Get Mystery Box with random crypto!

EMS Mereja

የቴሌግራም ቻናል አርማ emsmereja — EMS Mereja E
የቴሌግራም ቻናል አርማ emsmereja — EMS Mereja
የሰርጥ አድራሻ: @emsmereja
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 14.57K
የሰርጥ መግለጫ

👉 መረጃዎች፣ጥያቄዎች፣ አስተያየቶችና የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት ከፈለጉ በዚህ ያናግሩን👉 t.me/infoetrobot
👉 የዕለታዊ ዝግጅቶችና ዜናዎች በተባባሪ አቅራቢዎች እንዲደርሷችሁ👇👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@HAQMEDIA12
Subscribe ያድርጉ

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-06-08 17:22:16 ሰበር ዜና
ሕወሓት በራያ በኩል ከ23 ተሳቢ መኪና በላይ የታጠቀ ኃይሉን እያስጠጋ መሆኑ ተነገረ

ሕወሓት በዋናነት ከባለፈው ሰኞ ዕለት ጀምሮ በራያ በኩል በኩኩስቶ እና መሆኒ ተብለው በሚጠሩ ሥፍራዎች ከፍተኛ ቁጥር ያለው የታጠቀ ኃይል እያስጠጋ መሆኑ ተገለጸ፡፡

ከሰኞ ግንቦት 28 ጀምሮ እስከ ትናንት ጠዋት ግንቦት 30 ድረስ በ23 ተሳቢ መኪና ዲሽቃ፣ ስናይፐር፣ መትረጊስ እና ክላሽ የታጠቀ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የሕወሓት ታጣቂ ኃይል እየተጠጋ መሆኑን አዲስ ማለዳ በአካባቢው ከሚገኙ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ሰምታለች፡፡

የሕወሓት ኃይሎች በተደጋጋሚ ወደ ድንበር መጠጋት ለምን ዓላማ እንደሆነ በግልጽ የታወቀ ነገር የለም የተባለ ሲሆን፤ የሕወሓት ኃይሎች ትንኮሳ የሚያደርጉ ከሆነ የአላማጣ እና አካባቢው ሕዝብ የአፀፋ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ ነው ተብሏል።

የሕወሓት ታጣቂዎች በተጠጉበት አካባቢ የአገር መከላከያ ሠራዊት በመኖሩ ወደ ድንበር እየተጠጋ የነበረውን የአላማጣ እና አካባቢውን ሕዝብ የሕወሓት ኃይሎች ከድንበር አልፈው እንደማይመጡ በማሳወቅ ወጣት እና ሚሊሻዎች እንዲመለሱ መደረጉም ተጠቁሟል፡፡

የአላማጣ ከተማ ከንቲባ ኃይሉ አበራ፤ “እኛ የፕሪቶሪያውን ስምምነት ተቀብለን ተግባራዊ እያደረግን ነው፤ ከዚያ ባሻገር ችግር እንፈጥራለን ካሉ የማንታገስ መሆናችን ልናረጋግጥ እንወዳለን።” ሲሉ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል፡፡

በፌዴራል መንግሥት እና ሕወሓት መካከል በፕሪቶሪያ በተደረገው የሰላም ስምምነት መሰረት የሕወሓት ኃይሎች ትጥቅ መፍታትና ወደ ማኅበረሰቡ መቀላቀል ያለባቸው ሲሆን፤ ይኼው ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ አለመደረጉን ተከትሎ ታጣቂዎቹ በተለያዩ የአማራ ክልል አዋሳኝ ቦታዎች ትንኮሳ እየፈጸሙ እንዲሚገኙ ቅሬታዎች ሲቀርቡ ይስተዋላል፡፡

በቅርቡ በራያ አላማጣ የሚገኙ ስድስት ወረዳዎች የአካባቢው በጀት ወደ አማራ ክልል እንዲዞር እና ለወረዳዎች እንዲለቀቅ ፊርማ ማሰባሰብ ዘመቻ በማድረግ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ሊያስገቡ መሆኑን አዲስ ማለዳ መዘገቧ ይታወሳል። ሕወሓት በበኩሉ አካባቢው የትግራይ ግዛት አካል ነው በማለት በጀቱ እንዲለቀቅለት እየጠየቀ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዘዳንት ሌትናል ጄኔራል ጻድቃን ገብረ ትንሳኤ እንዲሁ፤ በወራሪዎች ሥር የሚገኙትን የትግራይ ህገ መንግስታዊ ግዛቶች በአጭር ጊዜ ወደ ትግራይ ክልል ለመመለሰ እየተረባረብን ነው ማለታቸው ተሰምቷል፡፡
መረጃ ህይወት ነው፣ ይህንንም መረጃ ለጓደኞቻችሁ#Share በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ


t.me/emsmereja
t.me/emsmereja
t.me/emsmereja
4.5K viewsedited  14:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-08 17:16:41 በሸገር ከተማ “ሕገ ወጥ ናቸው” የተባሉ ቤተ እምነቶችን የማፍረሱ ሥራ እንደሚቀጥል የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አስታወቁ

656 ቤተ እምነቶች ሕገ ወጥ ናቸው ተብሏል

ሸገር ከተማን ዘመናዊና በፕላን ብቻ ግንባታ የሚካሄድባት ለማድረግ ሕግ ወጥ ግንባታዎችን የማፍረሱ ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሸመልስ አብዲሳ ገለጹ።

በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼህ ሐጂ ኢብራሂም ቱህፋ የተመራ ልዑክ በኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሸመልስ አብዲሳ ጽ/ቤት በመገኘት፤ በሸገር ከተማ እየተከናወነ ባለው የመስጊድ ፈረሳ ጉዳይ ላይ ዉይይት ማድረጉን አስታውቋል።

ምክር ቤቱ ውይይቱን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ፤ “የሸገር ከተማ አስተዳደር ”ከፕላን ዉጭ ተሠርተዋል“ ያላቸውን መስጂዶች ለማፍረስ ሲነሳ የሚመለከተውን የእስልምና ጉዳዮች አካላትን አለማወያየቱ እና በተደጋጋሚ ጊዜ የቀረበለትን የውይይት ጥያቄ አለመቀበሉ ቅሬታ መፍጠሩን በሙስሊም ተወካዮች በኩል በውይይቱ መነሳቱን ገልጿል፡፡

ምክር ቤቱ ሕዝበ ሙስሊሙ የሸገር ከተማ መስጂድ ፈረሳ ጋር በተያየዘ በተፈጠሩት ሁኔታዎች እጅጉን መጎዳቱንና ማዘኑን በማብራራት፤ ተገቢውን ካሳና የሞራል ሕክምና እንደሚያስፈልገውም ጠቁሟል፡፡ የጸጥታ አካላት ሰላማዊ ሙስሊሞች ላይ በቀጥታ በመኮስ ሙስሊሞችን መግደላቸውና ማቁሰላቸው ተገቢ አለመሆኑን፤ እንዲሁም ንጹሃን ላይ በመተኮስ የገደሉና ያቆሰሉ አካላት በሕግ ተጠያቂ እንዲሆኑም በውይይቱ ላይ ጠይቀዋል።

በጉዳዩ ላይ ቅድሚያ ውይይት አለመደረጉ ስህተት መሆኑን ያነሱት የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሸመልስ አብዲሳ፤ በሸገር ከተማ ዉስጥ ካሉት 800 የኹሉም እምነት ተቋማት መካከል 656 የሚሆኑት ከፕላን ዉጭ የተሠሩ በመሆናቸው ገልጸዋል፡፡

ሸገር ከተማ ከ20 እስ3 30 ሚሊዮን ነዋሪዎች ያላት ዘመናዊና በፕላን ብቻ ግንባታ የሚካድባት ከተማ ሆኖ ለመግንባት ሕግ ወጥ ግንባታን መከላከል፣ የተገነቡትን ማፍረስ እንደሚቀጥል የገለጹት ፕሬዝዳንቱ፤ ለሂደቱ መሳካት የእምነት ተቋማት ተባባሪ እንዲሆኑ ጠይቀዋል፡፡

አዲስ የሚገነባውን የከተማ ፕላን “የማይመጥኑ” የተባሉ የቤተ እምነት ግንባታዎች በሕጋዊና ከተማውን በሚመጥኑ ተቋማት ለመተካት የሚደረገውን ሂደትም፤ የኦሮሚያ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አቅሙን በማጠናከር በዉይይት የእምነት ተቋማቱ ራሳቸው መፍረስ ያለባቸውን እንዲያፈሱ እንጂ ከአሁን በኋላ መንግሥት በራሱ ማፍረስ እንደሚያቆም አስታውቀዋል።

የእሰልምናን ጨምሮ የሌሎችም ቤተእምነቶችም ተቋማት በብዛት በሸገር ከተማ ፕላን ዉስጥ እንደሚካተቱ የጠቆሙት ፕሬዝዳንቱ፤ ለዚህም አስፈላጊውን የቤተእምነት መሥሪያ መሬቶችን በፕላኑ መሠረት ለምዕመኑ እንደሚሰጥና በቆርቆሮ ሳይሆን የከተማዋን ፕላን የሚመጥን በርካታ ዘመናዊ መስጊዶች በከተማው እንዲሰሩ እንደሚፈልጉም ተናግረዋል። አክለውም በሸገር ከተማ ለኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲ ግንባታ የሚሆን መሬት እንደሚሰጥም ተናግረዋል።

በሌላ በኩል፤ ካለፉት ኹለት ሳምንታት ጀምሮ እስከ ትናንት ድረስ የታሠሩትን ሙስሊሞችን መፈታትን አስመልክቶ ዛሬ ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ጀምሮ የፌደራልና አዲስ አበባ ፖሊስ አመራሮች ጋር ዉይይት እንደሚደረግ ያስታወቀው ምክር ቤቱ፤ ያለምንም ልዩነት የታሠሩት ሙስሊሞች በጠቅላላው እንደሚፈቱ ያለውን እምነት በመግለጫው ገልጿል።

እንዲሁም፤ ባለፉት ኹለት ሳምንታት በአንዋር እና ኑር መስጂድ በሸገር ከተማ የፈረሱትን መስጂዶችን በመቃወም ላይ እያሉ የተገደሉ ሙስሊሞች በሸገር ከተማ በፈረሱት መስጂዶች ምትክ ከሚሠሩት መስጂዶች መካከል አንዱ የሸሒዶች መስጂድ ተብሎ እነርሱን ለማስታወስ እንደሚሰየም ያስታወቀው ምክር ቤቱ፤ በመስጂዱ ቅጥር ጊቢ ዉስጥም የሟቾችም ሥም ዝርዝር በጉልህ በሚታይ መልኩ ይጻፋል ብሏል።
መረጃ ህይወት ነው፣ ይህንንም መረጃ ለጓደኞቻችሁ#Share በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ


t.me/emsmereja
t.me/emsmereja
t.me/emsmereja
4.3K viewsedited  14:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-08 07:47:07 ሐሙስ ጠዋት! ሰኔ 1/2015 ዓ.ም የEMS ዕለታዊ ዜናዎች

1፤ የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል በአዲስ አበባ ከተማ "ተከታታይ የተቀናጀ ኦፕሬሽን" እንደሚያካሂድ ትናንት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ግብረ ኃይሉ ኦፕሬሽኑን የሚያካሂደው፣ በከተማዋ የተለያዩ የጸጥታ ችግሮችን ለመፍጠር የተዘጋጁ ኃይሎች ስለመኖራቸው ስለደረሠበት እንደኾነ ገልጧል። ኅብረተሰቡ እንግዳ የኾኑ እንቅስቃሴዎችን ለጸጥታ ኃይሎች ሪፖርት እንዲያደርግ ያሳሰበው ግብረ ኃይሉ፣ ወደፊት የሚደርስበትን ውጤት ለሕዝብ ይፋ አደርጋለኹ ብሏል።

2፤ የወላይታ ብሄራዊ ንቅናቄ እና የወላይታ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ግንባር ፌደሬሽን ምክር ቤት ወላይታ ዞን ከሌሎች ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ጋር አንድ ክልል ለማቋቋም ሕዝበ ውሳኔ እንዲያካሂድ ያሳለፈውን ውሳኔ እንዲሽር በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ መመስረታቸውን "ኢትዮጵያ ኢንሳይደር" ዘግቧል። ፓርቲዎቹ የወላይታ ዞን ምክር ቤት ብቻውን ሕዝበ ውሳኔ ለማካሄድ ከአራት ዓመታት በፊት ያሳለፈውን ውሳኔ፣ ፍርድ ቤቱ እንዲያጸናው መጠየቃቸውን ዘገባው ጠቅሷል። ክሱ ፌደሬሽን ምክር ቤት "ከሕገመንግሥታዊ ሥልጣኑ ውጭ ተጠቅሟል" ማለቱን ዘገባው ጨምሮ ገልጧል። ፓርቲዎቹ የወላይታ ዞን ምክር ቤት የቀድሞውን ውሳኔ ቀይሮ፣ ከሌሎች አስተዳደራዊ መዋቅሮች ጋር ሕዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ የወሰነው ሕጋዊ ሰውነት ሳይኖረው ነው የሚል ክስ ጭምር አካተዋል ተብሏል።

3፤ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ አስተዳደር አማካኝነት በፈረሱ መስጅዶች ዙሪያ ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጥ አስታውቋል። ጠቅላይ ምክር ቤቱ ባለፉት ቀናት በመስጅዶች መፍረስ ዙሪያ መፍትሄ ለማፈላለግ ከፌደራልና ከኦሮሚያ ክልል መንግሥታት ጋር እየተነጋገረ መኾኑን ጠቅሶ፣ ሙስሊሙ ኅብረተሰብ በትዕግስት እንዲጠባበቅ መጠየቁ ይታወሳል።

4፤ የተመድ ጸጥታው ምክር ቤት የሱማሌላንድ ራስ ገዝ ወታደሮች በግጭት ከምትታመሰው ላስ አኖድ ከተማ ሙሉ በሙሉ ለቀው እንዲወጡ ትናንት ባወጣው መግለጫ ጠይቋል። ምክር ቤቱ የራስ ገዟ ወታደሮችና የላስ አኖድ አካባቢ የጎሳ ታጣቂዎች ግጭቱን ከማባባስ እንዲቆጠቡም ጥሪ አድርጓል። ምክር ቤቱ፣ ኢትዮጵያ እና ሱማሊያ ሁለቱ ተፋላሚ ወገኖች የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ እንዲደርሱና ሁሉን ዓቀፍ የፖለቲካ ንግግር በግዛቲቷ እንዲጀመር ያቀረቡትን ሃሳብ እንደተቀበለው ጨምሮ ገልጧል።

5፤ አሜሪካና ሳዑዲ ዓረቢያ የግጭት ማቆም ስምምነት ተቆጣጣሪ ቡድን ሱዳን ውስጥ እንዲሠማራ ሃሳብ ማቅረባቸውን ከዲፕሎማቶች መስማቱን ጠቅሶ ሱዳን ትሪቡን ዘግቧል። የፈጥኖ ደራሹ ሠራዊት ገለልተኛ የተኩስ አቁም ስምምነት ተቆጣጣሪ ቡድን ቢሠማራ እንደማይቃወም መናገሩን ዘገባው አመልክቷል። ሳዑዲ ዓረቢያና አሜሪካ ጅዳ የሚገኙ የሁለቱ ተፋላሚ ወገኖች ተደራዳሪዎች በተያዘው ሳምንት ሌላ ዙር የተኩስ አቁም ንግግር እንዲጀምሩ እያግባቡ እንደኾነ ተሰምቷል። የሱዳን ጦር ሠራዊት ባላንጣው ፈጥኖ ደራሹ ሠራዊት የተኩስ አቁም ስምምነቶችን አላከበረም በማለት፣ ወደፊት በተኩስ አቁም ንግግሮች እንደማይሳተፍ ባለፈው ሳምንት መግለጡ ይታወሳል። #ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                  
@emsmereja
4.5K views04:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-06 12:45:16
የ2016 አገራዊ በጀት 801.65 ቢሊየን ብር እንዲሆን ውሳኔ ተላለፈ
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 21ኛ መደበኛ ስብሰባ የ2016 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግሥት ረቂቅ የበጀት አዋጅ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

የ2016 በጀት የአገር ደህንነት ከማስጠበቅ፣ በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ ችግሮች ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጐችን ከመርዳት፣ በጦርነት  የወደሙ መሰረተ ልማቶች መልሶ ከማቋቋም፣ አኳያ የተቃኘ ነው ተብሏል። 

በዚሁ መሰረትም፤ ለፌደራል መንግሥት መደበኛ ወጪዎች ብር 369.6 ቢሊየን፣ ለካፒታል ወጪዎች ብር 203.9 ቢሊየን፣ ለክልሎች የሚሰጥ ድጋፍ ብር 214.07 ቢሊየን፣ ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ ድጋፍ ብር 14 ቢሊየን በጠቅላላው ብር 801.65 ቢሊየን ሆኖ ለምክር ቤቱ ቀርቧል።

ምክር ቤቱም በቀረበው የፌዴራል መንግሥት የ2016 በጀት ረቂቅ አዋጅ ላይ በስፋት ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ መወሰኑ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ምክር ቤቱ ያጸደቀው በጀት ከ2015 በጀት ዓመት የ15.04 ቢሊዮን ብር ዕድገት ያሳየ ሲሆን፤ የ2015 አጠቃላይ አገራዊ በጀት 786.61 ቢሊዮን ብር እንደነበር ይታወሳል።
#ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                  
@emsmereja
1.5K viewsedited  09:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-06 07:28:24 ማክሰኞ ጠዋት!ግንቦት 29/2015 ዓ.ም የEMS ዐበይት ዜናዎች

1፤ የኬንያው ኤንሲቢኤ ባንክ ኢትዮጵያ ውስጥ በዲጂታል ባንክ አገልግሎት ዘርፍ ለመሠማራት ከሳፋሪኮም ኩባንያ ጋር ንግግር መጀመሩን ደይሊ ኔሽን ዘግቧል። ባንኩ ከኢትዮጵያ ባንኮች ጋር ጥምረት መፍጠርን ሌላ አማራጭ አድርጎ እንደያዘው መናገሩን ዘገባው ጠቅሷል። ባንኩ እና ሳፋሪኮም ኬንያ ውስጥ "ኤም-ሸዋሪ" የተሰኘ በሞባይል የገንዘብ ብድር መስጫ ዘዴ ላይ ላለፉት 10 ዓመታት በጋራ በመስራት ላይ ናቸው። ኤንሲቢኤ ባንክ ከኢትዮጵያ በተጨማሪ፣ በዲጂታል ባንክ አገልግሎት ለመሠማራት በዲሞክራሲያዊት ኮንጎና ጋና ላይ ቀልቡን ጥሏል።

2፤ የደቡብ ክልል ፋይናንስ ቢሮ በተለያዩ አካላት እጅ ይገኛል ያለውን 4 ቢሊዮን ብር የሚገመት የማዳበሪያ ዕዳ ለማስመለስ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ መኾኑን መግለጡን ዶይቸቨለ ዘግቧል።
በክልሉ የተከማቸው የማዳበሪያ ዕዳ በወቅቱ አለመመለሱ፣ በመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝ ክፍያ ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩ ሲገለጥ ቆይቷል። የክልሉ መንግሥት ማዳበሪያውን የገዛው ዓመታዊ በጀቱን ዋስትና በማስያዝ እንደነበር ዘገባው ጠቅሷል። ገንዘቡን የሚያስመልስ ማዕከላዊ ክልላዊ ዕዝ መቋቋሙንና ባለ ዕዳዎች ማዳበሪያውን ከተረከቡበት ጊዜ ጀምሮ የተከማቸውን ወለድ ጭምር እንዲከፍሉ እንደሚደረግ ቢሮው መናገሩን ዘገባው ጨምሮ አመልክቷል።

3፤ ንግድ ሚንስቴር በሰኔ ወር የነዳጅ ዋጋ በግንቦት ወር በነበረው ዋጋ እንደሚቀጥል አስታውቋል። በውሳኔው መሠረት፣ ቤንዚን በሊትር 69 ብር ከ52 ሳንቲም፣ ነጭ ናፍጣ 71 ብር ከ15 ሳንቲም፣ ኪሮሲን 71 ብር ከ15 ሳንቲም፣ ቀላል ጥቁር ናፍጣ 57 ብር ከ97 ሳንቲም እንዲኹም ከባድ ጥቁር ናፍጣ 56 ብር ከ63 ሳንቲም ኾኖ እንደሚቀጥል ተገልጧል።

4፤ በመቀሌ፣ በአንዳንድ የትግራይና አፋር ክልሎችና የኤርትራ አካባቢዎች 4 ነጥብ 7 ሬክተር ስኬል የተለካ ርዕደ መሬት ዕሁድ'ለት እንደተከሰተ ዓለማቀፍ የርዕደ መሬት ተከታታይ ድርጅቶች ገልጸዋል። ርዕደ መሬቱ ከዓዲግራት በስተምሥራቅ እንደተነሳና፣ ከመሬት በታች 10 ኪሎ ሜትር ጥልቀት ላይ እንደተከሰተ መረጃዎች አመልክተዋል። ባለፈው ታኅሳስ ወር ተመሳሳይ ርዕደ መሬት በአካባቢው ተከስቶ የነበረ ሲኾን፣ ባለፈው ወር መጨረሻ ደሞ በኤርትራዋ ደቀመሃሪ አካባቢ ተከስቶ እንደነበር ይታወሳል።

5፤ የታላላቅ ሐይቆች አገራት መሪዎች የደቡባዊ አፍሪካ አገራት ቀጠናዊ ድርጅት በግጭት በሚታመሰው ምሥራቅ ኮንጎ ጦሩን እንዲያሠማራ መስማማፊታቸውን ዘ ኢስት አፍሪካን ጋዜጣ ዘግቧል። የቀጠናው አገራት ይህንኑ ስምምነታቸውን የገለጡት፣ ከምሥራቅ አፍሪካና ደቡባዊ አፍሪካ አገራት መሪዎች ጋር በምሥራቅ ኮንጎ ጸጥታ ዙሪያ ሰሞኑን ባደረጉት ስብሰባ ላይ ነው። የምሥራቅ አፍሪካ ቀጠናዊ ድርጅት ባለፈው ሳምንት የጦሩን ቆይታ ለስድስት ወር ያራዘመ ሲኾን፣ የኮንጎ መንግሥት ግን ከሦስት ወር በላይ አላራዝምም በማለት ቀደም ሲል አስጠንቅቆ ነበር። #ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                  
@emsmereja
2.4K views04:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-05 13:16:47 ሰኞ ግንቦት 28/2015 ዓ.ም የEMS ዐበይት ዜናዎች

1፤ የኢትዮጵያ ኮምንኬሽን ባለሥልጣን የኮምንኬሽን አገልግሎትና የፈቃድ ክፍያን የሚወስን ረቂቅ መመሪያ ማዘጋጀቱን ሪፖርተር ዘግቧል። ረቂቁ መመሪያ፣ ከኮምኬሽን አገልግሎት ፍቃድ፣ ከሬዲዮ ሞገድ፣ ከሬዲዮ ኮምንኬሽን፣ ከቴሌኮምንኬሽን ቁጥር ምደባና ዓመታዊ ክፍያና ከቴሌኮምንኬሽን መሣሪያዎች የቴክኒክ ብቃት ማረጋገጫ አገልግሎት የሚሰበሰበውን የክፍያ ተመን እንደሚወስን ዘገባው ጠቅሷል። ብሄራዊ የፖስታ አገልግሎትና ዓለማቀፍና አገር ዓቀፍ የፈጣን መልዕክት አገልግሎት የሚሰጡ ኩባንያዎች ለፍቃድ ማውጯና ለዓመታዊ አአስተዳደራዊ ክፍያ መወሰኑን ዘገባው አመልክቷል።

2፤ ኢሰመጉ የሲዳማ ክልልና የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ ጸጋ በላቸው በተባለች ወጣት ላይ የጠለፋ ወንጀል በመፈጸም የተጠረጠረውን ኮንስታብል የኋላመብራት ወልደ ማርያም በቁጥጥር ስር አውለው አስተማሪ ፍርድ እንዲሰጡ ጠይቋል። ኢሰመጉ ጠለፋ ፈጽሞ ሽምግልና በመላክ በግዳጅ ጋብቻ እንዲፈጸም የሚተባበሩ አካላትን ፖሊስ ለሕግ እንዲያቀርብም አሳስቧል። ፖሊስ ቤተሰቦቿ ለተጠርጣሪው መጥሪያውን ራሳችን እንድንሰጥ ተጠይቀናል ማለታቸውን የጠቀሰው ኢሰመጉ፣ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት የከንቲባው ጠባቂ የነበረውን ተጠርጣሪውን ከሥራ እንዳሰናበተና ፖሊስ ትጥቁን እንዲያስፈታው መጠየቁን ገልጧል።

3፤ የአሜሪካው ፔንታጎን ሦስት የአልሸባብ አዛዦችን ሱማሊያ ውስጥ በድሮን ጥቃት መግደሉን አስታውቋል። ፔንታጎን የአልሸባብ አዛዦችን ገደልኩ ሲል፣ ባንድ ሳምንት የአሁኑ ለሁለተኛ ጊዜ ነው። ፔንታጎን ጥቃቱን የፈጸመው፣ ጁባላንድ ፌደራል ግዛት ውስጥ በሚገኝ የአልሸባብ ይዞታ ላይ መኾኑን ገልጧል። ጁባላንድና ሳውዝ ዌስት ግዛቶች የሱማሊያ ጦር በአልሸባብ ላይ ሁለተኛውን ዙር አጠቃላይ የማጥቃት ዘመቻ የሚጀምርባቸው ግዛቶች ናቸው።

4፤ ፕሬዝዳንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ የአልሸባብ ታጣቂዎች ባለፈው ሳምንት በሱማሊያ በሚገኝ የኡጋንዳ ወታደራዊ ጣቢያ ላይ በፈጸሙት ጥቃት የተገደሉት ወታደሮች 54 እንደኾኑ አስታውቀዋል። የኡጋንዳ ወታደሮች ጦር ሠፈሩን መልሰው መቆጣጠራቸውን የገለጡት ሙሴቪኒ፣ ወታደሮች ወደኋላ እንዲያፈገፍጉ ትዕዛዝ የሰጡ አዛዦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንና ምርመራ እየተደረገባቸው መኾኑን ገልጸዋል። አልሸባብ ይህን ጥቃት ያደረሰው፣ አፍሪካ ኅብረት በቀጣዩ ወር 2 ሺህ ሰላም አስከባሪዎችን ከአገሪቱ ሊያስወጣ እየተዘጋጀ ባለበት ወቅት ነው።

5፤ የሱዳኑ ግጭት ከትናንት ጀምሮ በካርቱምና. ዳርፉር ግዛት ተባብሶ መቀጠሉን ዓለማቀፍ የዜና ምንጮች ዘግበዋል። ግጭቱ የተባባሰው ለአምስት ቀናት ተራዝሞ የነበረው ተኩስ አቁም ትናንት ማብቃቱን ተከትሎ ነው። የሳዑዲ ዓረቢያና አሜሪካ አደራዳሪዎች ጅዳ ውስጥ የሚገኙትን የጦር ሠራዊቱንና የፈጥኖ ደራሽ ሠራዊቱ ተወካዮች ንግግራቸውን እንዲቀጥሉ በማግባባት ላይ እንደኾኑ ገልጸዋል። #ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                  
@emsmereja
3.7K views10:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-03 06:03:52 ዘመነ ካሴ ነፃ ነህ መባሉ ተሰማ
መስከረም ወር 2015 በቁጥጥር ሥር የዋለው ዘመነ ካሴ፤ ዛሬ ግንቦት 25 /2015 በባህርዳር ከተማ እና አካባቢው ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት “ነፃ ነህ” መባሉን የአዲስ ማለዳ ምንጮች ገልጸዋል።

ዘመነ ካሴ በመስከረም ወር በቁጥጥር ሥር ውሎ መስከረም 23/ 2015 በባህርዳር እና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርቦ የ7 ቀናት ቀጠሮ ተሰጥቶት እንደነበር የሚታወስ ነው።

ምርመራውን የያዘው የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የምርመራ ቡድን "በተሰጠኝ 10 ቀናት ውስጥ ምርመራዬን ማጠናቀቅ አልቻልኩም" በማለት ተጨማሪ 14 ቀናት እንዲሰጠው ጠይቋል።

የዘመነ ካሴ ጠበቆችም ወንጀል የተባለውን ጉዳይ ለማጣራት በሚል ፖሊስ ላለፉት አራት ወራት ያጣራ በመሆኑ እና ፍርድ ቤቱ ባለፈው ችሎት ውሎ የፈቀደው 10 ቀናት በቂ መሆኑን እና ሌሎችን መከራከሪያዎች አቅርበዋል፡፡ ስለዚህም ”የጊዜ ቀጠሮ መስጠት አያስፈልግም“ በማለት ተከራክረው ዘመነ ካሴ በዋስ እንዲለቀቅ ለፍርድ ቤቱ ጠይቀዋል።

የምርመራ ቡድኑ ያቀረበው ምክንያት በቂ አይደለም ያለው ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ መርማሪ ቡድኑ ከጠየቀው 14 ቀናት ውስጥ የ7 ቀናት ጊዜ ቀጠሮ በመስጠት ፖሊስ እስከ ጥቅምት 01/2015 ድረስ ምርመራውን እንዲያጠናቅቅ ትዕዛዝ ተሰጥቶት፤ ዘመነ ካሴም ወደ ባህርዳር ማረሚያ ቤት መመለሱን ከዚህ ቀደም አዲስ ማለዳ መዘገቧ ይታወሳል።

"በከባድ የሰው መግደል ወንጀል" ተከሶ የነበረው የዘመነ ካሴ ጠበቆች የክስ መቃወሚያ ማቅረባቸውን ተከትሎ፤ ዐቃቤ ሕግ መልስ ለመስጠት የክስ ችሎት ለማሰማት ጊዜ ይሰጠኝ ማለቱም አይዘነጋም።

ፍርድ ቤቱም ዐቃቤ ሕግ በጠየቀው መሠረት ለኅዳር 12/2015 ቀን ዘጠኝ ሰዓት በድጋሜ እንዲቀርብ ትዕዛዝ ሰጥቶ፤ ዘመነ ካሴ ለፍርድ ቤቱ የቃልና የጽሑፍ አቤቱታን እንዲያቀርብ ተደርጓል።

በመጨረሻም ዛሬ ግንቦት 25 /2015 ቀን ሰባት ሰዓት በዋለው ችሎት፤ ዘመነ ካሴ ከወንጀል ነፃ ነህ መባሉን የአዲስ ማለዳ ምንጮች ገልጸዋል። አዲስ ማለዳ ይህን ዘገባ እስካጠናቀረችበት ጊዜ ድረስ ዘመነ ከማረሚያ ቤት እንዳልወጣ ማወቅ ተችሏል።

#ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                  
@emsmereja
5.6K viewsedited  03:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-02 21:38:09 ዓርብ ምሽት! ግንቦት 25/2015 ዓ.ም የEMS ዐበይት ዜናዎች

1፤ ሙስሊሞች በኦሮሚያ ክልል የሸገር ከተማ አስተዳደር መስጅዶችን ማፍረሱን በመቃወም ዛሬ በአንዋር መስጅድ ከሰላት በኋላ ባሰሙት ተቃውሞ ላይ ጸጥታ ኃይሎች ተኩስ ከፍተው ቁጥራቸው ያልታወቀ ሰዎች መሞታቸውንና መቁሰላቸውን የአገር ውስጥ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። የዓይን ምስክሮች፣ ጸጥታ ኃይሎች ተቃውሞ ባሰሙት ሙስሊሞች ላይ "ጥይት መተኮሳቸውን" እና "ድብደባ መፈጸማቸውን" መናገራቸውን ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል። በኦሮሚያ ክልልም፣ ሙስሊሞች የመስጅዶችን መፍረስ በመቃወም በሻሸመኔና ጅማ ከተሞች የተቃውሞ ድምጻቸውን ማሰማታቸውን ዘገባዎች አመልክተዋል። ፖሊስ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ በክስተቱ ዙሪያ ፖሊስ ያለው ነገር የለም።

2፤ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዛሬ በአንዋር መስጅድ በደረሰው "ሁከት" እና "አለመረጋጋት" ጸጥታ ኃይሎች በወሰዱት ርምጃ "ከፍተኛ ጉዳት" መድረሱን መረዳቱን ማምሻውን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። በሸገር ከተማ አስተዳደር የመስጅዶች መፍረስ "ሙስሊሙን ኅብረተሰብ አስቆጥቷል" ያለው ጉባኤው፣ ጸጥታ ኃይሉ "የዜጎችን ሰላምና ደኅንነት የማስጠበቅ ተግባሩን በከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያከናውን" ጥሪ አድርጓል። ጉባኤው፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ችግሩን ከመንግሥት ጋር ተነጋግሮ እስኪፈታ ሙስሊሞች በትዕግሥት እንዲጠብቁም ጠይቋል።

3፤ የአማራ ክልል አርሶ አደሮች የምርጥ ዘር እና የአፈር ማዳበሪያ እጥረት ገጥሞናል በማለት ሰሞኑን በተለያዩ ከተሞች የተቃውሞ ሰልፎችን ማድረጋቸውን የአገር ውስጥ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። አርሶ አደሮች በባሕርዳር በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤትና በግብርና ቢሮ ፊት ለፊት ቅሬታቸውን ቢያቀርቡም፣ አጥጋቢ ምላሽ እንዳላገኙ መናገራቸውን ዘገባዎች ጠቅሰዋል። የክልሉ ግብርና ቢሮ በተያዘው ዓመት ክልሉ ከጠየቀው 9 ነጥብ 2 ሚሊዮን ኩንታል ማዳበሪያ፣ ግብርና ሚንስትር ለክልሉ 5 ነጥብ 2 ሚሊዮን ኩንታል እንደገዛና እስካኹን ለክልሉ የደረሰው ግን 1 ነጥብ 9 ሚሊዮን ኩንታል ብቻ እንደኾነ መናገሩን ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል። አርሶ አደሮቹ ግን ከማዳበሪያ እጥረት ባሻገር፣ ወደ ክልሉ የገባው ማዳበሪያ በነጋዴዎች እጅ መግባቱንና ዋጋው በከፍተኛ ደረጃ መወደዱን ተናግረዋል ተብሏል።

4፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከትግራይ የሚነሱና ወደ ትግራይ የሚጓዙ መንገደኞች ላይ "ብሄርን፣ ጾታንና የትኬት ዋጋን መሠረት ያደረገ አድልዖ ይፈጽማል" ተብሎ የቀረበብኝ ውንጀላ "ሐሰተኛ ውንጀላ ነው" ሲል በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መግለጫ አስተባብሏል። በፌደራል መንግሥቱና ሕወሃት መካከል የተደረሰውን የግጭት ማቆም ስምምነት ተከትሎ፣ ታህሳስ 20 ላይ ወደ መቀሌ ከዚያም ወደ ሽሬ ከተሞች በረራ መጀመሩን የጠቀሰው አየር መንገዱ፣ በአሁኑ ወቅት ወደ ሁለቱ ከተሞች በቀን ዘጠኝ በረራዎችን እያደረገ መኾኑን ገልጧል። አየር መንገዱ "ብሄርን፣ ጾታንና ዕድሜን መሠረት ያደረገ አድልዖ" እንደማያደርግና መንገደኞችን የብሄር ማንነት ሰነድ እንደማይጠይቅ ገልጧል። አየር መንገዱ የመንገደኞችን ፍላጎት እያጠናኹ ወደፊት ወደ ክልሉ የማደርገውን በረራ እጨምራለኹ በማለትም ቃል ገብቷል።

5፤ አንድ የኬንያ የሠራተኛና አሠሪ ፍርድ ቤት ከሜታ ኩባንያ ኮንትራት የወሰደው ሳማ ኩባንያ ከናይሮቢ ቢሮው 184 የፌሰቡክ የመልዕክት ይዘት ተቆጣጣሪዎች ከሥራ ያሰናበተበትን ውሳኔ ማገዱን የተለያዩ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ፍርድ ቤቱ እግዱን የጣለው፣ ጉዳዩን መርምሮ ውሳኔ እስኪሰጥ መኾኑን ገልጧል። ፍርድ ቤቱ፣ የይዘት ተቆጣጣሪዎቹ ሠራተኞች በፌስቡክ መገናኛ ዘዴ ላይ አዕምሮን የሚረብሹ ምስሎችን በተደጋጋሚ በማየት ለደረሰባቸው የአዕምሮ ጭንቀት፣ ሜታ ኩባንያ የስነ ልቦና ምክርና የሕክምና አገልግሎት እንዲሰጥ አዟል። የይዘት ተቆጣጣሪዎች ከሥራ መሰናበታችን ሕጋዊ አይደለም በማለት ክስ የመሠረቱት ባለፈው መጋቢት ነበር።

6፤ ንግድ ባንክ ዛሬ የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋ 54 ብር ከ3204 ሳንቲም እና መሸጫ ዋጋው 55 ብር ከ4178 ሳንቲም ሆኖ እንደዋለ በድረገጹ ገልጧል። የአንድ የእንግሊዝ ፓውንድ መግዣ ዋጋ ደሞ 64 ብር ከ6555 ሳንቲምና መሸጫው 65 ብር ከ9486 ሳንቲም ሆኗል። በተመሳሳይ አንድ ዩሮ በ58 ከ1887 ሳንቲም ተገዝቶ፣ በ59 ብር ከ3525 ሳንቲም ሲሸጥ መዋሉን ባንኩ ገልጧል። #ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                  
@emsmereja
5.2K views18:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-02 07:16:35 ዓርብ ጠዋት! ግንቦት 25/2015 ዓ.ም የEMS ዐበይት ዜናዎች

1) በአማራ ክልል ምሥራቅ ጎጃም ዞን የደብረ ኤሊያስ ወረዳ ጸጥታ ጽሕፈት ቤት የሥላሴ አንድነት ገዳም ከመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች ጋር ለተፈጠረው ግጭት የታጠቀ ኃይሎችን ተጠያቂ አድርጓል። የታጠቁ ኃይሎች በገዳሙ ውስጥ "ወታደራዊ ሥልጠና" ይሰጡበታል ያለው ጽሕፈት ቤቱ፣ ገዳሙ "የሃይማኖት አባቶችን፣ የአገር ሽማግሌዎችንና የመንግሥት አመራሮችን እየገደሉ በሕግ ላለመጠየቅ የሚጥሩ የታጠቁ ሰዎች የሚኖሩበት ገዳም ኾኗል" ብሏል። የገዳሙ ካህናት ግን፣ በገዳሙ ውስጥ የታጠቀ ኃይል ነበር ወይም በገዳሙ ውስጥ ወታደራዊ ሥልጠና ይሰጥ ነበር መባሉ ሙሉ በሙሉ ሐሰት ነው ማለቱን ዶይቸቨለ ዘግቧል።

2፤ የኦሮሞ ፌደራሊስት ፓርቲ በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ አስተዳደር እና በአዲስ አባባ መንግሥት የሚካሄደውን የግለሰብ ቤቶችንና ቤተ እምነቶችን የማፍረስ ዘመቻ እንዲቆም ባወጣው መግለጫ ጠይቋል። ፓርቲው የቤት ማፍረስ ዘመቻው ቆሞ፣ ባለሥልጣናት የውሳኔውን ሕጋዊነትና አተገባበር እንደገና እንዲፈትሹ ጥሪ አድርጓል። ፓርቲው ድርጊቱን፣ ጊዜውን ያላገናዘበ፣ አማራጭ መፍትሄዌችን ከግምት ያላስገባ፣ ሕጋዊ አካሄድን ያልተከተለ እና በተሳሳተ ፖሊሲ ላይ የተመሠረተ በማለት ተችቶታል። ዘመቻው በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ቤት አልባ ያደረገና መስጅዶች እና የኦርቶዶክስና ፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያናትን ጭምር ያፈረሰ መኾኑን ገልጧል።

3፤ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ አስተዳደር የተካሄደውን የመስጅዶች ማፍረስ ድርጊት "አንዳንድ አካላት ለፖለቲካ ዓላማቸው መጠቀሚያ ለማድረግ እየሞከሩ" ነው በማለት ከሷል። ቀደም ሲል ያቋቋመው ኮሚቴ ለችግሩ መፍትሄ ለመፈለግ ከመንግሥት ጋር እየሠራ መኾኑን የገለጠው ምክር ቤቱ፣ ሕዝበ ሙስሊሙ ውጤቱን በትዕግስት እንዲጠብቅ አሳስቧል። የኦሮሚያ ክልል መንግሥት የቤት ማፍረስ ዘመቻው በእምነት ተቋማት ላይ ያነጣጠረ አይደለም በማለት ትናንት የሰጠውን መግለጫ፣ ምክር ቤቱ እንዳልተቀበለው ገልጧል።

4፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በትግራይ ተወላጆች ላይ "አድሏዊ አሠራር" ተከትሏል የሚል ክስ በፌደራል ፍርድ ቤት እንደተመሠረተበት ቪኦኤ ዘግቧል። "ቅድሚያ ለሰብዓዊ መብቶች" የተሰኘ መንግሥታዊ ያልኾነ ድርጅት በአየር መንገዱ ላይ የመሠረተው ክስ፣ አየር መንገዱ ከትግራይ ወደ አዲስ አበባ በሚጓዙ የትግራይ ተወላጆች የመዘዋወር መብት ላይ ይፋዊ ያልኾኑ ገደቦችን ጥሏል የሚል እንደኾነ ዘገባው አመልክቷል። ድርጅቱ በክሱ ላይ፣ ከጥር 4 ጀምሮ አየር መንገዱ ወደ ትግራይ በሚያደርጋቸው በረራዎች ላይ ገደብ መጣሉን በውስጣዊ መገናኛ መስመሮች ገልጧል ማለቱን ዜና ምንጩ አውስቷል። አየር መንገዱ ግን፣ በትግራይ ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ አድሏዊ ድርጊት አልፈጸምኩም ብሏል ተብሏል።

5፤ የምሥራቅ አፍሪካ ኢኮኖሚ ማኅበረሰብ አባል አገራት መሪዎች ቡሩንዲ ላይ ባደረጉት ልዩ ስብሰባ በምሥራቅ ኮንጎ የተሠማራው ቀጠናዊ ጦር ቆይታውን እስከ መስከረም ድረስ አራዝመዋል። የቀጠናውን መሪዎች ውሳኔ ግን፣ የኮንጎ መንግሥት ማጽደቅ ይጠበቅበታል። የኮንጎ መንግሥት ግን የቀጠናው ጦር "ኤም-23" የተባለውን አማጺ ቡድን ፊት ለፊት ተዋግቶ እስከ ሰኔ ወር የማይደመስስ ከኾነ፣ ጦሩን አስወጥቼ በምትኩ የደቡባዊ አፍሪካ አገራትን ቀጠናዊ ጦር አስገባለኹ በማለት በቅርቡ መዛቱ ይታወሳል። #ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                  
@emsmereja
5.1K views04:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-01 21:41:52
ኮ/ል መንግስቱ ሀይለማርያም ከዝምባቡዬ

#ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                  
@emsmereja
4.8K viewsedited  18:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ