Get Mystery Box with random crypto!

ታሰረ #Ethiopia | የጉማ አዋርድ መሥራችና አዘጋጅ ፤ ዳይሬክተር ዮናስ ብርሃነ መዋ መርኃ | EMS Mereja

ታሰረ
#Ethiopia | የጉማ አዋርድ መሥራችና አዘጋጅ ፤ ዳይሬክተር ዮናስ ብርሃነ መዋ መርኃ ግብሩን ሳያጠናቅቅ ትናንት ምሽት ታሰረ።

9ኛው የጉማ የሽልማት ዝግጅት በስካይላይት በደመቀ ሁኔታ ተከናውኖ ከምሽቱ 5:20 ሰዓት ላይ ተጠናቆ ነበር።
ወ/ሮ ሳምራዊት ከሰተ (ሊሊ) እንደተናገራቸው "አንቺን አንፈልግሸም ! ... እርሱን ግን ለጥያቄ እፈልገዋለን " በማለት ቦሌ ትራፊክ መምሪያ በተለምዶ ስሙ አንበሳ ጋራዥ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ መታሰሩን ተናግራለች።

***

[ ትውስታ : አምና፣ ካቻምና መድረክ ላይ ]

[ ልጅ አባቱን በመድረክ፣ በሕዝብ ፊት የሰጠው ማስጠንቀቂያ ]

እኔ አስራሃለሁ!"

"ፖለቲካ ውስጥ ተመልሰህ ብትገባ መንግሥት ሳይሆን እኔ አስራሃለሁ!"

"አንዳንድ ሰው እድለ ቢስ ሆኖ በልጅነቱ ሀገሩን እየጠላ አድጎ ሲያድግም ሀገሩን ለማፍረስ ይጥራል። አንዳንድ እድለኞች ደግሞ የሀገራቸውን ታላቅነት ተሰብከው አድገው ሀገራቸውን ለመገንባት ደፋ ቀና ሲሉ ህይወታቸውን ይጨርሳሉ። እንደዚህ ስለሀገር መልካምነት ተሰብከው ሀገር ለመገንባት ከባጁ እድለኞች መካከል አንዱ ወላጅ አባቴ ነው!"

ዮናስ ብርሀነ መዋ፣ የጉማ አዋርድ መሥራች እና ሥራ አስኪያጅ በፕሮግራሙ ላይ የተናገረው

"በሕይወት መቆየት እና በሕይወት መኖር ይለያያል። እኔ በሕይወት መኖር የጀመርኩት ዛሬ ነው። ይሁንና ልጄ፣ አባቱ የተነጠቀውን ሕይወት ለማኖር ዮናስ ብርሃነ መዋ ሲል አኑሮኛል። ልጄን በእናንተ ፊት በክብር እንዳመሰግነው ፍቀዱልኝ"
ብርሃነ መዋ

መረጃ ህይወት ነው፣ ይህንንም መረጃ ለጓደኞቻችሁ#Share በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ


t.me/emsmereja
t.me/emsmereja
t.me/emsmereja