሷል።

የፌደራል መንግስት እና የትግራይ ሀይሎች በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ጥቅምት 24 ቀን 2015 ዓ.ም የሰላም ስምምነት መፈራረማቸውን ተከትሎ ጦርነቱ ቆሟል።

የሰላም ስምምነቱን ተከትሎም በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳድር የተቋቋመ ሲሆን መንግስታዊ አገልግሎቶች ዳግም ወደ ስራ ተመልሰዋል።

አል ዐይን አማርኛ በትግራይ ከሰላም ስምምነቱ እና ከጊዜያዊ አስተዳድር መመስረት በኋላ ህይወት እንዴት እየቀጠለ ነው ሲል በክልሉ የተለያዩ ቦታዎች ነዋሪዎችን አነጋግሯል።

በክልሉ መዲና መቐለ ነዋሪ የሆነው አብርሃ ሀይለማርያም እንደነገረን ከሆነ በከተማዋ የሰላም ስምምነት በተፈረመበት ጊዜ ህዝቡ ፍጹም ደስታ ተሰምቶት እንደነበር ነግሮናል።

አሁንም ቢሆን እኔን ጨምሮ የከተማዋ ነዋሪ ለሰላም ስምምነቱ ትልቅ አክብሮት አለው የሚለን አብርሃ ስምምነቱ ግን የጠበቅነውን ያህል እየተፈጸመ እንዳልሆነ እንረዳለን ብሎናል፡፡

በከተማዋ የክልሉ እና የፌደራል መንግስት ተቋማት ወደ አገልግሎት መመለሳቸውን ተከትሎ የነበረው አስከፊ ዝርፊያ፣ የመንቀሳቀስ ነጻነት እና የኑሮ ውድነቱ መሻሻል ማሳየቱን አብርሃ አክሏል፡፡

አንድ ኩንታል ጤፍ እስከ 20 ሺህ ብር ድረስ ይሸጥ ነበር አሁን ግን ከ8 ሺህ እስከ 10 ሺህ ብር በመሸጥ ላይ ነው፣ ሌሎች ምርቶችም ከክልሉ ቦታዎችም ሆነ ከሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች ወደ ገበያ እየቀረቡ ነውም ብሏል፡፡

ይሁንና በከተማዋ ከባንኮች ውጪ ሌሎች አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የተሟላ አገልግሎት እየሰጡ አለመሆኑን፣ አሁንም በከተማዋ ምሽት ላይ ዝርፊያ መኖሩ፣ የሰላም ስምምነቱ በሙሉ ላይተገበር ይችላል፣ በየትምህርት ቤቶቹ ያሉ ተፈናቃዮች ወደ ቀድሞ መኖሪያቸው አለመመለስ እና እርዳታ የሚፈልገው ህዝብ መብዛት በከተማዋ ያለ ዋነኛ ችግር እንደሆነ አብርሃ አክሏል፡፡

ለደህንነቱ ሲል ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ እና የአዲግራት ከተማ ነዋሪ አስተያየት ሰጪ እንዳለው ከሆነ በከተማዋ እና በአካባቢው ባሉ የወረዳ ከተሞች አሁንም ከመልካም ነገሮች ይልቅ ስጋቶች እና ችግሮች እንደሚብሱ ነግሮናል፡፡

አብዛኞቹ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችን ከመቀበል ይልቅ የኤርትራ ጦር ከያዛቸው አካባቢዎች የተፈናቀሉ ዜጎች መኖሪያ ሆነዋል የሚለን ይህ የአዲግራት ከተማ ነዋሪ ምሽት ላይ ዘረፋ መኖሩን፣ እርዳታ የማይሰጡ ነገር ግን ለአይን የሚታክቱ የረድኤት ድርጅቶች እንቅስቃሴ መኖሩን እንዲሁም አገልግሎት የማይሰጡ የመንግስት ተቋማት መኖራቸውንም አክሏል፡፡

አስተያየት ሰጪው አክሎም የረድኤት ድርጅቶች ለተረጂዎች ምግብ እና ቁሳቁስ እየጫኑ ወደ ከተማዋ እና ወረዳዎች ሲሄዱ ብናይም የሚረዱት ግን ጥቂቶች ብቻ መሆናቸውን ነግሮናል፡፡

የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳድር ተዋቅሯል ሲባል መስማቱን የነገረን ይህ አስተያየት ሰጪ ነገር ግን የመንግስት ተቋማት አገልግሎት መስጫዎች በጦርነቱ ስለወደሙ እና ስለተዘረፉ አገልግሎት መስጠት አልቻሉም ብሏል፡፡

በአዲግራት አካባቢ ያለው ህዝብም አብዛኛወው እርዳታ ጠባቂ ነው ያለን ይህ ነዋሪ ህዝቡ ውጪ ሀገራት እና በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ካሉ ቤተሰቦቹ በሚላክለት ገንዘብ እንደሆነም አክሏል፡፡

በተጨማሪም ልጆቻቸውን ወደ ጦርነቱ የላኩ ቤተሰቦችም የልጆቻቸውን ሁኔታ ባለማወቃቸው አልያም ከዛሬ ነገ መርዶ ይመጣል በሚል ስጋት ውስጥ ያሉ ሰዎችም ቁጥር ቀላል እንዳልሆነ ይሄው ነዋሪ ነግሮናል፡፡

የኤርትራ ጦር አሁንም ዛላምበሳ እና አካባቢው ካሉ አካባቢዎች ካለመውጣቱ ባለፈ የተወሰኑ ቀበሌዎች ውስጥ ያሉ መኖሪያ ቤቶችን እና የሕዝብ ተቋማትን በማፍረስ ላይ መሆኑ የአካባቢውን ህዝብ እንዳሳሰበ ገልጿል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የኤርትራ ጦር ከዚህ በፊት ለኢትዮጵያ እና ኤርትራ ጦርነት መጀመር ምክንያት ከሆነው ከባድመ ውጪ የሆኑ የኢትዮጵያ እና ትግራይ ክልል ግዛት ስር የነበሩ ቀበሌዎችን እንደ ራሱ አድርጎ መሰረተ ልማቶችን በመገንባት ላይ መሆኑን ይሄው ነዋሪ ነግሮናል፡፡

ይህን ተከትሎም ህዝቡ ከትንሽ ጊዜ በኋላ ዳግም ጦርነት ልንገባ እንችላለን የሚል ስጋት ውስጥ መውደቁን ነዋሪው ገልጿል፡፡

ሌላኛው የአክሱም ከተማ ነዋሪ የሖነው እና ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ አስተያየት ሰጪ በበኩሉ የሰላም ስምምነቱ ለህዝቡ ትልቅ እፎይታን እንዳመጣለት ነግር ግን መሻሻል ያለባቸውን ጉዳዮች እንዳሉ ዘርዝሯል፡፡

በአክሱም እና አጎራባች አካባቢዎች ትምህርት ቤቶች በግማሽ መከፈታቸውን የነገረን ይህ ነዋሪ ትምህርት ቤቶች የተፈናቃዮች መኖሪያ መሆናቸው እና የጦርነቱ ውስብስብ ጠባሳዎች የተማሪዎችን የመማር ፍላጎት እንደጎዳው ነግሮናል፡፡
ከመንግስት ትምህርት ቤቶች ይልቅ የግል ትምህርት ቤቶች የተሻለ ተማሪ ቁጥር አላቸው ያለን ይህ አስተያየት ሰጪ የመሬት ይገባኛል ጥያቄ የሚነሳባቸው አካባቢዎች ችግር አለመፈታት ዋነኛ የአካባቢው ህዝብ ስጋት መሆኑን አክሏል፡፡

የኤርትራ ጦር ከክልሉ ይዞታዎች አሁንም አለመውጣቱ፣ የኢኮኖሚው ችግር አለመፈታት፣ የመንግስት ሰራተኞች ደመወዝ አለመከፈል እና ለተፈናቃዮች እርዳታ እየተሰጠ አለመሆኑ ሌላኛው የአክሱም እና አካባቢው ህዝብ ችግሮች ናቸውም ተብሏል፡፡

የረድኤት ድርጅቶች 10 ቤተሰብ ላለው ተረጂ የሶስት ሰው መስጠት ሶስት ቤተሰብ ላለው ደግሞ ለ10 ሰው የሚበቃ እርዳታ ሲሰጡ አያለሁ የሚለን ይህ አስተያየት ሰጪ ወደ አካባቢው እየተጓጓዘ ያለው የእርዳታ መጠን ከፍተኛ ቢሆንም እየተሰጠ ያለው እርዳታ ግን አነስተኛ መሆኑንም ነግሮናል፡፡

የሰላም ስምምነት በመፈረሙ ደስተኞች ነን የሚለው ይህ ነዋሪ አርሶ አደሮች ወደ እርሻቸው፣ ሌላውም ማህበረሰብ ወደ ለመደው የቀድሞ ህይወት በቶሎ እንደሚመለስ ተስፋ አድርገን ነበር ነገር ግን የሰላም ስምምነቱ የታሰበውን ያህል እየተፈጸመ አለመሆኑ ህዝቡ አሁንም ዳግም ወደ ጦርነት እንገባ ይሆን የሚል ስጋት አለውም ብሎናል፡፡

ህይወቴን በትምህርት ቤት በረንዳዎች ላይ ካደረግሁ ሶስተኛ ዓመቴ ሊመጣ ነው ያለችን ሌላኛዋ የሽሬ ከተማ ነዋሪ ነች፡፡

ሶስት ልጆቿን ይዛ ከአማራ ክልል አዋሳኝ ቀበሌ እንደተፈናቀለች የነገረችን ይቺ ስሟ እንዳይጠቀስ የፈለገች አስተያየት ሰጪ ከዛሬ ነገ ወደ ቤቴ እመለሳለሁ ብልም እስካሁን እንዳልተሳካላት ነግራናለች፡፡

የሰላም ስምምነት ተፈረመ ስንባል በደስታ እልል ብለናል የምትለው ይህች አስተያየት ሰጪ በፊት እርዳታ ጥሩ የነበረ ቢሆንም አሁን ግን ቆሟል አልፎ አልፎ ትንሽ ትንሽ ይሰጡናል ብላናለች፡፡
2.9K views07:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ