Get Mystery Box with random crypto!

ኮንዶሚኒየም ደርሷቸው “በቀበሌ ቤቶች” ውስጥ የሚኖሩ ግለሰቦች፤ በአንድ ወር ውስጥ ቤቶቹን እንዲያ | EMS Mereja

ኮንዶሚኒየም ደርሷቸው “በቀበሌ ቤቶች” ውስጥ የሚኖሩ ግለሰቦች፤ በአንድ ወር ውስጥ ቤቶቹን እንዲያስረከቡ ቀነ ገደብ ተሰጣቸው
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፤ ኮንዶሚኒየም ደርሷቸው “በቀበሌ ቤቶች” ውስጥ የሚኖሩ የከተማዋ ነዋሪዎች እስከ ሰኔ 30 ድረስ የተከራዩዋቸውን ቤቶች እንዲያስረክቡ ቀነ ገደብ አስቀመጠ። የከተማ አስተዳደሩ የሚረከባቸውን እነዚህን የቀበሌ ቤቶች “የደሀ ደሀ” ተብለው ለተለዩ ነዋሪዎች ለማከፋፈል እቅድ መያዙን አስታውቋል።

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የግንባታ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ቶማስ ደበሌ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” እንደተናገሩት፤ የቀበሌ ቤቶቻቸውን አስረክበው ወደ ኮንዶሚኒየም ቤት እንዲገቡ ደብዳቤ የተሰጣቸው የከተማይቱ ነዋሪዎች፤ በየካቲት 2011 ዓ.ም እና በዘንድሮ ዓመት ህዳር ወር ላይ ዕጣ የወጣላቸው ዕድለኞች ናቸው። በቀድሞ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ የሚመራው አስተዳደር፤ በየካቲት 2011 ዓ.ም. ዕጣ ያወጣባቸው የኮንዶሚኒየም ቤቶች ብዛት 51,200 ገደማ ነበር።

በወቅቱ ለነዋሪዎች ሊተላለፉ በዝግጅት ላይ እያሉ በተነሳባቸው ተቃውሞ ምክንያት ከባለ እድለኞች ጋር ርክክብ ሳይፈጸምባቸው የዘገዩት እነዚህ የኮንዶሚኒየም ቤቶች፤ የቁልፍ ርክክብ የተፈጸመባቸው ግን ባለፈው ዓመት ነው። የከተማ አስተዳደሩ በዚህ ዓመት ህዳር ወር በ25,791 ቤቶች ላይ ዕጣ ያወጣ ሲሆን፤ ከዕድለኞች ጋር ውል የመዋዋል ስራው የተከናወነው ደግሞ ካለፈው ጥር እስከ ግንቦት ወር ባሉት  አምስት ወራት ውስጥ ነበር።

በከተማ አስተዳደሩ የሚገነቡ የኮንዶሚኒየም ቤቶችን የመከታተል ኃላፊነት ያለበት የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን፤ የኮንዶሚኒየም ዕጣ ወጥቶባቸው ነገር ግን እስካሁን ድረስ ያላለቁ 139 ሺህ ቤቶች ላይ የማጠናቀቂያ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን የኮርፖሬሽኑ የግንባታ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጸዋል። ኮርፖሬሽኑ በ32 የግንባታ ሳይቶች ላይ የሚገኙትን እነዚህ ቤቶች ሙሉ ለሙሉ ለማጠናቀቅ፤ ባለፉት አራት ወራት ሲሰራ መቆየቱን አስረድተዋል።
መረጃ ህይወት ነው፣ ይህንንም መረጃ ለጓደኞቻችሁ#Share በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ


t.me/emsmereja
t.me/emsmereja
t.me/emsmereja