Get Mystery Box with random crypto!

ሰሞኑን ኹለት ሰዎች በጸጥታ ኃይሎች ተመትተው ሲገደሉ የሚያሳየው ተንቀሳቃሻ ምስል ባለፈው ዓመት ጥ | EMS Mereja

ሰሞኑን ኹለት ሰዎች በጸጥታ ኃይሎች ተመትተው ሲገደሉ የሚያሳየው ተንቀሳቃሻ ምስል ባለፈው ዓመት ጥር ወር ላይ የተፈጸመ መሆኑ ተገለጸ 

ከሰሞኑ በማህበራዊ ሚዲያ ሲሰራጭ የነበረውንና ኹለት ሰዎች በጸጥታ ኃይሎች ተመትተው ሲገደሉ የሚያሳየውን ተንቀሳቃሽ ምስል አስመልክቶ ዶይቸ ቬለ የሟች ቤተሰቦችን ጠቅሶ ባወጣው ዘገባ፤ ግድያው የተፈጸመው በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ድባጤ ወረዳ ውስጥ ባለፈው ዓመት ጥር ወር ላይ ነው ብሏል።

የሟች ቤተሰቦች "ባለፈው ዓመት ለተለያዩ ተቋማት፣ ሰብአዊ መብትን ጨምሮ አቤቱታ ብናቀርብም ፍትህ ማግኘት አልቻልንም፣" ሲሉ መናገራቸውም ነው የተገለጸው።

በዚህ ጉዳይ ላይ የኢትየጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የማጣራት ሥራ እየሰራ እንደሚገኝ የተጠቀሰ ሲሆን፤ ኮሚሸኑ ለጊዜው ማብራሪያ እንደማይሰጥ መግለጹም ተጠቁሟል፡፡

ከሰሞኑ በማኅበራዊ መገናኛ ዜደዎች ላይ ሲዘዋወር የነበረው የመከላከያ ሠራዊት የደንብ ልብስ የለበሱ ወታደሮች በጫካ ውስጥ ኹለት ግሰለቦችን ሲገድሉ የሚያሳየው የአንድ ደቂቃ ከአስራ ስድስት ሴኮንድ ተንቀሳቃሽ ምስል አነጋጋሪ የነበረ ሲሆን፤ ድርጊቱ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ድባጤ ወረዳ ጊጶ በሚባል ቀበሌ ውስጥ መፈጸሙ ነው የተገለጸው። ከገዳዮቹ ወታደሮች መካከል የአንዱ ወታደራዊ የደንብ ልብስ ላይ የታተመ የሲዳማ ክልል ባንዲራ ይታያል።

ከተገደሉት ኹለት ሰዎች መካከል አንዱ ታከለ መንገሻ ዱጉማ  እንደሚባሉ እና በዚያው ድባጤ ወረዳ ጫንጮ ቀበሌ ነዋሪ መሆናቸው እንዲሁም ሌላኛው ሀብታሙ አያና የተባሉ ግለሠብ መሆናቸው ተገልጿል።

በጉዳዩ ላይ ከመንግሥት በኩል እስካሁን ምንም ያልተባለ ሲሆን፤ ዶይቼ ቬለ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ማብራሪያ ማግኘት አለመቻሉን ጠቅሷል።
መረጃ ህይወት ነው፣ ይህንንም መረጃ ለጓደኞቻችሁ#Share በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ


t.me/emsmereja
t.me/emsmereja
t.me/emsmereja